2010–2019 (እ.አ.አ)
ተለወጡ
ኦክተውበር 2013


ተለወጡ

እውነተኛ መለወጥ የሚመጣው እውነት እንደሆኑ የምናውቃቸውን ትእዛዛቶች ስንተገብር እና እለት ተለት፥ ከወራት እስከ ወራት ስንጠብቃቸው ነው።

ወንድሞችና እህቶች፥ ብዙዎች የህይወቴ ጀግኖች በቆሙበት በዚህ የመናገሪያ ሰገነት ላይ በመቆሜ ትህትና ይሰማኛል። የተወሰኑትን የልቤን ስሜቶች በተለይ ወደ ወጣቱ በማተኮር አካፍላችሓለሁ።

በብሉይ ኪዳን ውስጥ ታላቅ ጀግና ከሆኑት አንዱ ወታደርና ነቢይ የነበረው ኢያሱ ነበር። ይህን ግብዣ ለእስራኤል ልጆች አቀረበ፣ “የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”1የኢያሱ አዋጅ ወደ ወንጌል በእውነት መለወጥን ያሳያል። ለኢያሱ እና ለሁላችንም፣ ወደ ወንጌል ምህሮች መቀየር የሚመጣው በወንጌል መርሆችበመኖር እና ከጌታ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን በማክበር ነው።

ከቤተሰቤ ታሪክ ውስጥ፥ከጀግኖቼ መካከል አንዷ ስለሆነችው የመለወጥ ታሪክን ላካፍላችሁ። ስሟም ኣግነስ ሆገን ይባላል። እንም እርሷና ባሏ በ1861 በስኮትላንድ ውስጥ ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቀሉ። በገዛ በተወለዱበት አገር ከባድ መሰደድን ሲገጥማቸው፥ ከልጆቻቸው ጋር ወደ አሜሪካ ተጓዙ። ከብዙ አመታት በሁአላ፥ ባሏ ሞቶ ኣግነስ ከስምንት ልጆች ጋር ቀረች፥ እናም እነርሱን መግባ አልብሳ ለማሳደግ ጠንክራ ሰራች። የአስራ ሁለት አመት ታላቅ ወጣት ሴት ልጇ እዛቤል ለአንድ የቤተክርስቲያን አባል ላልሆነ ባለሃብት ለቤት ሰራተኝነት ለመቀጠር እድለኛ ነበረች።

እዛቤል በትልቁ ቤታቸው ውስጥ እየኖረች ህጣናት ልጆቻቸውን በመጠበቅ ታግዝ ነበር። ለምትሰጠውም አገልግሎት የተወሰነ ደሞዝ ለናትየው በየሳምንቱ ይከፍሏታል። ብዙም ሳይቆይ የቤተሰቡ አካል ሆና የዳንስ ትምህርት መማርን፥ አዳዲስ ልብሶችን የመልበስ፥ ቲያትር የመከታተልን እድሎች አገኘች። ይህም እድል እዛቤል የሰራችበት ቤተሰብ ወደሌላ ክፍለ ሀገር እስከተዘዋወሩበት ጊዜ ድረስ በዚሁ መልክ ለአራት አመታት ያህል ቀጠለ። እዛቤልን በጥልቅ ፍቅር ከመውደዳቸው የተነሳ እናትየውን አግነስን ቀርበው በህጋዊ መንገድ ጉዲፈቻ ለማድረግ ፈቃድዋን ጠየቁ። ጥሩ ትምህርትን ለመስጠት፥ በጥሩ መልክ እንድታገብ ለማድረግ፥ ከልጆቻቸው ጋር የእርስታቸው ወራሽ ለማድረግ እና ደሞዟንም ለአግነስ ለመክፈል ቃል ገቡ።

ይህች ችግርተኛ ና ብቸኛ እናት አስቸጋሪ ውሳኔ ከፊቷ ገጥሟታል። ነገር ግን ለደቂቃ እንኳን አላመነታችም። ከብዙ አመታት በሁዓላ በልጅ ልጇ የተፃፈውን ቃላት አዳምጡ። “እምቢ እንድትል ፍቅሯ ባያስገድዳት እንኳ የተሻለ ምክንያት አላት። ለወንጌል ስትል ከስኮትላንድ ድረስ ተጉዛለች እናም ብዙ መከራዎችንና ችግሮችን አልፋለች። እሷ ይህንን ሁሉ ተጉዛ የመጣችበትን አላማ ልጇ እንድታጣ በማንኛውም ሰብአዊ መንገድ አልፈቀደችም።”2 ባለጠጋው ቤተሰብ የተቻላቸውን ድርድር ቢጠቀሙም፥ እዛቤል እንዲፈቀድላት እያለቀሰች ብትለምንም እንኳ፥ አግነስ ፀንታ ቆመች። እንደምታስቡት የ 16 አመት ወጣቷ እዛቤል ህይወቷ የተበላሸባት መሰላት።

እዛቤል ሆገን ቅድመ አያቴ ናት፥ በእናቷ ልብ ውስጥ ወገግ ብሎ ሲቃጣል ስለነበረው ምስክርነት እንዲሁም የልጇን የቤተክርስቲያን አባልነትን በአለማዊ ነገር ላለመቀየር ስለነበራት የፀና እምነት ከምንም በላይ ምስጋና አለኝ። ዛሬ የእሷ ትውልድ የሆኑ በመቶ የሚቆጠሩት የቤተክርስቲያን የአባልነትን በረከት የሚቋደሱት አግነስ ለወንጌል በነበራት ጥልቅ እምነት እና መለወጥ ምክንያት ነው።

ወጣት ጓዶች፥ አደገኛ ጊዜ ውስጥ ላይ ነው የምንኖረው፥ እናም በየቀኑ እንዲያውም በየሰአቱ በህይወታችሁ እንድትወስኑ የተሰጣችሁ ጥሪ ዘላለማዊ ውጤት አለው። በእለታዊ ህይወታችሁ ውስጥ የምታደርጉት ውሳኔዎች በሁአላ በናንተ ላይ ምን እንደሚከሰት ያሳያል። የሗለኛው ቀን ቅዱሳን የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ያለ እውነተኛ የእግዚአብሄር መንግስት እንደሆነ ጠንክሮ የዘለቀ ምስክርነት እና የፀና እምነት ከሌላችሁ፥ አስፈላጊውን ነገር አድርጋችሁ እምነት የምትቀበሉበት ጊዜ አሁን ነው። ይህንን የመሰለ የፀና እምነትን ለማግኘት የሚያስፈልገውን ጥረት ከማድረግ የምታዘገዩ ከሆነ ለነፍሳችሁ አስጊ ሊሆን ይችላል።

እውነተኛ መለወጥ የወንጌልን እውቀት ብቻ ከማግኘት እናም የነዚህን መሰረተ ሀሰቦች ምስክርነት ከማግኘት በላይ ነው። ወንጌልን ሳይንኖር ምስክርነትን ማግኘት ይቻላል። እውነተኛ መለወጥ ማለት ግን ባመነው ላይ ስንተገብር እና በውስጣችን ወይም “በልባችን ታላቅ ለውጥ እንዲፈጥር ስንፈቅድለት ነው።”3True to the Faith በሚለው ትንሽ መፅሃፍ ላይ “ወደ ወንጌል መለወጥ ሂደት እንጂ ክስተት አይደለም። የሚለውን እንማራለን። የመትለወጡት ክርስቶስን ለመከተል የፅድቅ ጥረት ስታደርጉ ነው።”4 ጊዜን፥ ጥረትን እና ስራን ይጠይቃል። የእኔ ቅድመ ቅድም አያት ወንጌል ለልጆችዋ ከምንም በላይ አስፈላጊ እንደሆነ የፀና እምነት ነበራት እናም ለወንጌል ስትል መስዋትነት አደረገች፥ እስከመጨረሻው ፀናች እንዲሁም በህይወቷ ኖረችው። የእርሷም መለወጥ የመጣው የወንጌል መሰረተ ሃሳቦችን በመኖር እና መስዋትነትን በመክፈል ነው።

ተመሳሳይ የሆነውን በረከት ለመቀበል፥ ተመሳሳይ የሆነውን ሂደት ማለፍ አለብን። አዳኛችን እንዳስተማረው፥ “ማንም ሰው የሱን ፍቃድ ቢያደርግ፥ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሄር ዘንድ ይሁን ፣ወይም ከእኔ ዘንድ እንደመነጨ ታውቃላችሁ”5 ብሎአል። አንዳንድ ጊዜ ይህንን ተግባር ከሗላ ጀምረን እንከውነዋለን። ለምሳሌ፥ “ የአስራትን ህግ ለመኖር እፈልጋለሁ፥ ነገር ግን መጀመሪያ እውነት እንደሆነ ማወቅ አለብኝ “ እንላለን። የአስራት ወረቀቷን እንኳ ሳንሞላ ፥ ፀሎትም አድርገን ጌታ በምስክርነት እንዲባርከን ተስፋ እናደርጋለን። በዚህ አይነት መንገድ አይሰራም። ጌታ የእምነት ልምምድ እንድናደርግ ይጠብቅብናል። የአስራትን ምስክርነት ለማግኘት ሳናቋርጥ ሙሉ እና ታማኝ አስራትን መክፈል አለብን። ይህ መንገድ ለሁሉም የወንጌል መሰረተ ሃሳቦች ፥ የንፅህና ህግ ይሁን፥ ላለባበሳችን፥ ለጥበብ ቃል፥ ወይም ለፆም ህግ ይሰራል።

የወንጌልን መሰረተ ሃሳብን መኖር ፥ ወደዛው እንድንለወጥ እንዴት እንደሚረዳን አንድ ምሳሌ ላካፍላችሁ። በስልሳዎቹ በወጣትነቴ ከትምህርት ቤቴ ብቸኛ የቤተክርስቲያን አባል ነበርኩ። ይህ ዘመን አብዮታዊ ጊዜና ባህላዊ ግብረ ገብነት የተካደበት ፥ ጎጂ እፅ የመጠቀም እና “ የመጣው ይምጣ “ የሚባልበት ዘመን ነበር። ብዙዎች ጓደኞቼ ጥሩ ቢሆኑም በአዲሱ ባህል፥ የድሮው የስነ ምግባር ጉድለት በሆነው ለመጠመድ ቀላል ሆኖላቸው ነበር። ሰውነቴን በአክብሮት መንከባከብ፥ ንፁህ አይምሮን መያዝ፥ ከሁሉም በላይ በእግዚያብሄር ትእዛዛት ላይ መታመን ቤተሰቦቼና አስተማሪዎቼ አጥብቀው ያስተማሩኝ ነገር ነው። መጠጥ ያለበትን ቦታ ለመራቅ ፥ ከሲጋራ እና ከጎጂ እፆች ነፃ ለመሆን ወሰንኩኝ። ያ ማለት በግብዣውች ላይ አልተካተትኩም እናም ወንዶችንም ለመተዋወቅ አልፈለኩም። በወጣቶች ዘንድ ጎጂ እፆችን መውሰድ የእለት ተለት ተግባር እየሆነ መጣ፥ እናም ጎጂነታቸው እንደዛሬው ይፋ አልወጣም ነበር። ብዙዎቹ ጓደኞቼ አይምሮን ከሚያዛባው እፅ ጉዳተኛ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከፍተኛ ሱስ ያዛቸው። በቤቴ ስለ ጥበብ ቃል በመማሬ አመሰገንኩኝ፥ እምነቴን በመለማመድ ስኖረው ደግሞ፥ ጥልቅ ምስክርነትን አዳበርኩኝ። የወንጌልን እውነተኛ መርህ በመኖር ያገኘሁት ጥሩ ስሜት፥እውነተኛ መርህ እንደሆነ ፥ ከመንፈስ ቅዱስ የመጣ ማረጋገጫ ነበር። በዚህ ጊዜ ነው ታዲያ እውነተኛ መለወጥ የሚጀምረው።

ነብዪ ሞሮኒ በመፃፈ ሞርሞን እንዳስተማረው፥ “እምነት ተስፋ ስለምናደርጋቸው ነገሮች እንጂ ስለምናያቸው ነገሮች እንዳልሆነ ለአለም አሳያለሁ። ስልለሆነም ስላላያችሁ አትከራከሩ። እምነታችሁ እስኪፈተን ድረስ ምስክርነትን አትቀበሉምና።”6 ባለማችን ፈጣን እርካታ በሚፈለግበት ወቅት፥ ላባችን ላልሆነው ሽልማትን ስንሻ እንገኛለን። ሞሮኒ የሚነግረን፥ መጀመሪያ ተግባርን ካስቀደምን፥ ወንጌልን በመኖር እምነትን ከተለማመድን፥ ከዚያ በሁዋላ የእውነተኝነትን ምስክርነት እንቀበላለን። እምነተኛ መለወጥ የሚመጣው፥ እውነተኛ እንደሆነ በምታውቁት ትምህርት ላይ መተግበርን ስትቀጥሉ እና ትእዛዛቱን ከእለት ለት እንዲሁም ከወራት ወራት ስትጠብቁ ነው፥

በዚህ ጊዜ የቤተክርስቲያን ወጣት አባል መሆን ታላቅ ነገር ነው። ኑ ተከተሉኝ በሚለው፥ እናንተን በዋናነት ወደ ክርስቶስ ወንጌል ለመቀየር የወጣው የወጣቶች መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ እናንተ የመጀመሪያዎቹ ናችሁ። ወላጆቻችንና የወጣት መሪዎቻችን ምን ያህል በመንፈስ ቢመሩም ለራሳችሁ መለወጥ ቅድሚያ ሃላፊነት አለባችሁ። “ማንም ሰው በናንተ ፋንታ ወደ ወንጌል አይለወጥም፥ እናም ማንም አያስገድዳችሁም።”7 በፀሎታችን ትጉህ ስንሆን፥ ቅዱሳን መፅሃፍትን ስናጠና፥ ቤተክርስቲያን ስንከታተል፥ ሌሎችን ስናገለግል፥ ለቤተ መቅደስ ስርአቶች በብቁነት ስንዘጋጅ መለወጥ ይመጣል። በቤታችን እና በትምህርት ቤት የምንማረውን ፅድቅ መርሆች ስንተገብር መለወጥ ይመጣል። ወንጌልን ስንኖር፥ መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር ሲሆን፥ ንፁህና ፃድቅ ህይወትን ስንመራ መለወጥ ይመጣል። የክርስቶስ ኢየሱስ ቤዛነትን ስንረዳ እና አዳኛችን እንደሆነ ስንቀበል እንዲሁም የሱ ቤዛነት በህይወታችን እንዲሰራ ስንፈቅድ መለወጥ ይመጣል።

የግል መለወጣችሁ በቤተ መቅደስ ቃል ኪዳን ለመግባት፥ የወንጌል አገልግሎት ለመስጠት፥ እንዲሁም የራሳችሁን እቤት እንድትመሰርቱ ያዘጋጃችሁአል። ስትለወጡ፥ የተማራችሁትን ለሌሎች ለማካፈል መሻት ይኖራችሃል እናም በራስ በመተማመን እና በሃይል የመመስከር ችሎታችሁ ይጨምራል። በራስ በመተማመን እና በድፍረት መመስከር በእውነት በመለወጣችን ምክንያት በተፈጥሮ የሚመጣ ውጤት ነው። አዳኛችን ጴጥሮስን ሲያስተምረው “ ወደ ወንጌሉ ስትለወጥ፥ ወንድሞችህን አጠንክር“ አለው።8

ነብዩንና ጦረኛውን እያሱን አስታውሱ። ብቻውን ተለውጦ የተቀመጠ ሳይሆን፥ ያለድካም እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ድረስ የእስራኤል ልጆችን ወደ ጌታ ለማምጣት ተጋ። በብሉይ ኪዳን ስናነብ፥ “እስራኤላውያን በእያሱ ዘመን ሁሉ ጌታን አገለገሉ።”9 በእውነት የተለወጠ ሰው የራሱን ነፍስ አድኖ እርሱን በሚያውቁት ላይ ጠንካራ ተፅእኖ ያሳድራል።

ወንጌልን መኖር እና በቅዱስ ቦታ ላይ መቆም ሁሌ የሚመች ወይም ቀላል አይደለም። ነገር ግን እመሰክርላችሁአለሁ ዋጋ አለው። ጌታ ኤማ ስሚዝን ሲመክራት፥ “ የምድር ነገሮችን ትተሽ፥ የተሻለ ነገሮችን ፈልጊ“ አላት።10 በተሻለው አለም ላይ ያሉትን ነገሮች እንዲሁ ተነስተን ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ለመገመት እንደማንችል እገምታለሁ።

ወንጌልን ለመኖር እና ለመለወጥ በምናደርገው ጥረታችን እኛን ለመርዳት እና ሊባርከን ታላቅ መሻቱ የሆነ አፍቃሪ የሰማይ አባት እንዳለን እመሰክራለሁ። ዋናው ትኩረቱና ስራው ለኛ “ዘላለማዊነት” እንደሆነ 11በግልፅ አስቀምጧል። ወደ እርሱ ዘንድ ወደ ሆነው ቤት ሊወስደን ይፈልጋል። በወንጌል ትምህርቶች ላይ ስንተገብር፥ በለት ተእለት ስራ ላይ ስናውል፥ እንለወጣለን እንዲሁም በቤተሰባችንና በአለም ላይ ብዙ መልካም ነገሮችን ለማከናወን መሳሪያ እንሆናለን። እዚህ አላማ ላይ ለመድረስ በምናደርገው በቀን ጥረታችን ሁላችንም እንድንባረክ ፀሎቴ ነው፥ በእየሱስ ስም አሜን።