2010–2019 (እ.አ.አ)
አይዞህ፤ አትፍራ
ሚያዝያ 2014


አይዞህ፤ አትፍራ

ተቃርኖ በሆነው አስተያየት ልዩ መልስ ለመስጠት ብርታት ሊኖርን ይገባል ።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ከእናንተ ጋር በድጋሜ መሆን እንዴት አስደሳች ነው። ይህን አድል ወስጄ እናንተን ሲናገርመለኮታዊ እርዳታ እንዲኖረኝ እፀልያለሁ።

ከዚህ የጉባዬ ማዕከል ውጪ በሺዎች በመሰብሰቢያ አዳራሽ እና በሌሎች ቦታዎች በዓለም ዙሪያ ብዙ ተሰብስበዋል። ሁላችንም እርስ ለእርሳችን ያስተሳሰረን የጋራ የሆነ ነገር አለን፣ የእግዚያብሔርን የክህነት ስልጣን እንድንሸከም ኃላፊነት ተሰቶናልና።

በታሪክ ውስጥ በአስገራሚ ጊዜ በዚህ ምድር ላይ ነው ያለነው። እድሎቻችን የተገደቡ አይደሉም፣ ነገር ግን በዛ ላይ ብዙ ፈተናዎችን ም እንጋፈጣለን. አንዳንዶቹም ፈተናዎች ለጊዜያችን የተለዩ ናቸው።

የስነ ምግባር ዋጋዎች በተጣሉበት፣ ሀጥያት በአደባባይ በግልፅ የሚታይበት፣ በቀችኗ እና በጠባቧ መንገድ በማያቋርጥ ኃይል እና በሚያታልሉ ተፅእኖች ታጋፍጠናል። የማያቋርጠው ኃይል መልካም የሆነውን እያጠፋና በእግዚያብሔር ላይ የተመረኮዘ ትምህርትን በማይረባ ፍልስፍና ለመተካት እየሞከሩ ነው።

በነኚህ እና በሌሎች ፈተናዎች ምክንያት፣ መድረሻችንን የሚወስኑ ውሳኔዎች ከፊታችን ሁለም አሉ። ትክክለኛውን ውሳኔዎች ለመወሰን ብርታት፣ እንዲሁም አይሆንም የማለት ብርታት፣ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ አሺ የማለትን፣ ትክክለኛውን ነገር ትክክክል ስለሆነ የማድረግ ብርታት ያስፈልጋል።

የማህበረሰቡ ደረጃዎች ጌታ ከሰጠን ዋጋዎች እና መመሪያዎች በፍጥነት እያረቁ ቢሆኑም፣ በእርግጥ ለምናምነው ነገር እንድንከላከል እንጠየቃለን። ይህንንም ለማድረግ ብርታት ይኖረናል?

ለብዙ አመታት የመጀመሪያው ቀዳሚ አመራር ውስጥ የነበሩት ፕሬሰዳንት ጄ. ሪዩበን ክላርክ፣ ታናሹ እንዲህ አሉ፣ “እምነት እንዳላቸው የሚያሳዩ ሰዎች፣ እምነታቸውን በማረጋገጥ በማያምኑት ሰዎች ይሳለቁበናል በማለት በማመን፣ እምነታቸውን ምክንያት በመስጠት ተራ ለማድረግ ወይም በጥፋት ለማዋረድ ወይም እንደሚቀረውሩት ለማስመሰል እንዳለባቸው እንደሚሰማቸው መኖሩ የማይታወቁ አይደሉም። እነዚህም ግብዝ ናቸው።”1 ማንኛችንም እንደዚህ አይነት ምልክት በእኛ ላይ እንዲኖሩ አንፈልግም፣ ግን በአንዳንድ ጉዳዮች ሀይማኖታችንን ለማወጅ የምንፈራበት አለ?

የእግዚያብሔር መንፈስ ምቾት የሚሰማበት እና ሀሳቦቻችን በመልካም ተፅዕኖ የሚወድቁበት ቦታና እንቅስቃሴዎች ላይ የምንለማመድ ከሆነ መልካምን የማድረግ ፍላጎታችንን ለመርዳት እንችላለን።

ከጥቂት ጊዜ በፊት ለትምህርት ራቅ ብሎ ለሚሄደው ልጁ አባት የሰጠውን ምክር ያነበብኩትን አስታውሳለሁ፣ “መሆን የሌለብህ ቦታ እራስክን ካገኘኸው፣ ከዚያ ውጣ”። ለእያንዳንዳችን ተመሳሳይ ምክርን አቀርባለሁ “እራሳችሁን መሆን የሌለባችሁ ቦታ ካገኛችሁት ፣ ከዚይ ውጡ።”

የብርታት ጥሪ በየጊዜው ለእያንዳንዳችን ይመጣል። በእያንዳንዷ የሕይወታችን ቀኖች ብርታት አስፈላጊ ነው ----- ለትልቅ ዝግጅቶች ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን በአብዛኛው ውሳኔ ስንወስን እና በዙሪያችን ላሉ ሁኔታዎች መልስ ስንሰጥም ያስፈልጋል። የስኮትላንድ ገጣሚ እና ደራሽ ሮበርት ሉዊ ኢስቴቨንሰን እንዲህ አለ፥ “በየቀኑ ብርታት በቁጥር ያነሱ መስካሪዎች አሉት። ነገር ግን የትኛውም ከበሮ ለእናንተ ባይመታም ወይም የትኛውም ህዝን የናንተን ስም እየጠራ ባይጮህም፣ የናንተ ብርታት መልካምነቱ ያነሰ አይደለም ።”2

ብርታት በብዙ መልኮች ይመጣል። የክርስቲያን ጸሀፊው ቻርልስ ስዊንዶል እንደጻፈው፥“ብርታት በጦር ሜዳ ላይ ብቻ የተወሰ..... ወይም በከፍተኛ ጉብዝና ሌባን ቤታችሁ ውስጥ መያዝ አይደለም። በአብዛኛዎቹ ፈተናዎች በአብዛኛው በቀጥታ የሚታዩ ናቸው። ውስጣዊ ፈተናዎች ልክ ማንም ሳይመለከታችሁ በእምነት መቆየት፣ ልክ ሰዎች ስል እምነታችሁ ሳይረዱ ሲቀሩ ለብቻ መቆም ናቸው።”3 በተጨማሪም ምንም ፈርተን ቢሆንም ትክክለኛው ነገር ማድረግና ምንም እንኳን አንዳንዶች ብያሾፉባችሁም ያጠቃልላል። እናም እምነታችንን በደንብ መጠበቅ አንዳንዴ ጓደኞቻችንን እና ማህበረሰቡን ለኛ ያለውን ቦታ ወደማጣት እንድንሄድ በሚያደርግ አደጋ ላይ ያደርሰናል።

በዩናይትድ ስቴት የባህር ኃይል በማገልገል ላይ ሳለሁ ፣ ስለ ጀግና የሆኑ ስራዎች ፣ የድፍረት ጊዜ፣ እናም የብርታት ምሳሌዎችን ተማርኩ። በጭራስ የማልረሳው የ18 አመቱን ወታደር ብርታት ነበር። የእኛ ቤተክርስቲያን አባል አይደለም----- ለመፀለይ የሚፈራም አልነበረም። አበረውት ከነበሩት 250 ወንዶች መካከል በእግዚአብሔር የማያምኑት ሲሳለቁበት እና ሲቀልዱበት በአልጋው ጫፍ ሁልጊዜም የሚንበረከክ እሱ ብቻ ነበር። ባጎነበሰ ጭንቅላቱ ለእግዚአብሔር ይጸልይ ነበር። ለመፀለይ ፈርቶም ወደ ኋላ ብሎም አያውቅም። ብርታት ነበረው።

በቅርብ ይህን ውስጣዊ ብርታት ስላጣ አንድ ሰው ሰማሁ። ጓደኛዬ መንፈሳዊ እና እምነትን የሚገነባ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ እሷ እና ባሏ በዋርዳቸው ውስጥ እንደተሳተፉ ነገረችኝ። በአሮናዊ የክህነት ስልጣን የካህንነት ሀላፊነት ያለ ወጣት ወንድ ልጅ ስለ ወንጌል እውነቶች እና የትዛዛትን መጠበቅ ደስታ ሲናገር እያለ የተሰብሳቢውን ሁሉ ልብ ነካ። የፀዳውን ነጭ ሸሚዝ እና ከረባቱን አድርጎ በመስበኪያው ላይ ቆሞ በመገልፅ የጋለ እና የሚነካ ምስክርነቱን ሰጠ።

በዚያኑው ቀን በኋላም፣ ይህች ሴት እና ባሏ ከዚያ መንደር በመኪና እየወጡ ሳለ፣ ከትንሽ ሰዓታት በፊት ያነሳሳቸውን ወጣጥ ወንድ ልጅ አዩት። ነገር ግን አሁን በእግረኛ መንገድ እየተግዋዘ ሳለ በፍፁም በተለየ ገፅታ ኖሮት፣ ያደፈ ልብስ ለብሶ ሲጋራ እያጨሰ ነበር። ግዋደኛዬ እና ባሏ በመከፋት እና በማዘን ውስጥ ብቻ አልነበሩም ነገር ግን በአሳማኝ ሁኔታ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ ሌላ ሰው እና ከዚያ በፍጥነት ሙሉ ለሙሉ ሌላ ሰው መሆን መቻሉ ግራ ገብቷቸው ነበር።

ወንድሞች፣ የትም ቦታ ሁኑ፣ ምንም ነገር ብታደርጉ፣ የሰማይ አባታችን እንድንሆን የሚፈልገውን አይነት ሰው እና የምታውቁትን መሆን ያለባችሁን አይነት ሰው ተመሳሳይ ናችሁን?

በብሔራዊ ካለ ምልልስ የታተመ መፅሄት ላይ፣ ታዋቂው የአሜሪካ የኤንሲኤኤ ቅርጫት ክዋስ ተጫዋች ጃባሪ ፓርከር፣ የቤተክርስቲያን አባል የሆነው ፣ ከአባቱ ከተቀበለው ምርጡን ምክር እንዲያካፍል ተጠይቆ ነበር። ጃባሪ እንዲ ሲል መለሰ፣ “በብርሃን ውስጥ ሳለህ ያለከውን ተመሳሳይ አይነት ሰው በጭለማ ውስጥ ስትሆን ሁን።”4 ወንድሞች ይህ ለሁላችንም ጠቃሚ ምክር ነው።

ቅዱስ መፅሐፍቶቻችንዛሬ ሁላችንም በምንፈልገው የብርታት አይነትምሳሌ የተሞሉ ናቸው። ነብዩ ዳንኤል ከፀለየ ሞት እንደሚደርስበት ማስፈራሪያ ቢደረግበትም እውነት ነው ብሎ ላወቀው ነገር በመቆም እና የፀሎት ብርታትን በማሳየት ታላቅ ብርታትን አሳየ።5

የብርቱ አብናዲ ሕይወት ባህርይ የታየው እውነቱን ከመካድ ህይወቱን ለመስጠት በነበረው ፍቃደኝነቱ ነበር።6

ለመንፃት እና ለመፅዳት የወላጆቻቸውን ትምህርት አስፈላጊ ብርታትን በአስተማሩት እና ባሳዩት በሄለማን 2,000 ወጣት ሰራዊት ልጆች አልተነሳሳንምን?7

እነኚ እያንዳንዳቸው ቅዱስ መፅሃፍታዊ መግለጫዎች ያለ ምንም መሰላቸት እስከ ህይወቱ መጨረሻ ለመዝለቅ ብርታት በነበረው ሞሮኒ ምሳሌ ይበልጣል።8

ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በህይወቱ ሙሉ መቆጠር የማይችሉ የብርታት ምሳሌዎችን አቅርቧል። እሱና ወንድሞቹ በሰንሰለት በአንድ ላይ ታስረው በሪችሞድ፣ ሙዙሪ ውስጥ ያለ ፍርድቤት አጠገብ ወደሚገኘው ያላለቀ ቤት ውስጥ ተይዘው በነበረበት ጊዜ ነበር ከሚያስደንቁ ነገሮች አንዱ ነገር የሆነው ። ከእርሱ ጋር አብሮ ከተያዙት አንዱ የነበረው ፓርለይ ፒ. ፕሬት በአንድ ምሽት እንዲ በማለት ፃፈ፣ “ አፀያፊ ቀልዶችን፣ መጥፎ መሃላዎችን፣ የምያስጥሉ ስድቦችን እና የጥባቂዎቹን ቆሻሻ እየሰማን እኩለ ሌሊት ሰዓት እስክታልፍ ድረስ ጆሮአችን እና ልባችን ታመው ነበር።”

የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ቀጥለውም

“ በጣም ያስጠላኝ፣ የደነገጥቁ፣ የተሳቀቅኩ፣ ያህል እስኪሰማኝ ድረስ በእግሮቼ ቆሜና ጥበቃዎቹን ከመገሰፅ እራሴን መቆጣጠር ከባድ ነበር። ከጆሴፍ ስሚዝ አጠገብ ተኝቼ እሱ እንቅልፍ እንዳልወሰደው ባውቅም ነገር ግን ለእሱና ለየትኞቹም ምንም አላልኩም ነበር። በድንገት በእግሩ ቆሞ በመብረቅ ድምፅ፣ ወይም አንበሳ እንደሚያገሳ፣ በፍፁም ድምፅ ማስታወስ እስከሚችለው ድረስ የሚከተለውን ተናገረ፥

“ ፀጥታ...... በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እገስፃችኋለሁ ፣ ዝም እንድትሉ አዛችኋለሁ; እንደዚ አይነት ንግግር በመስማት አንድ ደቂቃ መኖር አልችልም። እንደዚ አይነት ንግግር አቁሙ፣ አለበለዚያ እኔ ወይም አናንተ በዚች ቅፅፈት ውስጥ ትሞታላችሁ።”

በቤተክርስቲያን ሽማግሌ ፕሬት እንደተገለፀው፣ ጆሴፍ ስሚዝ “ በታላቅ ግርማ ቆመ፣”። ያለመሳሪያ በሰንሰለት ታስሮ ነበር፣ ግን የተረጋጋና ግርማ ሞገስ ያለው ነበር። ወደ ቤቱ ጥግ የሸሹት እና እግሩ ስር ቁጢጥ ያሉት በፍርሃት የተሞሉ ጥበቃዎችን ወደ ታች ተመለከታቸው። እነኚ የማይታረሙ ሰዎች ጆሴፍ ስሚዝ ይቅር እንዲላቸው ለመኑት እናም በፀጥታ ቆዩ።9

ሁሉም የብርታት ድርጊቶች አስደናቂ ወይንም አፋጣኝ ውጤቶችን አይመጣም፣ ነገር ግን ሁሉም የአእምሮ ሰላምን እና እውነተኛው እና ትክክለኛው እውነትን ያመጣል።

ድርጊታችሁ ከሰዎች በተደጋጋሚ በሚሰጡ አስተያየቶች እና በሌሎች ተቀባይነት ላይ የምትመሰርቱ ከሆነ የወንጌልን መመሪያዎች ለመቀጠል በጣም የማይቻል ነው። ትክክለኛ ነው ብለን የምናውቀውን ጠንክረን እንድንይዝ እና እንድንፀና ልክ እንደ ዳንኤል፣ አብናዲ፣ ሞርኒ ወይም አንደ ጆሴፍ ስሚዝ ብርታት ያስፈልጋል። ቀላል የሚሆነው ለማድረግ ሳይሆን ትክክል የሆነውን ለማድረግ ብርታት ነበራቸው።

ፍራቻን ፣ የሰዎች መሳለቅን እና ተቃርኖን እንጋፈጣለን ። ተቃርኖ በሆነው አስተያየት ልዩ መልስ ለመስጠት ብርታት ሊኖርን ይገባል ። ለመመሪያ ለመቆም ብርታት፣ መጥፎን ከጥሩ ያለ ማስታረቅ ብርታት ፣ የእግዚአብሔርን ተቀባይነት ያመጣል። ብርታት ህያውና የሚያስደስት ምግባር የሚሆነው እንደ ጀግና ለመሞት ፈቃደኛ በመሆን ብቻ ሳይሆን በመልካምነት ለመኖር በመወሰን ነው። ወደ ፊት ጉዞአችን ላይ መኖር እንዳለብን ለመኖር ስንጥር በእርግጥ ከጌታእርዳታ እንቀበላለን እናም በቃሎቹ ውስጥ መፅናናትን እናገኛለን ። በመፃፈ ኢያሱ የተመዘገበውን ቃልኪዳን እውደዋለሁ።

አልጥልህም ፣ አልተውህም …

“... በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚያብሄር ከናንተ ጋር ነውና ፅና አይዞህ፣ አትፍራ፣ አትደንግጥ።10

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ባረጋገጥነው ብርታት ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር አብረን እንዲህ እናውጃለን፣ “በክርስቶስ ወንጌል አልፈራም።”11 ከዚያም፣ በተመሳሳይ ብርታት የሐዋርያውን ጳውሎስ ምክር መከተል አለብን፣ “ በቃልና በኑሮ በፍቅም፣ በእምነትም፣ በንፅህናም፣ ለሚያምኑት ምሳሌ ሁን እንጂ።”12

ትልቅ የጦርነት ጥፋቶች ይመጣሉ እናም ይሄዳሉ፣ ነገር ግን ለሰዎች ነፍሳት ያለ ጦርነት ይቀጥላል። እግዚአብሄር ለእናንተ ፣ ለእኔ እና የትም ቦታ ላሉ የክህነት ተሸካሚዎች በግልፅ እንዳለው፣ “ስለዚህ፣ አሁን ሁሉም ሰው ኃላፊነቱን ይማር እናም በተቀባው የክህነት ክፍል ውስጥ በሙሉ ትጋት ይተግብር።”13 ከዚያም ሐዋርያው ጴጥሮስ እንዳለወጀም፣ በአላማ አንድነት እና ከላይ በተሰጠ ኃይል “ የንጉሥ ካህናት”14 እንሆናለን።15

ከጥንቱ ኢዮብ ጋር ዛሬ እዚህ ያለ እያንዳንዱ “እስትንፋሴ በእኔ ውስጥ ሳለ...... ፍፁምነቴን ከእኔ አላርቅም።”16 ለማለት ጠንካራ ፍላጎት እና ብርታት ይኑረን። ይህ ይሆን ዘንድ ትሁት ፀሎቴ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን ።