2010–2019 (እ.አ.አ)
ጥበብ ከጎደላችሁ
ሚያዝያ 2014


ጥበብ ከጎደላችሁ

በቅዱሳት መፅሐፍት ውስጥ እንደተገለፀው እውነትን ለሚሹ እግዚያብሔር እውነትን ይገልፃልና።

ባለፈው፣ የአስር ዓመት ልጄ ከኢንተርኔት ላይ ስለ ሰው አአምሮ እያጠና ነበር። አንድ ቀን የቀዶ ጥገና ሀኪም መሆን ይፈልጋል። ከኔ የበለጠ ጎበዝ መሆኑን ለማወቅ ቀላል ነው።

ኢንተርኔትን እንወዳለን። በቤታችን ውስጥ በማህበራዊ ድህረ ገፅ፣ በኢሜል አና በሌላ መንገዶች ከግዋደኞቻችን እና ከቤተሰባችን ጋር እንገናኛለን’ ልጆቼ አብዛኛውን የትምህርት ቤት ስራቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት ይፈፅማሉ’

ጥያቄው ምንም ቢሆንም፣ ተጨማሪ መረጃ ከፈለግን፣ ከኢንተርኔት ንፈልገዋለን’ በሰከንድ ውስጥ ብዙ ነገሮችን አናገኛለን’ ይህ አስደናቂ ነው።

ኢንተርኔት ብዙ አድሎችን ለመማር ያዘጋጃል’ ቢሆንም& ሰይጣን አንድንሰቃይ አና የነገሮችን ትክክለኛ አላማ ቅርፅ መለወጥ ይፈልጋል’ ይህን ታላቅ መሳሪያ ጥርጣሬን አና ፍራቻን ለማስተዋወቅ ይጠቀምበታል’ አምነት አና ተስፋን ያጠፋል’

በኢንተርኔት ላይ ብዙ የተዘጋጁ ነገሮች እያሉ፣ አንድ ሰው ጥረቶቹን በጥንቃቄ የት መተግበር እንዳለበት መገንዘብ አለበት። ሰይጣን በስራ ወጥሮ ሊይዘን፣ ትኩረታችንን ሊስብ አናም ልበክለን ይችላል፤

አንድ ሰው በቆሻሻ ውስጥ ያለ አላማ መንቀሳቀስ የለበትም።

በቅዱስ መፅሐፋት ውስጥ የተዘጋጀውን ይህን መመሪያ አዳምጡ : “የክርስቶስ መንፈስ ለሁሉም ተሰጧል፣ ጥሩውን ከመጥፎው ይለይ ዘንድ፣ ስለዚህ፣ መፍረድን መንገድ አሳያኋለሁ፤ መልካሙን እንድናደርግ ሚጋብዝ ሁሉ፣ በክርስቶስ እንድናምን የሚገፋፋ፣ በክርስቶስ ሀይል እና ስጦታ የተሰጠ ነው፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደሆነ ታውቃላችሁ።”1

በትክክለኛው ትርጉም፣ ዮሴፍ ስሚዝ በወጣትነቱ ያጋጠመውን ተመሳሳይ አጣብቂኝ ያጋጥመናል። አኛም ራሳችንን ጥበብ ጎሎን እናገኘዋለን።

በእግዝያብሔር መንግስት ውስጥ እውነትን ፍለጋ ይደነቃል፣ ይበረታታል እናም በጭራሽ አይጨቆንም አና አይስፈራራም። የቤተክርስቲያን አባሎች እውቀትን እንዲሹ በራሱ በጌታ አጠንክሮ ተመክረዋል።2 አንዲህም አለ፣ “በትጋት ፈልጉ… ፤ ከምርጥ መፅሐፍቶች ውስጥ የጥበብ ቃልን ፈልጉ; ትምህርትን ፈልጉ፣ በማጥናት እና እንዲሁም በመፀለይም።”3 ነገር ግን ይበልጥ ቀጥታ በሆነ ዓለም ውስጥ ማህበረሰቡ የእግዝያብሔር የሆነውን ነገር እያጠቃ እውነቱን አንዴት መገንዘብ እንችላለን?

ቅዱሳን መፅሀፎች አንዴት አንደሆነ ያስተምሩናል:

መጀመሪያ፣ ፍሬዎቹን በማየት አውነትን ማወቅ አንችላለን።

በታላቁ የተራራ ትምህርት ጊዜ& ጌታ እንዲህ አለ፣

እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል÷ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል …

“ስለዚህም በፍሬያቸው ታውኳቸዋላችሁ።”4

ነቢዩ ሞርሞን ይህንን ተመሳሳይ መመሪያ እንዲህ ሲል አስተማረ፣ “በስራዎቻቸው ታውኳቸዋላችሁ; ስራቸው መልካም ከሆነ፣ እነሱም መልካም ናቸው”5

የቤተክርስቲያኑን ስራዎች አና ፍሬዎች አንድያጠኑ ሁሉንም እንጋብዛለን።

በእውነቱ ላይ ፍላጎት ያላቸው ቤተክርስቲያኗ እና አባሎችዋ ባሉበት ማህበረሰብ ውስጥ የሚፈጥሩትን ልዩነት መገንዘብ ይችላሉ። የሱን ትምህርት በሚከተሉት ላይ በሕይወታቸው ውስጥ ያለውን መሻሻል ይመለከታሉ። ፍሬውን የሚመረምሩ የቤተክርስቲያኗ ፍሬዎች ታፋጭና ደስ የሚል አንደሆነ ይረዳሉ።

ሁለትኛ፣ የሱን ቃል በምቅመስ በራሳችን አውነቱን ማግኘት እንችላለን።

ነቢዩ አልማ አስተማረ:

እንግዲህ፣ ቃሉን ከዘር ጋር እናነፃፅራለን’ እንግዲህ፣ ስፍራን እስከምትሰጡት ዘሩ በልባችሁ ከበቀለ፣ እነሆ አውነተኛ ዘር ከሆነ ወይም መልካም ዘር ከሆነ ባለማመናችሁ የጌታን መንፈስ በመቃወም የማትጥሉት ከሆነ& አነሆ እርሱም በልባችሁ ውስጥ ማደግ ይጀምራል። አናም ይህ እድገት በልባችሁ ውስጥ ሲሰማ በውስጣችሁ እንዲህ ማለት ትጀምራላችሁ:--- ይህ መልካም ዘር ነው፣ ወይንም ቃሉ መልካም መሆን አለበት& ግንዛበዬን ያበራልኝ ጀምሯል፣ አዎን፣ ለእኔ አስደሳች መሆን ጀምሯል። …

አናም አሁን......... ይሄ እምነታችሁን አያጠነክርምን? አዎን& አምነታችሁን ያጠነክራል። …

ማንኛውም ዘር አራሱን መሰል ዘር ይሰጣል።6

በጌታ ነብይ የተሰጠ አንዴት አስገራሚ ግብዣ ነው ! ይህም ከሳይንስ ሙከራ ጋር ሊወዳደር ይችላል’ መመሪያውን የምንከተል ከሆነ ቃሉን አንድንቀምሰው ተጋብዘናል& መለኪያ መሳሪያ ተሰቶናል& የቅምሻውን ውጤት ተነግሮናል።

ፍሬዎቹን በመመልከት እውነትን ማወቅ አንደምንችል ቅዱሳት መፅሐፍቶች ያስተምሩናል; ወይም፣ እሱን በግላችን በመሞከር& ለቃሉ በልቦቻችን ቦታ በመስጠት፣ ልክ አንዴ ዘር በመኮትኮት፤

እውነቱን ለማወቅ ገና ሶስተኛ መንገድ አለ፣ አና አሱም በግል ራዕይን መቀበል ነው።

ትምህርትና ቃልኪዳን በክፍል 8 ላይ ራዕይ እውቀት አንደሆነ ያስተምረናል-----“ የማንኛውምን ነገር እውቀት[ እኛ ] በእምነት ከጠየቅን& በታማኝ ልብ& አናም [ እኛ ] አንደምንቀበል በማመን።”7

አናም ጌታ አንዴት ራዕይ አንደምንቀበል ይነግረናል። አንዲ አለ “አናም በእናንተ ላይ በሚመጣውና በሚያድረው በመንፈስ ቅዱስ፣ በአእምሮአችሁ አና በልባችሁ ነግራኋችለሁ።” 8

አንግዲህ፣ ራዕይ የምንቀበለው በንፁህ ልብ& እናም አንደምንቀበል በማመን በእምነት ስንጠይቅ አንደሆነ ተምረናል።

ጌታ ሲያስተነክቀን ግልፅ አድርጎልናል፣ “ያለ እምነት ምንም ማድረግ አንደማችሉ አስታውሱ ስለዚህ በእምነት ጠይቁ”9 እምነት ስራን ይጠይቃል…ስራውም በአእምሮ ውስጥ ማሰላሰል ከዚያም በአእምሯችንውስጥ ያሰላሰልነውንነገር ትክክል አንደሆነጌታን መጠየቅ።

ጌታ እንዲህ አለ፤

“ትክክል ከሆነበልባችሁ ውስጥ የነበልባል ስሜትን እፈጥራለሁ; ስለዚህም ትክክል አንደሆነ ይሰማችኋል።

ትክክል ካልሆነ ግን እንደዚህ አይነት ስሜቶች አይኖራችሁም፣ ነገር ግን ትክክል ያልሆነውን ነገር እንድትረሱ የሚያረጋችሁ እራሱን የሳተ ሃሳብ ይኖራችኋል።10

እምነት ያለ ስራ ከንቱ ነው። 11 ስለዚህ “ምንም ሳትተራጠሩ በእምነት ጠይቁ።”12

ከእኛ እምነት ያልሆነ፣ ግዋደኛ አለኝ፣ መንፈሳዊ እንዳልሆነ ገለፀልኝ። ቅዱሳን መፅሃፍትን አያጠናም አናም አይፀልይም ምክንያቱም የእግዚያብሔርን ቃል መረዳት አልችልም ይላል& እግዚያብሔር አንዳለም እርግጠኛ አይደለም። ይህ ባህርይ የሚያስረዳው የእሱ መንፈሳዊ አለሞሆን አናም ወደ ተቃራኒ ራዕይ እንደሚያመራ አልማ እብራርቷል። እንዲህም አለ፣ “ አናም ልቡን ለሚያጠጥር ለ አርሱ ከቃሉ ትንሹ ክፍል ይሰጠዋል”አ ልማ ሲቀጥል

እናም ልቡንም ለማያጠጥር “ለእሱ ሁሉንም በሙላት የእግዚያብሔርን ሚስጥር እስከሚያውቅ ድረስ ከቃሉ ትልቅ ክፍል ይሰጠዋል።” 13

አልማ አና የሞዛያ ልጆች እምነት ስራ ያስፈልገዋል ለሚለው ፅንሰ ሃሳብ ምሳሌዎች ናቸው’ በመፀሐፈ ሞርሞን አንድምናነበው፤

“የእግዚያብሔርን ቃል ያውቁ ዘንድ ቅዱሳት መፅሃፍትን በትጋት የሚያጠኑ እና በቀላሉ የሚረዱ ነበሩ።

“ነገር ግን ይህ ብቻ አይደለም አራሳቸውን በፀሎት አና በፆም አተጉ፣ ስለዚህ የትንቢት መንፈስ፣ እናም የራእይ መንፈስ ነበራቸው”።14

በዚህ ሂደት ውስጥ በታማኝ ልብ መጠየቅ እኩል ጠቀሜታ አለው። ከልባችን እውነትን የምንሻ ከሆነ፣ ለማግኘት በሃይላችን ሁሉ እናደርጋለን፣ ይህም ቅዱሳት መፅሃፍትን ማንበብ፣ ቤተክርስቲያን መሄድ ፣ የእግዚያብሔርን ትእዛዛት ለመጠበቅ የተቻለንን ማድረግ ሊያጠቃልል ይችላል። ይህ ደሞ ስናገኘው የእግዚያብሔርን ፍቃድ ለማድረግ ፍቃደኞች ሆንን ማለት ነው።

ጆሴፍ ስሚዝ ታማኝ ልብ ምን ማለት አንደሆነ ጥበብን እየፈለገበነበረበት ጊዜ የተገበራቸው ተግባሮች ፍፁም የሆኑ ምሳሌዎች ናችው’ አሱ አንዳለው ከነበሩት የተለያዩ እምነቶች ውስጥ የትኛው ትክክል አንደነበር ማወቅ ፈለገ፤” [ እሱ ] የትኛውን ለመቀላቀል ያውቅ ዘንድ” 15ከመፀለዩ በፊትም፣ በሚቀበለው መልስ ላይ ተግባሩን ለማዋል ዝግጁ ነበር።

በእምነት እና በታማኝ ልብ መጠየቅ አለብን። ነገር ግን ይህ በቂ አይደለም: ራእይ እንደምንቀበል ራሱ ማመን አለብን። በጌታ እምነታችንን ልንጥል አና በገባልን ቃል ኪዳን ተስፋ ሊኖረን ይገባል’ የተፃፈውን አስታውሱ “ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን ኤግዚያብሔርን ይለምን÷ ለእርሱም ይሰጠዋል “ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፣ ለእርሱም ይሰጠዋል።”16 ምን አይነት አስደናቂ ቃል ኪዳን ነው!

ከእነኚህ መንገዶች በየትኛውም መንገድ፣ ነገር ግን በተለይ ከእግዚያብሔር በሆነ በግል ራእይ አማካኝነት፣ ሁላችሁም እውነትን እንድትሹ እጋብዛኋችለሁ። በቅዱሳት መፅሐፍት ውስጥ እንደተገለፀው እውነትን ለሚሹ እግዚያብሔር እውነትን ይገልፃልና። ኢንተርኔት ላይ ብቻ ከመፈለግ የበለጠ ጥረት ይጠይቃል& ነገር ግን ዋጋ አለው።

ይህ ትክክለኛ የኢየሱስ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ምስክርነቴን አካፍላለሁ። በማህበረሰቡ አና በብዙ ሺህ ህይወቶች ውስጥ ፍሬዎቹን አይቻለሁ። ይህም የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ: በመሆኑም እውነት እንደሆነ አውቃለሁ። ለብዙ አመታት ቃሉን በሕይወቴ ውስጥ ሞክሬዋለሁ እናም በነፍሴ ላይ ውጤቶቹ ተሰምቶኛል፣ በመሆኑም እውነት እንደሆነ አውቃለሁ። ነገር ግን የተቀመኝ፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በራእይ ሙሉ እውነታውን ተምሬያለሁ; በመሆኑም እውነት እንደሆነ አውቃለሁ። ሁላችሁንም ተመሳሳይ ነገር እንድታደርጉ እጋብዛችኋለሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።