2010–2019 (እ.አ.አ)
“አትፍሩ፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ”
ሚያዝያ 2014


“አትፍሩ፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ”

በጌታ ታላቅ መታመን እና እምነትን ስናዳብር፣ ለመባረክ እና ለማዳን ያለውን ሀይል ልናገኝ እንችላለን።

ጥቂት ስሜቶች ወላጅ ከመሆን ጋር ካለው ስሜት ይነጻጸራሉ። ውድ ህጻን ቀጥታ ከሰማይ ከመቀበል በላይ ታፋጭ የለም። ከወንድሞቼ አንዱ በተለየ አሳዛኝ መንገድ ይህ ተሰምቶት ነበረው። የመጀመሪያ ወንድ ልጁ ያለጊዜው ነበር ተወለደው እና 1.3 ኪሎ ግራም ይመዝን ነበር። ሐንተር የመጀመሪያዎቹን ሁለት ወራት በታላቅ የሆስፒታል መንከባከቢያ ክፍል ነበር ያሳለፈው። ከጌታ ተስፋ እና እርዳታ ስንለምን ለመላው ቤተሰብ ጥልቅ የሆኑ ወራት ነበሩ።

ትንሹ ሐንተር በጣም ጥገኛ ነበር። ለመኖር የሚያስፈልገውን ጥንካሬ ለማግኘት ተታገለ። የአፍቃሪው አባቱ ጠንካራ እጅ ተጠቂውን ትንሽ ልጁን ለማበረታታት ወደ ልጁ ትንሽ እጅ ይደርሱ ነበር።

ለሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች እንደዚሁ ነው። ሙሉ በሙሉ መረዳት በማንችለው ፍቅር የሰማይ አባታችን ወደ እያንዳንዳችን ይደርሳል። በሁሉም ነገሮች ላይ ሀይል አለው እና እኛ እንድንማር ፍላጎት አለው፣ እንድናድግ እና ወደ እሱ እንድንመለስ ለመርዳት ይፈልጋል። ይሄ የአባታችንን አላማ ይገልጻል፤ “የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት ማምጣት።”1

በጌታ ታላቅ መታመን እና እምነትን ስናዳብር፣ ለመባረክ እና ለማዳን ያለውን ሀይል ልናገኝ እንችላለን።

በሁሉም ገልጾቹ መጽሀፈ ሞርሞን ይህን ጣፋጭ ጌታ ልጆቹን የሚያድንበት ሀይልን ያወራል። ኔፊ በመጽሀፉ መጀመሪያ ምእራፍ አስተዋውቆታል። በቁጥር 20 እናነባለን፣ “ነገር ግን እነሆ እኔ ኔፊ የጌታ ምህረትንና ርህራሄ በእምነተታቸው ምክንያት በተመረጡት ላይ ሁሉ መሆኑንና እንዲሁምሀይይል እና እራሳቸውን ለማዳን የሚያስችላቸው መሆኑን አሳያችኋለሁ።”2

ከብዙ አመታት በፊት በዚህ ቁጥር የተገለጹት እውነታዎች በታላቅ ግልጽነት ታይተውኝ ነበረ። ምን ያህል የሰማይ አባታችን በጣም ቅርብ እንደሆነ እና ምን ያህል እኛን ለመርዳት እንደሚፈልግ አወኩኝ።

አንድ ምሽት ሌሊቱ እየገፋ ሲሄድ፣ በኮረብታማ አከባቢ ከልጆቼ ጋር መኪና እነዳን ነበር። የጀርባ ቦርሳ አዝሎ በመንገዱ ዳርቻ የሚጓዝ አንድ ወጣት ልጅ ተመለከትኩ። ካለፍኩት በኋላ፣ መመለስ እና መርዳት እንዳለብኝ ለየት ያለ ስሜት ተሰማኝ። የማያውቀው ሰው በማታ ወደ እሱ መኪና ሲያቀርብ ይፈራል ብዬ፣ መንዳቴን ቀጠልኩ። ጠንከር ያለ ስሜት ከቃላት ጋር እንደገና መጣ “ ሄደሽ ልጁን እርጂው!”

ወደ እርሱ ነዳሁ እና ጠየኩት፣ “እርዳታ ያስፈልግሀል? መረዳት እንዳለብኝ ይሰማኛል።”

ወደ እኛ ዞረ እና በጉንጩ እንባ እየፈሰሰ እንዲህ አለ፣ “ትረዱኛላችሁ? አንድ ሰው እንዲረዳኝ እየጸለይኩ ነበር።”

የእርዳታ ጸሎቱ ወደ እኔ በመጣው ከሰማይ በተላከ መነሳሳት ተመለሰ። ይህም ከመንፈስ ግልፅ መመሪያ የመቀበል አጋጣሚ በልቤ ውስጥ አሁንም የሚገኘውን የማይረሳ አሻራ ተወ።

አሁን ከ25 አመታት በኋላ እና በታላቅ ምህረት ምክንያት፣ ልክ ከወራት በፊት ከዚያ ልጅ ጋር እንደገና ተገናኘን። ተሞክሮው የእኔ ብቻ ታሪክ እንዳልሆነ ተረዳሁ፣ የእርሱም ታሪክ ነው። ዴሪክ ናንስ የራሱ ቤተሰብ ያለው አባት ነው። እሱም ያንን ሞክሮ በፍጹም አልረሳውም። ሁለታችንም ልጆቻችንን እግዚአብሔር እንደሚጠብቀን ለማስተማር ተጠቅመንበታል። እግዚአብሔር ጸሎትን እንደሚሰማ እና እንደሚመልስ የእምነት መሰረት ለማግኘት ይረዳናል።እግዚአብሔር እንደሚያዳምጠን እና ለጸሎታችን መልስ እንደሚሰጥ የእምነት መሰረት ለመመስረት አስችሎናል።

ዴሪክ ከራሱ እይታ አንጻር ስለሞክሮው የበለጠ ገለጸለልኝ። በዚያ ምሽት፣ ዴሪክ ለዝግጅት ትምህርት ቤት ቆይቶ የመጨረሻው ባስ አምልጦት ነበር። በአስራዎቹ ውስት እንዳለ ወጣት፣ ቤት መድረስ አንደሚቻል በመተማመን መጓዝ ጀመረ።

ብቸኛውን መንገድ ሲጓዝ አንድ ሰአት ከግማሽ አለፈ። ከቤቱ ኡንም ብዙ እየራቀው ምንም ቤቶች ስለማይታዩ ፈርቶ ነበር። በተስፋ፣ በአሸዋ ኮረብታ ጀርባ ፣ ተንበረከከ እና የሰማይ አባትን እርዳታ ጠየቀ። ዴሪክ ወደ መንገዱ ከተመለሰ ከደቂቃዎች በኋላ፣ የጸለየለትን እርዳታ ለመስጠት መኪናውን አቆምኩኝ።

አሁን ከእነዚህ ብዙ አመታት በኋላ፣ ዴሪክ እንዲ ስታውሳል፣“ቀጭንና እና እሩቅ የማላይ ልጅ ብሆንም ጌታ ያስበኝ ነበር። ምንም አይነት ነገር በአለም ቢደረግ፣ ሁኔታዬን ያውቅ ነበር እና እርዳታ እስከመላክ ድረስ ወዶኛል። ከዚያ የተነጠለ መንገድ ዳርቻ በኋላም ጌታ ብዙ ጊዜ ጸሎቴን መልሷል። መልሶቹ ሁሌ እንደዚያ ፈጣን እና ግልጽ አይደሉም፣ ነገር ግን ስለእኔ ማወቁ በዚያ ብቸኛ ምሽት እንደነበረው ዛሬም የሚታ ነው። መቼም የህይወት የጨለማ ጥላ አለሜን ሲሸፍን፣ ወደ ቤት በደህንነት ለማድረስ ሁሌም እቅድ እንዳለው አውቃለሁ።”

ልክ ዴሪክ እንዳለው፣ ጸሎቶች ሁሉ በፍጥነት አይመለሱም። ነገር ግን በእውነት አባታችን ያውቀናል እና የልባችንን መማጸን ይሰማል። በየተራ በተአምር ጸሎትን ያሳካል።

እንደሚረዳን መተማመን እንችላለን፣ እኛ በምንፈልገው መንገድ ባይሆንም ግን እኛ ለማደግ በሚረዳን መንገድ መልኩ። ከእኛ መንገድ የእሱ መንገድ እነደሚሻል ለማመን መማር አለብን። ፍላጎታችንን ወደ እሱን ፍቃድ መቀየር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ እንደ እሱ ለመሆን እና የሚሰጠንን ሰላም ለማግኘት ግን ወሳኝ ነው።

ሊሰማን ይችላል፣ ልክ በሲ. ኤስ. ሊውስ እደተለጸው፣“ የምጸልው እራሴን መርዳት ስለማልችል ነው፣ ረጂ ስለሌለኝ ነው።በምራመድበት እና በምተኛበት የምጸልው አስፈላጊነቱ ሁሌም ከእኔ ስለሚፈስ ነው።.. እግዚአብሔርን አይቀይርም፣ እኔን ይቀይራል።”3

እምነታቸውን በጌታ ስላደረጉ እና በእርሱ የተረዱ እና የዳኑ ሰዎች የሚናገር ብዙ ቅዱስ መጽሀፍት መዝገብ አለ። ወጣቱን ዳዊት አስቡ፣ በጌታ በመመካት ከታላቁ ጎልያድ እጅ ሞት ያመለጠው። ኔፊን አስቡ፣ ታን በመማጸኑ ካሰሩት ገመዶች እንዴት እንዳወጣው። ወጣቱን ዮሴፍ ስሚዝን አስታውሱ፣ በጸሎት የጌታን እርዳታ የፈለገው። ከጨለማ ሀይል ወትቶ እና ተአምራዊ መልስ ተቀበሉ። አሁንም በእና ጊዜ፣ የእግዚአብሄር ሀይል እና ፍቅር በልጆቹ ህይወት ውስጥ ይታያል።

በቅርቡ በዝምባብዌ እና ቦትስዋና በእምነት በተሞሉ ቅዱሳን ህወት ውስጥ አይቼዋለሁ። በትንሷ ቺዋሪዞ ቅርንጫፍ የጾም እና የምስክርነት ወቅት፣ በህጻናት፣ ወጣቶች እና በጎልማሶችም ምስክርነት ትሁት ሆኜ እና ተነሳስቼ ነበር። ሁሉም በጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስ እምነትን በታላቅ አገላለጽ አካፈሉ። ውጣ ውረድ እና ከባድ ሁኔታዎች ቢከባቸውም፣ እምነታቸውን በእግዚአብሔር በማድረግ እንዳንዷን ቀን ይኖራሉ። በህይወታቸው የእግዚአብሔርን እጆች ያያሉ እናም በአብዛኛው ጊዜም “ለእግዚአብሔር በጣም አመስጋኝ ነኝ” በሚለው እምነታቸውን ይገልጻሉ።

ከጥቂት አመታት በፊት ይሄን ተመሳሳይ በጌታ መታመን አንድ ቤተሰብ ለአጥቢያችን አባላት ምሳሌ ሆኑ። አረን እና ቬኒታ ጋትሬል ከድንቅ ቤተሰብ ጋር ደስተና ህይወት እየኖሩ ነበር። አረን የተሳካ ስራ ነበረው፣ እና ከዚያ፣ በድነገት፣ አደገኛ የካንሰር በሽታ ያዘው። የህክምና ሂደቱ ጥሩ አልነበረም- የጥቂት ሳምንታት ህይወት ብቻ ነበረው። ለአንድ መጨረሻ ጊዜ ቤተሰቡ አንድ ላይ ለመሆን ፈለጉ። ሁሉም ልጆች ተሰበሰቡ፣ አንዳንዱ ከሩቅ ቦታ በመምጣት። አብሮ ለመሆን 48 ውድ ሰአታት ብቻ ነበር የቀራቸው። ቤተሰቡ በአጽኖት አስፈላጊውን ነገሮች ለማድረግ መረጡ፣ የቤተሰብ ፎቶ፣ የቤተሰብ እራት እና የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ አንድ ክፍለ ጊዜ መካፈል። ቬኒታ እንዲህ አለች “ከቤተመቅደስ በሮች ወጥተን ስንሄድ፣ በዚህ ህይወት አብረን የምንሆንበት የመጨረሻው ጊዜ ነበር።”

ከዚህ አለም ይበልጥ እንዳላቸው በመተማመን ሄዱ። በቅዱስ የቤተመቅደስ ቃልኪዳኖች ምክንያት፣ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ተስፋ አላቸው። እስከ ዘለአለም አብረው መሆን ይችላሉ።

ቀጣዮቹ ሁለት ወራት መቁጠር በማይቻሉ በረከቶች የተሞሉ ነበሩ። የአረን እና ቬኒታ እምነት እና በጌታ መመካት በቬኒታ ቃላት እንደታየው እያደገ ነበር፣“ተሸክሞኝ ነበር። በቀውስ ውስጥ ሰላም ሊሰማ እንደሚችል ተማርኩኝ። የመጨናነቅ ስሜት ሲሰማኝ፣ ወደ መኝታ ክፍሌ እሄዳለሁ፣ እንበረከካለሁ እና እጸልያለሁ። ከዚያ በኋላ በሰላም እሄዳለሁ። ጌታ እኛን እንደሚተብቀን አውቄ ነበር። በጌታ የምንተማመን ከሆነ፣ የትኛውንም የህይወት ውጣ ውረዶች ማሸነፍ እንደሚቻል ተምሬአለሁ።”

አንዷ ሴት ላጃቸው አክላም፣ “ወላጆቻችንን ተመለከትን እና ምሳሌያቸውንም አየን። እምነታቸውን እና እንዴት እነደያዙት አየን። ለዚህ መከራ በፍጹም አልጠይቅም ነበር፣ ነገር ግን በፍጹም ወደዚያ አልተወውም። በመንፈስ ቅዱስ ተከበን ነበር። ይህም ቀየረን።”

በእርግጥ፣ የአረን ሞት የጋትሬል ቤተሰብ ተስፋደረጉት ውጤት አልነበረም። ውድቀታቸው ግን የእምነት ውድቀት አልነበረም። የኢየሱስ ክርሰቶስ ወንጌል መደረግ ያለባቸው ነገሮች ዝርዝር አይደለም፣ በሌላ መልኩ፣ በልባችን መኖር ይችላል። ወንጌል “ክብደት ሳይሆን፣ ክንፍ ነው”4። ሊሸከመን ይችላል። የጋትሬስን ቤተሰብ ተሸክሟል። በማእበሉ መሀል ሰላም ተሰምቷቸዋል። እርስ በእርስ ተደጋግፈዋል እና ለገቧቸው እና ለጠበቋቸው የቤተመቅደስ ቃልኪዳኖች ጸንተዋል። በጌታ በመመካት ባላቸው ብቃት አድገዋል እና በእየሱስ ክርስቶስ እና በሀጢያት ክፍያው ባላቸው እምነት ጠንክረዋል። በጌታ የቃል በረከቶች ተስፋ አላቸው።

በደቀመዛሙርትነት መንገድ እራሳችንን የትም ብናገኝ፣ ምንም አይነት ፍራቻዎች እና ውጣውረዶች ቢኖሩን፣ እንደ ዴሪክ የአፍሪካ ቅዱሳን፣ የጋትሬል ቤተሰብ እና ሌሎች ብዙዎች- በፍላጎታችን የእግዚአብሔርን እጅ በእምነት ለማግኘት መምረጥ እንችላለን። በጸሎት እና በጌታ በመታመን ውጣውረዶችን መጋፈጥ እንችላለን። እና በሂደት ውስጥም ልክ እንደ እሱ እየመሰልን እንመጣለን።

ጌታ ለሁላችንም ተናገሯል፣ “ አትፍሩ፣.. እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ አትታበዩ፣ እኔ አምላካችሁ ነኝና፤ አጠነክራችኋለሁ፤ እረዳችኋለሁ፤…አዎ፣ በጽድቄ ቀኝ እጅ ከፍ አደርጋችኋለሁ።”5

እግዚአብሄር እንደሚያውቀን እና እንደሚረዳን እርግጡን ምስክርነቴን አካፍላችኋሁ። በተወዳጁ ልጁ ፣ኢየሱስ ክርስቶስ፣አማካኝነት አለምን ማሸነፍ እና ወደ ቤት በደህንነት የምንችል እንደሆነ እመሰክራሁ። በእርሱ ለመታመን እምነት የኑረን፣ ጸሎቴ ነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ሙሴ 1:39.

  2. 1 ኔፊ 1:20.

  3. Spoken by the character of C. S. Lewis as portrayed in William Nicholson, Shadowlands (1989), 103.

  4. Harry Emerson Fosdick, Twelve Tests of Character (1923), 88.

  5. ኢሳይያስ 41:10.