2010–2019 (እ.አ.አ)
ምርጥ ትውልድ
ሚያዝያ 2014


ምርጥ ትውልድ

በዚህ ጊዜ ትክክለኛውን ምርጫ ለመምረጥ እንደምትችሉ ስለሚያምናችሁ በዚህ ስራ እንድትሳተፉ ተመርጣችኋል።

ወጣቶች፣ ከዚህ በፊት “ምርጥ ትውልዶች” ናችሁ ተብላችሁ ስትጠሩ ሰምታችሁ ይሆናል፣ ይህም እግዚአብሔር እናንተን በዚህ ጊዜ ለታላቅ አላማ እንድትመርጡ መርጦ አዘጋጅቷችኋል ማለት ነው። ይህ እውነት እንደሆነ አውቃለሁ። ነገር ግን በዚህ ምሽት እናንተን እንደ “ምርጥ ትውልዶች” የምጠራችሁ ምክንያት ከዚህ ጊዜ በፊት ባልነበረ በበዙ ምርጭዎች ስለተባረካችሁ ነው። ብዙ ምርጫዎች ማለት ብዙ እድሎች ማለት ነው፣ እናም ብዙ እድሎችም መልካም፣ እናም በሚያሳዝን ሁኔታም፣ ክፉ ለማድረግ ያሉ ብዙ ችሎታዎች አሉ ማለት ነው። እግዚአብሔር በዚህ ጊዜ የላካችሁ እናንተ በብዛታቸው በሚያስደንቁ ምርጫዎች መካከል በውጤታማነት ለማስተዋል እንደምትችሉ በእናንተ ላይ እምነት ስላለው እንደሆነ እምነቴ ነው።

በ1974 (እ.አ.አ)፣ ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው. ኪምባል እንዳሉት፣ “ጌታ በእጆቻችን ውስጥ እኛ ከማናስበው በላይ የሆኑ ቴክኖሎጆዎች ለመስጠት በጉጉት እንደሚጠብቅ አምናለሁ” (“When the World Will Be Converted,” Ensign, Oct. 1974, 10)።

እንዲህም አድርጓል። የምታድጉት በሰው ታሪክ ውስጥ ከነበሩት ሁሉ በጣም ጠቃሚ ከሆነ መሳሪያ ጋር ነው፥ ይህም ኢንተርኔት ነው። ከዚህም ጋር የተለያዩ ምርጫዎች መጥተዋል። የምርጫ ብዛት ግን እኩል የሆነ የተቀባይነት ክፍሎችን ይዞ ይመጣል።አለም ከምታቀርባት ከሁሉ ይበልጥ ጥሩ የሆነውን እና ከሁሉም ይበልጥ መጥፎ የሆነውን ለማግኘት እንድንችል ያደርጋል። በዚህም ታላቅ ነገሮችን በአጭር ጊዜ ለማከናወን ትችላላችሁ፣ ወይም ጊዜአችሁን በሚያጠፋ እና ችሎታችሁን በሚያዋርዱ መጨረሻ በሌላቸው ነገሮች እራሳችሁን ለማጥመድ ትችላላችሁ። የኮምፒውተሩን መተየቢያ በመንካት ልባችሁ የፈለገውን በፍጥነት ለማግኘት ትችላላችሁ። ይህም ዋናው መሰረታዊ መርሆ ነው---ልባችሁ ምን ነው የሚፈልገው? ወደ ምን ነው የምትሳቡት? ፍላጎታችሁ ወደምን ይመራችኋል?

እግዚአብሔር “እንደፍላጎታቸው” እንዲሚሰጣቸው (አልማ 24፥4) እናም “ሁሉንም ሰዎች በስራዎቻቸው መሰረት፣ እንደልባቸውም ምኞት” እንደሚፈርድባቸው (ት. እና ቃ. 137፥9፤ ደግሞም አልማ 41፥3 ተመልከቱ) አስታውሱ።

ሽማግሌ ብሩስ አር. መካንኪ እንዲህ ብለዋል፥ “እውነተኛ ቢሆንም በምሳሌ፣ የህይወት መፅሐፍ በሰውነታቸው ውስጥ የተጻፈ የሰዎች ስራ መዝገብ ነው።…ይህም ማለት፣ እያንዳንዱ ሀሳብ፣ ቃል፣ እና ስራ በሰው ሰውነት ላይ ተፅዕኖ አለው፤ እነዚህ በሙሉ ምልክቶች፣ በዘለአለማዊው በመፅሀፍ የተጻፉት እንደሚነበቡት ለመነበብ የሚችሉ ምልክቶች ጥለው ይሄዳሉ” (Mormon Doctrine, 2nd ed. [1966], 97)።

ኢንተርኔትም የኮምፒውተሩን መተየቢያ በምትነኩበት በሙሉ ፍላጎታችሁን ይመዘግባል። እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት የሚጠብቁ ብዙ ነገሮች አሉ። በኢንተርኔት መግለጫዎችን ስትፈትቹ፣ ማን እንደሆናችሁ፣ የምታስተላልፉትን ነገሮች፣ የት እንደሄዳችሁ፣ ለስንት ጊዜ በዚያ ቦታ እንደቆያችሁ፣ እና የምትወዱት ምን ነገሮች እንድሆኑ የሚገልጹ ነገሮች ወደኋላ ትታችሁ ትሄዳላችሁ። በዚህም መንገድ፣ ኢነተርኔት እናንተ በኢንተርኔት የምታደርጉትን የሚመዘግቡ፣ በዚህም፣ የኢንተርኔት ህይወት መፅሀፍ ለእናንተ ሰራል። እንደ ህይወትም፣ ኢንተርኔት የምትፈልጉትን ይሰጣችኋል፣ ይህንንም በቀልጣፋነት ያደርገዋል። ፍላጎታችሁ ንጹህ ከሆኑ፣ መልካም የሆኑትን ድርጊቶች ለማከናወን ቀላል እያስደረገ፣ ኢንተርኔት እነዚህን ያጎላቸዋል። ነገር ግን ከዚህ ታቃራኒውም እውነት ነው።

ሽማግሌ ኔል ኤ. ማክስዌል እንዳሉት፣

“በጣም የምንፈልገው፣ ከጊዜም በኋላ፣ በመጨረሻም ይህም እኛ የምንሆነው እናም በዘለአለም የምንቀበለውም ነው።…

“…ፍላጎቶቻችንን በማስተማር እና በማሰልጠን ብቻ ነው የእኛ ጠላት ሳይሆን ተባባሪ የሚሆነው” (“According to the Desire of [Our] Hearts,” Ensign,, Nov. 1996, 21–22)።

ውድ ወጣት ወንድሞቼ፣ ፍላጎታችሁን ለማሰልጠን በደንብ ካልጣራችሁ፣ አለም ይህን ያሰለጥንላችኋል። በየቀኑ፣ አለም ፍላጎታችሁ ላይ ተፅዕኖ ለማግኘት፣ አንድ ነገር እንድትገዙ፣ በኮምፒውተር አንድ ነገርን እንድትነኩ፣ አንድ ነገርን እንድትጫወቱ፣ አንድ ነገርን እንድታነቡ ወይም እንድታዩ ለማባመል ይፈልጋል። በመጨረሻም ምርጫው የእናንተ ነው። እናንተ ነጻ ምርጫ አላችሁ። ይህም በፍላጎታችሁ ለመስራት ብቻ ሳይሆን ደግሞም ፍላጎታችሁ ለማጥራት፣ ለማጽዳት፣ እና ከፍ ለማስደረግ የሚያስችል ሀይል ነው። ነጻ ምርጫ የመሆን የሚያስችል ሀይል ነው።እያንዳንዱ ምርጫ እናንተ ለመሆን ከምትችሉት የሚያቀርብ ወይም ወደ ርቀት የሚገፋ ነው፤ እያንዳንዱ በኮምፒውተሩ መተየቢያ የምትነኩት ትርጉም አለው። ሁልጊዜም “ምርጫዬ የት ይወስደኛል?” በማለት እራሳችሁን ጠይቁ። ካላችሁበት ሁኔታ በላይ ለመመልከት ችሎታችሁን አሳድጉ።

ለመቆጣጠር ይፈልጋል። ይህን የሚያደርግበት አንድ ጥሩ መንገድ ቢኖር ሱስ በሚሰጥ ጸባይ እናንተን በማጥመድ ነው። ምርጫችሁ ቴክኖሎጂ እናንተን በይል እንደሚሰጣችሁ ወይም እንደሚያስራችሁ ለመወሰን ይችላል።

እናንተን ምርጥ ትውልዶች ሊረዳችሁ፣ ፍላጎታችሁን ለማሰልጠን፣ እና ቴክኖሎጊ የምትጠቀሙበትን ሊመራላችሁ የሚችስችሏችሁ አራት መሰረታዊ መርሆች ልስጣችሁ።

በመጀመሪያ፥ ማን እንደሆናችሁ ማወቅ ውሳኔ ማድረግ ያቀልላል

ይህን እውነት ለእራሱ ያወቀ አንድ ጓደኛ አለኝ። ልጁ በወንጌል አድጎ ነበር፣ ነገር ግን በመንፈስ ይወላዘግ ነበር። ክህነቱን የመጠቀም እድሉን በየጊዜ ያሳልፍ ነበር። በሚስዮን አልሄድም በሚልበት ጊዜ ወላጆቹ አዝነው ነበር። ጓደኛዬ ለልጁ ልጁ ሀሳቡን ይቀይር ዘንድ በቅንነት ጸለየ። ከቤተመቅደስ ውጪ ለማግባት እንደወሰነ ሲነግራቸውም ተስፋቸው ጠፋ። የፓትሪያርክ በረከቱን እንዲያገኝም አባት ልጁን ለመነው። ልጁም በመጨረሻ ተስማማ ግን ፓትሪያርኩን በብቻም ለመጎብኘት ችክ አለ።

ከበረከት በኋላ ወደቤት ሲመለስ፣ ብዙ ስሜት ያለው ነበር። የሴት ጓዳኛውን በብቻቸው ወደሚነጋገሩበት ወሰዳት። አባትየውም በመስኮት ወደ ውጪ ሲመለከተ ሁለቱም እምባቸውን ሲጠርጉ ተመለከተ።

በኋላም ለአባቱ ምን እንደደረሰ ነገረው።፡በታላቅ ስሜት፣ በበረከቱ ጊዜ ከምድር ህይወት በፊት ማን እንደነበረ በአዕምሮው ታየው። ሌሎች ክርስቶስን እንዲከተሉ እንዴት ተፅዕኖ እንደነበረው እና ጀግና እንደነበረ አየ። ማን እንደነበረ በማወቅ፣ እንዴት ሚስዮን ለማገልገል አይችልም?

ወጣቶች፣ ምን እንደሆናችሁ አስታውሱ። ቅዱስ ክህነት እንዳላችሁም አስታውሱ። ይህም ኢንተርኔትን ስትጠቀሙበት እና በህይወታችሁ በሙሉ ትክክለኛውን ምርጫ እንድትመርጡ ያነሳሳችኋል።

ሁለተኛ፥ የሀይል መንጭን ተክሉ

በእጃችሁ ላይ የአድሜዎች ጥበብ አላችሁ--ከዚህ በላይ አስፈላጊ በሚሆን፣ ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ እስከ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን የመጡ የነቢያት ቃላት አላችሁ። ነገር ግን ይህን በየጊዜው የእጅ ስልካችሁን ባትሪ ካልሞላችሁት ይህም ጠቃሚ አይደለም፣ እናም የጠፋችሁ እና ግንኙነት የሌላችሁ ይመስላችኋል። ባትሪአችሁን ሳትሞሉ ለአንድ ቀን እንኳን ለመቆየት አታስቡበትም።

ከቤት ስትወጡ የእጅ ስልካችሁ ባትሪ ሙሉ መሆኑ አስፈላጊ እንደሆነ፣ በመንፈስ ሙሉ መሆንም ከዚህ በላይ አስፈላጊ ነው። የስልካችሁን ባትሪ ለሞምላት በምትተክሉበት ጊዜ፣ በመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት የሚያዘጋጃችሁ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ከሆነው የመንፈስ ሀይል መንጭ ከሆኑት፣ እንዲሁም ከጸሎት እና ከቅዱሳት መጻህፍት ጥናት፣ እራሳችሁን ለመተከል እንደቻላችሁ እራሳችሁን የምትጠይቁበት ማስታወሻ አድርጉት (ት. እና ቃ. 11፥12–14 ተመልከቱ)። በህይወታችሁ የምትሄዱበትን ለመወሰን በየቀኑ አስፈላጊ የሆነውን ውሳኔ ለማድረግ የጌታን አስተሳሰብ እና ፍላጎት እንድታውቁ ይረዳችኋል። አብዛኛዎቻችን የምናደርገውን ወዲያው አቁመን በእጅ ስልክ የምንቀበለውን መልእክት እናነባለን--በጌታ መልእክት ላይ ከዚህ በላይ የሆነ አስፈ፤አጊነትን መስጠት አይገባንምን? ከዚህ ሀይል ጋር መገናኘትን ችላ ማለት ለእኛ ያማናስበው መሆን ይገባዋል (2 ኔፊ 32፥3 ተመልከቱ)።

ሶስተኛ፥ ኢንተርኔት ለመግባት የሚያስችል ስልክ ሲኖራችሁ ይህም አዋቂ አያደርጋችሁም፤ በጥበብ መጠቀሙ ግን አዋቂ ያደርጋችኋ

ወጣቶች፣ ወደ ኢንተርኔት በሚገባው ስልካችሁ መጥፎ ነገሮች አታድርጉ። ምን ማለቴን ታውቃላችሁ (ሞዛያ 4፥29 ተመልከቱ) ለምሳሌ፣ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ከሆነው ትኩረት የሚስብ ብዙ የቴክኖሎጂ ዘዴዎች አሉ። “ባለችሁበት፣ በዚያም ተገኙ” የሚለውን አባባል ተከተሉ። ስትነዱ፣ ንዱ። በትምህርት ቤት ስትሆኑ፣ በትምህርት ላይ አተኩሩ።፡ከጓደኞች ጋር ስትሆኑ፣ ለእነርሱ ትኩረት ስጡ።፡አዕምሮአችሁ በሁለት ነገሮች ላይ ሊያተኩር አይችልም። ብዙ ነገሮችን በአንድ ጊዜ ማከናወን ማለት ትኩረታችሁን በፍጥነት ከአንድ ወደ ሌላ ማዘዋወር ነው። ምሳሌው እንደሚለው፣ “ሁለት ጥንቸሎች ካባረራችሁ፣ ማንኛውንም አትይዙም።”

በመጨረሻም፣ ጌታ እቅዱስን ለማሟላት ቴክኖሎጂ ይሰጣል

የቴክኖሎጂ መለኮታዊ አላማ የደህንነትን ስራ ለማፋጠን ነው። እንደ ምርጥ ትውልዶች አባላት፣ እናንተ ከማንም በላይ ቴክኖሎጂን ትረዳላችሁ። ብዙ ስለተሰጣችሁም፣ ብዙ መስጠት አለባችሁ (“ብዙ ስለተሰጠኝ” መዝሙር፣, ቁጠር 219 ተመልከቱ)። ጌታ እነዚህን ታላቅ መሳሪያዎች በመጠቀም ስራውን ወደፊት እንድትገፉ፣ የእኔ ትውልድ ሊያስብበት ከሚችለው በላይ በሆኑ መንገሮች ወጌልን እንድትካፈሉ ይፈልጋል። የድሮ ትውልዶች በጎረቤቶቻቸው እና በከተማቸው ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው፣ እናንተም በኢንተርኔት በሌሎች መተላለፊያዎች ከድንበራችሁ አሳልፎ ለመድረስ እና በአለም ላይ ሁሉ ተፅዕኖ እንዲኖራችሁ የሚያስችል ሀይል አላችሁ።

ይህ የጌታ ቤተክርስቲያን እንደሆነ እመሰክራለሁ። በዚህ ጊዜ ትክክለኛውን ምርጫ ለመምረጥ እንደምትችሉ ስለሚያምናችሁ በዚህ ስራ እንድትሳተፉ ተመርጣችኋል። እናንተ ምርጥ ትውልዶች ናችሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።