2010–2019 (እ.አ.አ)
ለልጅ ልጆቼ
ኦክተውበር 2013


ለልጅ ልጆቼ

ፈተናን እንድንቋቋም እና ወደ ደስተኛ የቤተሰብ ኑሮ የሚመራን አንድ ተዛዝ አለ።

በዚህ አመት የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ የልጅ ልጆቻችን ያገባሉ።በትንሽ አመት ዉስጥ ወደ 10 የሚጠጉ የአጉት እና የ አክስት ልጆቻቸዉ በ ግሩሙ አልም የቤተሰብ ምስረታ ዉስጥ የሚሳተፉበት ነጥብ ላይ ደርሰዋል።

ያ ደስታ እነርሱ ለምክር ሲጠይቁኝ ጥልቅ ምርምር ዉስጥ እንደገባ አድርጎኛል። “ምን አይነት ምርጫ ብመርጥ ነው ወደ ደስታ ሚመራኝ?” እና በሌላ መንገድ “ምን አይነት ምርጫዎች ናቸዉ ወደ አለመደሰት ሚመሩኝ?”

የሰማይ አባት እያንዳንዳችንን ልዩ አድርጎናል።ሁለታችን ተመሳሳይ ልምድ አይኖረንም።ሁለት ቤተሰቦች አንድ አይደሉም።ስለዚህ በቤተሰብ ህይወት ውስጥ ደስታን እንዴት እንደመምረጥ እንደሚቻል ምከር መስጠት አስቸጋሪ ቢሆን አያስገርምም።የሰማይ አባት ግን አንዳይነት የደስታን መንገድን ለሁሉም ልጆቹ አስቀምጡዋል።ሁኔታችን እና ልምዳችን የሆነዉ ቢሆን አንድ አይነት የደስታ እቅድ ብቻ ነው ያለዉ።ያ እቅድ የ እግዚአብሄርን ተዛዛት መከተል ነው።

ለሁላችንም፣ ስለትዳር የሚያስቡትን የልጅ ልጆቼን ጨምሮ፣ ፈተናን እንድንቋቋም እና ወደ ደስተኛ የቤተሰብ ኑሮ የሚመራን አንድ ተዛዝ አለ ።ለሁሉም ግንኙነቶች ተግባራዊ ይሆናል ሁኔታዎቹ የሆነዉ ቢሆን።በ ቅዱሳት መጻህፍት እና በግዚያችን ባሉ ነብያቶች ትምህርት ውስጥ ተደጋግሙዋል።የመጽሃፍ ቅዱስ የጌታ ቃል ለዘላለሙ በደስታ ለመኖር ለሚፈልጉ ይህን ይመክራል፡

“ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው።

“መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው።

“ኢየሱስም እንዲህ አለው። ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።

“ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።

“ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም። ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።

“በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።”1

ከዚ ቀላል ቃል የትኛው ምርጫ ቤተሰባዊ ደስታን እንደሚያመጣ የተማርኩትን ማጠቃለሉ ከባድ አየደለም።በጥያቄ ልጀምር፣ “የትኛዉ ምርጫዮ ነው ጌታን በሙሉ ልቤ እና መንፈሴ እና አ እምሮዬ እንድወድ የመራኝ?” ለእኔ በጌታ የሃጥያት ክፍያ አማካኝነት የይቅርታን ደስታን ሲሰማኝ ነው።

ከብዙ አመት በፊት አንድ ወጣትን እኔና ባልደረባዮ ያስተማርነዉን በ አቡከርኪ ኒው ሜክሲኮ አጥምቄ ነበር።ውሃ ዉስጥ ከትቼው አወጣሁት።ቁመቱ ከኔ እኩል መሆን አለበት በጆሮዬ ቀጥታ ነበር የተናገረዉ።እንባ በፊቱ ላይ ይወርድ ነበር በደስታ በድምጹ ይህን አለ “ንጹ ነኝ፣ንጹ ነኝ።’

ተመሳሳይ የደስታ እንባዎችን የእግዚአብሄር ሃዋርያ ቃሎችን በደገመ ሰው አይን ላይ አይቻለሁኝ፡እሱም አላት ከ ቃለመጠይቅ ብኋላ ፣ “በጌታ ስም እምርሻለሁ።በራሱ ግዜ እና መንገድ የቅር ይልሻል።” እናም አደረገዉ።

ጌታ ለምን ሃጢያት ይቅር ሲባል እንደማያስታዉሳቸው አይቻለሁ።በሃጥያት ክፍያ ሃይል፣የማዉቃቸው እና የምወዳቸው ሰዎች አዲስ ሲሆኑ እና የሃጥያት ተጸእኖ ሲወገድ ።ልቤ ለአዳኝ እና ለወዳጁ አባት በፍቅር የተሞላ ነው።

ያ ታላቅ በረከት የማስብላቸዉን ሰዎች እሱ ብቻ ወደሚሰጠዉ የሃጥያት ስቃይ ፈዉስ እንዲሄዱ በማበረታታት የመጣ ነው።ለዛ ነው የምወዳቸዉን ጥሪያቸዉን እንዲያጎሉ እና እንዲቀበሉ የምወተዉተዉ።ያምርጫ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፍ ነው።

የሂዎት ግፊት ጌታን ከማገልገል ቸልተኞች እንድንሆን ያደርገናል።አንዳንዶቹ ጥሪዎች አስፈላጊ ላይመስሉ ይችላሉ ነገር ግን የእኔህይወት ና ቤተሰቤ ዲያቆኖችን ለማስተማር በተቀበልኩት ጥሪ ተለዉጥዋል።እነዚያ ዲያቆኖች ለአዳኝ ያላቸዉን እና አዳኝ ለነሱ ያለዉን ፍቅር ተሰምቶኛል።

በቀድሞ የአካባቢ እና የ ሚሽን ፕሬዘዳንት ህይወት ዉስጥ አይቻለሁኝ።ሌላም አይቻለሁኝ ቄስ እና የሰባዎቹ ሆኖ በ አደጋ ተጎድቶ የነበረን ልጅ እንዲረዳ በጌታ ሲደረግ።የአገልግሎት ተአምራቶች የብዙ ሂዎቶችን ነክትዋል እናም ለ አዳኝ ያላቸዉን ፍቅር ጨምርዋል።

ሌሎችን በማገልገል፣የመንፈስ ቅዱስን ጉዋደኝነት እናገኛለን።በሱ አገልግሎት ስኬት ከሃይላችን ውጪ የሆነ ተአምራቶችን ያመጣል።አመጸኛ ልጅ ያለዉ ወላጅ ይህ እዉነት እንደሆነ ያዉቃሉ፣የቤት ለቤት መምህር ያገኛትም ባልዋ ትትዋት ሊሄድ ያሰበችንም ሴትም እንደዛዉ።ሁለቱም አገልጋዮች በዛን ጠዋት ለ መንፈስ ቅዱስ ረዳትነት መጸለያቸዉን ያመሰግናሉ።

በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው በ ጋብቻ ዉስጥ ያለ ችግር መኖር ምንችለዉ።የአንደነት ተአምር የሰማይ ረዳትነት ያስፈልገዋል፣ግዜም ይወስዳል።ግባችን በሰማይ አባት እና በ አዳኝ መገኛ አንድ ላይ ለዘላለሙ መኖር ነው።

አባቴ እና እናቴ አንዳይነት አልነበሩም።እናቴ ዘፍኝ እና የጥበብ ሰዉ ነበረች።አባቴ ኬሚስትሪ ይወድ ነበር።በአንድ ኮንሰርት ላይ እናቴ አባቴ ጭብጨባዉ ከመጀመሩ በፊት ተነስቶ ሊሄድ ሲል አይታ በጣም ገረማት።የት እንደሚሄድ ጠየቀችዉ።በየዋህነት መልሱ ይህ ነበር “አለቀ አይደል፣አላለቀም እንዴ?” የ መንፈስ ቅዱስ ደግነት ነዉ ከስዋ ጋር ደጋግሞ ያመላለሰዉ።

እናቴ ኒው ጀርዚ ዉስጥ ለ 16 አመት ኖራለች አባቴ ጥናቱን እያደረገ እና ኬሚስትሪ እያስተማረ ቤተሰቡን እንዲረዳ።ለስዋ ባልዋ ከሞተማት እናትዋ እና ካላገባችዉ እህትዋ መለየቱ መስዋትነት ነበር።ሁለቱም እናቴ ኒዉ ጀርዚ እያለች ሞቱ።ያኔ ብቻ ነበር እናቴ ስታለቅስ ያየዋት።

ከአመታት ብህዋላ አባቴ ዩታ ዉስጥ ስራ አገኘ።እናቴን ጠየቃት ፣ “ሚልድሬድ ምን ይመስልሻል ማድረግ ያለብኝ?’

እስዋም፣ “ሄነሪ፣ጥሩ የመሰለክን አድርግ” አለችዉ።

ከዛም ሰራዉን ሳይቀበለዉ ቀረ።በሚቀጥለዉ ቀን ደብዳቤ ጻፈችለት።ከብዙ አመታት በፊት የሚችል ከሆነ ከቤተሰቦችዋ ቀርባ እንድትኖር እንደሚያረጋት ቃል ገብቶላት ነበር።የልብዋን ፍላጎት አላወቀዉም ነበር።ከዛም በአስቸክዋይ ሰራዉን እንደሚቀበል ደብዳቤ ጻፈ።

እሱም አለ ፣ “ሚልያርድ፣ለምን አልነገርሽኝም?”

እስዋም “ማስታወስ ነበረብክ።”

ከዛም ብህዋላ ወደ ዩታ ያደረገዉ ለዉጥ የራሱ ምርጫ እንደሆነ ነው የተናገረዉ።የአንደነትን ተአምርን ተቀብለዋል።በ መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት አባቴ ቢያስታዉስ ኖሮ ይበልጥ ጥሩ ይሆነ ነበር።ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ልቡን አራርቶ የሷ ምርጫ የሱ እንዲሆን ፈቅድዋል።

የሰማይ አባት ሁላችንንም ያዉቀናል እናም የወደፊት እድላችንንም ጭምር።የምናልፍባቸዉን መከራዎች ያዉቃቸዋል።ልጁንም ልኮ ከፈተናችን እንዲያወጣን አድርግዋል።

የሰማይ አባት የመንፈስ ልጆች እንዳሉት እናዉቃለን ሃጢያትን እና ደስተኛ አለመሆንን የሚመርጡ።ለዛም ነው አንደኛ ተወላጁን እንዲያድነን የላከዉ፣ታላቁ የፍቅር ድርጊት በሁሉም ፍጥረት።ለዛም ነው የእግዚአብሂር ረዳትነት መጠበቅ ያለብን ለዘላለም ሂዎት እንዲያዘጋጀን እና ከ አባታችን ጋር እንድንኖር እንዲያደርገን።

የቤተሰብ ሂዎት ይፈትነናል።ያ ነዉ አንዲ የ እግዚአብሄር አላማ የህም የሟችነት ስጦታ ሲሰጠን-እንዲያጠነክረን በፈተና ዉስጥ በማለፍ።ደስታም እና ታላቅ ሃዘን እና ፈተናዎች በምናገኝበት ቤተሰብ ዉስጥ ያ በተለይ እዉነት ይሆናል።

ፕሬዘዳን ጆርጅ ኪው ካነን እግዚአብሄር እንዴት እናንተን እና እኔን እና የኛን ልጆች ለሚደርሱብን ፈተናዎች እንዳዘጋጀን ተናግረዋል፡ “እኛ ሳንሆን እግዚአብሄር የወደደዉ ነው ሚሆነዉ።ለሁላችንም ይጨነቃል።ሁላችንንም ለማዳን ይፈልጋል።ለሁላችንም መላክቶችን ሃላፊነት እንዲወስዱ ሰትቶናል።በራሳችን እና በሌሎች አይን የማንረባ ልንመስል እንችላለን ነገር ግን እዉነቱ የእግዚአብሂር ልጆች ነን በእዉነትም መላክቶችን ሰጥቶናል-የማይታዩ ሃይሎች-ሃላፊነትን ለኛ ሚወስዱ እናም ያዩናል፣ይጠብቁናልም።”2

ፕሬዘዳንት ካነን ያስተማሩት ትክክል ነው።ማረጋገጫ ያስፈልጋችህዋል ልክ እኔ እንደፈለኩት እና እንደተመካሁበት።

የምወደዉ ሰዉ የሃጢያትን ክፍያ እንዲፈልገዉ እና ሃይሉ እንዲሰማዉ ጸልያለሁኝ።የሰዎች መላእክቶች ለእርዳታቸዉ እንዲመጡላቸዉ በእምነት ጸልያለሁኝ ደሞም መተዋል።

እግዚአብሄር ሁሉንም ልጆቹን የሚያድንበትን መንገድ አዘጋጅትዋል።ለብዙዎች፣ከ ሚወዱዋቸው ወንድሞች ወየም እህቶች ወይም እድመ አያቶች ጋር አንድ ላይ መኖርን ያካትታል።

ከብዙ አመት በፊት አንድ ጉዋደኛ ሰለ አያቱ ተናገረ።ሙሉ ህይወት ኖራለች፣ሁሌም ለጌታ እና ለቤተክርስትያኑ ታምኝ።ግን አንዱ የልጅ ልጅዋ የወንጀልን ሂዎት መረጠ።በስተመጨረሻ ተፈርዶበት ወህኒ ገባ።ጉዋደኛዮ ያስታዉሳል የልጅ ልጅዋን እስር ቤት ለመጠየቅ እየነዳች እያለቀሰች የጸለየችዉን “ጥሩ ሂዎት ለመኖር ሞክሪያለው።ለምድነዉ እሱ ህይወቱን እያጠፋ የሚመሰል የልጅ ልጅ ያልኝ?”

መልሱ በዚ ቃል ወደ ጭንቅላቷ መጣ “ላንቺ የሰጠዉሽ ምንም ቢያደርግ እንደምትወጂዉ ስለማዉቅ ነው።’

ለዉላችንም ጥሩ ትምህርት ነው።በዚ እየበሰበሰ ባለ አለም ዉስጥ ለወላጆች፣አያቶች እና ለሁሉም የ እግዚአብሂር አገልጋዮች ቀላል አይሆንም።የእግዚአብሂርን ልጆች ወደ ደስታ አናስገድዳቸዉም።እግዚአብሄር ያን አያደርግም በሰጠን ነጻ ምርጫ አማካይነት።

የሰማይ አባት እና ተወዳጁ ልጁ የእግዚአብሄርን ልጆች የፈለጉትን ቢያደርጉ ወይም ቢሆኑ ይወድዋቸዋል።የቱንም የከፋ ቢሆን አዳኝ ለሁሉም ሃጢያት ዋጋዉን ከፍልዋል።ፍትህ መኖር ቢገባዉ እንክዋን የ ይቅርታ እድል ፍትህን በማይሰርቅ መልኩ ተዘርግትዋል።

አልማ ለልጁ ኮሪአንቶን ተስፋን ሰቶታል “ስለዚህ፣ እንደፍትህ ከሆነ፣ በዚህ በሙከራው ጊዜ፣ አዎን፣ በዝግጅቱ ወቅት፣ ሰዎች ንስሃ ካልገቡ በቀር የቤዛነት ዕቅድ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም፤ በዚህ ሁኔታ ካልሆነ በቀር ምህረት የፍትህን ስራ ካላጠፋው በቀር በስራ ላይ ሊውል አይችልም። እናም የፍትህ ስራ ሊጠፋ አይችልም፤ ከጠፋ ግን እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ያቆማል።”3

ለልጅ ልጆቼ እና ዘላለማዊ ቤተሰብ ለሚፈልጉ ሁሉ መለክቴ ለታማኞች ደስታ ተረጋግጧል።ከአለም በፊት ወዳጁ የሰማይ አባት እና ተወዳጁ ልጁ ከሚያስቡት ጋር ሰርተዋል።እግዚአብሄር ሁሌም ይወዳቸዋል።

ከመንፈስ አለም ሳሉ ስለ ደህንነት እቅድ እንደተማሩ የማወቅ ጥቅም አላችሁ።እነርሱ እና እናንተ ብዙዎች ባልቻሉበት ወቅት እምነት ስለነበራችሁ ወደ አለም እንድትመጡ ተጋብዛችዋል።

በመንፈስ ቅዱስ ሁሉም እዉነታ ወደ ትዉስታችን ይመጣል።በሌሎች ላይ ማስገደግ አንችልም ግን በ ህይወታችን ውስጥ ማሳየት እንችላለን።ከለታት አንደ ቀን የሰማይ አባታችን ተወዳጅ የቤተሰብ አካል መሆናችንን የነበርን መሆኑን በማሰብ ማረጋገጫ መዉሰድ እንችላለን።ከ እግዚአብሄር እርዳታ ጋር ያንን ተስፋ እና ደስታ ከንደገና ሊሰማን ይገባል።ለሁላችንም እንዲሆን በየሱስ ክርስቶስ ስም እጸልያለሁኝ፣አሜን።