2010–2019 (እ.አ.አ)
በምንም በብቻችን አንጓዝም
ኦክተውበር 2013


በምንም በብቻችን አንጓዝም

አንድ ቀን ወደ አስቸጋሪ ጊዜዎቻችሁ በትዝታ ተመልክታችሁ ሁልጊዜም እርሱ በአጠገባችሁ እንደነበረ ትረዳላችሁ።

ውድ እህቶቼ፣ በዚህ ምሽት የሚሰማን የመንፈስ ስሜት የጥንካሬአችሁ፣ የአምልኮአችሁ፣ እና የመልካምነታችሁ ነጸብራቅ ነው። መምህርን በመጥቀስ፣ “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ።... እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ።”1

እናንተን ለማነጋገር ስላለኝ እድል ሳስብበት፣ ውድ ባለቤቴ ለሴቶች መረዳጃ ማህበር ስለነበራት ፍቅር እንዳስታውስ ሆንኩኝ። በህይወቷ በሴቶች መረዳጃ ማህበር ውስጥ በብዙ ጥሪዎች አገልግላ ነበር። በእኔ እና በእርሷ 31 አመት፣ የካናዳ ሚስዮን ፕሬዘደንት እንድሆን ተጠራሁ። በዚያ በተመደብንበት ሶስት አመታት፣ ፍራንሲስ በኦንቶሪዮና ኩቤክ አካባቢ በሚገኙት ቦታዎች በሙሉ የሴቶች መረዳጃ ማህበራትን ትመራ ነበር። ከጓደኞቿ መካከል ቅርብ የሆኑት የመጡት በዚህ ሀላፊነት ምክንያት እና በዎርዳችን ውስጥ፡በሴቶች መረዳጃ ማህበር በነበራት ጥሪ ምክንያት ነበር። የሰማይ አባታችን ታማኝ ሴት፣ እና ውድ ጓደኛዬ ነበረች። ቃላቶች ሊገልጹ በማይችሉ ሁኔታ እናፍቃታለሁ።

እኔም የሴቶች መርዳጃ ማህበርን አፈቅራለሁ። በመንፈስ መነሳሻ እንደተመሰረተች እና በምድር ላይ ለጌታ ቤተክርስቲያን አስፈላጊ እንደሆነች እመሰክራለሁ። ከዚህች ድርጅት የመጡትን መልካም ነገሮች እና በዚህም ምክንያት የባረከችውን ህይወቶች በሙሉ ለመቁጠር አስቸጋሪ ነው።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር በተለያዩ አይነት ሴቶች ይገኙባታል። ያላገቡት፣ ምናልባት በትምህርት ላይ ያሉት፣ ምናልባት የሚሰሩ፣ ግን ሙሉ እና ሀብታም የሆነ ህይወት ያላቸው ሴቶች አሉ። አንዳንዳቻችሁ ብዙ ስራ ያላችሁ የሚያድጉ ልጆች እናቶች ናችሁ። ሌሎቻችሁም በሞት ወይም በመፋታት ምክንያት ባለቤት የላችሁም እናም ያለባለቤትና ያለአባት ልጆቻችሁን ለማሳደግ ትታገላላችሁ። አንዳንዶቻችሁ ልጆቻችሁን አሳድጋችኋል ነገር ግን ከእናንተ የሚፈልጉት እርዳታ የሚቀጥል እንደሆነ ታውቃላችሁ። እናንተ ለመስጠት የምትችሉትን እንክብካቤ የሚፈልጉ ያረጁ ወላጆች ያላችሁ ብዙዎች አላችሁ።

በህይወትየትም ብንሆንም፣ ሁላችንም ፈተናዎችና ችግሮች ያሉብን ጊዜዎች አሉ። ከእርስ በራስ የተለያዩ ቢሆኑም፣ ለሁሉም አንድ ናቸው።

አብዛኛዎቹ ፈተናዎቻችን የሚገኙት የተለያዩ ሰዎች በሚገኙበት በስጋዊ አለም ስለምንኖር ነው። አንዳንዴ ተስፋ ቢስ በመሆን፣ “በቲለስቲያል አለም ስጓዝ አይኖቼን ሰለስቲያል አለም ላይ ለመጠበቅ እችላለሁ?” በማለት ትጠይቃላችሁ።

እሾህ በተዘራበት እና ትግል ባለበት መንገድ እንሄዳለን። መልካም ስጦታ ከሚሰጠው የተለየንበት ስሜት የሚኖርበትም ጊዜ አለ። በብቸኝነት የምትሄዱ እየመሰላችሁ ታስባላችሁ። ፍርሀት እምነትን ይተካል።

እራሳችሁን በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ ስታገኙ፣ ለመጸለይ እንድታስታውሱ እለምናችኋለሁ። ፕሬዘደንት ኤዝራ ታፍት ቤንሰን ስለጸሎት ያሉትን ቃላት እወዳለሁ..

“በህይወቴ በሙሉ ከህይወቴ ከተሰጡኝ ምክሮች ሁሉ በላይ የሆነው በጸሎት ላይ እንድመካ የተመከርኩበት ነው። ይህም በህይወቴ አስፈላጊ፣ እንደ መልህቅ፣ የጥንካሬ መንጭ፣ እና ለመለኮታዊ ነገሮች እውቀቴ መሰረት ሆናል።...

“...ምንም እንኳን ወደኋላ የሚኬድበት ቢመጣም፣ በጸሎት መረጋገጫ ለማግኘት እንችላለን፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለነፍስ ሰላም ይናገራልና። ያም ሰላም፣ ያም የመንፈስ እርካታ፣ የህይወት ታላቅ በረከት ነው።”2

ሐዋርያው ጳውሎስ እንደገሰጸው፥

“ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ።

“አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።”3

ምን አይነት አስገራሚ የተስፋ ቃል ነው! ሰላም በጉጉት የምንፈልገው ነው።

በዚህች ምድር በብቻችነንድንጓዝ የተላክን አይደለንም።፡ለእያንዳንዳችን ምን አይነት የሀይል፣ የጥንካሬ፣ እና የምቾት ምንጮች አሉልን። እኛ እራሳችንን ከምናውቀው በላይ እርሱ ያውቀናል፣ ሁሉንም የሚመለከት እና መጨረሻውን ከመጀመሪያ የሚያውቀውም ከጠየቅን እኛን ለመርዳት እንደሚገኝ ማረጋገጫ ሰጥቶናል። “ዘወትር ጸልዩ፣ እናም እመኑ፣ ሁሉም ነገሮች ለእናንተ በጎነት አብረው ይሰራሉ።”4

ጸሎቶች ወደ ሰማይ ሲሄዱ፣ በአዳኝ የተማርናቸው ቃላቶች አንርሳ። በገትሰመኔ እና በመስቀል ላይ ከፍተኛው ስቃይ ሲያጋጥመው፣ ወደ አብ እንዲህ ጸለየ፣ “የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ።”5 በጊዜ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ የምንፈልገው እርዳታ የሰማይ አባታችን እንዴት እና መቼ፣ እና በምን ሁኔታ ሊሰጠን እንደሚችል ከሁሉም በላይ እንደሚያውቅ ማመን ያስፈልገናል።

የገጣሚውን እነዚህ ቃላት እወዳለሁ፥

በምን አይነት ልዩ በሆኑ መንገዶች እንደሆነ አላውቅም

ግን እግዚአብሔር ጸሎትን እንደሚመልስ አውቃለሁ።

ቃሉን እንደሰጠ አውቃለሁ

ይህም ጸሎትን እንደሚሰማ ይነግረኛል

ይህም አሁንም ይሁን በኋላ መልስ ያገኛል፣

ስለዚህ ጸልዬ በጸጥታ እጠብቃለሁ።

የምፈልጋቸው በረከቶች

ባሰብኩበት እንደሚመጡ አላውቅም፣

ግን ጸሎቴን ከእርሱ

ፈቃዱ ከእኔ በላይ ጠብ ካለው ጋር ብቻ እተዋለሁ፣

የጠየኩትን እንደሚሰጠኝ

ወይም ከዚያ በላይ በረከት የሆነ መልስ እንደሚሰጠኝ ተረጋግጬ።6

ጸሎት ለችግር ጊዜ ብቻ አይደለም። በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ “ዘወትር ጸልዩ”7 እና በልባችሁ ጸሎት አቅርቡ8 ተብለናል። ራሳችንን በየቀኑ መጠየቅ የሚገባንን ጥያቄ የሚወደደው መዝሙርም ይጠይቃል፥ “ለመሰለይ አስበህ ነበርን?”9

በአስቸጋሪም አለማችን እንድንጸና ከጸሎት ጋር የሚተባበረውም የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ነው። በቅዱሳት መጻህፍቶቻችን ውስጥ የሚገኙት የእውነት ቃላት እና መነሳሻዎች ለእኔ ታላቅ ዋጋ ያላቸው ንብረቶቼ ናቸው። እነርሱን ማንበብ አይደክመኝም። ቅዱሳት መጻህፍትን ስፈትሽ በመንፈስ ከፍ ከፍ እላለሁ። የእውነት እና የፍቅር ቅዱስ ቃላት ለህይወቴ መመሪያ ይሰጣሉ እናም ለዘለአለማዊ ፍጹምነት መንገድ ይጠቁማሉ።

ቅዱሳት መጻህፍትን ስናነብና ስናሰላስል፣ መንፈስ ወደ ነፍሳችን አስደሳች ቃላትን ያሾከሹካል። የእግዚአብሔር ትእዛዛትን በማክበር ስለሚመቱ በረከቶች እንማራለን። ስለሰማይ አባታችንና ስለአዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እናም እነርሱ ለእኛ ስላላቸው ፍቅር እንማራለን። ከሰሎታችን ጋር ሲተባበር፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ውስንጌል እውነት እንደሆነ በእርግጥም እናግቃለን።

ፕሬዘደንት ሒንክሊ እንዳሉት፣ “ቅዱስ [ቃላቱን] እንድንመገብ እና [ከእነርሱም ‘ከምንረዳበት በላይ የሆነውን’ ያን ጥንካሪ፣ ያን ሰላም፣ እና ያን እውቀት እያንዳንዳችን ለማግኘት እንችላለን” (ፊልጵስዮስ. 4:7)።”10

ለመጸለይ እና ቅዱሳት መጻህፍትን ለማንበብ ጊዜ ስንወስድ፣ ህይወታችን ከሁሉም በላይ የተባረከ እና ሽከማችን ቀላል የሆነ ይሆናል።

የሰማይ አባት የአንድ ሴትን ጸሎት እና ልመና እንዴት እንደመለሰ እና በጣም ትፈልገው የነበረውን ሰላም እና ማረጋገጫ እንዴት እንደሰጣት ታሪክ ልንገራችሁ።

የትፍኒ አስቸጋሪ ህይወት የተጀመረው በምስጋና በዓል እንደገና በገና ጌዜ በቤቷ እንግዳዎች በነበሩበት ጊዜ ነበር። ባለቤቷ ዶክተር ለመሆን ትምህርት ላይ ነበር እናም አሁን በሆስፒታል እየሰለጠነ ነበር። ለብዙ ሰዓት መስራት ስለሚያስፈልገው፣ እርሱን እንድሚፈልጉት ያህል ሊረዳት አልቻለም ነበር፣ እናም በበዓል ቀናት ለመደረግ የሚያስፈልጉት ነገሮች በሙሉ፣ እናም ልጆቹን መልከባከብም፣ በእርሷ ላይ አርፎ ነበር። ተጥለጠለቀች፣ ከዚያም በጣም የምትወደው ሰው ነቀርሳ እንዳላቸው እንዳወቁ ሰማች። ጭንቀቱና ሀሳቡ ከባድ ሆነባት፣ እናም ተስፋ ወደመቁረጥ እና ወደ መከፋት ሄደች። የሀኪም እርዳታን ፈለገች፣ ግን ምንም ሊረዳት አልቻለም። ምግብ መግባት አልፈለገችም፣ ሰውነቷ ሊፈቅደው በማይችለው ሁኔታ ክብደቷ ቀነሰ። ካሸነፋት የማተከሽ ስሜት ለማምለጥ ሰላምን በቅዱሳት መጻህፍትና በጸሎት ፈለገች። ሰላም ወይም እርዳታ የማይመጣ ሲመስልም፣ እግዚአብሔር የተዋት መሰላት። ቤተሰቧና ጓደኞቿ ጸለዩላት እናም እርሷን ለመርዳት በጣም ሞከሩ። ሰውነቷ ጤንነት እንዲኖረው የምትወደውን አይነት ምግብ አመጡላት፣ ነገር ግን ትንሽ ትበላና ለመጨረስ አትችልም ነበር።

በአንድ በሚያናድድ ቀን፣ ጓደኛዋ በምትወደው ምድብ እንሷን ለማታለል ሞከረች። ምንም ነገር የማይሰራ ሲመስላትም፣ ጓደኛዋ እንዲህ አለች፣ “ለአንቺ መልካም የሚመስል አንድ ነገር መኖር አለበት።”

ትፍኒ ለጥቂት ጊዜ አሰበችና እንዲህ አለች፣ “መልካም ይሆናል የማስብበት ነገር ቢኖር በቤት የተሰራ ዳቦ ነው።”

ግን ምንም በቤት አልነበረም።

በሚቀጥለው ቀን የትፍኒ በር ተንኳኳ። ባለቤቷ በቤት ስለነበረ በሩን ከፈተ። ሲመለስ በእጁ በቤት የተሰራ ዳቦ ይዞ ነበር። ዳቦይ እስከዚህም ከማያውቋት ሼሪ ከምትባል ሴት የመጣ እንደሆነ ሲነግራት ትፍኒ በጣም ተደነቀች። በደንቨር ኮለራዶ ውስጥ ከምትኖረው ከትፍኒ እህት ኒኮል ጋር ጓደኛ ነበረች። ኒኮል እና ቤተሰቧ ከትፍኒ ጋር ለምስጋና በዓል አብረው ሲዎዩ ሼሪ ከትፍኒና ከባሏ ጋር እንዲተዋወቁ አደርጋ ነበር። በኦማሀ ትኖር የነበረችው ሼሪ ኒኮልን ለመጋበዝ ወደ ትፍኒ ቤት ሄዳ ነበር።

አሁን ከወሮች በኋላ፣ የሚጣፍጥ ዳቦ ይዛ ትፍኒ እህቷን ኒኮል ሼሪን ለእርዳታ ስለላከቻት ለማመስገን ደወለች። ኒኮል ይህን ጉብኝት አላስነሳችም እና ምንም አታውቅበትም ነበር።

ኒኮል ጓደኛዋን ሼሪን ለምን ዳቦ ለማድረስ እንተተነሳሳች በምትጠይቅበት ጊዜ ሁሉም ታሪኩ ታወቀ። የተማረችው ለእርሷ፣ ለትፍኒ፣ እና ለሼሪ የሚያነሳሳት ነበር፣ እና ይህም ለእኔ የሚያነሳሳ ነበር።

ዳቦውን ሼሪ ባደረሰችበት ቀን፣ ለመጋገር አላማ ከነበራት በተጨማሪ ሌላ ሁለተኛ ዳቦ እንድትጋግር ተነሳስታ ነበር። ለተኛውን ዳቦ በመኪና ስትጓዝ ይዛው እንድትሄድም መነሳሻ ስሜት ነበራ፣ ምክንያቱን ግን አላወቀችም ነበር። በጓደኛዋ ቤት ምሳ ከበላች በኋላ፣ የአንድ አመት ልጇ ማልቀስ ጀመረች እና እርሷን ለማስተኛት ወደ ቤት መሄድ ነበረባት። ሼሪ ዳቦውን ከምትኖርበት በሰላሳ ደቂቃ መንዳት ባለባት ከተማ ውስጥ ወደምትኖረውና እስከዚህም ለማታውቃት ወደኒኮል እህት ትፍኒ ቤት ዳቦውን መውሰድ እንደሚገባት ስሜት ሴምጣባት ተጠራጥራ ነበር። የደከማትን ልጆን ወደ ቤ ለማድረስ ፈልጋና እንግዳ ለሆኑ ሰዎች ዳቦን ለመስጠት አፍራ ሀሳቡን ችላ ለማለት ሞከረች። ነገር ግን፣ ወደ ትፍኒ ቤት እንድትሄድ የነበራት ስሜት ጠንካራ ነበር፣ ስለዚህ መነሳሻውን አድምጣ ሄደች።

ወደዚያ ስትደርስ፣ የትፍኑ ባለቤት በሩን ከፈተ። ሼሪም የኒኮል ጓደኛ እንደሆነች እንዲያስታውስ አደረገች እናም ዳቦውን ሰጠችውና ሄደች።

እንደዚህ ጌታ እንግዳን ከከተማው ሩቅ ቦታ ተጉዛ የተፈለገውን በቤት የተጋገረ ዳቦች ለማድረስ ብቻ ሳይሆን ለትፍኒ ያለውን ግልጽ ፍቅር እንድታደርስ ተጠቀመባት። የደረሰባት ከዚህ በተለየ ለመግለፅ አይቻልም። ያም ዳቦ የተሰጣት እስከዚህም በማታውቀው፣ ስለፍላጎቷ ምንም በማታውቅ፣ ግን በመንፈስ የምትነሳሳበትን በምታደምጥ እና በምታከናውን ሴት ነበር። ይህም ለትፍኒ የሰማይ አባቷ ስለፍላጎቷ እንደሚያውቅ እና እርዳታ ለእርሷ እስከመላክ ድረስ እንደሚያፈቅራት ምልክት ነበር። እረፍት ለማግኘት ያለቀሰችበትን መልሶላት ነበር።

ውድ እህቶቼ፣ የሰማይ አባታችሁ እያንዳንዳችሁን ያፈቅራል። ያም ፍቅር በምንም አይቀየርም። በአመለካከታችሁ፣ በንብረቶቻችሁ፣ በባንክ ውስጥ ባላችሁ ገንዘብ ያህል ምክንያት ተፅዕኖ የሚደረግበት አይደለም። በችሎታችሁ የሚቀየር አይደለም። በኁሉም የሚገኝ ነው። በሚከፋችሁና በምትደሰቱበት፣ ትሰፋ በምትቆርጡበትና ተስፋ በሚኖራችሁ ጊዜ ይገኛል። ፍቅር የሚገባችሁ ቢሆንም ባይሆንም የእግዚአብሔር ፍቅር ይገኛል። ሁልጊዜም አለና።

የሰማይ አባታችንን ልብ በሚነካ፣ በልባዊ ጸሎት እና ቅን፣ አላማ ባለው የቅዱስ መጻህፍት ጥናት፣ ምስክራችን የጠነከሩና ዝልቅ ስር ያላቸው ይሆናሉ። እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን። በብቻችን በምንም እንደማንጓዝ እናውቃለን። አንድ ቀን ወደ አስቸጋሪ ጊዜዎቻችሁ በትዝታ ተመልክታችሁ ሁልጊዜም እርሱ በአጠገባችሁ እንደነበረ እንደምትረዱ ቃል እገባላችኋለሁ።

ፍቅሬን እሰጣችኋለሁ። በረከቴንም እሰጣችኋለሁ። ለምታደርጉት መልካም ነገሮች በሙሉ እና ለምትንሩበት ህይወት በሙሉ ምስጋናዮእን አቀርብላችኋለሁ። በማንኛውም መልካም ስጦታ እንድትባረኩ የምጸልየው በአዳኛችንና በቤዛችን ስም፣ እንዲሁም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።