2010–2019 (እ.አ.አ)
የእርሱን ቃል ለመግለጥ የተጠራ
ኦክተውበር 2013


የእርሱን ቃል ለመግለጥ የተጠራ

ትሁት ከሆናችሁ፣ታዛዥ እና የመንፈስን ድምጽ የምትሰሙ ከሆነ፣እንደ አገልጋይነታችሁ ታላቅ ደስታን በአገልግሎታችሁ ዉስጥ ታገኛላችሁ።

ለጠቅላላ ጉባአኤ ባለፈዉ ሚያዚያ ስጠራ ፣በ ህንድ ዉስጥ የአካባቢ የሚስዮን አገልግሎት ፕሬዘዳንት ሆኜ እያገለገልኩ ነበር።በአገልግሎቴ ወቅት በመጀመሪያ የታዘብኩት የቀድሞ የአካባቢ የሚሲዮን ፕሬዘዳንት ሆነዉ ያገለገሉት የነገሩኝን ነው “የዚ ቤተክርስቲያን ሚሲዮናዊያን ግሩም “እንደሆኑ ነው።1

ከሚገርሙት ሚስዮናዊያን አንዱ ከ እህት ፈንክ እና ከኔ ጋር ያገለገለዉ ፖክህረል ከ ኔፓል ነበር።ለሁለት አመት ብቻ የቤተክርስቲያኑ አባል ከሆነ ብኋላ እንግሊዘኛ ተናጋሪ በሆነዉ በ ህንዱ ባንግሎር ሚሽን ተጠራ።የነግራችኋል በደንብ ተዘጋጅቶ አልነበረም።ግልጽ ነበር።አንደ አመት እስኪሞላዉ ድረስ ምንም አይነት ሚስዮናዊያንን አላየም።የጥሪዉን መመሪያ ለመረዳት እንኳ እንግሊዘኛ በደንብ አያነብም ነበር።ለ ሚሲዮናዊ ስልጠና ማእከል ካኪ፣ተጭ ሸሚዝ እና ከረቫት ከማምጣት ይልቅ በሱ ቃል “አምስት ጂንሶች፣ቲሸርቶች እና ብዙ የ ጸጉር ጄሎችን” አዘጋጀ። 2

ተገቢ ልብሶችን ካገኝ ብኋላ እንክዋን ለተወሰኑ ሳምንታት የበቂነት ስሜት አልተሰማዉም።የዛን ግዜዉን አገልግሎቱን እንዲ ይገልጸዋል፡ “እንግሊዘኛዉ ብቻ ሳይሆን አስቸጋሪ የነበረዉ፣ስራዉ እራሱ አስቸጋሪ ነበር…..ከሁሉም በላይ ይርበኝ ነበር፣የደክመኝ እና ቤቴን እናፍቅ ነበር………ሁኔታዎች አስቸጋሪ የነበሩ ቢሆንም ጸንቼ ነበር።ደካማነት እና ያለበቂነት ሰሜት ተሰማኝ።በዛን ግዜያን ለሰማይ አባት እንዲረዳኝ እጽልይ ነበር።በጸለይኩበት ሰአት ሁሉ መጽናናት የሰማኝ ነበር።3

ለፖክህረል የ ሚስዮናዊ አገልግሎት አዲስ አና አስቸጋሪ ቢሆንም በታላቅ እምነት እና ከቅዱሳን መጽሃፍት፣ ከPreach My Gospel, እና ከሚስዮን መሪዎቹ የተማረዉን ለመገንዘብ እና ለመከተል በመሻት አገልግሏል።የወንጌል ሃይለኛ መምህር ሆነ-በ እንግሊዘኛ-ግሩም መሪም።ከ አገልግሎቱ እና ከተወሰነ ግዜ የኔፓል ቆይታ ብኋላ ወደ ህንድ ትምህርቱን ለመቀጠል ተመለሰ።ከ ጥር አንስቶ በ ኒው ደልሂ ቅርንጫፍ በፕሬዘዳንትነት አገልግሏል።በ አገልግሎቱ ወቅት ትክክለኛ እድገት በማየቱ፣ በህንድ ለሚገኘዉ ቤተክርስቲያን እድገት ማበርከትን ጀመረ።

እንዴት ነው ሚስዮናዉያንን አይቶ የማያዉቅ ወጣት የመንፈሳዊ ጥንካሬ ሊኖረዉ ቻለ?እንዴት ነው የመንፈሳዊ ሃይልን እንደሚሲዮናዊ የምትቀበሉን የምታገለግሉበትን ሰዎች በር፣ሳጥን እና ልብ ለመክፈት።እንደተለመደዉ፣መልሱ ቅዱስ መጽሃፍቶች ዉስጥ እና በህያዉ ነብያቶች እና ደቀመዝሙሮች ዘንድ ይገኛል።

በኢንግላንድ በ 1837 ለመጀመሪያ ግዜ ወንጌል ሲሰበክ ጌታ ይህን ገለጠ፣ “በስሜ ማንንም ብትልኩ፣ በወንድሞቻችሁ ድምጽ፣አስራሁለቱ፣በናንተ የተመረጡት እና ስልጣን የተሰጣቸዉ፣ስልጣን ይኖራቸዋል የ መንግስቴን በር ለሁሉም ህዝቦች ለመክፈት።4

የትም ብትላኩ ፣ ለየትኛዉም ቦታ፣እወቁ የአስራሁለቱ አባላት ያንን ተለኮ መርጠዉታል እናም በጌታ ነብያቶች ተጠርታችኋል።እጅን በመጫን ተጠርታችኋል።’ 5

ጌታ እነዚ ቃል ኪዳኖች የሚፈጸሙበትን ሁኔታዎችን ሰጥቷል።እንዲ አለ “ይህን የሚሆነው [ይህም ማለት ቃል ኪዳኑ የሚሟላው እነርሱ የሚቀጥለውን ካደረጉ ነው] በፊቴ ራሳቸውን [ይህም ማለት እነርሱ ሚስዮኖች] [1] ትሁት እስካደረጉ፣ እና [2] በቃሌም እስከኖሩ፣ እና [3] የመንፈሴንም ድምፅ እስካደመጡ ድረስ ነው።”6

የጌታ ቃል ኪዳኖች ግልጥ ናቸዉ።ለተላካችሁበትን ሃገር የእግዚአብሄርን መንግስት በር ለመክፈት የሚያስችለዉን መንፈሳዊ ሃይል ለማግኘት እራሳችሁን ማዋረድ፣መታዘዝ እና መንፈስ ቅዱስን ለመስማት እና ለመከተል ችሎታ ለማግኘት።

እነዚህ ሶስት ባህሪያት እርስ በእርሳቸዉ የተያያዙ ናቸው።ሩሩ ከሆናችሁ፣ለመታዘዝ ትሻላቹ።ታዛዥ ከሆናቹ፣መንፈሱ ይሰማችኋል።መንፈሱ አስፈላጊ ነው፡ለኛ እዝራ ቴፍት ቤንሰን አስተማሩ “ያለመንፈሱ፣መቼም ችሎታዉ እና አቅሙ ቢኖራችሁ እንኳ አይሳካላችሁም።”7

እንደ ሚስዮን ፕሬዘዳንት፣አንዳንዴ ሚስዮናዊያንን ሙሉ ለሙሉ ንጹ ስላልሆኑ ቃለ መጠይቅ አደርግ ነበር።ከመንፈሳዊ አቅማቸዉ በታች ይኖራሉ።ምንም ያህል ቢሰሩም ወይም ጥሩ ነገር ቢሰሩ፣ሰላም አይሰማቸዉም እናም የመንፈስ ቅዱስን ጉዋደኝነት አይደሰቱበትም እራሳቸዉን እስከሚያዋርዱ ድረስ፣ሙሉ ለሙሉ ንሰሃ እስከሚገቡ ድረስ እና የአዳኝን ምህረት እና ክብር እስከሚያገኙ ድረስ።

ጌታ አገልጋዮቹን ሩሩ እንዲሆኑ ያዛል፣ምክንያቱም መንፈሳዊ ሙሉነት ከተሰበረ ልብ ይጀምራል።ከተሰበሩ ነገሮች የሚመጡትን ጥሩነቶችን አስቡ፡አፈር ስንዴት ለማምረት ይሰበራል።ስንዴ ዳቦ ለመጋገር ይሰበራል።ዳቦ ተሰብሮ ደግሞ ለቅዱስ ቁርባን ይሆናል።አንድ ሰዉ በተሰበረ ልብ ቅዱስ ቁርባን ሲወስድ እሱ ወይም እስዋ ምሉእ ይሆናሉ።8 ንሰሃ ገብተን ምሉእ ስንሆን በ እየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አዳኝን ስናገለግለዉ ብዙ የምናበረክተዉ አለ። “እናንተ ኑ ወደእኔ እናም ነብሳችሁን ሁሉ እንደስጦታ ለሱ አበርክቱለት።”9

ሃጢያት ብትሸከሙም እና ንስሃ መግባት ብትፈልጉ፣እባካቹ በፍጥነት አድርጉት።የተጎዱትን ጌታ ሲያድን፣ሁሌም እንዲነሱ ይጋብዛቸዋል።10 ከመንፈሳዊ ስቃያችሁን ለመዳን እባካቹ የእርሱን የእንድትነሱ ግብዣ ተቀበሉ።ያለምንም መዘግየት ኢፒስ ቆፖሱን ፣ የቅርንጫፍ ፕሬዘዳንቱን ወይም የ ሚሲዮን ፕሬዘዳንቱን አናግሩዋቸው እናም የንሰሃን ጉዞ ካሁኑ ጀምሩ።

የሃጢያት ክፍያዉ የማዳን ሃይል ለምንፈሳቹ ሰላምን እና መንፈሳቹ መንፈስ ቅዱስን እንዲሰማቹ ያደርጋችዋል።የአዳኝ መስዋትነት ከልኬት በላይ ነው ነገር ግን ሃጢያታችን ብዙ ቢሆኑም ሊቆጠሩ እና ሊነዘዙ፣ሊረሱ እና ይቅር ሊባሉ ይችላሉ። “ንሰሃ በሚገባ ነብስ እንዴት ደስታዉ ታላቅ ነዉ።”11

ይህ የ ትምህርት እና ቃልኪዳን ቃልኪዳን ሃይል አለዉ “ሃቅኝነት ሃሳባችሁን ይምራዉ፤መተማመናቹ በጌታ መገኛ ዘንድ ያጸዳችኋል።”12 ትክክለኛ ህይወት ስትኖሩ፣በ እግዚአብሄር ዘንድ ስትቆሙ ሰላማዊ መተማመንን ይሰማችኋል እናም የመንፈስ ቅዱስ ሃይልም ከናንተ ይኖራል።13

አዳዲስ የቤተክርስቲያኑ አባላት ወየም ከንደገና ወደ ሙሉ አባልነት የተመለሱት እንዲ ይላሉ “እኔ አሁን ብቁ ነኝ እናም ለማገልገል ፍላጎት አለኝ ግን በቂ እንደማዉቅ አላዉቅም።” በሚያዚያ ፕሬዘዳንት ቶማስ አኤስ ሞንሰን ይህን አስተማሩ “የእዉነት እዉቅት እና የ ታላቁ ጥያቄ መልስ ለ እግዚአብሄር ት እዛዛቶች ስንታዘዝ ይመጣል።”14 ምን ያህል አበረታች ነው በታዛዥነታችን እውቀትን ማግኘታችን።

አንዳንዶች የተወሰነ ችሎታ፣ብቃት እና ልምድ ለመለገስ እንዳላቸዉ ሊሰማቸዉ ይችላል።ይህን መሰል ጭንቀት ካለባችሁ የ ፓክህረልን ልምድ አስታዉሱ።ተዘጋጁ እናም የሰማይ አባታችን ሩሩነታችሁን እና የመታዘዝ ጥረታችሁን ያጎላዋል።ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ ስካት ይህንን አበረታች ምክር ለግሰዋል፡ “የጌታን ተዛዛት ስንታዘዝ እና የሱን ልጆች ያለራስ ወዳድነት ሰናገለገላቸዉ፣ውጤቱ ሃይል ከ እግዚአብሄር ነው-በራሳችን ከምናደርገዉ በላይ እንድናደርግ የሚያደርገን ሃይል። የኛ ችሎታ ከጌታ ጥንካሬን እና ሃይልን ስለምንቀበል ይሰፋል።”15

በጌታ ሰታምኑ ሃያሉ እግዚአብሄር ልጆቹን በናንተ በኩል ይባርካል።16 ሽማግሌ ሆሊንግስ ከ ነቫዳ በመጀመሪያዎቹ የአገልግሎቱ ግዜ ተማረ።ህንድ ውስጥ ከደረሰ ብህዋላ ከ እህት ፈንክ እና እኔ ጋር ወደ ራጃመንድሪ ተጓዘ።ያን ከሰአት ሆሊንግስ እና ጋንፓራም የቤተክርስቲያን አባል የሆነችዉን እና የስዋን እናት ለመጎብኘት ሄዱ።እናትየዉ ሰለቤተክርስቲያኑ ለመማር ፈለገች ምክንያቱም ወንጌሉ የሷን ልጅ ምን ያህል እንደባረክ አየች።ትምህርቱ በእንግሊዘኛ ሰለሆነ እናትየዉ ደግሞ ተልጉ ብቻ ሰለሆነ የሚናገሩት አንድ ወንድም ከቅርንጫፉ ትምህርቱን ለመተርጎም ነበር።

ሆሊንግስ የመጀመሪያዉ ትምህርቱ የመጀመሪያዉን ራእይ ማስተማር ነበር፣የነብዩን የዮሴፍን ቃል በመጠቀም።በትምህርቱ ወቅት ወደ እህት ፈንክ ዞሮ ይህን ጠየቀ “ቃል በ ቃል ማለት አለብኝ?” እንደሚቶረገም በማወቅ።

እስዋም መልሳ፣ “ቃል በ ቃል በለዉ መንፈስ ቅዱስ አንተ ምትለዉን ይመሰክራል።”

ይህ አዲስ አገልጋይ የመጀመሪያዉን እራእይ በጥልቀት ሲያስብ የነቢያቶችን ቃላት በመጠቀም የዉዷ እህት እምባ መዉረድ ጀመረ።ሆሊንግስ ያንን ታላቁን መለክት ጨረሰ በራስዋ ቋንቋ በእንባ በመታገዝ ጠየቀች “ልጠመቅ እችላለዉን?ወንዱን ልጄን ታስተምሩታላችሁን?”

በሮች እና ልቦች በየግዜዉ ለ ወንጌል መለክት ይከፈታሉ-ተስፋን እና ሰላምን እና ደስታን በአለም ላሉ ለ እግዚአብሄር ልጆች የሚያመጣ። ትሁት ከሆናችሁ፣ታዛዥ እና የመንፈስን ድምጽ የምትሰሙ ከሆነ፣እንደ አገልጋይነታችሁ ታላቅ ደስታን በአገልግሎታችሁ ዉስጥ ታገኛላችሁ።17 ጌታ ስራውን በሚያፋጥንበት በዚህ አስደናቂ ጊዜ ሚስዮን መሆን እንዴት አስደሳች ነው።

“ሰለ አዳኛችን እና ስለ እርሱ “መለኮታዊው ትዛዝ” 18 እመሰክራለሁ “ሂዱ ሁሉንም ስዎች አስተምሩ”።19 ይህ የእርሱ ቤተክርስቲያን ነው።በህያዉ ነቢያቶች እና ደቀመዝሙሮች ይመራዋል።እንደ ሞርሞን ጥሪው ሲመጣ ብቁ 20 እና በመንፈስ ሃይል ለመግለጥ “እነሆ፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ነኝ። ዘላለማዊ ህይወትንም ያገኙ ዘንድ፣ በህዝቡ መካከል ቃሉን እንዳሰራጭ በእርሱ ተጠርቻለሁ።”21 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።