2010–2019 (እ.አ.አ)
“አልጥልህም፥ አልተውህም”
ኦክተውበር 2013


“አልጥልህም፥ አልተውህም”

… የሰማይ አባታችን መቋቋም ባለብን ፈተናዎች ለመማር፣ ለማደግና፣ ለመጠናከር እንደምንችል ያውቃል።

በዚህ ምሽት በማስታወሻዬ ውስጥ ይህን እጸፋለሁ፣ “ይህ ጉባኤ ከተሳተፍኩባቸው አጠቃላይ ጉባኤዎች ሁሉ በላይ የሚያነሳሳ ነበር። ሁሉም ነገሮች ከሁሉም በላይ መንፈሳዊ ጉዳይ ነበር።”

ወንድሞችና እህቶች፣ ከስድስት ወር በፊት በዚህ አጠቃላይ ጉባኤ ስንገናኝ፣ ውድ ባለቤቴ ፍራንሲስ በአደገኛ ሁኔታ ወድቃ በሆስፒታል ተኝታ ነበር።በግንቦት ከተጎዳችበት ለመዳን ከታገለች በኋላ፣ ወደ ዘለአለም ሄደች። የእርሷ ሞት ከባድ ነበር። እርሷ እና እኔ በጥቅምት 7 ቀን 1948 ዓ.ም በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ ተጋብተን ነበር። ነገ የተጋባንበት 65 አመትን እናከብር ነበር።እርሷ የህይወቴ ፍቅር፣ የማምናት፣ እና ቅርብ ጓደኛዬ ነበረች። እናፍቃታለሁ ማለቴ የእኔን ስሜት የሚገልጽ አይደለም።

ይህ ጉባኤ በፕሬዘደንት ዴቪድ ኦ መኬይ እንደ አስራ ሁለት ሐዋርያ የተጠራሁበት 50 አመት ይማከብርበት ነው። በእነዚህ አመቶች በሙሉ የውድ ጓደኛዬን ድገፋ አገኝ ነበር። ከእርሷ እና ከልጆቹ በመራቅ በሀላፊነት የተሰጠኝን ሳከናውን በምንም የቅሬታ ቃል ከእርሷ ሰምቼ አላውቅም። በእርግጥም እንደ መልዓክ ነበረች።

ፍራንሲስ ከሞተች በኋላ ለእኛ ለነበረው ምክር የእኔንና የቤተሰቤን ምስጋና ለማቅረብ እፈልጋለሁ። ብዙ መቶ ፖስታዎችና ደብዳቤዎች ለእርሷ ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ እና ለቤተሰባችንም የሀዘን መግለጫን ተልከውልን ነበር። በእርሷ ስም ለቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ የሚስዮን ገንዘብ በበጎ ድርገት ለተሰጡትም እርዳታዎች በጣም እናመሰግናለን። በልብ ከመጣውና ለደግ ቃላቶቻችሁም ዝልቅ ምስጋና አቀርባለሁ።

በዚህ በመለያየታችን ጊዜ ለእኔ ከፍተኛ ምቾት ይሰጠኝ የነበረው ስለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ያለኝ ምስክርነት እና ውዷ ፍራንሲስ ህያው እንደሆነች በማወቄ ነው። የተለያየንበት ጊዜአዊ እንደሆነ አውቃለሁ። በምድር እና በሰማይ ውስጥ ለማስተሳሰር ስልጣን በነበረው ሰው በእግዚአብሔር ቤት እንደተሳሰርን አውቃለሁ። አንድ ቀን እንደገና እንደምንገናኝ እና መብንም እንደገና እንደማንለያይ አውቃለሁ። ይህም እውቀት ይደግፈኛል።

ወንድሞችና እህቶች፣ ማንም ሰው ሀዘን እና ስቃይ ሳያገኝ አይኖርም ለማለት አይቻልም፣ ወም በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ መተራመስና መሰቃየት ያልነበረበት ጊዜ የለም።

የህይወት መንገድ ወደ መጥፎ ሁኔታ ሲዞር፣ “ለምን እኔን?” የሚል ጥያቄ ለመጠየቅ ግፍፍት ይኖራል። አንዳንዴ ችግሩ መጨረሻ የሌለው ይመስላል፣ ጨለማውን የሚያጠፋ የጸሀይ ብርሀን ያለም አይመስልም። በተሰበረ አላማ ተስፋ በቆረጥ እና በጠፉ ተስፋዎች ፍርሀት ምክንያት እንደተከበብን ይሰማንል። በመፅሐፍ ቅዱስ ያለምንም ልመና እንዲህ እንደግማለን፣ “በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን?”1 እንደተረሳን፣ ልባችን እንደተሰበረ፣ እና ብቸኛ እንደሆንን ይሰማናል። የግል መጥፎ እድላችንን መጥፎ ሀሳብ ባለበት አስተያየት እንመለከተዋለን። በአብዛኛው ጊዜ የሰማይ ትዕግስት እንደሚያስፈልግ እየረሳን፣ ለችግራችን መፍትሄ ለማግኘት እንቸኩላለን።

የሚመጡብን ችግሮች ለመፅናት ያለንን ችሎታ ይፈትኑልናል። በእያንዳንዳችን መመለስ ያለ መሰረታዊ ጥያቄም አለ፥ ልደናቀፍ፣ ወይስ ልፈፅም? አንዳንዶች ከፈተናቸው በላይ ከፍ ለማለት በማይችሉበት ምክንያት ይደናቀፋሉ። ለመፈጸም እስከ ህይወት መጨረሻ ድረስ መፅናትን ያስፈልገዋል።

የሚደርሱብንን ነገሮች ስናስብባቸው፣ ከጥንቱ ኢዮብ ጋር “ሰው እንዲሁ ለመከራ ተወልዶአል”2 እላለን። ኢዮብ “ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ”3 ሰው ነበር። በሚያደርገው ጻድቅ፣ በንብረቱ ሀብታም የነበረው ኢዮብ ማንንም ሰው ሊያጠፋ ይችል የነበረ ፈተና አጋጠመው። ንብረቶቹን አጥቶ፣ በጓደኞቹ ተሰድቦ፣ ተሰቃይቶ፣ ቤተሰቡን በማጣት አዝኖ፣ “እግዚአብሔርን ስደብና ሙት”4 ተብሎ ነበር። ይህን ፈተና ተቋቋመ እናም ከልዑል ልቡም እንዲህ በማለት አወጀ፥

አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ የሚመሰክርልኝም በአርያም ነው።”5

“እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ...አውቃለሁ።” 6

ኢዮብ እምነቱን ቀጠለ። ወደ እኛ የሚመጡት ፈተናዎች ሲያጋጥሙን እንደ ኢዮን እናደርጋለን?

በህይወት ምታት ምክንያት ሽከም እንዳለን ሲሰማን፣ ሌሎች እንዲህ አጋጣሚ እንደነበራቸው፣ እናም እንዳሸነፉት እናስታውስ።

በዚህ የጊዜዎች ፍጻሜ ዘመን ውስጥ የቤተክርስቲስያኗ ታሪክ ትግል ቢኖርባቸውም ቀጥተኛና ደስተኛ በሆኑት አጋጣሚዎች የተሞላ ነው። ምክንያቱ ምንድን ነው? የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን የህይወታቸው ዋና ክፍል አደረጉት። ከሚያጋጥመን የሚያድነንም ይህ ነው። አስቸጋሪ ፈተናዎች ይኖሩናል፣ ነገር ግን እነዚህን ለመቋቋ እና ለማሸነፍ ችሎታ ይኖረናል።

ከበሽታ መኝታ፣ በእምባ ከረጠበ ትራስ፣ “አልጥልህም፥ አልተውህም”7 በሚለው በመለኮታዊ ማረጋገጫ እና ውድ ቃል ኪዳን በሰማይ ከፍ እንላለን።7 እንደዚህ አይነት መፅናኛ ታላቅ ዋጋ አለው።

በአለም አቀፍ የጥሪዬን ሀላፊነት ለማሟላት ስጓዝ፣ ብዙ ነገሮችን ለማወቅ ችያለሁ –– ከእነዚህም ታናሽ ያልሆነውም ሀዘን እና ስቃይ ሀለንተናዊ እንደሆነ ነው። በሀዘን ያሉትን፣ የታመሙትን፣ ከጋብቻ መፋታት የሚያጋጥማቸውን፣ መንገዳቸውን ያጡ ልጆች ያላቸውን፣ ወይም በኃጢያት ምክንያት የሚሰቃዩትን ስጎበኝ ለመግለጽ የማይቻል የልብ መሰበር እና ሀዘን ተመልክቻለሁ። ዝርዝሩ ረጅም ነው, ምክንያቱም ሊደርሱብን የሚችሉ ችግሮች ለመቆጠር አይቻሉምና። አንድ ምሳሌን አውጥቶ ለመጠቆም አስቸጋሪ ነው፣ ግን ስለፈተና ሳስብ ሀሳቤ በልጅነቴ የሰንበት ትምህርት አስተማሪ ስለነበሩት ወንድም ብረምስ ይሄዳል። እርሳቸውም በጣም ጡ የሆኑ ታማኝ የቤተክርስቲያኗ አባል ነበሩ። እርሳቸው እና ባለቤታቸው ሴዲ ስንት ልጆች ነበሯቸው፣ እድሜአቸውም ከእኛ ቤተሰብ ካሉት ካር አንድ የሆነ ነበር።

ፍራንሲስ እና እኔ ከተጋባንና ከዎርዱ ከወጣን በኋላ፣ ወንድም እና እህት በርምስ እና ቤተሰቢቻቸውን በጋብቻና በለቅሶዎች ጊዜ እናያቸው ነበር።

በ1968 ዓ.ም ወንድም በርምስ ባለቤታቸውን በሞት አጡ። አመቶችም ሲያልፉ ከስምንቱ ሁለት ልጆቻቸውም ሞቱባቸው።

ከ13 አመት በኋላ አንድ ቀን፣ የወንድም ብረም የልጅ ልጅ በስልክ ደወለችልኝ። አያቷ 105ኛ አመታቸው ላይ እንደደረሱ ነገረችኝ። እንዲህም አለች፣ “በትንሽ መንከባከቢያ ቦታ ይኖራሉ፣ ግን በየሳምንቱ በሰንበት ከቤተሰባቸው ጋር ተገናኝነትው የወንጌል ትምህርትን ያስተምራሉ።” ቀጥላም፣ “ባለፈው እሁድ አያታችን እንዲህ አሉን፣ ‘ውዶቼ፣ በዚህ ሳምንት እሞታለሁ። ቶሚ ሞንሰንን እባካችሁ ጥሩልኝ። ምን መደረግ እንደሚገባው ያውቀዋል።’”

ወንድም ብረምስን በሚቀጥለው ምሽት ጎበኘኋቸው። ለብዙ ጊዜ አይቻቸው አላውቅም ነበር። መስማት ስለማይችሉ ላነጋግራቸው አቻልኩም። አይናቸው ስለማያይ እንዲያነቧቸው የሚችሉትን መልእክት ልፅፍላቸው አልቻልኩም። ቤተሰባቸው ሊያነጋገሯቸው የሚችሉት የቀኝ እጃቸውን ይዘው የሚጎበኘውን ሰው ስም በግራ እጃቸው ላይ መመጻፍ እንደሆነ ተነገረኝ። የተነሩኝን ተከትዬ በእጃቸው ላይ በልጅነት በሚያውቁኝ ስም “ቶሚ ሞንሰን” በማለት ጻፍኩኝ። ወንድም ብረምስ ተደሰቱ፣ እናም እጆቼን ወስደው በራሳቸው ላይ አሳረፉ። ፍላጎታቸው የክህነት በረከት ለመቀበል እንደሆነ አወቅሁኝ። ከዚያም በኋላ እምባ በፊታቸው ላይ ፈሰሰ። እጆቼንም በምስጋና አጥብቀው ያዙ። ምን እንኳን የሰጠናቸውን በረከት ለመስማት ባይችሉም፣ መንፈስ በዚያ ጠንካራ ነበር፣ እናም ያስፈለጋቸውን በረከት እንደሰጠናቸው ለማወቅ መነሳሻ እንደነበራቸው አምናለሁ። ይህ አስደሳች ሰም ለማየት አይችሉም ነበር። ለመስማትም አይችሉም ነበር። በሚንከባከቡበት ቦታ በቀንም ይሁን በምሽት በትንሽ ክፍል ውስጥ ይቀመጡ ነበር። ነገር ግን በፊታቸው የነበረው ፈገግታ እና የተናገሩት ቃላት ልቤን ነክተው ነበር። አመሰግናለሁ፣ የሰማይ አባቴ ለእኔ መልካም ነበር” አሉ።

ከሳምንት በኋላ፣ ልክ ወንድም ብረምስ እንዳሉት ሞቱ። ባልነበራቸው ላይ አላተኮሩም፤ ግን ለነበራቸው ብዙ ለነበራቸው በረከቶች ዝልቅ ምስጋና ሁልጊዜም ነበራቸው።

የሚያስደስቱን ብዙ ነገሮች የሚሰጠን የሰማይ አባታችን መቋቋም ባለብን ፈተናዎች ለመማር፣ ለማደግና፣ ለመጠናከር እንደምንችል ያውቃል። ልባችን የሚሰበርበት እና የምናዝንበት፣ የናለቅስበት፣ እና ምን ያህል እንደምንችል የሚመዝንበት ጊዜም እንደሚኖር ያውቃል። ነገር ግን፣ እንደዚህ አይነት ችግሮች ለሚሻል ሁኔታ እንድንቀየር፣ የሰማይ አባታችን በሚያስተምረን መሰረት ህይወታችንን እንድንገነባ፣ ከነበርንበት የተለየ፣ እንዲሁም የተሻለ እንድንሆን፣ ከዚህ በፊት የተሻለ እውቀት እንዲኖረን፣ የሌሎች ጉዳን የሚሰማን እንድንሆን፣ እና ከነበረን በላይ የሆነ ምስክሮች እንዲኖረን ያደርጉናል።

ይህም አላማችን መሆን ይገባዋል–– በጸሀይ ብርሀን እና በጥላ ስንሄድም የምንቋቋምና የምንጸና፣ አዎን፣ ደግሞም በተጨማሪ በመንፈስ የተጣራን መሆን ይገባናል። በምናሸንፋቸው ፈተናዎች እና በምንቋቋማቸው ችግሮች ባይሆን ኖሮ፣ እንዳለንበት የዘለአለም ህይወት ወደሆነው አላማችን በትንሽም ይሁን በምንም አናድግም ነበር። ገጣሚው በሚቀጥሉት ቃላት ይህንንም ሀሳብ አቅርቦ ነበር፥

ጥሩ እንጨት በቀላል አያድግም፣

ጠንካራው ንፋስ፣ ዛፉን ያጠናክራልና።

ሰማይም ሲርቅ፣ ርዝመቱ ታላቅ ነው፣

አውሎ ንፋሱ ሲጨምር፣ ጥንካሪውም ብዙ ነው።

በጸሀይና በብርድ፣ በዝናብና በበረዶ፣

በዛፍና ሰዎች፣ ጥሩ እንጨት ያድጋል።8

መምህር ብቻ የፈተናችንን ዝልቅነት፣ ህመማችንን፣ እና የምንሰቃይበትን የሚያውቅው። በፈተና ጊዜ ዘለአለማዊ ሰላም የሚያቀርብልን እርሱ ብቻ ነው። የሚሰቃየውን ነፍሳችንን በሚያፅናኑ ቃላት የሚነካውም እርሱ ብቻ ነው፥

“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።

“ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤”

“ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።”9

መልካም ጊዜ ይሁን መጥፎ፣ እርሱ ከእኛ ጋር ነው። እንደማይቀየርም ቃል ገብቶልናል።

ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በህይወት ፈተና ጊዜ የማይቀንስ እና የማይጨምር ለሰማይ አባታችን ታማኝነት ይኑረን። እርሱን ለማስታወስ ችግሮች እንዲያጋጥሙን አያስፈልጉን፣ እናም ለእርሱ እምነታችንን ለመስጠት ወደ ትሁትነት መገፋት አያስፈልገን።

ወደ ሰማይ አባታችን ለመቅረብ ሁልጊዜም እንጣር። ይህን ለማድረግ፣ ወደ እርሱ እንጸልይ እና በየቀኑም እርሱን እናድምጥ። የጸሀይ ብርሀን ወይም የዝናብ ቀን ቢሆኑም፣ ሁልጊዜ እርሱን እንፈልጋለን። እንዲህ የሚለው የእርሱ ቃል ኪዳን እኛ የምንፈልገው ይሁን፣ “አልጥልህም፥ አልተውህም።”10

በነፍሴ ጥንካሬ በሙሉ እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ እንደሚያፈቅረን፣ አንድያ ልጁ ህያው እንደሆነ እና ለእኛ እንደሞተ፣ እናም የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በህይወታችን ጭለማ ሰብሮ የሚገባው ብርሀን እንደሆነ እመሰክራለኁ። ይህም እንዲሆን የምጸልየው በቅዱሱ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።