2010–2019 (እ.አ.አ)
ሰቆቃመ ኤርምያስ፥ ስለባርነት ተጠንቀቁ
ኦክተውበር 2013


ሰቆቃመ ኤርምያስ፥ ስለባርነት ተጠንቀቁ

የእኛ ፈተናችን የትኛዉንም ባርነት ማስወገድ ነው፣ጌታን የተመረጡትን እንዲሰበስብ እና ለሚነሳዉ ትዉልድ መስዋት ማድረግ።

በጋብቻችን መጀመሪያ ላይ ባለቤቴ ሜሪ፣እና እኔ ሁለታችንም የምንካፈልባቸዉን እንቅስቃሴዎች ለመምረጥ ወሰንን። አቅማችንንም ያገናዘበ እንዲሆንም ፈለግን። ሜሪ ሙዚቃ በጣም ትወዳለች እና እኔ እስፖርት ላይ በታም እንዳላተኩር ታስብ ነበር እናም ለማንኛዉም ለተገዛ የ ኳስ ጨዋታ የ ሙዚቃ፣አኦፔራ እና ባህላዊ ድርጊቶች ትኬት ለመግዛት ተስማማን።

በመጀመሪያ ኦፔራዉን ተቃዉሜ ነበር ግን ከግዜ ብህዋላ ሃሳቤን ቀየርኩ። 1 የጉሰፔ ቨርዲ ኦፔራ በተለይ ወድጄዉ ነበር። ይህ ሳምንት የእርሱ የ200 አመት ልደቱ ነው።

በወጣትነቱ ቨርዲ በ ነብዩ ኤርሚያስ ይማረክ ነበር እና በ 1842 ናቡኮ, በተባለዉ የኦፔራዉ ስራዉ ዝናን አተረፈ ። ይህ ኦፐራ ከ አኤርሚያስ እና መዝሙረ ዳዊት ከብሉ ኪዳን መጸሃፍ የተወሰደ ሃሳብ የያዘ ነበር። የኦፔራው ሃሳብ የእየሩሳሌም ወደቀትን እና የ አይሁዳዉያን ወደባርነት መወሰድን ያካትታል። መዝሙረ ዳዊት 137 ነበር የ ቨርዲ መነሻ “በባርነት ቀምበር ዉስጥ በባቢሎን ወንዝ አጠገብ አይሁዳዊያን አለቀሱ-በሃዘናቸው ምክንያት ፣ የ ጺዮንን መዝሙር ሊዘምሩ አልቻሉም። ”

አላማዮ ብዙ አይነት በደሎችን እና የባርነት ቀንበርን መዳሰስ ነው። የአሁኑን ግዜ ሁኔታ እና ከእየሩሳሌም ውድቀት በፊት የነበረዉን የእነ ኤርሚያስን ግዜ አዛምዳልሁ። የዚህን የማስጠንቀቂያ ድምጽ ሳቀርብ፣ምስጋና አለኝ አብዛኛዎቹ የቤተክርስቲያን አባላት በጸድቅታ በአኤርሚያስ ግዜ ለጌታ አጸያፊ የነበሩትን ባህሪያት በማስወገዳቸዉ።

የኤርሚያስ ትንበያዎች ለኋለኛዉ ቅዱሳን አስፈላጊ ናቸዉ። ኤርሚያስ እና የሱ ግዜ እየሩሳሌም የመጽሃፈ ሞርሞን የጅማሬ ምረአፎች ናቸዉ። ኤርሚያስ የግዚያችን ሌሂ ነበር። 2 ጌታ ኤርሚያስን አስቀድሞ አስጠንቅቆታል፡ “በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። ”3

ሌሂ የተለየ ጥሪ፣ተል እ ኮ ከጌታ ነበረው። በወጣትነቱ ሳይሆን በአዋቂነቱ ነበር የተጠራዉ። በመጀመሪያ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ነበር ግን ከዛ እንደኤርሚያስ ተመሳሳይ መለክቶችን ከገለጠ ብኋላ፣ጌታ ቤተሰቦቹን ይዞ ወደ በርሃ እንዲሰደድ አዘዘው። 4 ይህን ሲያደርግ፣ሌሂ የሱን ቤተሰቦች ብቻ ሳይሆን መላዉን ህዝብ ነበር የባረከዉ።

ከእየሩሳሌም ጥፋት 5 በፊት ጌታ ለኤርሚያስ የሰጠዉ መለክት ተደጋጋሚ ናቸው። እሱም አለ፡

“ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋልና፤ እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል፥

“…  የተቀደዱትንም ጉድጓዶች፥ ውኃውን ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጉድጓዶች፥ ለራሳቸው ቆፍረዋል። ”6

በእየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ ስለሚመጣው ጥፋት ስናወራ ፣ ጌታ አለ “መርሁ አልፍዋል፣በጋዉ አብቅቷል እናም አልዳኑም። ”7

እግዚአብሄር ወንዶች እና ሴቶች በ ክፉ እና በጎ መካከል ነጻ ዉሳኔ እንዲወስኑ ፈልግዋል። የክፋት ውሳኔዎች ባህል ወይም የሃገር የመገለጫ ባህሪያት ሲሆኑ በዚህም ሆነ በመጪዉ ሂዎት ወሳኝ የሆነ ውጤት ይኖራቸዋል። ሰዎች ለጎጂ እጾች እና ነገሮች ብቻ ሳይሆን ለጎጂ እና ሱስ ለሚያስይዙ ከቅዱስ ህይወት ለሚያወጡ ፍልስፍናዎች ባሮች ሊሆኑ ይችላሉ።

እውነተኛዉን እና ህያዉን እግዚአብሄርን ከማምለክ የውሸት አምላኮችን እንደ ሃብት እና ዝናን ማምለክ እና ግብረገብ የሌለው እና ጻድቅ ያልሆነ ስራ ላይ መሰማራት በሁሉም መልኩ ወደ ባርነት ይወስዳል። ይህም መንፈሳዊ፣አካላዊ እና አምሮአዊ ባርነት አንዳንዴ ጥፋትን ያመጣል። ኤርሚያስ እና ሌሂ አስተምረዋል ጻድቅ የሆኑት ጌታን ቤተክርስቲያኑን እና መንግስቱን እንዲያቋቁም በማድረግ የተበታተኑትን እስራአኤላዊያንን በመሰብሰብ መርዳት አለባቸው። 8

ይህ መለክት በሁሉም ዘመናት ሲስተጋባ እና ሲተገበር ኖርዋል። የእየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመመለሱ ላይ ናቸዉ በዚ መጨረሻ ግዜ።

የአይሁዳዉያን ባርነት እና የተበታተኑት የእስራኤል ነገዶች አስሩን ነገድ ጨምሮ ወንጌሉን በመመለሱ ላይ አንዱ የትምህርቱ አካል ናቸው። የጠፉት አስሩ የእስራኤል ነገዶች የሰሜናዊዉን የእስራኤልን መንግስት አቋቋሙ እናም በ 721 ም አ ወደ አስሪያ ባርነት ገቡ። ወደ ሰሜናዊ ሃገራት ሄዱ። 9 አሰረኛዉ የእምነት አንቀጻችን ይህን ይላል “በእስራኤል መሰብሰብ እና በአስሩ ነገዶች መምጣት እናምናለን። ”10 ጌታ ለአብረሃም ቃል እንደገባዉ የአብረሃም ዘር በቻ ሳይሆን ሁሉም የምድር ሰው ሁሉ እንደሚባረክ እናምናለን። ሽማግሌ ሩሴል አኤም ኒልሰን እንዳሉት፣ስብሰባው “የአካል ቦታ አይደለም፡የግል ቃል ኪዳን ነው። ”ሰዎች ወደ ጌታ እዉቀት ሊመጡ ይችላሉ” [3 ኔፊ 20:13] ቤታቸዉን ሳይለቁ። ”11

ትምህርታችን ግልጥ ነው “ጌታ አስራሁለቱን ነገዶች የበተናቸዉ እና ያሰቃያቸዉ በአመጸኝነታቸዉ እና ጻድቅ ባለመሆናቸዉ ነው። ነገር ግን የዚህን የተመረጡትን ህዝቦች መበታተን ጌታ እነዛኑ ህዝቦች ለመባረክ ተጠቅሞበታል። ”12

ከዚ ግዜ ጠቃሚ ትምህርቶችን እንማራለን። በሃይላችን ሁላ ሃጥያትን እና አመጸኝነትን ወደ ባርነት የሚመሩንን ለማስወገድ መስራት አለብን። 13 የጽድቅና ኑሮ ጌታን የተመረጡትን እና እስራኤላዊያንን እንዲሰበስብ በማድረጉ የምንረዳበት መስፈርት ነው።

ባርነት፣ሱሰኝነት በተለያዩ መልኩ ይመጣሉ። የአካል ባርነት ሊሆኑ ይችላሉ ግን እድገታችንን የሚቀጩ የ ሞራል ነጻነትን የሚያሳጡም ይሆናሉ። ኤርሚያስ የእስራኤል ውድቀት እና የባቢሎን ወደ ባርነት መወሰድ ከ ሃጢያተኝነት እና አመጸኝነት እንደመጣ በግልጽ ያስቀምጣል። 14

ሌላዉ አይነት ባርነት ለሰው መንፈስ መጥፋት እኩል ናቸዉ። 15 የሞራል ነጻነት በተለያዩ መልኩ ሊበላሹ ይችላሉ። በአሁኑ ባህል ታዋቂ የሆኑቱን አራቱን እጠቁማለሁ።

በመጀመሪያ፣ነጻነትን የሚያጎድል ሱሰኝነት፣የሞራል እምነትን ይጻረናል እና ጥሩ ጤንነትን በማጥፋት ባርነትን ይፈጥራል። የ እጽ እና አልክሆል ተጽፍኖ፣የራቁት ምስል፣ቁማርተኝነት፣የፋይናንስ ችግርን እና ሌሎች ስቃዮችን በማምጣት የማህበረሰብ ሸክም መሆን መቁጠሩ እራሱ አስቸጋሪ ነው።

ሁለተኛ ሱሰኝነት ወስጣዊ መጥፎ ባይሆንም ለምልካም ነገሮች ማዋል የምንችለዉን ግዜያችንን ይወስዳል። ይህም ማህበራዊ ገጾችን ፣ቪዲዮችን፣ስፖርቶችን፣መዝናኛዎችን እና ብዙ ሌሎች አላግባብ መጠቀም ያካትታል። 16

በብዙ ባህሎች ለቤተሰብ የምንሰጠዉ ግዜ ወሳኝ ጉዳይ ነው። በህግ ቢሮዋችን ብቸኛዉ የቤተክርስቲያኑ አባል ሳለሁ፣አንድ ሴት ጠበቃ እንዴት ብቻዋን ሶስት ኩዋሶችን እየወረወረች መሆኑን አብራራች። አንዱ ኳስ የህግ ሙያዋ፣አንዱ ደግሞ ጋብቻዋ ሌላዉ ደግሞ ልጆቿ ነበሩ። ለራሷ ግዜ መስጠት አቁማ ነበር። አንዱ ኳስ መሬት ላይ መሆኑ ያሳስባት ነበር። በግሩፕ ተሰብስበን ቅድሚያ የምንሰጣችዉን ነገሮች እንድንወያይ ሃሳብ አቀረብኩ። የምንሰራበት ዋንኛዉ ምክንያት ቤተሰቦቻችንን ለመርዳን መሆኑን ተስማማን። በዙ ገንዘብ መስራት ከቤተሰብ እንደማይበልጥ ተስማማን፣ነገር ግን ደንበኞቻችንን በምንችለዉ አቅም መርዳት አስፈላጊ መሆኑን ተረዳን። ወይይቱ ከዛ ስራ ላይ እያለን ስለምንሰራቸዉ አላስፈላጊ ነገሮች አመራ። ስራ ላይ እንድናሳልፍ የሚያደርገን አላስፈላጊ የሆነ ተጸእኖ ነበር?17 ግባችን ቤተሰባችን እንዲሆን ተስማማን። ለቤተሰባችን ጌዜ ለመስጠት ግምባር ቀደም እንሁን።

ሶስተኛ፣አለማቀፋዊዉ ባርነት በጊዚያችን ከ እየሱስ ክርስቶስ ወንጊኤል ጋር የማይሄድ ፖለቲካዊ እምነት ወይም ሃሳብ ነው። የሰዎችን ፍልስፍና የወንጌልን እዉነታ እንዲቀይር ማድረግ ከአዳኝ መለክት እንድንርቅ ያደርገናል። ሃዋሪያዉ ጳውሎስ አቴንስን በጎበኘበት ወቅት የ እየሱስ ክርስቶስን ትንሳአኤ ለማስተማር ሞክርዋል። የሱን ጥረት በሃዋሪያ ስራ ላይ እናነባለን “የአቴና ሰዎች ሁሉና በዚያ የኖሩ እንግዶች አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር በሌላ ጉዳይ አይውሉም ነበርና።”18 ህዝቡ የፓዉሎስን ቀላል የእምነት ትምህርት ባህሪ ከተረዳ ብኋላ አዲስ ባይሆንም አልተቀበሉትም።

ይህ የጊዚያችን መገለጫ ነው፣የወንጌል እዉነታዎች ሲተዉ እና ሲቀየሩ ወየም ከግዚያዊ ባህሎች እና ፍልስፍናዎች ጋር እንዲሄዱ ሲደረጉ ። ካልተጠነቀቅን ፣በ ኧምሮአዊ ባርነት ውስጥ ልንገባ እንችላለን። አሁን ብዙ ድምጾች አሉ ሴቶችን እንዴት መኖር እንዳለባቸው የሚነግሩ።19 እርስ በእርሳቸዉ ይቃረናሉ። የሚያሳስበዉ እናት ለመሆን መስዋትነት በመክፈል የሚጥሩትን ሴቶችን የሚወቅሱት እና የሚያንኳስ ሱት ፍልስፍናዎች ናቸዉ።

ከትንሽ ወር በፊት ሁለቱ ሴቶች የልጅ ልጆቻችን ጎበኙን። ቤት ነበርኩ እና በሩን ከፈትኩ። ባለቤቴ ሜሪ፣ሌላ ክፍል ዉስጥ ነበረች። ከተቃቀፍን ብኋላ፣አንዳይነት ነገር አሉ። ዞር ዞር በለዉ አየተዉ “በአያታችን ቤት ስንሆን ደስ ይለናል። አያታችን የታለች?። አሉ። አላልኳቸዉም ግን አሰብኩ “የሄ የወንድ አያታቹ ቤት ጭምር አይደል?። ግን ገባኝ ልጅ እያለሁ፣ቤተሰባችን የሴት አያቴ ቤት ይሄድ ነበር። የማስታዉሰዉ መዝሙር መጣ ወደ ኧምሮዮ፡ “በወንዙ ላይ በጫካ ዉስጥ ወደ ሴት አያቴ ቤት እንሂድ። ” የሚል።

አሁን ልበል ለሴቶች በተዘረጋዉ የተምህርት እና ሌሎች እደሎች እገረማለሁኝ። ወገብ የሚሰብረዉ ሰራ እና ከሴቶች የሚጠበቀዉ የቤት ዊስጥ ሃላፊነት ሴቶች በብዙ ዘርፎች በሚያደርጉት አስተዋጾ እና በዘመናዊዉ ምቾት እየቀነሰ መሆኑን አደንቃለሁኝ። ነገርግን ባህላችንን ልዩዉን ልጆች ከ እናቶቻቸዉ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት እንዲቀንሱ ብናደርግ እንጸጸታለን።

አራተኛዉ፣ልባዊ ሃይማኖታዊ መርህዎችን የሚጻረን ወደ ባርነት ሊመራ ይችላል። አንዱ መንገድ ጻድቃን ለ እግዚአብሄር ለድርጊታቸዉ ሃላፊነትን የሚወስዱት ኧምሮአቸዉን የሚጻረን ነገር ሲያደርጉ ነው-ለምሳሌ፣የጤና ባለሙያዎች ማስወረደን መምረጥ ወየም ስራቸዉን ማጣት ለመምረጥ ሲገደዱ ነው።

ቤተክርስቲያኑ አነስተኛ ነው ከንደነዛ አየነት ሰዎች ጋር ሲዛመድ። ማህበረሰብን መለወጥ አስቸጋሪ ነው፣ግን የሚከበንን የ ሞራል ባህል ለማሻሻል መስራት አለበን። የኋለኛዉ ቀን ቅዱሳን በሁሉም ሃገር ጥሩ ዜጋ፣በማህበረሰባዊ ተግባራት ዉስጥ መሳተፍ፣እራሳቸዉን በጉዳዮች ላይ ማስተማርን እና መምረትን መሆን አለባቸዉ።

ትኩረታችን፣ቤተሰቦቻችንን እና መጪዉን ትዉልድ መጠበቅ ላይ መስዋትነት መክፈል መሆን አለበት።20 አብዛኛዉ በባርነት ወየም ሱሰኝነት ዉስጥ አየደለም። ኤርሚያስ እና ሌሂ ከለመዱት ልምድ ከሚመሰል አለም ለማዉጣት መርዳት አልብን። በተጭማሪ፣የተቀደሱ ቃልኪዳኖችን እንዲፈጽሙ ለማዘጋጀት መርዳት አለብን።21 ት እና ቃ እንደሚነበበዉ “ጻድቃኖች ከሁሉም ህዝብ መካከል ወተዉ ይሰበሰባሉ እናም ጽዮን ትመጣለች የዘላለም የደስታ መዝሙር በመዘመር። ” 22

ጥረታችን ባርነተን ማስወገድ ነው፣ጌታን እጩዎቹን እንዲመርጥ መርዳት እና ለሚነሳዉ ትዉልድ መስዋት ማደረግ። እራሳችንን እንደማናደን ሁሌም ማስታወስ አለብን። በፍቅሩ፣ሞገሱ እና በ አዳኝ ሃጥያት ክፍያዉ ነጻ ወተናል። የሌሂ ቤተሰብ ሲሰደድ፣በ ጌታ ብርሃን ነበር የተመሩት። ለብርሃሁ እዉነተኛ ከሆንን፣ት እዛዙን የምንከተል ከሆነ እና በእጣ ፋንታዉ ላይ የምንመረኮዝ ከሆነ ከ መንፈሳዊ፣አካላዊ እና አ እምሮአዊ ባርነት የምናስወግድ ከሆነ ሊያደነን ይችላል።

በባርነት የወደቁትን ሃዘን እና መከራ እናስወግድ እናም የ ጺዮንን መዝሙር እንዘምር። በየሱስ ክርስቶስ ስም ፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Many Verdi operas, like Aida, La traviata, and Il trovatore, are among the most popular operas performed across the world today.

  2. 1 ኔፊ 5:137:14 ተመልከቱ

  3. ኤርምያስ 1:5.

  4. 1 ኔፊ 2:2–3 ተመልከቱ

  5. The destruction of Solomon’s temple, the downfall of Jerusalem, and the captivity of the tribe of Judah occurred in about 586 b.c.

  6. ኤርምያስ 2:11፣ 13

  7. ኤርምያስ 8:20. ኤርምያስ ከዚህ በፊት ጌታ ንስሀ እንዲገቡያለቀሰውን፣ “ልቤ በጣም ታምሞአል” (ኤርምያስ 4:19) እና የለመነውን፣ “ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ” (ኤርምያስ 5:1)።

  8. ኤርምያስ 311 ኔፊ 10:14 ተመልከቱ።

  9. 2 ነገሥት 17:6፤ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110:11

  10. የእምነት አንቀፅ 1:10፤ ደግሞም 2 ኔፊ 10:22 ተመልከቱ።

  11. Russell M. Nelson, “The Book of Mormon and the Gathering of Israel” (address given at the seminar for new mission presidents, June 26, 2013).

  12. Guide to the Scriptures, “Israel,” scriptures.lds.org.

  13. ጌታ በዚህ ቀን እንዲህ ብሏል፣ “እና አለምም ሁሉ በኃጢአት ተይዟል ፣ እናም ለበጭለማ እና በኃጢአት ባርነት ስር ይቃሰታል። እናም በዚህም በኃጢአት ለባርነት ስር እንደሆኑም ታውቃላችሁ፣ ምክንያቱም ወደ እኔ አይመጡምና።” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84:49–50)።

  14. ንጹህ ሰዎች በባርነት ሊወድቁም ይችላሉ።

  15. የትምህርት መርሆች አይለወጡም፣ ነገር ግን የባርነት፣ የተገዢነት፣ እና ጥፋት ከዚህ በፊት በማይታወቅ ሁኔታ ፈጥነዋል።

  16. ይህም በNew York Times Magazine ባለፈው አመት (Apr. 8, 2012) በሚያስቅ ሁኔታ የኮምፒውተር ጨዋታ ሱስ እንደሚያመጣ አትመውበት ነበር። ምንባቡምእንዲህ ነበር፣ “ወዲያው ሱስ የሚያመጣው፣ ጊዜን የሚያጠፋው፣ ግንኙነትን የሚሰብረው፣ አዕምሮን የሚሰብረው የኮምፒውተር ጨማታ ሀይል እና መሳቢያ።” ከዚያም፣ በትትንሽ ጽሁፎች፣ “(እና እነዚህ አንወዳቸውም ማለታችን አይደለም”) ይላል። ይህም በሚያስቅ ሁኔታ በዚህ ዘመን የተሰሩትን አስገራሚ ቴክኖሎጊዎች በጥንቃቄ መጠቀም እንዳለብን ትኩረት ይሰጠዋል።

  17. በብዙ የስራ ቦታዎች በየጎዜ የሚባለው “በሀይል እንሰራለን፣ እናም በሀይል እንጫወታለን” የሚለው ነው። የሰራተኞች አንድነት አስፈላጊ ቢሆነም፣ “ስራ እና ጨዋታ” የቤተሰብን ጊዜ ሲወስድ፣ ይህም እራስን እንደማሸነፍ ነው።

  18. የሐዋሪያት ስራ 17:21ትኩረት ተጨምሮ።

  19. See Keli Goff, “Female Ivy League Graduates Have a Duty to Stay in the Workforce,” Guardian, Apr. 21, 2013, www.theguardian.com/commentisfree/2013/apr/21/female-ivy-league-graduates-stay-home-moms; Sheryl Sandberg, Lean In: Women, Work, and the Will to Lead (2013); Anne-Marie Slaughter, “Why Women Still Can’t Have It All,” The Atlantic, June 13, 2012, www.theatlantic.com/magazine/print/2012/07/why-women-still-cant-have-it-all/309020; Lois M. Collins, “Can Women ‘Have It All’ When It Comes to Work and Family Life?” Deseret News, June 28, 2012, A3; Judith Warner, “The Midcareer Timeout (Is Over),” New York Times Magazine, Aug. 11, 2013, 24–29, 38; Scott Schieman, Markus Schafer, and Mitchell McIvor, “When Leaning In Doesn’t Pay Off,” New York Times, Aug. 11, 2013, 12.

  20. ኤጲስ ቆጶሶች ቤተሰቦችን ለመርዳት ከወጣቶች ጋር ተጨማሪ ጊዜ እንዲያሳልፉ በቤተክርስቲያኗ ተጠይቀዋል። ኤጲስ ቆጶሶች በዎርድ ሸንጎ ውስጥ ለመልከ ጼዴቅ ክህነት ቡድኖች፣ ለደጋፊዎች፣ እና ሌሎችን በትክክል ለመርዳት ልዩ ችሎታ ላላቸው አባላት ተጨማሪ ሀላፊነቶችን እንዲያሳልፉም ተጠይቀዋል።

  21. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 29:7 ተመልከቱ።

  22. }ትምህርት እና ቃል ኪዳን 45:71.