Skip main navigation
ሚያዝያ 2014 | በመልሶ በተቋቋመው ስራ ውስጥ እየተሳተፋችሁ ነውን?

በመልሶ በተቋቋመው ስራ ውስጥ እየተሳተፋችሁ ነውን?

ሚያዝያ 2014 አጠቃላላ ጉባኤ

ይህም ቅዱስ ስራ በጣም አስፈላጊ ሆኖ እንደ ግለሰቦች፣ እንደ ቤተሰቦች፣ እና እንደ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የግማሽ ልብ ጥረት ብቻ መሰጠት የማይገባው አይደለም።

ከ200 አምት በፊት፣ የአሜሪካ አጭር ታሪክ “ሪፕ ቫን ዊንክል” ወዲያው ታዋቂ ሆነ። የታሪኩ ዋናው ሰው፣ ሪፕ፣ ሁለተ ነገሮች፣ እንዲሁም ስራን እና ሚስቶን፣ በማስወገድ ብቻ ጎበዝ የሆነ ታላቅ ፍላጎት የሌለው ሰው ነበር።

አንድ ቀን፣ ከውሻው ጋር በተራራ ላይ ዞር ዞር ሲል፣ ልዩ ልብስ የለበሱ ሰዎች ሲጫወት እና ሲጠጡ አገኛቸው። ከእነርሱ አንዳንድ መጠጣቸውን ከተቀበለ በኋላ፣ ሪፕ ደከመው፣ እናም አይኖቹን ለትንሽ ጊዜ ጨፈነ። አይኖቹን እንደገና ሲከፍት፣ ውሻው በዚያ ባለመገኘቱ፣ ጠመንጃው ዝጎ፣ እና አሁን ረጅም ጢም እንዳለው በማግኘቱ ተደንቆ ነበር።

ሪፕ ወደ መንደሩ ሲመለሰ ሁሉም ነገሮች ተቀይረው አገኘ። ሚስቱ ሞታለች፣ ጓደኞቹ የሉም፣ እናም በቡና ቤት ውስጥ የነበረው የንጉስ ጆርጅ፣ ሶስተኛው ስዕል በማያውቀው፣ በጀነራል ጆርጅ ዋሽንግተን፣ ሰዕል ተተክቶ ነበር።

ሪፕ ቫን ዊንክል ለ20 አመት ተኝቶ ነበር! በዚህም ሁኔታ፣ በሀገሩ ውስጥ አስደናቂ የነበሩትን ጊዜዎች ሳያያቸው አለፉ--የአሜሪካ አብዮት ተኝቶ አለፈ።

በግንቦት 1966፣ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ ታናሹ፣ “አብዮቱ እስኪያልፋችሁ ድረስ አትተኙ” በሚለው ንግግራቸው ውስጥ ይህን ታሪክ ተጠቀሙበት።1

ዛሬ፣ ይህን ጭባጥ መልእክት ለመጠቀም እና የእግዚአብሔር ካህናትን በሙሉ፥ በመልሶ በተቋቋመው ስራ ውስጥ እየተሳተፋችሁ ነውን? በማለት ለመጠየቅ እፈልጋለሁ።

በዳግም መመለስ ጊዜ ውስጥ ነው የምንኖረው።

አንዳንዴ የወንጌል በዳግም መመለስ የተፈጸመው፣ በኋላችን እንደሆነ ያስባሉ--ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን ተርጉሟል፣ የክህነት ቁልፎችን ተቀብሏል፣ ቤተክርስቲያኗ ተደራጅታለች። በእውነት ግን፣ የዳግም መመለስ የሚቀጥል ስራ ነው፤ አሁን የምንኖርበት ነው። ይህም “እግዚአብሔር የገለጻቸውን፣ እና አሁን የሚገልጻቸውን” እና ገና የሚገልጻቸውን “ብዙ እና አስፈላጊ ነገሮች” የያዘ ነው።2 ወንድሞች፣ በዚህ ጊዜ የሚገኙት አስደሳች ነገሮች በአዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ አስገራሚ ዳግም ምፅዓት ጊዜ ለሚፈጸሙት ነገሮች አስቀድመው ተገግረው የነበሩ መዘጋጂያዎች ናቸው።

ይህም በአለም ታሪክ ውስጥ ከሁሉም በላይ አስደናቂ የሆነ ጊዜ ነው። የጥንት ነቢያት ጊዜአችንን ለማየት በጉጉት ይፈልጉ ነበር።

የምድር ህይወታችን ሲፈጸም፣ ስለዚህ የህይወታችን ታላቅ ትርጉብ ባለው ጊዜ እና የጌታን ስራ ወደፊት በመግፋት ምን ያህል ተሳታፊነት እንደነበረን ምን አጋጣሚያችንን ለመካፈል እንችላለን።? በሙሉ ልባችን፣ በሀይላችን፣ በአዕምሮአችን፣ እና በጥንካሬአችን በሀይል ሰራን ለማለት እንችላለን? ወይም ሀላፊነታችሁ እንደ ተመልካች ብቻ እንደሆነ በግዴታ የምታስታውቁ ትሆናላችሁን?

የእግዚአብሔርን መንግስት በመገንባት ስራ በሚመለከት ተሳታፊ አለመሆን ቀላል የሚሆንበት የተለያዩ ምክንያቶችን እንደሚኖሩ አስብበታለሁ። ከእነዚህ ውስጥ ታላቅ የሆኑትን ሶስቶች ልጥቀስ። ማናውም እናንተን የሚያመለክት ከሆነ እንድታሰላስሉበት እጋብዛችኋለሁ። ለማሻሻል የሚቻል ከሆነ፣ ለማሻሻል ምን ለመቀየር ምኝ ማድረግ እንደምትችሉ እንድታስቡበትም እጠይቃለሁ።

ራስ ወዳድነት

መጀመሪያ ራስ ወዳድነት

ራሳቸውን የሚወዱት ከሁሉም በላይ የራሳቸውን ፍላጎት እና ደስታ ይፈልጋሉ። ራስ ለሚወድ ሰው ዋናው ጥያቄ “ለእኔ ምን ጥቅም አለው?” የሚል ነው።

ወንድሞች፣ ይህ ጸባይ የእግዚአብሄርን መንግስት ለመገንባት ከሚያስፈልገው መንፈስ ተቃራኒ እንደሆነ እንደምትመለከቱ እርግጠኛ ነኝ።

ሌሎችን ከማገልገል በላይ ራሳችንን ለማገልገል ስንፈልግ፣ ቀዳሚ ማከናወን የሚያስፈልጉን ራስ ታዋቂነት እና ደስታ ላይ የሚያተኩሩ ይሆናሉ።

የድሮ ትውልዶች በተለያዩ ስስትነቶች ይታገሉ ነበር፣ ነገር ግን ዛሬ በዚህ ከእነርሱ ጋር በጣም እየተፎካከርን ነን። በቅርብ የኦክስፈርድ መዝገብ ቃላት በእንግሊዘኛ “የግል ፎቶን ማንሳት” የሚል ትርጉም ያለው ቃል የአመቱ ታዋቂ ቃል ነው ብለው ማወጃቸው አጋጣሚ አይደለም።3

ሁላችንም ታዋቂ ለመሆን ፍላጎት አለን፣ እናም በመዝናናት እና እራሳችንን በማስደሰት ምንም ጥፋት የለውም። ነገር ግን “የአለም ጥቅምና ሙገሳን”4 መፈለግ የሚያነሳሳን ዋና ነገር ከሆነ፣ ለጌታ ስራ በፈቃደኝነት ስንፋተፍ የሚመጣጡት የሚያድኑ እና አስደሳች አጋጣሚዎች ያመልጡናል።

መፍትሄው ምንድን ነው?

መልሱም እንደ ሁልጊዜም በክርስቶስ ቃላት ውስጥ ይገኛሉ።

“በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።

“ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል።”5

እግዚአብሔርንና ሰዎችን ለማገልገል እና ወደአዳኝ ህይወታችንን በሙሉ ልባችን አሳልፈው የሚሰጡ ራስን የሚወዱ ሥተኞች በህይወታቸው ሊያጋጥማቸው የማይችል የህይወት ሀብትን እና ሙሉነት ያገኛሉ። ራስ ወዳጅ ያልሆኑት ያላቸውን ይሰጣሉ። እነዚህም ታላቅ ተፅዕኖ የሚኖራቸው የፈገግታ፣ የእጆች መጨበጥ፣ የማቀፍ፣ ለማዳመጥ ጊዜ የመውሰድ፣ የምያበረታቱ ቃላት፣ ወይም እንደምታሰቡላቸው የሚያሳይ ምልክት አይነት ትንሽ የልግስና ስጦታዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ከባለቤቶቻችን እና ቤተሰቦቻችን በተጨማሪ ሰዎችን የማፍቀርና የማገልገል መጠን የሌላቸውን እድሎች ስንጠቀምባቸው፣ እግዚአብሔርን የማፍቀር እና የማገልገል ችሎታችን በጣም ይጨምራሉ።

ሌሎችን የሚያገለግሉ በመልሶ በተቋቋመው ስራ ውስጥ ይሳተፋሉ።

ሱስ

በዚህ አለም በመልሶ በተቋቋመው ስራ ውስጥ እንዳንሳተፍ ከሚያደርጉብን ነገሮች አንዱ ሱስ ነው።

ሱስ በአብዛኛው ጊዜ የሚጀመረው በቀስታ ነው። ሱስ በተደጋጋሚ ስራ ምክንያት ጸባይ የሚሆን ነገር ነው። መጥፎ ልምዶች ለማጥፋት የሚችሉ ሱስ ለመሆን የሚያስችል አቅም አላቸው።

የሚያሳስሩ እንደ ወሲብ ነገሮችን መመልከት፣ መጠጥ፣ ወሲባዊ ግንኙነት፣ አደንዛዥ እጽ፣ ትምባሆ፣ ቁማር፣ ምግብ፣ ስራ፣ ኢንተርኔት፣ ወይም እውነት የሚመስሉ መጫወቻዎች አይነት የሱስ ሰንሰሎቶች ልዩ አይነት ቅርጽ ሊኖራቸው ይችላሉ። ጠላታችን ሰይጣን በጌታ መንግስት ውስጥ ሚስዮናችንን የምናከናውንበትን መለኮታዊ ችሎታችንን ለመስረቅ ብዙ የሚወዳቸው መሳሪያዎች አሉት።

አንዳንዱ ልዑል ልጆቹ በፈቃደኝነት እጆቻቸው በሚያጠፋው ሱስ ሰንሰለት እንዲታሰሩ ለመስጠት ፈቃደኛ እንደሆኑ በመመልከቱ የሰማይ አባታችን ያዝናል።

ወንድሞች፣ ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ዘለአለማዊ ክህነት አለን። የልዑል እግዚአብሔር ወንድ ልጆች ነን እናም ለመናገር በማይቻል ችሎታዎች ባርኮናል። ከሁሉም በላይ ታላቅ የሆነውን መለኮታዊ ችሎታችንን ለማከናወን እንድንችል የተነደፍን ነን። በምድራዊ ፍላጎት እና በሱስ ምክንያት መለኮታዊ ችሎታችንን ለመገደብ የታቀደልን አይደለንም።

መፍትሄው ምንድን ነው?

በመጀመሪያ ሊገባን የሚያስፈልገው ሱስ እንዳይጀመር ለማስወገድ ከማዳን በላይ የቀለለ እንደሆነ መረዳት ነው። አዳኝ እንዳለው፣ “ከእነዚህ ነገሮች ማንኛውም ወደ ልባችሁ እንዲገባ አትፍቀዱ።”6

ከብዙ አመት በፊት፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እና እኔ የአየር ሀይል አንድ ተብሎ የሚጠራውን የአሜሪካ ፕሬዘደንትን የሚያጓጉዝ አስደናቂ አውሮፕላንን ለመጎብኘት እድል ተሰጥቶን ነበር። ሀይለኛ የጥንቃቄ ፍተሻዎች ነበሩ፣ እናም ነቢዩ አውሮፕላኑ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ጠባቂዎቹ ሲፈትሿቸው ስመልከት ፈገግ ብዬ ነበር።

አዛዥ የነበረው የአውሮፕላኑ አብራሪ የአብራሪውን መቀመጫ እንድቀመጥበት ጋበዘኝ። ለብዙ አመታት አበራቸው የነበሩ አይነት አስደናቂ የማብረሪያ መዚን ላይ እንደገና መቀመጥ በጣም አስደናቂ አጋጣሚ ነበር። ባህር እና ክፍለ አህጎሮችን በማቋረጥ የመብረሩ ትዝታዎቼ ልቤንና አዕምሮዬን ሞሉ። በአለም በተለያዩ የአውሮፕላን ማረፊያ ቦታዎች በሚያስደስት ሁኔታ ከምድር የምነሳበትን እና የማርፍበትን በአዕምሮዬ ለማየት ቻልኩኝ።

ሳላስብበትም፣ አውሮፕላኑን በማበርበት መሳሪያዎች ላይ እጆቼን አሳረፍኩኝ። በዚያ ጊዜም፣ የቶማን ኤስ. ሞንሰን ተወዳጅ እና ስህተት የማይደረግበት ድምጽ ከኋላዬ መጣ።

“ዲየተር፣ አታስብበት” አሉኝ።

ለምንም ነገር ተቀባይ አይደለሁም፣ ግን ፕሬዘደንት ሞንሰን በአዕምሮዬ ላይ የነበረውን የተመለከቱ ይመስላል።

ማድረግ የማይገባንን ነገር ለማድረግ ፈተና ሲመጡብን፣ ከምያፈቅር ቤተሰብ፣ ጓደኞች፣ ውድ ነቢያችን፣ እና ሁልጊዜም ከአዳኝ የሚመጡትን ማስጠንቀቂያዎች እናድምጥ።

ሱስን ከሁሉም በላይ በፍጹም የሚከላከለው አለመጀመሩ ነው።

እራሳቸውን በሱስ አጥብቆ የተያዙትስ?

መጀመሪያ ተስፋ እንዳለ እባካችሁ እወቁ። ከምታፈቅሯቸው፣ ከቤተክርስቲያን መሪዎች፣ እና ከተሰላጠኑ አማካሪዎች እርዳታ ፈልጉ። በአካባቢዎቹ የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ በኢንተርኔት፣ 7 እና በአንዳንድ ቦታዎችም በLDS Family Services [በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የቤተሰቦች አገልግሎት ድርጅቶች] ከሱስ የሚዳንበት እርዳታን ቤተክርስቲያኗ ታቀርባለች።

በአዳኝ እርዳታ ከሱስ ነጻ ለመሆን እንደምትችሉም ሁልጊዜም አስታውሱ። ረጅም እና አስቸጋሪ መንገድ ይሆናል፣ ነገር ግን ጌታ በእናንተ ላይ ተስፋ አይቆርጥም። ያፈቅራችኋል።፡ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተ እንድትቀየሩ፣ ከኃጢያት ምርኮ እናንተን ነጻ ለማድረግ የተሰቃየበ ነው።

ለሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነው ቢኖር ሁልጊዜም መጣር ነው--አንዳንዴ ሰዎች ውጠኢታማነትን ከማግኘታቸው በፊት በተደጋጋሚ መጣር አለባቸው። ስለዚህ አታቁሙ። እምነታችሁን አታጥፉ። ልባችሁን ወደጌታ አቅርቡ፣ እናም የመዳን ሀይል ይሰጣችኋል። ነጻም ያደርጋችኋል።

ውድ ወንድሞች፣ ወደሱስ ከሚመሩት ጸባዮች እራሳችሁን አስወግዱ። ይህን የሚያደርጉትም ልባቸውን፣ አዕምሮአቸውን፣ እና ጥንካሬአቸውን እግዚአብሔርን ለማገልገል መስዋዕት ለማድረግ ይችላሉ።

በመልሶ በተቋቋመው ስራ ውስጥ ይሳተፋሉ።

የሚፎካከሩ ቅድሚያዎች

በዚህ ስራ በሙሉ ከመሳተፍ ከሚያስወግዱን ሶስተኛውም የሚያጋጥሙን ብዙዎቹ የሚፎካከሩ ቅድሚያዎች ናቸው። አንዳንዶቻችን በጣም በስራ ተጠምደን ወደተለያዩ መንገዶች በአስራ ሁለት እንስሣት እንደምንጎተት ጋሪ አይነት ይሰማናል። ብዙ ሀይል ይጠቀማል፣ ግን ጋሪም ምንም ቦታ አይሄድም።

በብዙ ጊዜ ከሁሉም የሚሻለውን ጥረታችንን ልምዶችን፣ ስፖርትን፣ ለስራ የምንወደውን፣ እና የህብረተሰብን ወይም የፖለቲካን ጉዳይ በመከታተል ላይ መስዋዕት እናደርጋለን። እነዚህ ነገሮች ሁሉ መልካም እና የሚከበሩ ናቸው፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ቅድሚያ ሊኖራቸው ለሚገቡ ነገሮች ጊዜ እና ሀይል ይተዉልናልን?

መፍትሄው ምንድን ነው?

እንደገናም ይህም የሚመጣው ከአዳኝ ቃላት ነው፥

“ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።

“ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።

“ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም። ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።”8

ከእነዚህ ሁለተ ታላቅ ቅድሚያዎች በስተቀር በህይወት የሚገኙ ሌሎች ሁለተኞች መሆን ይገባቸዋል።

በቤተክርስቲያን አገልግሎትም፣ የደቀመዛሙርትነት ልብ ወይም ፍላጎት ሳይኖር መደረግ የሚገባውን በማከናወን ብቻ ብዙ ጊዜዎችን ማሳለፍ ቀላል ነው።

ወንድሞች፣ እኛ እንደ ካህናት እግዚአብሔርን እና ባልንጀራዊቻችንን ለማፍቀር የልብ ውሳኔ አድርገናል እናም ያንን ፍቅር በቃል እና በስራ ለማሳየትም ፈቃደኞች ነን። ያም የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆን ማንነት ነው።

በእነዚህ መሰረታዊ መርሆች የሚኖሩትም በዳግም መመለስ ጊዜ አያንቀላፉም።

የንቃት ጥሪ

ሐዋሪያው ጳውሎስ እንደጻፈው፣ “ስለዚህ፣ አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል።”9

ውድ ጓደኞች፣ የብርሀን ልጆች እንደሆናችሁ እወቁ።

ራስ ወዳጅነትን አትፍቀዱ! ወደሱስ የሚቀየሩ ጸባዮችን አትፍቀዱ! የሚፎካከሩ ቅድሚያዎች ችላ ወደማለት ወይም ከሚባርክ ደቀ መዛሙርትነት እና ልዑል ከሆነ የክህነት አገልግሎት ለይቶ እንዲመሯችሁ አትፍቀዱ!

ይህም ቅዱስ ስራ በጣም አስፈላጊ ሆኖ እንደ ግለሰቦች፣ እንደ ቤተሰቦች፣ እና እንደ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የግማሽ ልብ ጥረት ብቻ መሰጠት የማይገባው አይደለም።

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙር መሆን በሳምንት የአንድ ቀን ወይም የአንድ ቀን አንድ ጥረት ብቻ አይደለም። ይህም ሁልጊዜ የሚደረግ ጥረት ነው።

ጌታ ለእውነተኛ የክህነት ባለስልጣኖቹ የሰጠው የተስፋ ቃል ታላቅ ሆኖ ለመረዳት የሚያስቸግር ነው።

ለእነዚህ ሁለት ክህነቶች ታማኝ የሆኑት እና ጥሪአቸው የሚያጎሉት “ሰውነቶታቸውን ወደማደስ የተጸደቁ ናቸው።” ስለዚህ፣ አባታችን ያለውን በሙሉ ለእነርሱ ይሰጣቸዋል።10

የኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢያት ክፍያ የሚያጸዳው ሀይል እና የመንፈስ ቅዱስ የሚቀይረው ሀይል የሰው ዘርን ለመፈወስ እና ለማዳን እንደሚችሉ እመሰክራለሁ። እርሱን ፈቃደኛ በሆነ አዕምሮ እና በሙሉ ልብ አላማ እንድንከተል የተሰጠንን የአዳኝ ጥሪ ማድመጥ የእኛ መብት፣ ቅዱስ ሀላፊነት፣ እና ደስታ ነው። እኛም “የታሰራችሁበትን ሰንሰለት አውልቁ፣ ከጨለማም ውጡ፣ ከትቢያም ተነሱ።”11

እንንቃ እና መልካም በማድረግ አንድከም፣ ምክንያቱም “የታላቅ ስራን መሰረት እየሰራን ነን”12፣ እንዲሁም ለአዳኝ በዳግም መመለስም እየተዘጋጀን ነን። ወንድሞች፣ የምሳሌአችሁን ብርሀን በዳግም በተመለሰው እውነት ወብት እና ሀይል ላይ ስትጨምሩ፣ በመልሶ በተቋቋመው ስራ ውስጥ ተሳተፉ። ስለነዚህ ነገሮች የምመሰክረው እና በረከቴን የምሰጣችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

Left
Right
ማጣቀሻወችን ያሳዩማጣቀሻወችን መደበቅ

  ማስታወሻዎች

  1. See Martin Luther King Jr., “Don’t Sleep Through the Revolution” (1966 Ware Lecture, Unitarian Universalist Association General Assembly, Hollywood, Florida, May 18, 1966).

  2. የእምነት አንቀጽ 1:9.

  3. See blog.oxforddictionaries.com/press-releases/oxford-dictionaries-word-of-the-year-2013.

  4. 2 ኔፊ 26:29.

  5. ማርቆስ 8:34–35.

  6. 3 ኔፊ 12:29.

  7. ለምሳሌ lds.org/topics/addiction ተመልከቱ.

  8. ማቴዎስ 22:37–39.

  9. ኤፌሶን 5:14.

  10. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84:33, 38 ተመከቱ.

  11. 2 ኔፊ 1:23.

  12. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64:33 ተመከቱ.