2010–2019 (እ.አ.አ)
በምንም አጋጣሚ ውስጥ አመስጋኝ
ሚያዝያ 2014


በምንም አጋጣሚ ውስጥ አመስጋኝ

እራሳችንን በምናገኝበት በማንኛውም ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ሆነን በአመስጋኝነት ለመሞላት ምክንያት የለንምን?

በአመታት ውስጥ፣ ሀዘናቸው የነፍሶቻቸው ጥልቆች ላይ የደረሰ ከሚመስሉ ከብዙ ሰዎች ጋር ለመገናኘት ቅዱስ የሆነ እድል ነበረኝ። በነዚህ ሰአት ውስጥ፣ ውድ ወንድሞቼንንና እህቶቼን አዳምጫለው እንዲሁም ከእነርሱ ጋር በሸክማቸው ላይ አብሬ አዝኛለው። ለእነርሱ ምን ማለት እንዳለብኝ አሰላስያለው፣ እናም በፈተናቸው ውስጥ እንዴት እንደምደግፋቸውና እንደማፅናናቸው ለማወቅ ትግል አድርጌያለው።

በተደጋጋሚ ሀዘናቸው የተከሰተው ለእነሱ እንደአላቂ በሚመስላቸው ነገር ነው። እንዳንዶቹ የሳሱለትን ግንኙነት መጨረሻ እያጋጠማቸው ነው፣ እንደ የሚወዱት ሰው ሞት ወይም ከቤተሰብ አባል ባይተዋረኝነትን። ሌሎቹ የተስፋ መጨረሻ እየተሰማቸው ነው-የመጋባት ተስፋ ወይም ልጆች የመውለድ ወይም ህመምን የማሸነፍ። ሌሎች ምናልባት የእምነታቸው መጨረሻ እያጋጠማቸው ነው፣ በአለም ውስጥ ያሉ ግራ የሚያጋቡና የሚያጋጩ ድምፆች አንዴ እውነት ነው ብለው ያወቁትን ነገሮች እንዲጠይቁ፣ እንዲሁም እንዲተዉ እያደረጋቸው ነው።

በቅርብ ወይም ከጊዜ በኋላ፣ የብቸኝነት ስሜት እንዲሰማን እየተወን፣ እንድንደክም እናም ካለ አላማ እንድንኖር እያደረገን፣ የአለማችን የልብስ ስፌት ሲተረተር ሁላችንም አጋጣሚ እንደሚኖረን አምናለው።

ለማንም ሰው ሊከሰት ይችላል። ማንም ሰው ማምለጥ አይችልም።

አመስጋኝ መሆን እንችላለን

የእያንዳንዱ ሰው ሁኔታ ልዩ ነው፣ የእያንዳንዱ የሕይወት ዝርዝሮች ልዩ ናቸው። ይሁን እንጂ፣ ወደ ሕይወቶቻችን የሚመጡትን መራራነት የሚወስድ የሆነ ነገር እንዳለ ተምሬያለው። ሕይወትን የበለጠ ጣፋጭ፣ የበለጠ አስደሳች፣ እንዲሁም ክብራዊ ለመድረግ መስራት የምንችለው አንድ ነገር አለ።

አመስጋኝ መሆን እንችላለን!

አንድ በሀዘን ሸክሙ የከበደ ሰው ለእግዚአብሔር ምስጋና መስጠት አለበት ሲባል ከአለም ጥበብ ጋር የተፃረረ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን የመራራ ጠርሙሳቸውን ወደ ጎን የሚተዉና በምትኩም የምስጋና ፅዋቸውን ወደ ላይ የሚያነሱ፣ የሚያፀዳ የፈውስ፣ የሰላምና የመረዳት መጠጥ ለማግኘት ይችላሉ ።

እንደ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት፣ “ጌታ አምላካችንን በሁሉም ነገር እንድናመሰግን፣”1 “ለጌታ በምስጋና አቅራቢነት እንድንዘምር፣”2 እና “ልባችን ለእግዚአብሔር ሙሉ አመስጋኝ እንዲሆን እንድንፈቅድ።” ታዘናል።3

ለምንድን ነው እግዚአብሔር አመስጋኞች እንድንሆን ያዘዘን?

ሁሉም ትዕዛዞቹ በረከቶችን ለእኛ እንዲገኙ ለማስቻል የተሰጡ ናቸው። ትዕዛዞች ነፃ ምርጫዎቻችንን ለመለማመድና በረከቶችን ለመቀበል የሚያስችሉ እድሎች ናቸው። የሚወደን የሰማይ አባታችን የምስጋና መንፈስን ማዳበር እውነተኛና ታላቅ ደስታን እንደሚያመጣልን ያውቃል።

ለነገሮች አመስጋኝ ሁኑ

ነገር ግን አንዳንዶች እንዲህ ሊሉ ይችላሉ፣ “አለሜ እየፈራረሰ ሳለ ስለምንድን ነው አመስጋኝ የምሆነው?”

ምናልባት አመስጋኞች የሆንበት ነገር ላይ ማተኮር የተሳሳተ አካሄድ ሊሆን ይችላል። የእኛ አመስጋኝነት መቁጠር ከምንችላቸው በረከቶች ጋር ብቻ የሚመጣጠን ከሆነ የአመስጋኝነትን መንፈስ ማዳበር ከባድ ነው። እውነት ነው በተደጋጋሚ “በረከቶቻችንን መቁጠር” አስፈላጊ ነው-- እና ይሄንን የሞከረ ሁሉ ብዙ እንዳሉ ያውቃል-- ነገር ግን ጌታ በፈተናዎች ሰአት ከሚተረፈረፍልን ሰአት በላይ ትንሽ አመስጋኞች እንድንሆን እንደሚጠብቀን አላምንም። በእርግጥ፣ በዙዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጣቀሻዎች ለነገሮች አመስጋኞች ስለመሆን አያወሩም ነገር ግን በምትኩ የአጠቃላይ መንፈስን ወይም የአመስጋኝነትን በሀሪ ሀሳብ ያቀርባሉ።

ሕይወት ወደ እኛ አቅጣጫ እየመጣ ሲመስል ለነገሮች አመስጋኝ መሆን ቀላል ነው። ነገር ግን የምንመኘው ነገር ከምንደርስበት ውጪ በሚመስልበት ሰአትስ?

አመስጋኝነትን እንደ አቋም፣ በእኛ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሚመሰረት እራሱን ችሎ የሚቆም የሕይወት መንገድ አድርገን እንደምናየው ልገምት? በሌላ አገላለፅ፣ “ለነገሮችአመስጋኞች” ከመሆን ፋንታ፣ ምንም ይሁኑ ምንም “ባለንበት ሁኔታዎች ውስጥ አመስጋኞች” መሆን ላይ እንድናተኩር አስተያየት እየሰጠው ነው።

የአንድ አስተናጋጅ እንድን ደንበኛ ምግቡን እንደወደደው ስለጠየቀችው ጥያቄ የቆየ ታሪክ አለ። እንግዳውም ሁሉም ነገር መልካም እንደነበር፣ ነገር ግን ብዙ ዳቦ ቢያቀርቡ አሪፍ ይሆነ እንደነበር መለሰ። በሚቀጥለው ቀን፣ ሰውዬው ሲመለስ፣ አስተናጋጇ የዳቦውን መጠን በእጥፍ አሳደገችው፣ ከሁለት ቁራጭ ይልቅ አራት እየሰጠችው፣ ነገር ግን አሁንም ሰውዬው ደስተኛ አልነበረም። በሚቀጥለው ቀን፣ አስተናጋጇ ያለምንም ውጤት ዳቦውን እንደገና በእጥፍ አሳደገችው።

በአራተኛው ቀን፣ አስተናጋጇ ሰውዬውን ለማስደሰት ቆርጣ ተነሳች ነበር። የ2.7m እርዝማኔ ያለው ዳቦ ወሰደች፣ ግማሽ በግማሽ ቆረጠችው፣ እናም በፈገግታ ለደንበኛው አቀረበችለት። አስተናጋጇ የሰውዬውን ተቃውሞ አልጠበቀችም ነበር።

ከምግቡ በኋላ፣ ሰውዬው ቀና አለና እንዲህ አለ፣ “እንደ ሁሌው መልካም ነው። ነገር ግን ሁለት ቁራጭ ዳቦ ብቻ ወደመስጠታችሁ እንደተመለሳችሁ አይቻለው።”

በሁኔታዎቻችን ውስጥ አመስጋኞች መሆን

ወንድሞችና እህቶች፣ ምርጫው የራሳችሁ ነው። ያጣናቸው መስለው በሚሰሙን በረከቶች ላይ በመመርኮዝ፣ ምስጋናችንን ለመወሰን መምረጥ እንችላለን። ወይንም እንደ ኔፊ ለመሆን መምረጥ እንችላለን፣ አመስጋኝ ልቡ ወላውሎ እንደማያውቀው ። ወንድሞቹ መርከቡ ላይ አስረውት በነበረ ጊዜ--ወደ ቃል-ኪዳኗ ምድር ሊወስዳቸው በገነባው መርከብ ላይ--ቁርጭምጭሚቶቹና እጆቹ ያሙት ነበር “እጅግ በጣም አብጠው ነበር” እናም ኃይለኛ መአበል ወደ ባሕሩ ጥልቅ ውስጥ ሊውጠው አስፈረራው። “ይሁን አንጂ” ኔፊ እንዲህ አለ፣ “ወደ አምላኬ ተመለከትኩኝ፣ እናም ቀኑን ሙሉ እርሱን አመሰገንኩኝ፤ እናም በመከራዬ የተነሳ በጌታ ላይ አላጉረመረምኩም።” 4

ሁሉም ነገሮች ያሉት የመሰለ ነገር ግን ከዛ በኋላ ሁሉንም እንዳጣቸው፣ እንደ እዮብ ለመሆን መምረጥ እንችላለን። ነገር ግን እዮብ እንዲህ ብሎ መለሰ፣ “ራቁቴን ከእናቴ ማህፀን ወጥቻለው፣ ራቁቴንም ወደዚህ እመለሳለው፤ እግዚአብሔር ሰጠ፣ እግዚአብሔርም ነሳ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።”5

በዝግተኛውና በሚያመው ወደ ታላቋ የሶልት ሌክ ጉዞአቸው ወቅት፣ እየዘመሩና እየደነሱ እንዲሁም በእግዚአብሔር መልካምነት ክብር እየሰጡ የአመስጋኝነትን መንፈስ ጠብቀው እንደቆዩት፣ እንደ ሞርሞን መስራቾች ለመሆን መምረጥ እንችላለን። 6ብዙዎቻችን ለማቋረጥ፣ ለመነጫነጭና ስለ ጉዞው አድካሚነት ለመጨነቅ አዘንብለን ይሆን ነበር።

በሊበርቲ ወህኒ በአስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ እስረኛ ሆኖ እያለ እነዚህን አነሳሽ ቃሎችን፤ “የምትወደዱ ውድ ወንድሞቼ፣ በኃይላችን ስር የሚኖሩትን ነገሮች በሙሉ በደስታ እንስራ፤ እናም በፍፁም ማረጋገጫ፣ የእግዚአብሄርን ድህንነት ለማየት፣ እና ክንዱ እንዲገለፅ ለማድረግ፣ ባለንበት እንቁም፣።”ብሎ እንደለጠፈው እንደ ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለመሆን መምረጥ እንችላለን።7

ምንም ይሁን ምንም፣ አመስጋኞች ለመሆን መምረጥ አለብን።

የዚህ አይነት አመስጋኝነት በዙሪያችን ምንም አይነት ነገር ቢፈጠር ይበልጠዋል። መከፋትን፣ አለመበረታታትን፣ እና ተስፋ መቁረጥን ይበልጣቸዋል። ልክ በአስደሳቹ የበጋ ሙቀት ውስጥ እንደሚያደርገው በክረምቱ የሚያምር የበረዷማ የመሬት አቀማማጥ ውስጥ ያብባል።

በሁኔታዎቻችን ውስጥ ለእግዚአብሔር አመስጋኞች በምንሆንበት ሰአት፣ በመከራችን ውስጥ የተረጋጋ ሰላምን እንለማመዳለን። በሀዘን ውስጥ፣ ልቦቻችንን በምስጋና ከፍ ማድረግም እንችላለን። በህመም ውስጥ፣ በክርስቶስ የሐጢያት ክፍያ መደሰት እንችላለን። በመራራ ሀዘን ቅዝቃዜ ውስጥ፣ የሰማይን እቅፍ ቀረቤትና ሙቀት መለማመድ እንችላለን።

አንዳንድ ጊዜ አመስጋኝ መሆን ችግሮቻችን ከተፈቱ በኋላ የምናደርገው ነገር ነው ብለን እናስባለን፣ ነገር ግን ያ እንዴት በጣም የሩቅ እይታ ችግር ነው።

በጭንቅ ጊዜ ውስጥ አመስጋኝ መሆን ማለት በሁኔታዎቻችን ውስጥ ደስተኞች ነን ማለት አይደለም። በእምነት አይኖች ከአሁኑ የቀን ውጣ ውረዶቻችን አሻግረን እናያለን ማለት ነው።

ይህ የነፍስ እንጂ የከንፈሮች ምስጋና አይደለም። ልብን የሚፈውስና አእምሮን የሚያሰፋ ምስጋና ነው።

ምስጋና እንደ የእምነት ተግባር

በሁኔታዎቻችን ውስጥ አመስጋኝ መሆን ማለት በእግዚአብሔር ያለን የእምነት ተገባር ነው። እግዚአብሔርን እንድናምንና ማየት በማንችላቸው ነገሮች ነገር ግን እውነት በሆኑት ነገሮች ተስፋ እንድናደርግ ይጠይቃል።8 አመስጋኝ በመሆን፣ “ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን፣ የአንተ እንጂ።” ያለውን የውድ አዳኛችንን ምሳሌ እንከተላለን።9

እውነተኛ ምስጋና የተስፋና የምስክርነት መገለጫ ነው። ሁልጊዜ የሕይወትን ፈተናዎች አለመረዳታችንን ነገር ግን አንድ ቀን እንደምንረዳ ማመናችንን ከመቀበል ጋር ይመጣል።

በማንኛውም ሁኔታዎች ውስጥ፣ የአመስጋኝነታችን ትርጉም በምናውቃቸው በብዙና በቅዱስ እውነታዎች ይመገባል፥ አባታችን ለልጆቹ ታላቁን የደስታ እቅድ እንደሰጠ፤ በልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የሀጢያት ክፍያ አማካኝነት ከምንወዳቸው ጋር ለዘላለም መኖር እንደምንችል፤ በመጨረሻውም ጊዜ፣ ሁላችንም የከበረ፣ ፍፁምና የማይሞት አካል፣ በህመም ወይም በአካለ ጎዶሎነት ያልተጫነ እንደሚኖረን፤ የሀዘንና የማጣት እንባዎቻችን በተትረፈረፈ ደስታና ተድላ እንደሚተኩ፣ “መልካም መስፈሪያ፣ የተጨቆነና የተነቀነቀ፣ የተትረፈረፈም።”10

እንደዚህ አይነቱ ምስክርነት መሆን አለበት የአዳኙን ሐዋርያቶች ከፈሪ፣ ተጠራጣሪ ሰዎች ወደ የማይፈሩ፣ የጌታቸው ደስተኛ ተወካዮች የቀየራቸው። ከስቅለቱ በኋላ ባሉት ሰአታቶች ውስጥ፣ በተስፋ መቁረጥና በሀዘን ተውጠው ነበር፣ ስለተፈጠረው ነገር መረዳት በለመቻል። ነገር ግን አንድ ክስተት ሁሉንም ቀየረው። ጌታቸው ተገለፀላቸውና፣ “እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ።” አላቸው። 11

ሐዋርቶቹ ከሞት የተነሳውን ክርስቶስ ባዩት ጊዜ--የሚወዱትን የአዳኛቸውን ግርማዊ ትንሳኤ ባዩ ጊዜ--የተለዩ ሰዎች ሆኑ። ተልዕኳቸውን ከሟሟላት የሚያግዳቸው ነገር ምንም የለም። በምስክርነታቸው ምክንያት ወደ እነርሱ የሚመጣውን ስቃይ፣ ውርደትና እንዲሁም ሞት በድፍረትና በቆራጥነት ተቀበሉ።12 ጌታቸውን ከማምለክና ከማገልገል እራሳቸውን አልገደቡም ነበር። በሁሉም ቦታ የህዝቦችን ሕይወት ቀየሩ። አለምን ቀየሩ።

ተመሳሳይ የሆነ መለወጥን ለመለማመድ፣ ሐዋርያቶቹ እንዳዩት፣ አዳኙን ማየት አያስፈልጋችሁም። በመንፍስ ቅዱስ እንደተመሰከረላችሁ፣ በክርስቶስ ላይ ያላችሁ ምስክርነት፣ በሟች ሕይወት ውስጥ የሚስከፉ መጨረሻነቶችን አሳልፋችሁ እንድታዩና የአለም አዳኝ ያዘጋጀውን ብሩህ ተስፋ እንድታዩ ይረዳችኋል።

ለመጨረሻነቶች አይደለም የተፈጠርነው

ስለ ዘላለም ዕጣፋንታችን በምናውቀው ብርሀን ውስጥ፣ የሕይወት መራራ መጨረሻነቶች በሚያጋጥሙን ጊዜ፣ የማንቀበላቸው መምሰላቸው ይገርማልን? በውስጣችን መጨረሻዎችን የሚቃወም የሆነ ነገር ያለ ይመስላል።

ይህ ለምን ሆነ? ምክንያቱም በዘላለማዊ ነገሮች ስለተሰራን ነው። እኛ ዘላለማዊ ፍጡሮች፣ ስሙ መጨረሻ የሌለው13 እና ዘላለማዊ በረከቶችን ካለስፍር ቁጥር ቃል የገባ የኃያሉ እግዚአብሔር ልጆች ነን። መጨረሻነቶች የእኛ ዕጣፋንታ አይደለም።

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የበለጠ ስንማር፣ በዚህ ሟች ሕይወት ውስጥ ያሉ መጨረሻነቶች በፍፁም መጨረሻነቶቸ እንዳልሆኑ የበለጠ እየተገነዘብን እንመጣለን። እንቅፋቶች ብቻ ናቸው--አማኙን ከሚጠብቀው ዘላለማዊ ደስታ ጋር ሲወዳደሩ አንድ ቀን ትንሽ የሚመስሉ ጊዜያዊ ማቆሚያዎች ናቸው።

በዕቅዱ ውስጥ ዘላለማዊ በረከቶች እንጂ ምንም እውነተኛ መጨረሻነቶች ስለሌሉ ለሰማይ አባቴ እንዴት አመስጋኝ ነኝ።

አመስጋኞች የሚሆኑት ሁሉ ክብራማ ይደረጋሉ

ወንድሞችና እህቶች፣ እራሳችንን በምናገኝበት በማንኛውም ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ሆነን በአመስጋኝነት ለመሞላት ምክንያት የለንምን?

ልባችንን “ለእግዚአብሔር በምስጋና እንዲሞላ”14 ለመፍቀድ ሌላ ታላቅ ምክንያት ያስፈልገናልን?14

“ለመደሰት ታላቅ ምክንያት አይኖረንምን?”15

የእግዚአብሄርን ስራ በድንቁ የሕይወት ውስብስብ ውስጥ ከተገነዘብን ምነኛ ተባርከናል። በሰማይ ላለው አባታችን የምንሰጠው ምስጋና እይታችንን ያሰፋዋል እንዲሁም ራዕያችንን ያጠራዋል። ትህትናን ይጭራል እንዲሁም የጓደኞቻችንን እና የሁሉንም የእግዚአብሔር ፍጡር ስሜት መረዳትን ያሳድጋል። አመስጋኝነት ለሁሉም ክርስቶሳዊ ባህሪያት ማብላያ ነው! አመስጋኝ ልብ የሁሉም ፀጎች ወላጅ ነው። 16

ጌታ ቃሎቹን ሰቶናል “ሁሉንም ነገሮች በአመስጋኝነት [የሚቀበሉ] ሁሉ ክብራማ ይደረገሉ፤ እናም የዚህ ምድር ነገሮች ይጨመር[ላቸዋል]።”17

“በየቀኑ ምስጋና በመስጠት እንኑር”18--በተለይ የሟች ሕይወት አካል የሆኑ በማይገለፁ መጨረሻነቶች ወቅት። ነፍሶቻችን ወደ መሐሪው የሰማይ አባታችን በአመስጋኝነት እንዲሰፉ እንፍቀድ። በሰማይ ላለው አባታችንና ለተወደደው ልጁ ምስጋናችንን ለማሳየት ሁሌና በቋሚነት ድምፆቻችንን ከፍ እናድርግ እንዲሁም በቃልና በተግባር እናሳይ። ለዚህ እፀልያለው እንዲሁም ምስክርነቴንና በረከቴን እተውላችኋለው፣ በኢየሱስ ክርሰቶስ ስም፣ አሜን።