2010–2019 (እ.አ.አ)
ቃል ኪዳኖችን ማክበር ይጠብቀናል፣ ያዘጋጀናል፣ እናም ሀይል ይሰጠናል
ሚያዝያ 2014


ቃል ኪዳኖችን ማክበር ይጠብቀናል፣ ያዘጋጀናል፣ እናም ሀይል ይሰጠናል

የስጋዊ ጉዞን ወደ እርሱ የምንጓዝ ቃል ኪዳን የምንሰራ የሁሉም እድሜ ሴቶች ነን።

በቅርብ ጊዜ ሜክሲኮን ስጎበኝ፣ በዚህ ምሽት የሚሰማንን እህትነት ለማየች ችዬ ነበር። የእሁድ ጠዋት የመጀመሪያ ክፍልን ጨርሰን ነበር፣ እናም ልጆቹ፣ አስተማሪዎቹ፣ እና እኔ ብዙ ሰዎች በሚገኙበት ኮሪደር ውስጥ ገብተን ነበር። በዚያም ጊዜ የወጣት ሴቶች ክፍል በር ተከፈተ፣ እናም ወጣት ሴቶችን እና መሪዎቻቸውን አየሁ። እነርሱን ለማቀፍ ሄድን። ልጆቹ ቀሚሴን ይዘው እና ሴቶቹ በቅርቤ ሆነው፣ ስሜቴን በዚያው ጊዜ ለመግለጽ ፈልጌ ነበር።

ስፓኒሽ ለመናገር አልችልም ነበር፣ ስለዚህ የእንግሊዘኛ ቃላት ብቻ በአዕምሮዬ መጡ። ፊታቸውን ተመልክቼ እንዲህ አልኩኝ፣ “የሚወደን እና የምንወደው የሰማይ አባት ሴቶች ልጆች ነን።” ሁሉም በስፓኒሽ ከእኔ ጋር ይህን ማለት ቀጠሉ። “በሁሉም ጊዜ እና በሁሉም ነገሮች፣ እናም በሁሉም ቦታዎች እንደ እግዚአብሔር ምስክሮችእንቆማለን” ብለው አብረው ይህን የወጣት ሴቶችን ጭብጥ በልዕክት የሚሉ ብዙ ሰዎች በኮሪደር ውስጥ ነበሩ።

በዚህ ምሽት የእግዚአብሔርን መንግስት ለመደገፍ እና ለመከላከል ፍላጎት እንዳለን ደቀ መዛሙርት በአለም አቀፍ ተሰብስበናል። የሰማይ አባታችን ሴቶች ልጆች ነን። የስጋዊ ጉዞን ወደ እርሱ የምንጓዝ ቃል ኪዳን የምንሰራ የሁሉም እድሜ ሴቶች ነን። ቃል ኪዳኖችን ማክበር ይጠብቀናል፣ ያዘጋጀናል፣ እናም ሀይል ይሰጠናል።

በዚህ ምሽት የመጀምሪያ ክፍል እድሜ ያላቸው ሴት ልጆች በመካከላችን ይገኛሉ። አንዳንዳችሁ በጥምቀት ስርዓት ወደ ዘለአለም ህይወት የሚመራውን መንገድ ላይ የመጀመሪያውን እርምጃ በቅርብ አድርጋችኋል።

በአካባቢያችሁ ተመልከቱ። ወደፊት ያለውን መንገድ ሊያሳዩአችሁ የተዘጋጁ ቃል ኪዳን የገቡ ሴቶችን ስትመለከቱ ወደፊቱ ብርሀን ያለው ነው።

እናንተ በጉባኤ አዳራሽ ውስጥ፣ በቤታችሁ፣ ወይም በአለም ውስጥ በመሰብሰቢያ ቤቶች ውስጥ የምትኙ የ8፣ 9፣ 10 ወይም 11 አመት ያላችሁ ከሆናችሁ፣ ለመነሳት ትችላላችሁ? ለአጠቃላይ ሴቶች ስብሰባ እንኳን ደህና መጣችሁ። እባካችሁ ተነሱ፤ በዚህ ምሽት እንድትሳተፉ እንድንጋብዛችሁ እንፈልጋለን። የመጀመሪያ ክፍል መዝሙርን አንጎራጎራለሁ። የዚህን መዝሙር ማንነት ስታውቁ፣ ከእኔ ጋር አብራችሁ ለመዘመር ጀምሩ። አሁን፣ ሁላችንም እንድንሰማችሁ ዘንድ በከፍተኛ ድምጽ ዘምሩ።

በፍቅሩ ብርሀን ለመራመድ አስተምረኝ፤

ወደ ላይ ላለው አባቴ ለመጸለይ አስተምረኝ፤

ትክክል የሆኑትን ነገሮች እንዳውቅ አስተምረኝ፤

አስተምረኝ፣ በብርሀርን እንድራመድ አስተምረኝ፤

ሴቶች፣ አስራ ሁለት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው ሁለተኛውን የመዝሙር አንቀጽ ሲዘምሩ በመቆም ቅሩ።

ኑ ትንሽ ልጆች አብረን እንማራለን

ስለ ትእዛዛቱ፣ እንድንመለስ ዘንድ

ወደ እርሱ ፊት፣ በእይታው ለመኖር

ሁልጊዜም፣ ሁልጊዜም በብርሀን ለመራመድ።1

ያም አስደናቂ ነበር። አሁን ለመቀመጥ ትችላላችሁ። አመሰግናለሁ።

ሁሉም እድሜ እንዳላቸው ሴቶች፣ በብርሀኑ እንራመዳለን። ጉዞአችን የግል ነው እናም በአዳኝ ፍቅር በደንብ የበራ ነው።

የዘለአለም ህይወትን ደጅ በጥምቀት ስርዓት እና ቃል ኪዳን በኩል እንገባለን፣ እና ከዚያም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እንቀበላለን። ሽማግሌ ሮበርት ዲ ሄልስ እንደጠየቁን፣ “ስንጠመቅ ለዘለአለም እንደምንቀየር ይገባናል እናም ልጆቻችን ገብቷቸዋልን።”

ቀጥለውም እንዲህ ገለጹ “የጥምቀት ቃል ኪዳናችንን እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታችንን ስንረዳዋቸው፣ ህይወታችንን ይቀይራሉ እናም ለእግዚአብሔር መንግስት ያለንን ሙሉ ታማኝነት ይመሰርታሉ። ፈተናዎች ሲመጡብን፣ ካዳመጥን መንፈስ ቅዱስ አዳኛችንን እና የእግዚአብሔር ትእዛዛትን ለማስታወስ ቃል እንደገባን እንድናስታውስ ያደርገናል።”2

የቅዱስ ቁርባን ምልክትን በየሳምንቱ ስንቀበል፣ የጥምቀት ቃል ኪዳናችንን እናሳድሳለን። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ በድናር እንዳሉት፣ “በጥምቀት ውሀዎች ውስጥ ስንቆም፣ ወደ ቤተመቅደስ እንመለከታለን።ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል፣ ወደ ቤተመቅደስ እንመለከታለን። በቤተመቅደስ ቅዱስ ስርዓቶች ለመሳተፍ ስንዘጋጅ አዳኝን ሁልጊዜ ለማስታወስ እና ትእዛዛቱን ለማክበር ቃል እንገባለን።”3

የቤተመቅደስ ስርዓቶች በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ወደሚገኙ ታላቅ በረከቶች ይመራል። በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ከፍተኛነትን ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑት እነዚያ ስርዓቶች ናቸው። ቃል ኪዳኖቻችንን ለመጠበቅ ስንጥር፣ የቤተመቅደስ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች ህያው ሲሆኑ፣ ብቁ እና ፍጹም ያለመሆን ስሜታችን ለመጥፋት ይጀምራሉ። ሁሉም ያን የዘለአለም ህይወት መንገድ ለመጓዝ ይችላሉ።

በአለም ውስጥ በተገናኘኋቸው፣ በመንገዱ ላይ በፍጹም የተተከሉት በትንሽ ሴቶች፣ በወጣት ሴቶች፣ እና በጎልማሳ ሴቶች ጥንካሬ ተገርሜአለሁ። የቃል ኪዳን የሆኑ የትንሽ ልጆች እና ሴቶችን ምሳሌ ከእናንተ ጋር ልካፈል።

በቦይነስ አይረስ፣ አርጀንቲና ቤተሰቧን ስጎበኝ ሉአና 11 አመቷ ነበር። በልጅነቷ በደረሰባት አደጋ ምክንያት ሉአና መናገር አትችልም ነበር። ለብዙ አመታት አልተናገረችም ነበር። ስንነጋገርም በዝምታ ትቀመጥ ነበር። ትንሽ ስታሾከሹክ ለመስማት ተስፋ ነበረኝ። በልቧ ያለውን እኔ እንዳውቅ ዘንድ ቃላት አስፈላጊ እንዳልሆኑ አይነት በትኩረት ተመለከተችኝ። ከጸሎት በኋላ፣ ለመሄድ ተነሳን፣ እናም ሉአና ስዕል ሰጠችኝ። ኢየሱስ ክርስቶስን በገትሰመኔ የአትክልት ስፍራ ውስጥ የሚያሳይ ሰእል ስላ ነበር።ምስክሯን በግልጽ አወቅሁኝ። በጥምቀቷ በሁሉም ጊዜ እና በሁሉም ነገሮች፣ እናም በሁሉም ቦታዎች እንደ እግዚአብሔር ምስክር”4 ለመሆን ሉአና ቃል ኪዳን ገብታ ነበር። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያን መረዳቷን በስዕሏ መስክራለች። በኃጢያት ክፍያ በሚያጠናችር እና በሚያስችል ሀይል በኩል ለመፈወስ እንደምትችል አውቃለችን? ከአኢያ ቀን ጀምሮ ለሶስት አመታት፣ ሉአና ለመናገር በምታደርገው ጥረት አድጋለች። አሁን ከጓደኞቿ ጋር በወጣት ሴቶች ቡድን ትሳተፋለች።በጥምቀት የገባችውን ቃል ኪዳን ታማኝ በመሆን፣ ስለአዳኝ ያላትን ምስክርነት በመካፈል ትቀጥላለች።

በአለው ውስጥ በሙሉ ወጣቶች ወደ ቤተመቅደስ ይሳባሉ። በሊማ፣ ፔሩ ውስጥ በቤተመቅደስ መግቢያ ላይ አንድ አባትን እና ሶስት ሴት ልጆቹን አገኘሁ። በፊታቸው ብርሀን ይታይ ነበር። ሁለቱ ሴቶች ልጆች አካለ ስንኩል ነበሩ እና በጋሪ ላይ ይቀመጡ ነበር። ሶስተኛዋ ሴት ልጅ በቤት ሁለት ተጨማሪ እህቶች በቤት እንዳላት ገለጸች። እነዚህ ሁለቱም ጋሪ የሚጠቀሙ ነበሩ። ወደቤተመቅደስ ለመጓዝ 14 አመት የሚፈጀውን ጉዞ ለመጓዝ አልቻሉም ነበር። ቤተመቅደስ ለዚህ አባት እና አራት ሴት ልጆቹ በጣም ታላቅ ትርጉም ኖሮት በዚያ ቀን ወደ ቤተመቅደስ መምጣት ነበረባቸው፣ ሁለቱ ለሙታን ለመጠመቅ እና ቅዱስ ስርዓቶችን ለማከናወን የምትችለውን ለመመልከት ብቻ ነው የምትችለውን። እንደ ኔፊ፣ “በጌታ ቃል ኪዳን ይደሰታሉ”።5

የማውቃት ያላገባች ሴት ለየሳምንቱ የቅዱስ ቁርባን ስርዓቶች እናም “መንፈስር ከእርሷ ጋር ይሆን ዘንድ”6 ለሚለው ለቅዱስ ቃል ኪዳን ዋጋ እንዳላቸው ታያለች። ያም የሁልጊዜ ጓደኝነት የብቸኝነት ስሜትን የሚያለሳልሰው ቃል ኪዳን ነው። ችሎታዋን እና ጌታን ለማገልገል ያላትን ፍላጎት በማሳደግ ውስጥ በጥልቅ ለመንከር ጥንካሬ ይሰጣታል። በህይወቷ የሚገኙትን ልጆችን በሙሉ የመውደድን ታላቅ ደስታ አገኘትች፣ እናም ሰላምን ስትፈልግም በቤተመቅደስ ውስጥ ታገኟታላችሁ።

በመጨረሻም፣ የ90 አመት የሆናቸው ሴት ልጆቻቸው እና የልጅ ልጆቻቸው ሲያድጉ እና የልጅ ልጅ ልጆቻቸው ሲወለዱ ተመልክተዋል። እንደ ብዙዎቻችን፣ በሀዘኖች፣ በጉዳቶች፣ እና ሊገለጽ በማይቻል ደስታ የተሞላ ነበር። የህይወት ታሪካቸውን ሊጽፉ ቢሆን፣ የተጻፉትን አንዳንድ ምእራፎችን ለመጨመር እንደማይፈልጉ ይናገሩ ነበር። ነገር ግን ፈገግ ብለው እንዲህ አሉ፣ “ለትንሽ ጊዜ እኖራለሁ እና እንዴት እንደሚሆን እመለከታለሁ!” በመንገዱ ላይ በቃል ኪዳናቸው ቀጥለዋል።

ኔፊ እንዳስተማረው፣

“በጠባቡና በቀጭኑ ጎዳና ከገባችሁ በኋላ፣ ሁሉ ሀተደርጓልን? ብዬ እጠይቃችኋለሁ። እነሆ፣ አይደለም፣…

“ስለሆነም ፍጹም የሆነ የተስፋ ብርሃን፣ እናም የእግዚአብሔርና የሰዎች ሁሉ ፍቅር እየኖራችሁ በክርስቶስ ባላችሁ ፅኑነት መቀጠል አለባችሁ። ስለሆነም አብም፣ የክርስቶስን ቃል በመመገብ፣ እናም እስከመጨረሻው በመፅናት የምትቀጥሉ ከሆነ፣ እነሆ አብ እንዲህ ይላል፥ የዘለዓለም ህይወት ይኖራችኋል።”7

እያንዳንዳችን በመንገዱ ላይ ነን። በዚህ ምሽት በብርሀን በመንገዱ ስለመራመድ ዘምረናል። እንደ ግለሰቦች፣ እኛ ጠንካራዎች ነን። ከእግዚአብሔር ጋር፣ ለመቆም የማንችል ነን።

ጌታ ለኤማ ስሚዝ እንዳላት፣ “ልብሽን አቅኚ እናም ተደሰቺ፣ እና ከገባሽውም ቃል ኪዳን ጋርም ተጣበቂ።”8

የሰማይ አባታችን እና የአዳኛችን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ፣ ፍቅር እንዲሰማን ቃል ኪዳኖቻችን በመጠበቅ እንደሰታለን። እነርሱ ህያው እንደሆኑ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።