2010–2019 (እ.አ.አ)
ዘለአለማዊ ውሳኔ
ኦክተውበር 2013


ዘላለማዊ ውሳኔ

ጥበባዊ የሆነ ሰው ነፃነቱን ተጠቅሞ ለአሁን እና ዘላለማዊ ውሳኔ ማድረግ ለመንፈሳዊ ዕድገቱ አስፈላጊ ነው።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች እያንዳንዱ ቀን የውሳኔ ቀን ነው። ፕሬዝዳንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን ውሳኔ አስቀድሞ የመወሰን እጣ ፋንታ እንደሆነ አስተምሮናል።1 ጥበባዊ የሆነ ሰው ነፃነቱን ተጠቅሞ ለአሁን እና ዘላለማዊ ውሳኔ ማድረግ ለመንፈሳዊ ዕድገቱ አስፈላጊ ነው። ለመማር በፍፁም ልጆች አይደላችሁም ለመለወጥም ያረጀ አይደላችሁም። ለመማር እና ለመለወጥ ፍላጎታችሁ የሚመጣው ከመለኮታዊ ዕድገት መጣጣር ነው።2 እያንዳንዱ ቀን ለዘላለማዊ ውሳኔ ዕድል ያመጣል።

እኛ የሰማይ ወላጆች መንፈሳዊ ልጆች ዘላለማዊ ፍጡሮች ነን። መፅሀፍ ቅዱስ እንደጠቀሰው፣ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።3 በቅርቡ ተወዳጅ የሆነው የልጆች መዝሙር እኔ የእግዚአብሄር ልጅ ነኝ 4የሚለውን ሰምቼ ነበር። ተገርምኩኝ፣ በእናቶች እና ታምኝ አባቶች አልፎ አልፎ ይህን ስዘምሩ ለምን አልሰማሁም? ሁላችንም የእግዚአብሄር ልጆች አይደለንም? ስለ እውነት ማናችንም የእግዚአብሄር ልጆች አለመሆናችን በፍፁም ማቆም አንችልም

እንደ እግዛብሄር ልጅነታችን በሙሉ ልባችን እና ነፍሳችን እሱን ከምድራዊ ቤተሰባችን የበለጠ መወደድ አለብን።.5 ጎሮበታችን እንደ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን መውደድ አለብን።6 ከዝህ የበለጠ ትዕዛዝ የለም። የሰዎች ህይወት ዋጋን በብዙ ደረጃ በፍፁም መወደስ የለብንም።

የሰው አካልና መንፈስ የሰዎች ህይወት እንደሆነ ቅዱስ መፅሀፍ ታስተምራል።.7 እንደ ጥንድ ፍጡር እያንዳንዳችሁ ዋጋ ልገመት ለማይችለው የአካልና መንፈስ ስጦታ እግዚአብሄርን ማመስገን አለባችሁ።

የሰው አካል

ለብዙ አመታት የህክምና ዶክተርነት ሙያዬ ለሰው ልጆች አካል ታላቅ ክብር እንድሰጥ አድርጎኛል። ለናንቴ እንደ ስጦታ በግዚአብሄር የተፈጠረ ነው፣ በፍፁም የሚያስገርም ነው። የሚያይ አይናችሁ፣ የሚሰማ ጆሮአችሁ እና የሚዳሥስ ጣታችሁን አስቡ። አንጎላችኈንድትማሩ፣ እንድታስቡ ያደርጋል። ልባችሁ እናንተ ሳታውቁ ያለድካም ቀንና ሌሊት ይነፋል።8

ሰውነታችሁ እራሱን ይጠብቃል። ህመም እንደ ማስጠንቀቂያ አንድ ነገር ትክክል እንዳልሆነ እና ትኩረት እንድደረግ ተብሎ ይመጣል። የቁስል ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ ይመጣል፣ ፀረ እንግዳ አካል በመፈጠር ቅስሉን እንድከላከል ያደርጋል።

አካላችሁ እራሱ ይጠግናል። ቁስል እና ሠንበር ይድናል። የተሰበረ አጥንት እንደገና ጠንካራ ይሆናል። እግዚአብሄር ከሰጣችሁ ብዙ ጥረት ያለው አካላችሁ ጥቅቶቹን ጠቅሻለሁ።

ምንም እንኳ በእያንዳንዱ ሰው ባይሆንም በአንዳንድ ቤተሰቦች ልዩ እንክብካቤ የሚስፈልጋቸው የአካል ሁነታዎች ይኖራሉ።9 ይህን ፈተና ለመቋቋም በጌታ የተሰጠ ዛዴዎች አሉ። ሰዎች ትሁት እንዲሆኑ ድካምን እሰጣቸዋለሁ፤ እናም ፀጋዬም እራሳቸውን በፊቴ ዝቅ ላደረጉ ሁሉ በቂ ነው፤ እነርሱም በፊቴ እራሳቸውን ዝቅ ካደረጉ እናም በእኔም እምነት ካላቸው ደካማ የሆኑትን ጠንካራ እንዲሆኑ አደርጋለሁ።10

አንዳኔ የኮከብ መንፈስ ፍፁም ባልሆነ አካል ልኖር ይችላል።11 የዝህ አይነት አካል ስጦታ ወላጆችን እና ልጆች ልዩ እንክብካቤ ለሚያስፍልገው የተወለደ ልጅ ጋር ህይወታችዋ እንድያዳብሩ ይረዳቸዋል።

የማርጀት ስጦታ ሂደት የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፣ ሞትም ስጦታ ነው። የሟችነት አካላችሁ ለእግዚአብሄር ታላቅ ዕቅድ ደስታ አስፈላጊ ነው።12 ለምን? ምክንያቱም ሞት መንፈሳችሁ ወደ እሱ እንድመለስ ያደርጋል።13 ከዘላለማዊ ገፅታ አመለካከት ሞት ያል ጊዜው የተከሰተ የሚሆነው ከእግዚአብሄርን ጋር ለመገናኘት ላልተዘጋጁ ብቻ ነው።

አካላችሁ ለእግዚአብሄር ዘላለማዊ ዕቅድ ዋነኛ አካል መሆን፣ ሀዋሪያው ጳውሎስ የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ14 ማለቱ የምያስገርም አይደለም። መስታወት ስትመለከቱ አካላችሁ በተመቅደሳችሁ መሆኑን ተመልከቱ። እውነታው በየቀኑ ለአካላችሁ እንደት እንደምታስቡ እንደት እንደምትጠቀሙ ውሳኔያችሁ ላይ ትፅዕኖ ያደርጋል። ይህም ውሳኔ የእጣ ፋንታችሁን ያረጋግጣል። ይህ እንዴት ልሆን ይችላል? ምክንያቱም አካላችሁ ለመንፈስ ቤተመቅደስ ነው። አካላችሁን እንዴት እንድምትጠቀሙ መንፈስ ላይ ውጤት ያመጣል። ዘላለማዊ ጉዞያችሁን የሚወስኑ አንዳንድ ውሳኔዎች ያቀፉት፣

  • አካልችሁን እንዴት መንከባከብ እና መጠቀም አለባችሁ?

  • የትኛውን መንፈሳዊ ባህርይ ለማዳበር ትመርጣላችሁ?

የሰዎች መንፈስ

መንፈሳችሁ ለዘላለም ብቻውን መኖር ይችላል። ጌታ ለነቢዩ አብረሀም ከመወለድህ በፍት ተመርጠሀል አለው።15 ጌታ እንድዚሁ ተመሳሳይ ለኤርምያስና 16 ሌሎች 17ብዙዎች ብሏል። ስለ እናንተ እንኳ ተናግረዋል።18

የሰማይ አባታችሁ ለብዙ ጊዜ አውቆአችዋል። በዝህን ወቅት እንደ ወንድ ልጁና ሴት ልጅ ወደ ምድር መጥታችሁ ለምድር ላይ ታላቅ ሥራው መሪዎች እንድትሆኑ መረጣችሁ።19 የተመረጣችሁ ለአካልችሁ ባህርይ ሳይሆንለመንፈስ ባህሪያችሁ ነው። ይህም በጀግንነት፣ በጉብዝና፣በልበ ንፁህ ታማኝነት፣ ለእውነት ጥማት፣ ለጥበብ በመራብ እና ሌሎችን ለማገልገል ፍላጎትን ያመጣል።

እንኝህን ባህሪይዎች ከመወለዳችሁ በፍት አዳብራችዋል። ሌሎች በዚህች ምድር20 ላይ በመፈለግ ማዳበር ትችላላችሁ።21

ዋናው የመንፈሳዊ ባህርይ እራስን መቆጣጠር ነው፣ የመብላት ፍላጎት ላይ ምክንያት ለማድረግ ብርታትን ማግኘት ነው። እራስን መቆጣጠር ጠንካራ ህሊና ያዳብራል። ህሊናችሁ አስቸጋሪ ነገር እና ፈተና ስያጋጥማችሁ ለስነምግባር አመላለሳችሁን ይወስናል። ፆም ማድረግ መንፈሳችሁን በማዳበር የመብላት ፍላጎትን እንድቋቋም ይረዳል። ፆምና ፀሎት የሰማይ እርዳታን ይጨምርላችዋል። እራስን መቆጣጠር ለምን አስፈለገ? እግዚአብሄር ለሰው ዘሮችዋነኛ የሆነውን የማፍቀር እና የመመገብ ፍላጎት ተክሎብናል።22 በእግዚአብሄር ህግ ራሳችን ስንገዛ በረጅም ህይወትና ታላቅ ፍቅር መደሰት እንችላለን።23

ስለዝህ የሚያስገርም አይደለም፣ ከእግዚአብሄር የእቅድ ደስታ የመባከን ፈተና የሚመጣው አስፈላጊ የሆነውን እግዚአብሄር የሰጣን ፍላጎት ካለ አግባብ ስንጠቀም ነው። ፍላጎታችን መቆጣጠር ሁል ጊዜ ቀላል አይደለም። ማናችንም ፍፁም በሆነ መቆጣጠር አንችልም። 24ስህተት ይፈጠራል፣ መሳሳት ይደረጋል። ሀጢያት ይደረጋል። ስለዝህ ምን ማድረግ አለብን? ክዝሁ መማር እንችላለን። እናም እውነተኛ የሆነ ንሰሀ መግባት እንችላለን።25

ባህርያችን መቀየር እንችላለን። ፍላጎታችን ልቀየር ይችላል። እንዴት? አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው። እውነተኛ እና ቋሚ ለውጥ ልመጣ የሚችለው በምያድነው እና በሚያነፃው የኢየሱስ ክርስቶስ ሀጢያት ክፍያ ሀይልብቻ ነው።26 እሱ እያንዳንዳችሁን ይወዳል።27 ትዕዛዙን በፍላጎት እና ከልብ በትክክል የሚትጠብቁ ከሆነ የእርሱን ሀይል እንድታገኙ ያደርጋችዋል። ቀላልና እርግጠኛ የሆነ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልis የለውጥ ወንጌል ነው።28

ሥጋዊ አካልን የሚቆጣጠር ሀይለኛ የሰው ዘር መንፈስ በጥልቅ ስሜት ሥር ባሪያ ሳይሆን አዛዥ ነው። የዝህ አይነት ነፃነት ኦክስጅን ለአካል አስፈላጊ እንደሆነ ይህም ለነፍስ በጣም አስፈላጊ ነው።ከራስ ባሪነት መላቀቅ እውነተኛ ነፃነት ነው።29

እኛ ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነፃ ነን፣ ወይም እስረንነትን፣ ስቃይን እና ሞትን ለመምረጥ ነፃ ነን።30 ወደ ዘላለማዊ ህይወትና የነፃነት መንገድ ግብረገብነት አስተሳሰብ ስንመርጥ ያ መንገድ ጋብቻን ያቀፈ ይሆናል።31 የኃለኛው ቀን ቅዱሳኖች በወንድና በሴት መሀከል ያለው ጋብቻ በግዚአብሄር የታወጀ መሆኑን ያውቃሉ። እናም ለፈጣሪ ልጆች ዘላለማዊ ዕቅድ ጉዞ ቤተሰቦች ዋነኛ አስፈላጊ እንደሆኑ ናቸው። ፆታም ከመወለዳቸው በፍት እና በምድር እናም ለዘላለማዊ አላማ አስፈላጊ የሆነ መለያ ባህሪይ መሆኑን እናውቃለን።32

በወንድና በሴት መካከል ያለው ጋብቻ ለጌታ ህግጋት እና ለእግዚአብሄር ዘላለማዊ እቅድ መሰረታዊ ነው። በወንድና በሴት መካከል ያለው ጋብቻ በምድር እና ስማይ ሙሉ ህይወት የሚሰጥ የእግዝአብሄር ንድፍ ነው። የእግዚአብሄር ጋብቻ ንድፍን መስደብ፣አለመግባባት ወይም አዛብቶ መተርጎም አይቻልም።33 እውነተኛ ደስታ የሚትፈልጉ ከሆነ! የእግዚአብሄር ጋብቻ ንድፍ ቅዱስ የሆነ ነፍስ የመፍጠር ሀይልን እና የጠበቀ የጋብቻ ወዳጅነትን ደስታን ይጠብቃል።34 አዳምና ህዋን የባልና ምስትነት ደስታ ልምድ ከማግኘታቸው በፍት በግዚአብሄር እንደተጋቡ እናውቃለን።35

በዘመናችን መንግስት ጋብቻን ለመጠበቅ ፍላጎት አላቸው፣ ምክንያቱም ጠንካራ ቤተሰብ ለጤንነት፣ ለትምህርት፣ ለበጎአድራጊነት እና በማደግ ላይ ላሉት ትውልዶች ብልፅግና ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለምያደርጉ ነው።36 ነገር ግን መንግስት በማህበራዊ ዝንባሌ እና መንፈሳዊ ባልሆኑ ፈላስፋዎች ተፅእኖ አድሮባቸዋል። እነሱም ህግን ለማስጠበቅ ደጋግመው ይፅፋሉ። ምንም እንኳ ህግ አውጪዎች የፈለጉትን ብያሳልፉ ስለጋብቻ እና ቅድስና የጌታ ህግጋት ሊለወጥ አይችልም።37 ምንም እንኳ ሀጥያት በህግ አውጭዎች ብወጣም በእግዚአብሄ ፍት ሀጢያት መሆኑን አስታውሱ።

የአዳኝን ርህራሄ የበለጠ በማሰብ ለግዚአብሄር ልጆች መብትና ስሜት ዋጋ ብንሰጥም ህግጋቱን መቀየር አንችልም። ለመለወጥ የኛ መብት አይደለም። የእሱ ህግጋት ማጥናት፣ መረዳት እና መደገፍ አንብን።

የአዳኝ የህይወት መንገድ ጥሩ ነው። መንገዱም ከጋብቻ በፍት ንፅህናን ያቀፈ እና ከጋብቻ በኃላም ሙሉ ታማኝነት ያስፈልጋል።38 ዘላቂ የሆነ የደስታ ልምድ የሚናገኘው በጌታ መንገድ ብቻ ነው። የእሱ መንገድ ለነፍሳችን ቋሚ ፅናት እና ለቤታችን ስላምን ያመጣል። እናም ከሁሉም በላይ የእርሱ መንገድ ወደ እሱ ቤት እና የሰማይ አባታችን ዘላለማዊ ህይወት ይመራናል።39 ይህ የእግዚአብሄር ሥራና ክብር ነው።40

ውድ ወንድሞች እና እህቶች እያንዳዱ ቀን የውሳኔ ቀን ነው። እና ውሳኔያችን ጉዞያችን ይወስናል። አንድ ቀን ሁላችንም ለዳኝነት በጌታ ፍት እንቆማለን።41 ሁላችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የግል ቃለ መጠይቅ ይኖረናል።42 ስለ አካላችን፣ስለ መንፈሳዊ ባህሪያችን እና ስለ እግዚአብሄር ጋብቻ ንድፍ እንዴት ክብር እንደሰጠን እና ስለ በቤተስ ያደረግነው ውሳኔያችን ተጠያቂዎች ነን። ይህንን ዘላለማዊ ውሳኔ በየዕለቱ ጥበባዊ በሆነ መምረጥ እንዳለብን የልብ ፅሎቴ በተቀደሰው ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።