2010–2019 (እ.አ.አ)
አሁን ማድረግ ትችላለህ!
ኦክተውበር 2013


አሁን ማድረግ ትችላለህ!

ከንደገና ተነስተን በመንገዱ ለመቀጠል እስከፈቀድን ድረስ፥ ከስህተታችን ተምረን የተሻለ እና ደስተኞች እንሆናለን።

ወጣት ሳለሁ መውደቅና መነሳት አንድ እንደሆኑ እና ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዳላቸው አስብ ነበር። ከአመተት በሗላ ግን የፊዚክስ ህጎች መቀየራቸውን ያልሰከነ መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ። ሆኖም እኔን አልጠቀመኝም።

በቅርብ ጊዜ ካስራ ሁለት አመቱ የልጅ ልጄ ጋር የበረዶ መንሸራተት እየተጫወትን ነበር። አብረን በጊዜያችን እየተደሰትን እያለ የበረዶ ግግር መትቼ ከባድ ግጭት አጋጥሞኝ ወደቁልቁለት ወደኩኝ።

ለመቆም የተቻለኝን ዘዴ ብጠቀምም አልቻልኩም። ወድቄ መነሳት አቃተኝ።

በአካል ደና ብሆንም የራስ አመለካከቴ ግን ተጎድቶ ነበር። ስለዚህ የራስ ቆቤን እና የመከልከያ መነጥሬን አወለኩኝ። ሌሎች በረዶ ተንሸራታቾች ባይመለከቱኝ መረጥኩኝ። እራሴን ሳልረዳ እዛ ቁጭ ብዬ ሌሎች በድንቅ ሁኔታ ሲንሸራተቱ እና በደስታ ጩሐት “ ወንድም ኡክዶርፍ! “ እያሉ ሲጣሩ በህሊናዬ መጣ።

እኔን ለማዳን ምን እንደሚያስፈልግ ማሰብ ጀመርኩ። በዚህን ጊዜ ነው የልጅ ልጄ አጠገቤ የመጣው። ምን እንደተከሰተ ብነግረውም ልምን መነሳት እንዳልቻልኩ ስነግረው ላገላለፄ ያን ያህል ትኩረት አልሰጠውም። አይኔን እየተመለከተ እጁን ዘርግቶ አወጣኝና በፀና ድምፅ “ኦፓ፥ አሁን መነሳት ትችላለህ“ አለኝ።

ወዲያውኑ ቅምኩኝ።

እስካሁኑ ድረስ በዚህ ነገር ላይ እየተገረምኩኝ ነው። ከአፍታ በፊት የማይቻል የመሰለኝ ነገር ወዲያውኑ እውን ሆነ፥ ምክንያቱም የአስራ ሁለት አመት ልጅ መቶ “ አሁን መነሳት ትችላለህ“ ስላለ ነው። ለኔ ይሄ በራስ የመተማመን የጉጉት አና የጥንካሬ ድብልቅ ሁነብኝ።

ውንድሞችና እህቶች በህይወታችን መነሳትና ጎዞአችንን መቀጠል ከችሎታችን በላይ የሆነ የሚመስለን ጊዜ አለ። በዛ ቀን በረዶ በተሸፈነ ቁልቁለት ላይ አንድ ነገር ተማርኩ። መነሳት አልችልም ብለን ባሰብንበት ወቅት እንኳ ተስፋ አለ። ታዲያ አንዳንዴ በቀጥታ አይናችንን እየተመለከተ እጃችንን በማንሳት “ አሁን መነሳት ትችላለህ “የሚለን ሰው ያስፈልጋል።

የጥንካሬ አሳሳችነት።

ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ለብቁነት ስሜት ማነስ እና ለብስጭት የተጋለጡ ይመስለናል። ይህ እውነት መሆኑን ግን እርግጠኛ አይደለሁም። ወንዶች የጥፋተኝነት ስሜት፥ የመተከዝ ስሜትና ስኬት ላይ ያለመድረስ ስሜት ይሰማቸዋል። እነዚህ ስሜት አያስጨንቁንም ብለን ልናስመስል እንችላለን፥ ነገር ግን ያስጨንቁናል። የውድቀታችን እና የድክምእታችን ጫንቃ ሲደራረብብን በፍፁም አይሳካልንም ብለን እናስባለን። ከዚህ በፊት ስለወደቅን፥ ውድቀትነ እንደእጣ ፋንታችን አድርገን እንቆጥረዋለን። አንዱ ፀሃፊ እንዳስቀመጠው፥ “ ያለ ማቆም ወደሗላ የሚሄደውን ጀልባ ሞገዱን ለማሸነፍ እንቀዝፋለን “1

በችሎታ እና በሞገስ የተሞሉ ሰዎች አንዴ ወይም ሁለቴ ስለወደቁ ብቻ አስቸጋሪ የሁነውን የእግዚአብሄርን መንግስት ከመገንባት ሲቆጠቡ ተመልክቻለሁ። እነዚህም ልዩ የክህነት ሰዎችና የእግዚአብሄር አገልጋዮች መሆን የሚችሉ የቃል ኪዳን ሰዎች ናቸው። ነገር ግን ተሰናክለው ተስፋ ስለቆረጡ ከክህነት ስራቸው ራሳቸውን አግለው ቀላል ፥ነገር ግን ጠቀሜታው አናሳ የሆነን ጥረት ይመርጣሉ።

እናም ከዚያ ፥ ሊመሩት ከሚገባው ህይወት ይልቅ በጥላው ብቻ እየኖሩ፥ የትውልድ መብታቸው የሆነውን ችሎታቸው ላይ ሳይደርሱ በዚያው ይቀጥላሉ። ገጣሚው እንዳለው “ ብዙውን ሙዚቃቸውን በውስጣቸው እንደቀበሩ የሚሞቱ“ እድለቢስ ነፍሳት ናቸው። 2

ማንም ሰው መውደቅን አይወድም። በተለይ ደግሞ የምንወዳቸው ሰዎች ስንወድቅ እንዲመለከቱን አንፈልግም። ሁላችንም ክብርንና ከፍተኛ ግምትን ከሰው እንፈልጋለን። አሸናፊዎች ለመሆን እንፈልጋለን። ነገር ግን እኛ ሟቾች ያለ ጥረት እና ያለ ስነስርአት ወይም ያለስተት አሸናፊዎች መሆን አንችልም።

ወንድሞቼ እጣ ፋንታችን ምን ያህል ጊዜ በተሰናከንለው አይወሰንም፥ ነገር ግን ምን ያህል ጊዜ ቆመን፥ አዋራችንን አራግፈን ወደ ፊት ቀጠልን በሚለው ነው።

ከእግዚአብሄር ፍቃድ የሆነ ሃዘን

ይህ ሟች ህይወት ፈተና እንደሆነ እናውቃለን። ነገር ግን የሰማዩ አባታችን በፍፁም ፍቅር ይወደናል። መልሶችን የት እንደምናገኝ ያሳየናል። ባላወቅነው መልከአ ምድር እንድንጓዝና ያልተጠበቁ መከራዎችን እንድንጋፈጥ ካርታ ሰቶናል። የነቢያት ቃላት የካርታው አንዱ ክፍል ነው።

መንገዱን ስንስት፥ ስንወድቅ ወይም ከሰማዩ አባታችን መንገድ ስንገነጠል የነቢያት ቃላት እንዴት እንደምንነሳ እና መንገዳችንን እንደምንቀጥል ይነግሩናል።

በዘመናት ሁሉ ነቢያት በተደጋጋሚ ካስተማሩት መመሪያዎች መካከል በተስፋ የተሞላውና አበረታታች የሆነው ሰው ሁሉ ንስሃ መግባት፥ መንገዱን መቀየር እና የደቀመዝሙር እውነተኛ መንገድን መከተል እንደሚችል የሚያሳየው ነው።

ይህም በድክመታችን፥ በስህተታችን ወይም በሃጥያታችን ተመቻችተን መቀመጥ አለብን ማለት አይደለም። ወደ ንስሃ በሚመራው ሃዘንና ወደ ተስፋ መቁረጥ የሚመራው ሀዘን መካከል ጠቃሚ ልዩነት አለ።

ሃዋርያ ጳውሎስ እንዳስተማረው “ እንደ እግዚያብሄር ፈቃድ የሆነው ሀዘን ወደ መዳን የሚያበቃ ንስሃ ሲመራ፥ አለማዊ ሃዘን ግን ለሞት ያበቃል። “ 3 እንደ እግዚያብሄር ፈቃድ የሆነው ሀዘን ለውጥን እና በቤዛነቱ ተስፋን ወደ መግኘት ያነሳሳል። አለማዊ ሃዘን ወደ ታች ይጎትተናል፥ ተስፋን ያጠፋል፥ ለሚመጡት ፈተናዎች እጅ እንድንሰጥ ያሳምነናል።

እንደ እግዚያብሄር ፈቃድ የሆነው ሀዘን ወደ መቀየር 4እና የልብ ለውጥ ይመራል። 5 ሀጥያትን እንድንጠላ እና መልካምን እንድንወድ ያደርገናል።6 እንድንቆምና በክርስቶስ ፍቅሩ ብርሃን እንድንጓዝ ያበረታታናል። እውነተኛ መቀየር ስለመቀየር እንጂ ስለመሰቃየት አይደለም። እውነት ነው፥ ላለ መታዘዛችን ከልብ የሆነ ፀፀት እና እውነተኛ ሀዘን አብዛኛውን ጊዜ የሚያም እና ቅዱስና ጠቃሚ የንስሃ ደረጃዎች ናቸው። ነገር ግን ጥፋተኝነት ወደ እራስን መጥላትና ዳግም እንዳንነሳ ሲከለክለን ንስሃን ከመበረታታት ይልቅ ንስሃን እየገደበ ነው።

ወንድሞቼ የተሻለ መንገድ አለ። እንነሳና የእግዚአብሄር ሰዎች እንሁን። ለኛ ሲል በሞት ጥላ ሸለቆ የተጓዘ አሸናፊ አዳኝ አለን።ለኛ ሀጥያት ምትክ እራሱን አሳልፎ ሰጠ። ማንም ሰው ከዚህ የበለጠ ፍቅር ልክ እንደ እየሱስ ክርስቶስ ያለ እንከን የሌለው በግ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም7 እስኪከፍል ድረስ እራሱን በመሰዊያ ላይ በፈቃዱ አቅርቧል። መከራችንን በራሱ ላይ ወሰደ። ሸክማችንን ፥ ጥፋታችንን፥ በትከሻው ላይ ወሰደ። ውድ ወንድሞቼ ወደሱ ለመምጣት ስንወስን፥ ስሙን በላያችን ላይ ስንወስድ እና በድፍረት በደቀመዝሙር ጎዳና ላይ ስንጓዝ፥ በቤዛነቱ ምክንያት ደስታ እና ምድራዊ ሰላም ብቻ ሳይሆን “ለሚመጣው አለም ዘላለማዊ ህይወትን” ቃል ተገብቶልናል።8

ስንሳሳት፥ ሃጢያት ሰርተን ስንወድቅ፥ በእውነት ንስሃ መግባት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እናስብ። ልባችንና ፍካዳችንን ቀይረን ወደ እግዚአብሄር መዞር እና ሀጢያትን ማቆም ነው። እውነተኛ ከልብ የሆነ ንስሃ “ አሁን መነሳት እንደምንችል“ ከሰማይ ማረጋገጫ ያመጣል።

ማናችሁ?

ከማደግ የሚከለክለን አንዱ የጠላት ዘዴ ፥ እኛ በርግጥ ማን እንደሆንን እና ፍላጎታችንን ግራ ማጋባት ነው።

ከልጆቻችን ጋር ጊዜ ማሳለፍ እንፈልጋለን፥ ነገር ግን ደግሞ በምንወደው የትርፍ ጊዜ መዝናኛ እንጠመዳለን። ክብደት መቀነስ እንፈልጋለን ነገር ግን ደግሞ የምንጓጓውን ምግብ ለመብላት እንፈልጋለን። እንደ ክርስቶስ መሆን እንፈልጋለን፥ ነገር ግን ደግሞ በጎዳና መንገድ ላይ አቋርጦን ላለፈው ሰውዬ ያይምሮአችንን ብስጭት እንወጣበታለን።

የሴጣን አላማ፥ ከዋጋ በላይ የሆነውን እንቁ እውነተኛ ደስታንና ዘላለማዊ እሴቶችን በጥቃቅን እና በከንቱ ጌጣጌጦች፥ የውሸት ደስታን ለመቀየር መፈተን ነው።

ሌለው እንዳንነሳ ተስፋ ለማስቆረጥ የሚጠቀመው ዘዴ ደግሞ፥ ትእዛዛቶችን እንደ ግዳጅ አድርገን እንድንመለከት በማድረግ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ የኛ ሃሳብ ያልሆነውን መቋቋም የሰው የተፈጥሮ ባህሪ ነው።

ጤናማ አመጋገብንና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከሃኪም የተሰጠ ግዴታ አድርገን የምንወስድ ከሆነ፥ በርግጥ እንወድቃለን። እነዚህን ምርጫዎች እንደማንነታችንና ምን መሆን እንደምንፈልግ ካየነው በመንገዱ ላይ ለመቆየት እና ውጤታማ ለመሆን የተሻለ እድል አለን።

የቤት ለቤት ትምህርትን የካስማ ግብ ብቻ አድርገን አድርገን ከወሰድን ለመከወን ያነሰ አመለካከትን ማስቀመጣችን ነው። እንደክርስቶስ እንድንሆንና ለሌሎች ለማገልገል እንደራሳችን ግብ አድርገን ከወሰድነው ግን፥ግዴታችንን ብቻ ሳይሆን የምንወጣው፥ የምንጎበኛቸውን ቤተሰቦች እና የራሳችንኑ ቤተሰብ በሚባርክ መልኩ እንወጣዋለን።

አብዛኛውን ጊዜ፥እርዳታ ከጓደኞች ወይም ከቤተሰብ ተቀባዮቹ እኛው ነን። ነገር ግን በተመልካች አይንና በተቆርቋሪ ልባችን ዙሪያችንን ከቃኘን ፥ ሌሎችን በድጋሚ እንዲነሱ እና ወደ እውነተኛው ብቃታቸው እንዲደርሱ ለመርዳት፥ ጌታ የሚያዘጋጃቸውን እድሎች እንገነዘባለን። ቅዱሳን መፅሃፍት እንደሚጠቅሱት፥ “የምታደርጉትን ሁሉ፥ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት ቆጥራችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት“።9

ቀናና ፃድቅ ህይወትን መምራት እና አይናችንን ለዘላለም መሆን የምንፈልግበት ቦታ ላይ ማተኮር፥ ታላቅ የመንፈሳዊ ሀይል ምንጭ ነው።

ትኩረታችን በለት ስኬታችን ወይም ውድቀታችን ላይ ሲሆን፥ መንገዳችንን ስተን፥ ተደናብረን እንወድቃለን። ከፍ ያሉ ግቦች ላይ በማተኮር፥ በተለይ በሰማይ የከፍታው እጣ ፈንታ ላይ በማተኮር፥ በመንገዱ ላይ እንቆያለን፥ እንዲሁም የተሻሉ ልጆችና ወንድሞች፥ ደግ አባቶች እና አብዝቶ አፍቃሪ ባሎች እንሆናለን።

ልባቸውን በመለኮታዊ ግብ ላይ የጣሉ እንኳ አንዳንድ ጊዜ ሊሰናከሉ ይችላሉ፥ ነገር ግን አይሸነፉም። በእግዚያብሄር ቃል ኪዳን ላይ ይተማመናሉ እናም ይሞረኮዛሉ። በፃድቁ አምላክ እና በሚያነሳሳ የወደፊት ራእይ ላይ ብሩህ ተስፋ በመጣል ዳግም ይነሳሉ፥ አሁኑኑ እንደሚያደርጉት ያውቃሉ።

አሁኑን ማድረግ ትችላላችሁ።

ሁሉም ሰው፥ወጣት እና ያረጀ፥ የራሱ የሆነ የመውደቅ ተሞክሮ አለው። መውደቅ የኛ የሟቾች ስራ ነው። ነገር ግን፥ ዳግም ለመነሳት እስከፈቀድን ድረስ እና እግዚአብሄር ወደሰጠን መንፈሳዊ ግቦች መንገድ ላይ እስከቀጠልን ድረስ ከውድቀት አንድ ነገር እንማራለን በስተመጨረሻም የተሻልንና ደስተኞች እንሆናለን።

ወንድሞች፥መነሳት ወይም መቀጠል አልችልም ብለን የምናስብበት ጊዜ ይኖራል። እባካችሁ አዳኙንና ፍቅሩን ተማመኑ። በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት እና ዳግም በተመለሰው ወንጌል ሃይል እና ተስፋ በማድረግ መቆም እና መቀጠል ትችላላችሁ

ውንድሞች፥ እናፈቅራችሗለን። እንፀልይላችሗለን። ወጣት አባት ብትሆኑ፥ ሽማግሌ የክህነት ተሸካሚ፥ ወይም አዲስ የተሾመ ዲያቅን፥እናውቃችሗለን። ጌታ ያውቃችሗል።

ጉዞአችሁ አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በጌታ ስም ይህንን ቃል እተውላችሗለሁ። ተነሱና ያዳኛችንን መንገድ ተከተሉ። እናም አንድ ቀን ወደሗላ ትመለከቱና ቤዛነቱን በመተማመናችሁ እና ከፍ ስላደረጋችሁና ጥንካሬን ስለሰጣችሁ በዘላለም ምስጋና ትሞላላችሁ።

ውድ ጓደኞቼና ወንድሞቼ፥ ምንም ያህል ተንሸራታችሁ ብትወድቁም፥ ተነሱ! እድላችሁ ክብር ያለው ነው። ከፍ ብላችሁ ቁሙ፥ በተመለሰው የክርስቶስ ብርሃን ተራመዱ። ከምታስቡት በላይ ጠንካራ ናችሁ። ከመትገምቱት በላይ ችሎታ አላችሁ። አሁኑኑ ማድረግ ትችላላችሁ። ይህንንም የምመሰክረው በእየሱስ ስም ነው አሜን።