Skip main navigation
ሚያዝያ 2014 | በታማኝነታችን አማካኝነት መታዘዝ

በታማኝነታችን አማካኝነት መታዘዝ

ሚያዝያ 2014 አጠቃላላ ጉባኤ

ለበላይ ስልጣን መታዘዝ፣ የእግዚአብሄር ጥበብ እና ሀይል ላይ ያለን የእምነታችን መገለጫ ነው።

ሁሌ ሰኞ እኔና እህት ፔሪ እናዘጋጅ የነበረው የቤተሰብ ምሽት በመጠኑ እየጨመረ ነው። ወንድሜ፣ ሴት ልጁ፣ የባርባራ ወንድም፣ እና የአክስተ(የአጎት) ልጅ እና ባሏ ወደ ቾንዶሚንየማችን ግቢ ገብተዋል። ከልጅነቴ ጊዜ ጀምሮ ቤተሰብ በቅርቤ በመኖራቸው የተባረኩበት ብቸኛው ጊዜ ነው። ከዛም፣ ቤተሰቤ ከእናቴ ተቀጥያ የቤተሰብ አባላት ጋር አብሮ በአንድ ህንጻ ላይ ኖሩ። ከእኛ ቤት የወንድ አያቴ ጎን ቤት ከበሰተ ሰሜን ቀጣዩ ቤት ነበር፣ እና የአክስቴ ኤማ ቤት ደግሞ በስተ ደቡብ ቀጣዩ ቤት ነበር። ከህንጻው በስተ ደቡብ ጎን አክስቴ ጆሴፊን ትኖር ነበር፣ እና በስተ ምስራቅ አጎቴ አልማ የሚኖርበት ነበር።

በልጅነት ጊዜዬ ከተቀጥያ የቤተሰብ ኣባላት ጋር ልዩ የሆኑ የስራ፣ የጨዋታ፣ እና የጉብኝት ጊዜያትን በየቀኑ በመቀራረብ አብረን ተጋራን። ለእናቶቻችን መረጃው ሳይደርስ ታላቅ ረብሻ ውስጥ መግባት አልቻልንም ነበር። አሁን አለማችን የተለየ ነው፣ የአብዛኞቹ ቤተሰቦች ኣባላት ተበታትነዋል። በአንጻሩ እርስ ከእርሳቸው በቅርብ ቢኖሩም፣ ጎን ለጎን ግን አይኖሩም። አሁንም፣ የልጅነት ጊዜዬ እና የአሁኑ ሁኔታዬ ትንሽ ገነት እነደሚመስሉ ማመን አለብኝ፣ ተወዳጅ የቤተሰብ አባላት በቅርበት የሚኖሩበት። የዘለአለማዊ ተፈጥሮ የቤተሰብ ክፍልን ሁሌም እንዳስታውስ ያገለግለኛል።

እያደኩ ስመጣ፣ ከወንድ አያቴ ጋር ልዩ ቅርርብ ነበረን። በቤተሰብ ውሰጥ ታላቅ ወንድ ልጅ በመሆኔ፣ የእኛ ቤት፣ የአያቴ ቤት እና የሁለቱ አክስቶቼ ቤት በበጋ በረዶ አስወግድ ነበር እና ሳሮችን እንከባከብ ነበር። ሳሮቹን ሳጭድ አያቴ የፊት በረንዳ ላይ ሁሌ ቁጭ ይል ነበር። ስጨርስ፣ የደረጃዎቹ መጀመሪያ ላይ ቁጭ ብዬ አዋራው ነበር። እነዚያ ጊዜያት ትልቅ ሀብት የሆኑ ትውስታዎች ናቸው።

ህይወት የምታቀርበው ብዙ አማራጮች እነዳሉ ሆነው፣ ሁሌ ትክክለኛውን ነገር ማድረጌን እንዴት ላውቅ እችላለሁ ብዬ አያቴን ጠየኩት። አያቴ ሁሌ በአብዛኛው ጊዜ እንደሚያደርገው፣ ከግብርና ተሞክሮው መለሰልኝ።

የፈረሶችን ቡድን አብረው እንዲሰሩ እነዴት ማለያየት እንደሚቻል አስተማረኝ። የፈረሶች ቡድን ማን የበላይ እንደሆነ ሁሌም ማወቅ እናዳለባቸው አብራራልኝ። ፈረስ በመቆጣጠር እና በመምራት ቁልፉ ሉጋም እና ልባብ ነው። የቡድኑ አባል የነጂውን ፍላጎት መታዘዝ አስፈላጊ አይደልም ብሎ ቢያምን፣ ቡድኑ አብሮ በመስራት አቅሙን በፍጹም ስቦ ሊያሳድግ አይችልም።

አሁን ይህን ምሳሌ በመጠቀም አያቴ ያስተማረኝን ትምህርት እንፈትሽ። የፈረሶቹ ቡድን መሪ ማን ነው? ጌታ እንደሆነ አያቴ ያምን ነበር። እቅድ እና አላማ ያለው እሱ ነው። የፈረሶቹ ቡድን እንዲሁም የእያንዳነዱ ፈረስ አሰልጣኝ እና ገንቢ እሱ ነው። ነጂው የተሸለ ያውቃል፣ ሁሌም ትክክለኛውን ማድረጉን አንድ ፈረስ የሚያውቅበት ብቸኛ መንገድ በመታዘዝ እና የነጂውን ምሬት በመከተል ነው።

አያቴ ከሉጋሙ እና ከልባቡ ጋር ያመሳሰለው ምንድን ነው? የመንፈስ ቅዱስን ግፊት እንድከተል አያቴ እያስተማረኝ እንደነበር ያኔ እንዳመንኩት፣ አሁንም አምናለሁ። በአእምሮው እይታ፣ ሉጋሙ እና ልባቡ መንፈሳዊ ነበሩ። ታዛዥ ፈረስ፣ በደንብ የሰለጠኑ ፈረሶች ቡድን አባል የሆነ፣ በትክክል የፈለገውን እንዲያደርግ ላላ ያለ ጉተታ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። ይህ ላላ ያለ ጉተታ፣ ጌታ እኛን የሚናገርበትን ዝግ ያለ፣ ትንሽ ድምጽ ጋር እኩሌታ አለው። ለነጻ ምርጫችን ካለን አክብሮት የተነሳ፣ ጠንካራ እና ሀይል ያለው ጉተታ በፍጹም አይደለም።

የመንፈስ ቅዱስን ግፊት ንቀው የሚተዉ ወንዶች እና ሴቶች፣ ልክ አባካኙ ልጅ እንደተማረው፣ ባለመታዘዝ እና በተመሰቃቀለ ኑሮ ተፈጥሮአዌ ውጤቶች በየጊዜው ይማራሉ። አባካኙ ልጅ ከተፈጥሮአዌ ውጤቶች በኋላ ብቻ ነበር ወደ “ልቡ ተመልሶ” ትሁት ሆኖ ወደ ኣባቱ ቤት እንዲመለስ የነገረውን የመንፈስ ቅዱስ ሹክሹክታ ያዳመጠው (ሉቃስ 15፣11–32 ተመልከቱ)

ስለዚህ አያቴ ያስተማረኝ ትምህርት ላላ ያለውን የመንፈስ ቅዱስ ጉተታ ለመቀበል ሁልጊዜ ዝግጁ እንድሆን ነበር። ከመስመር ማፈንገጥ ስጀምር ሁሌም የመንፈስ ቅዱስ ግፊቶችን እንደምቀበል አስተማረኝ። እናም የመንፈስ ቅዱስን ምሬት በህይወት ውሳኔዎች ውስጥ ከተቀበልኩኝ በፍጹም ከበድ ያሉ መጥፎ ድርጊቶችን ፈጻሚ አልሆንም።

ያዕቆብ 3፣3 እንደሚለው፣ “እነሆ፣ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናስገባለን፣ ስጋቸውንም ሁሉ እንመራለን።”

ለመንፈሳዊ ሉጋሞቻችን ስሜታዊ መሆን አለብን። በጌታ ላላ ያለ ጉተታም ቢሆን፣ ሙሉ ለሙሉ አቅጣጫችንን ለማሻሻል ፍቃደኞች መሆን አለብን። በህይወት ስኬታማ ለመሆን፣ መንፈሳችንን እና አካላችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለመታዘዝ አብረው እነዲሰሩ ማስተማር አለብን። የመንፈስ ቀዱስን ዝግ ያሉ ግፊቶች የምናዳምጥ ከሆነ፣ መንፈሶቻችንን እና አካላቶቻችንን በማጣመር እና ከሰማይ አባታችን ጋር ወደ ዘላለማዊ ቤታችን እንድንመለስ ሊመራን ይችላል።

በሶስተኛው የእምነት አንቀጽ ላይ፣ የመታዘዝን አስፈላጊነትን እንማራለን፣ “በክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ አማካኝነት፣ ለወንጌል ህግጋትና ስርአቶች በመታዘዝ፣ ሁሉም ሰው ይድናል።”

በምሳሌው ላይ አያቴ የገለጸው የመታዘዝ አይነት ልዩ ተአማኝነትን ይጠይቃል፣ ያም ደግሞ፣ በቡድኑ ነጂ ላይ ሙሉ በሙሉ እምነት ማኖር ነው። አያቴ ያስተማረኝ ትምህርት፣ ስለዚህ፣ እምነት በእየሱስ ክርስቶስ ከሚለው የመጀመሪያው የወንጌል መሰረተ ሀሳብ ጋር የተቆራኘ ነው።

ሐዋሪያው ጳውሎስ አስተማረ፣‹‹እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ ፣ የማናየውንም ነገር የሚያሥረዳ ነው። (ዕብራውያን 11፥1)። ከዛም ጳውሎስ ስለ እምነት ለማስተማር የአቤልን ፣የሄኖክን፣የኖህን እና አብረሃምን ምሳሌዎችን ተጠቀመ' አብረሃም የአማኞች አባት በመሆኑ፣ በአብረሃም ታሪክ ላይ ቆየ። ጳውሎስ ፃፈ፤

“አብረሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፣ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ።

“ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖረ …

“ተስፋ የሰጠውን የታመነ እንደሆነ ስለ ቆጠረች፣ ሳራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመጸነስ ሀይልን በእምነት አገኘች።” (ዕብራወያን 11፥8–9፣11)

የአብረሀምና ሳራ ልጅ፣ ይሰሐቅ፣የተነሳ ለአብረሃም ቃልኪዳን እንደተሰጠ እናውቃለን ፤የዘር መብዛት ቃልኪዳን “እንደ ሰማይ ኮኮብ እንደማይቆጠርም በባህር ዳር እንዳለ አሸዋ ’’(ቁጥር 12 ተመልከቱ፤ ደግሞም ዘፍጥረት 17፥15–16ተመልከቱ) እናም ከዛ ፣አብዛኛዎቻችን የማይታሰብ በምንለው መንገድ የአብረሃም እምነት ተፈትኖ ነበር።

በብዙ ሁኔታዎች የአብረሃምንን እና ይሳቅን ታሪክ አሰላስያለሁ፣አሁንም ድረስ የአብረሃምን አማኝነትና መታዘዝ ሙሉ ለሙሉ ተረድቻለሁ ብዬ አላምንም›› በእርግጥ በጠዋት ለመሄድ መዘጋጀቱን ማሰብ እችላለሁ ፣ነገር ግን ከልጁ ይሳቅ ጎን እንዴት ነው ያንን ሁሉ ደረጃዎች የወሰደው፣ወደ ሞሪያ ተራራ ከሶስት ቀን ጉዞ በላይ? የእሣትእንጨቱን አንዴት ወደ ተራራው ላይ ተሸከመው? መሰውያውንስ እንዴት ገነባ?ይሳቅን አስሮ መሰዊያው ላይ ከማድረጉ በፊት፣ የሚሰዋው እሱ እንደሆነ እንዴት ነው የገለፀለት? ልጁን ለማረድ ቢላውን ለማንሳት ጥንካሬው እንዴት ሊኖረው ቻለ? የአብረሃም እምነት የእግዚያብሄርን ምሬት በሙሉነት እንዲከተል ሀይል ሰጪዎች መልአክ ከሰማይ ጠርቶት ለአብረሃም የማይቻለውን ፈተና ማለፉን እስካሳወቀበት ተአምረኛ ጊዜ ድረስ። እና ከዛም የጌታ መልአክ የአብረሃምን ቃልኪዳን ደግሞ ተናገረ።

እምነት በእየሱስ ክርስቶስ ማኖርን ተያይዞ ያሉ መሰናክሎችን አስተውላለሁ እና መታዘዝ ለአንዳንዶች ከሌሎች የበለጠ ይከብዳል። የበቂ አመታት ልምድ አለኝ የፈረሶቹ ግላዊ ባህሪያት እንደሚለያይ፣ እና ለማሰልጠን ቀለል ያለ ወይም ከበባድ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ የሰዎች መለያየት የበለጠ ነው። እያንዳንዳችን የእግዚአብሔር ወንድ ወይም ሴት ልጆቹ ነን፣ እና ልዩ የሆኑ ቅድመ ሟችነት እና ምድራዊ ታሪኮች አሉን። ስለዚህ፣ ሁሉንም ሁኔታዎች የሚመጥኑ ጥቂት መፍትሄዎች ብቻ ነው ያሉት። እና የህይወትን የሙከራና ስህተት ተፈጥሮ አስተውላለለሁ እና፣ በይበልጥ፣ የሁለተኛውን የወንጌል መሰረተ ሀሳብ የሁልጊዜም አሰፈላጊነትን፣ ንስሀ።

እውነትም ነው አያቴ የኖረበት ጊዜ፣ ቀላል ጊዜ ነበር፣በተለይ ትክክለኛውን እና ስህተቱን በመምረጡ ረገድ።ጥቂት በጣም አዋቂ እና አስተዋይ ሰዎች ውስብስብ የሆነውን ጊኤያችን ውስብስብ መፍትሄ ያስፈልገዋል ብለው ስያምኑ፣ትክክል ናቸው ብዬ ከመስማማት የራኩ ነኝ። ባይሆን፣ የዚህ ጊዜ መወሳሰብ ቀሊልነት እንደሚሻ ከሚያስቡት ነኝ፣ ትክክለኛው እና ስህተት መካከል ስላለው ልዩነት አያቴ ለትሁቱ ጥያቄዬ እንደሰጠው መልስ። ዛሬ የምሰጠው ቀላል የሆነ መሰረታዊ ደንብ እንደሆነ አውቃለሁ። ለሁሉም ሰው ላይሰራ ይችላል፣ ነገር ግን ለኔ በደንብ እንደሚሰራ ልመሰክር እችላለሁ። እናንተም አድርጉት እና በቃላቶቼ ላይ ሙከራ እንድታደርጉ ጠይቃችኋለሁ፣ እና ካደረጋችሁት፣ በምርጫ በተደናገራችሁ ጊዜ ግልጽ ወደ ሆነ ምርጫ እንደሚመራችሁ እና የተማሩ እና ጠቢብ ነን ብለው የሚያስቡትን ግራ የሚያጋቡ ጥያቄዎችን ቀላል እንደሚያደርጉ ቃል እገባለሁ።

አብዛኛው ጊዜ መታዘዝን የበላይ ንቁ ባልሆነ እና ሀሳባዊ ያልሆነ የበላይ ስልጣን ምሬትን መከተል አድርገን እናስባለን። በእርግጥ፣ በተቻለን መጠን ለበላይ ስልጣን መታዘዝ፣ የእግዚአብሄር ጥበብ እና ሀይል ላይ ያለን የእምነታችን መገለጫ ነው። አብሬም የማየናወጥ አማኝነትን እና ለእግዚአብሄር ታዛዥነትን ሲያሳይ፣ ልጁን እነዲሰዋ ሲታዘዝም እነኳ፣ እግዚአብሄር አድኖታል። በተመሳሳይ፣ በእምነታችን የተነሳ መታዘዝን ስናሳይ፣ እግዚአብሄር በመጨረሻም ያድነናል።

በራሳቸው የሚመኩ እና የራሳቸውን ፍላጎት ብቻ የሚከተሉ እግዚአብሄርን ከሚከተሉ እና በእርሱ እያታ፣ ሀይል እና ስጦታ ውስጥ ከሚገቡት ጋር ሲነጻጸሩ የተገደቡ ናቸው። እንደባለው “ በራሱ ወየይም በራሷ ዙሪያ የተጠቀለለ ሰው በጣም አነስተኛ ውጤት የሰጣል” ጠንካራ ወይም በጣም ንቁ ታዘዥነት ደከም ያለ እና ዝግ ያለ ነው። በእግዚአብሄር እምነታችንን የምናውጅበት እና እራሳችንን የሰማይን ሀይል ለመቀበል ብቁ የምናደርግበት መንገድ ነው። መታዘዝ ምርጫ ነው። በእኛ የተወሰነ እውቀት እና ሀይል እና በእግዚአብሄር ገደብ የሌለው ጠበብ እና ሁሉን ቻየነት መካከል ያለ ምርጫ ነው። እንደ አያቴ ትምህርት፣ የመንፈሳዊ ሉጋሙን በአፋችን ውስት ስሜት መስጠት እና የነጂውን ምሬት የመከተል ምርጫ ነው።

በእምነታችን እና የተመለሰውን ወንጌል ስርአት በመቀበል የቃልኪዳን ወራሾች እና የአብረሃም ዘር እንሁን። አማኝ እና ታዛዥ ለሆኑ ሁሉ የዘላለማዊ ህይወት በረከቶች እንደሚደርሳቸው ቃል እገባላችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

Right