Skip main navigation
ሚያዝያ 2014 | የክህነት ሰው

የክህነት ሰው

ሚያዝያ 2014 አጠቃላላ ጉባኤ

ታላቅ ተምሳሌት፣ መካከለኛ፣ ወይም መጥፎ ተምሳሌት መሆን ትችላላችሁ። ለእኛ ትርጉም የለውም ብላችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ለጌታ ትርጉም አለው።

ሁላችንም ጀግና የምንላቸው አሉን፣ በተለይ ወጣት ሆነን። ተወልጄ ያደኩት ፕሪነስ ታውን፣ ኒው ጄርዚ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ነበር።እኛ በኖርንበት አቅራቢያ የነበሩት ታዋቂ የስፖርት ቡድን ማእከላቸው በኒው ዮርክ ነበር። የሶስት ቤዝቦል ቡድኖች መኖሪያ ነበር፣ የብሮክሊን ዶጀርስ፣ ኒው ዮር ጃየንትስ፣ እና ኒው ዮርክ ያንኪስ። ፊላዴልፊያም ለኛ ቤት የበልጥ ቅርብ ነበር እና የአትሌቶች እና የፊሊስ ቤዝቦል ቡድን መኖሪያም ነበር።

ጆ ዲማጂዮ፣ ለኒው ዮርክ ያንኪስ ይጫወት የነበረ፣ የቤዝቦል ጀግናዬ ሆነ። ወንድሞቼ እና ጓደኞቼ ከቤታችን ቀጥሎ ባለው ትምህርት ቤት ቤዝቦል ሲጫወቱ፣ ልክ ጆ ዲማጊዮ ያደርጋል ብዬ እንዳሰብኩት ምምቻውን አንዠዋዥው ነበር። ያ ቴሌቭዢን ከመኖሩ በፊት ነበር፣ ስለዚህ የሱን አመታት ለመኮረጅ የጋዜጣ ምስሎች ብቻ ነበሩኝ።

እያደኩኝ ስመጣ፣ አባቴ ወደ ያንኪስ ስቴድየም ይዞኝ ሄደ። ይሄ ጆ ዲማጂዮ ሲጫወት ያየሁበት ብቸኛ ወቅት ነበር። አሁንም እዚያ እንዳለሁ ይመስል፣ በመምቻው ሲመታ እና የቤዝቦል ኳሷ በቀጥታ ወደ ሜዳው መሃል ስትበር በአየምሮዬ ማየት እችላለሁ።

አሁን፣ የቤዝቦል ችሎታዬ እንደ ልጅነቴ ጀግኖች በፍጹም አልሆነም። ነገር ግን ቤዝቦል ጥሩ አድርጌ በመታሁባቸው ጥቂት ጊዜያት፣ እንደቻልኩት መጠን የሱን ሀያል አመታት ኮርጄያለሁ።

ጀግኖች ስንመርጥ፣ አስበንም ሆነ ሳናስብ፣ ከእነሱ ውስጥ ይበልጥ የምናደንቀውን መኮረጅ እንጀምራለን'

በደስታ፣ በልጅነቴ ጠቢቦቹ ወላጆቼ ታላቅ ጀግኖችን በመንገዴ አደረጉ። የቤዝቦል ጀግናዬ ሲጫወት እንዳይ አባቴ አንዴ ብቻ ወደ ያንኪ ስቴዲየም ወሰደኝ፣ ነገር ግን ጀግና የሆነ የክህነት ሰውን ሁሌ እሁድ እንድመለከት አደረገ። ያ ጀግና ህይወቴን ቀረጸው። አባቴ በቤታችን የምንገናኝበት የትንሹ ቅርናጫፍ ፕሬዘዳንት ነበር። ቅርንጫፋችን ከ30 ሰዎች በላይ አስተናግዶ አያውቅም።

እናቱን ለስብሰባዎች በመኪና ያመጣ አንድ ወጣት ነበር፣ ወደ ቤት ግን ገብቶ አያውቅም። አባል አልነበረም። ወደ ቤታችን እሱን በመጋበዝ የተሳካለት አባቴ ነበር። ተጠመቀ እና ብቸኛው እና የመጀመሪያዬ የአሮናዊ ክህነት መሪዬ ሆነ። የክህነት ጀግናዬ ሆነ። ለአንድ እመበለት የእሳት እንጨት በመቁረጥ ስራ ከጨረስን በኋላ የሰጠኝን የእንጨት ቅርጽ አሁንም አስታውሳለሁ። ለእግዚአብሔር አገልጋይ ትክክለኛ ክብር ስሰጥ ልክ እንደሱ ለመሆን ሞክሬያለሁ።

በዚያች ትንሽ ቅርንጫፍ ሌላ ጀግና መረጥኩ። አረንጓዴ የደንብ ልብሱን ለብሶ ወደ ስብሰባችን የሚመጣ የዪናይትድ ስቴት የባህር ሀየል ላይ የሚሰራ ነበር። የጦርነት ጊዜ ነበር፣ ስለዚህ ያ በራሱ የኔ ጀግና አደረገው። በትምህርቱ እንዲቀጥል በባህር ሀይል ወደ ፕሪንስቶን ዩንቨርሲቲ ተልኮ ነበር። ከጦር የደምብ ልብሱ በይበልጥ፣ ለፕሪንስቶን ዩንቨርሲቲ እግርኳስ እንደ አምበል ሆኖ በፓልመር ስቴድየም ሲጫወት ተመለከትኩት። በዩኒቨርሲቲው ቅርጫት ኳስ ቡድን ሲጫወት አየሁት እና እንደ ኮከብ ቀላቢ ሆኖ ቤዝቦል ሲጫወትም ተመለከትኩት።

በይበልጠም ደግሞ፣ በቀኝም በግራም እጄ እንዴት የቅርጫት ኳስ እንደሚሾት ሊያሳየኝ ወደ ቤቴ መጣ። በጥሩ ቡድኖች ወደፊት ስለምጫወት ጥበቡ እንደሚያስፈልገኝ ነገረኝ። ያኔ አልተገነዘብኩትም ነበር፣ ነገር ግን እሱ፣ ለአመታት፣ የእውነተኛ ክህነት ሰው ተምሳሌቴ ነበር።

እያንዳንዳቹ መሆን ብትፈልጉም ባትፈልጉም የክህነት ሰው ተምሳሌት ትሆናላችሁ። ክህነትን ስትቀበሉ የተለኮሰ ሻማ ሆናችኋል። በዙሪያችሁ ላሉት ሰዎች መንገዱ ላይ እንድታበሩላቸው ጌታ የሻማ ማስቀመጪያ ላይ አድርጓችኋል። ይሄ በተለይ በክህነት ጉባኤያችሁ ላሉት ይሰራል። ታላቅ ተምሳሌት፣ መካከለኛ፣ ወይም መጥፎ ተምሳሌት መሆን ትችላላችሁ። ለእኛ ትርጉም የለውም ብላችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ለጌታ ትርጉም አለው። በዚህ መልኩ ተናግሮታል፤

“እናንተ የአለም ብርሀን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።

“ማብራትንም አብርተው ከእንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።

“መልካሙን ስራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሀናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።1

ለማገልገል በታደልኩባቸው ጉባኤ ውስጥ በነበሩ ታላቅ የክህነት ተሸካሚዎች ምሰሌነት ተባርኬአለሁ። ሌሎች ምሳሌአችሁን እንዲከተሉ በማድረግ እነሱ ለእኔ የደረጉትን ማድረግ ትችላላችሁ።

የእኔ ጀግኖች የነበሩትን የክህነት ተሸካሚዎች ሶስት የጋራ መገለጫዎችን አስተውያለሁ። አንዱ ቀጣይነት ያለው ጸሎት ነው፣ ሁለተኛው የማገልገል ልምድ፣ እና ሶሰተኛው ታማኝ ለመሆን እንደ አለት የጠነከረ ውሳኔ ነው።

ሁላችንም እንጸልያለን፣ ነገር ግን መሆን የምትፈልጉት የክህነት ተሸካሚ በየጊዜው እና ከልቡ ይጸልያል። በምሽት በጉልበታችሁ ትንበረከካላችሁ እና ለቀኑ በረከቶች እግዚአብሔርን ታመሰግናላችሁ። ስለ ወላጆች፣ መምህሮች እና ለመከተል ላሉት ታላቅ ምሳሌዎች ታመሰግኑታላችሁ። በጸሎታችሁ በተለይ ማን እና እንዴት በቀኑ ጊዜ ህይወታችሁን እንደባረከው ትገልጻላችሁ። ያ ከጥቂት ደቂቃዎች በላይ እና ከማሰብ በላይ ይጠይቃል። የደንቃችኋል እና ይለውጣችኋል።

ይቅር ለመባል ስትጸልዩ፣ እራሳችሁ ሌሎችን ይቅር ስትሉ ትገኛላችሁ። ለደግነቱ እግዚአብሔርን ስታመሰግኑ፣ የእናንተን ደግነት የሚፈልጉ ሌሎችን፣ በስም፣ ታስባላችሁ። እንደገና፣ ያ ተሞክሮ በየቀኑ ይደንቃችኋል፣ እና ከጊዜም በኋላ ይለውጣችኋል።

በዚህ ትጉህ ጸሎት ከምትቀየሩበት መንገድ አንዱ በእውነትም የእግዚአብሔር ልጅ መሆናችሁ ይሰማችኋል። የእግዚአብሔር ልጅ መሆናችሁን ስታውቁ፣ ከእናንተ የበለጠ እንደሚጠብቅ ታውቃላችሁ። እንደ ልጁ፣ የእርሱን እና የተወዳጁ ልጁን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ትምህርቶች እንድትከተሉ ከእናንተ ይጠብቃል። ለሌሎች ለጋስ እና ደግ እንድትሆኑ ይጠብቃል። ኩራተኛ እና እራስ ተኮር ከሆናችሁ በእናንተ ያዝናል። የሌሎችን ፍላጎት ከእራሳችሁ እንድታስበልጡ ይባርካችኋል።

አንዳንዶቻችሁ አሁን ቢሆን ራስ ወዳድ ያልሆነ የክህነት አገልግሎት ምሳሌዎች ናችሁ። በቤተመቅደስ በአለም ዙሪያ፣ የክህነት ተሸካሚዎች ጸሀይ ሳይወጣ ይደርሳሉ። እና አንዳንዶቹ ጸሀይ ከጠለቀ በኋላ ቆይተው ያገለግላሉ። ለጊዜ እና ለስራ መስዋእትነት መታወቅ ወይም ህዝባዊ አድናቆት በዚህ አለም ላይ የለም። የቤተመቅደስን በረከቶች ለራሳቸው ማድረግ ለማይችሉት በመንፈስ አለም ያሉትን ሲያገለግሉ ከወጣቶች ጋር ሄጃለሁ ።

በጠዋት እና ከረፈደ በኋላም የሚያገለግሉ ሰዎችን ፊት ከድካም ይልቅ ደስታ ስመለከት፣ ለዚያ አይነቱ ራስ ወዳድ ያልሆነ የክህነት አገልግሎት ታላቅ ሽልማት እንዳለው አውቃለሁ፣ ነገር ግን ካገለገሏቸው በመንፈስ አለም ካሉት ጋር የሚጋሩት የደስታ ምልክት ብቻ ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት አባል በመሆን ስለሚመጣው በረከቶች ለሌሎች የሚናገሩ ሰዎች ፊት ላይም ያንን ደስታ ተመልክቻለሁ። በየቀኑ ሚስኦናውያን እንዲያስተምሩአቸው ሰዎችን የሚያመጣ የቅርንጫፍ ፕሬዘዳንት አውቃለሁ። ከጥቂት ወራት በፊት እሱ ገና የቤተክርስቲያን አባል አልነበረም። አሁን በሱ ምክንያት ሚስኦናውያን እያስተማሩ ነው እና ቅርንጫፉ እያደገ እና እየጠነከረ ነው። ግን ከዛም በላይ፣ አፋቸውን ለሚከፍቱ እና የሰማይ አባትን ልጆች የጌታ የመሰብሰብ ስራ ለሚያፋጥኑ ብርሀን ነው።

ስትጸልዩ እና ሌሎችን ስታገለግሉ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆናችሁ ያላችሁ እውቀት ያድጋል። በምንም አይነት መልኩ ታማኝ ባትሆኑ እንደሚያዝንባችሁ ይበልጥ ታውቃላችሁ። ለእግዚአብሔር እና ለሌሎች ቃላችሁን ለመጠበቅ በይበልጥ ጽኑ ትሆናላችሁ። የራሳችሁ ያልሆነን ነግር ስለ መውሰድ የበለጠ ትገነዘባላችሁ። ለአሰሪዎቻችሁ የበለጠ ታማኝ ትሆናላችሁ። ሰአት አክባሪ እና የተቀበላችሁትን በጌታ የተሰጣችሁን የስራ ድርሻ ሁሉ ለማጠናቀቅ የበለጠ ጽኑ ትሆናላችሁ።

የቤት ለቤት አስተማሪዎች መምጣት አለመምጣታቸው ከማሰብ ይልቅ፣ እናንተ እንድታስተምሯቸው የተጠራችሁት ልጆች የእናንተን ጉብኝት በጉጉት ይጠብቃሉ። ልጆቼ ያንን በረከት ተቀብለዋል። እያደጉ ሲመጡ፣ ጌታን በማገልገል የራሳቸውን መስመር እንዲያበጁ የክህነት ጀግኖቻቸው እረድተዋቸዋል። ያ የተባረከ ምሳሌ አሁን ወደ ሶስተኛ ትውልድ እየተሸጋገረ ነው።

መልእክቴ ስለ ምስጋናም ነው።

ስለ ጸሎታችሁ አመሰግናችኋለሁ። ሁሉም መልስ እንደሌላችሁ በመገንዘብ በጉልበታችሁ ስለምትንበረከኩ አመሰግናችኋለሁ። ምስጋናችሁን ለመግለጽ እና በህይወታችሁ እና ቤተሰባችሁ ላይ በረከቱን እንዲልክ ለሰማዩ እግዚአብሔር ትጸልያላችሁ። ለሌሎች ስለምትሰጡት አገልግሎት እና ለአገልግሎታችሁ እውቅና እንዲሰጥ ስለማይሰማችሁ አመሰግናችኋለሁ።

በዚህ አለም ለአገልግሌታችን ዋጋ የምንፈልግ ከሆነ፣ ታላቅ በረከቶችን እንደምናጣ ጌታ ያስጠነቀቀንን ተቀብለናል። እነዚህን ቃላት ታስታውሳላችሁ፤

“ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፣ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም።

“እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፣ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፣ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።

“አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ፣ ቀኝህ የምትሰራውን ግራህ አይወቅ፤

“ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን፤ እና በስውር የሚያይ አባትህ በግልጥ ይከፍልሃል።”2

ታላቅ ክህነት ተሸካሚ የሆኑት ተምሳሌቶቼ የጀግንነት ብቃት እንዳላቸው በቀላሉ አይገነዘቡም። በእርግጥ፣ እኔ የማደንቃቸው ነገሮች ለማየት የሚቸግራቸው ይመስላል። አባቴ በኒው ጀርዚ የነበረች ትንሽ ቅርንጫፍ ታማኝ ፕሬዘዳንት እንደነበረ ጠቅሼ ነበር። ቀጥሎም የቤተክርስቲያን የሰንበት አጠቃላይ አመራር አባል ነበር። ዛሬ እኔ ስለ እሱ የክህነት አገልግሎት ለማውራት በትህትና ለማውራት እጠነቀቃለሁ፣ ምክንያቱም እሱ ነበር።

የልጅነት ጀግናዬ ለነበረው የባህር ሀይል አባልም ይሄ ይሰራል። ስለ ክህነት አገልግሎቱ ወይም ስላሳካቸው ነገሮች በፍጹም ነግሮኝ አያውቅም። በቃ እሱ ዝምብሎ አገልግሎት ሰጠ። ስለ እሱ ተአማኝነት ከሌሎች ሰማሁ። የማደንቅለትን ባህሪው በራሱ ላይ ያለውን ባህርይ ማየቱን እነኳን፣ እኔ ማወቅ አልቻልኩም።

ሌሎችን በክህነታችሁ መባረክ ለምትፈልጉ የምመክራችሁ እግዚአብሔር ብቻ ስለሚያውቀው ግላዊ ህይወታችሁ ነው።

ለእርሱ ጸልዩ። በህይወታችሁ መልካም ስለሆነው ሁሉ አመስግኑት። እንድታገለግሉ ማንን በመንገዳችሁ እንዳስቀመጠ ጠይቁት። ያንን አገልግሎት እንድትሰጡ እንዲረዳችሁ ተማጸኑት። ይቅር ማለት እንድትችሉ እና ይቅር መባል እንድትችሉ ጸልዩ።

ከሁሉም በላይ፣ ከምትሰጡት አገልግሎት፣ ሌሎች ለዘለአለማዊ ህይውት እንዲበቁ ከመርዳት በላይ እንደሌለ አስታውሱ። ክህነታችንን እንዴት መጠቀም እንዳለብን እግዚአብሔር የማይለወጥ ምሬት ሰቶናል። እሱ የዛ ፍጹም ምሳሌ ነው። በእርሱ ምርጥ የምድራዊ አገልጋዮች ትንሽ ክፍል ውስጥ የምናየው ምሳሌ ነው፤

“እና ጌታም ለሙሴ አለው፤ ሰማያት፣ ብዙ ናቸው፣ እና ለሰው ሊቆጠሩ አይችሉም፤ ለእኔ ግን ይቆጠራሉ፣ የእኔ ናቸውና።

“እና አንድ ምድር እና ሰማይ ሲያልፍ፣ እናም ሌላ ይመጣል፤ እና ለእኔ ስራ ፍጻሜ የለውም፣ ለቃላቶቼም እንዲሁ።

“ስለሆነም፣ ይህ የእኔ ስራ እና ክብር ነው- የሰውን ሟች አለመሆንን እና ዘለአለማዊ ህይወትን ማምጣት።”3

በዚያ ስራ መርዳት አለብን። እያንዳንዳችን ለውጥ ማምጣት እንችላለን። ለእኛ ጊዜ እና ቦታ በኋለኛው ቀን ለፃዲቁ ስራ የተዘጋጀን ነን። እያንዳንዳችን ያንን ስራ የዚህ ምድር ጊዜአቸው ቀደሚ ባደረጉ ሰዎች ምሳሌ ተባርከናል።

ለእዚያ እድል ለመነሳት እርስ በእርስ እንድንረዳዳ ጸሎቴ ነው።

አብ እግዚአብሄር ህያው ነው እና በደምብ እሱን ለማገልገል እንዲረዳችሁ ያላችሁን ጸሎት ይመልሳል። የተሸከማችሁት ክህነት በስራው ውስጥ በእሱ ስም የእግዚአብሔርን ልጆች ለማገልገል በስሙ ለመስራት ሀይል ነው። ለዚህ ስራ ሙሉ ልባችሁን ስትሰጡ፣ ጉልህ ያደርጋችኋል። ቃል እገባላሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማጣቀሻወችን ያሳዩማጣቀሻወችን መደበቅ

    ማስታወሻዎች

    1. ማቴዎስ 5:14–16.

    2. ማቴዎስ 6:1–4.

    3. ሙሴ 1:37–39.