2010–2019 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ
ሚያዝያ 2014


የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ

የናዝሬቱ ኢየሱስ ከሞት የተነሳ አዳኝ እንደሆነ፣ እናም ከእርሱ የትንሳኤ እውነታዎች የሚከተሉትን ሁሉንም እመሰክራለው።

ኢየሱስ ሲሰቃይና መስቀሉ ላይ ሲሞት እንዲሁም አካሉ ህይወት አልባ ሆኖ በመቃብር ውስጥ ሲቀመጥ የእርሱ ሀዋርያቶች የመሸነፍና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ዋጣቸው። አዳኙ ምንም እንኳን ስለሞቱና በኋላ መነሳቱ በተደጋጋሚ ቢናገርም፣ አልገባቸውም ነበር። ይሁን አንጂ፣ የስቅለቱ የጨለማው ከሰአት በአስደሳቹ የትንሳኤው ጠዋት ተከተለ። ነገር ግን ያ ደስታ ደቀመዝሙሮቹ የትንሳኤው የአይን ምስክር በመሆናቸው ምክንያት ብቻ መጣ፣ እንዲሁም የመላዕክቶቹ የተነስቷል እወጃ እራሱ በመጀመሪያ ለመግለፅ የሚከብድ ነበር--- በአጠቃልይ አቻ የለሽ ነበር።

መቅደላዊት ማሪያምና ሌሎች የተወሰኑ አማኝ ሴቶች፣ የጌታ አካል በችኩል ሰንበት ከመድረሱ በፊት በመቃብር ውስጥ ሲቀመጥ የተጀመረውን መቀባባት ለመፈፀም ቅመማቅመሞችንና ዘይቶችን በመያዝ፣ ቀደም ብለው ወደ አዳኙ መቃብር በዛ እሁድ ጠዋት መጡ። በዚህ የጠዋቶች ጠዋት፣ በተከፈተ መቃብር፣ የድንጋዩ መዝጊያ በተንሸራተተውና በሁለት ማላዕክቶች እወጃ ሰላምታን ተቀበሉ፥

“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ?

“ተነስቶአል እንጂ በዚህ የለም፥ በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ፣

“የሰው ልጅ በሀጦአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው እያለ።”1

“ጌታ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።

“ፈጥናችሁም ሂዱና ከሙታን ተነሳ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው።”2

በመላዕክቶቹ እንደተነገራት፣ መቅደላዊት ማሪያም መቃብሩ ውስጥ አየች፣ ነገር ግን በአዕምሮዋ ውስጥ የተመዘገበው ነገር የጌታ አካል እንደሌለ ነበር። ለሐዋርያቶቹ ለመዘገብ ፈጠነች እና ጴጥሮስንና ዮሐንስን አግኝታም እንዲህ አለቻቸው፣ “ጌታን ከመቃብር ወስደውታል፣ ወዴትም እንዳኖሩት አናውቅም።”3 ጴጥሮስና ዮሐንስም ወደ ቦታው በመሮጥ፣ “የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ… በራሱ የነበረውን ጨርቅ… ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደነበር።”4 በማየት በትክክል መቃብሩ ባዶ መሆኑን አረጋገጡ። ዮሐንስ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ የትንሳኤን አስደናቂ መልዕክት መገንዘብ የቻለው። እርሱ፣ “አየም፣ አመነም፣” ሲፅፍ ሌሎቹ ግን ለዛ ነጥብ፣ “[ኢየሱስ] ከሙታን ይነሳ ዘንድ እንዲገባው የሚለውን የመጽሐፉን ቃል ገና አላወቁም ነበር።”5

ጴጥሮስና ዮሐንስ ሄዱ፣ ነገር ግን ማርያም ወደኋላ በሀዘን ቀረች። በዛ ሰአት ውስጥ መላዕክቶቹ ተመልሰው በትህትና ጠየቋት፣ “አንቺ ሴት ስለምን ታለቀሻለሽ? እርስዋም ጌታዬን ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም አለቻቸው።”6 በዛች ቅፅበት ከሞት የተነሳው አዳኝ አሁን ከኋላዋ ቆሞ ተናገረ፣ “አንቺ ሴት ስለም ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ? እርስዋም፣ የአትክልት ጠባቂ መስሎአት፣ ጌታ ሆይ፣ አንተ ወስደኸው እነደ ሆንህ፣ ወዴት እዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው።”7

ሽማግሌ ጄምስ ኢ ታልሜጅ እንደፃፈው፥ “ምንም እንኳን ባታውቀውም፣ለኢየሱስ፣ ለእርሷ ውድ ጌታ፣ ነበር የተናገረችው። ከሕያው ከንፈሮቹ የወጣው አንድ ቃል የእርሷን የሚጎዳ ሀዘን ወደ አስደሳች ደስታ ቀየረው። ‘ኢየሱስም እንደዚ አላት፣ ማርያም ።’ ድምፁ፣ አነጋገሩ፣ ከዚህ ቀደም የሰማችውና የወደደችው ትሁት የሆነው የአነጋገር ዘይቤው ከሰመጠችበት ከተስፋ መቁረጥ ጥልቅ ውስጥ ከፍ አደረጋት። ዞር ብላም ጌታን አየችው። በደስታ በመጓዝ ፣ የፍቅርና የአምልኮት ቃል ብቻ እያወጣች እርሱን ለማቀፍ እጆችዋን ዘረጋች፣ ‘ራቦኒ፣’ ማለትም የኔ ውድ አለቃ ማለት ነው።”8

እናም ስለዚህ ይህች የተባረከች ሴት ትንሳኤ ያደረገውን ክርስቶስ ለማየትና ከእርሱም ጋር ለማውራት የመጀመሪያዋ የሟች ስጋ የለበሰች ሰው ሆነች። ከዛ በኋላ በዛው ቀን ለጴጥሮስ በኢየሩሳሌም ውስጥ ወይም አቅራቢያ ተገለፀለት፤9 ለሁለቱ ደቀ መዛሙራት ወደ ኤማሁስ፤10 መንገድ ወደሚያመራው ላይ፤ እናም በማታ ለ10 ሐዋርያቶችና ለሌሎች፣ በመሀከላቸው በድንገት በመገለፅ፣ እንዲህ በማለት፣ “እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ስጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ።”11 ከዛ በኋላ የበለጠ ሊያሳምናቸው “እነረርሱም ከደስታ የተነሳ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ፣”12 የተጠበሰ አሳና የመር ወለላ በፊታቸው በላ።13 ከዛ በኋላ አሰለጠናቸው፣ “በኢየሩሳሌምም፣ በይሁዳም ሁሉ፣ በሰማርያም፣ እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”14

ከነዚህ በኢየሩሳሌም ውስጥ ከተረጋገጡ ምስክሮች ባሻገር፣ የማይነፃፀረው ከሞት የተነሳው ጌታ ለጥንታውያን የምዕራብ ንፍቀ-ክበብ ህዝቦች የሰጠው አገልግት አለን። በተትረፈረፈው ምድር ላይ፣ ከሰማይ ወረደና 2500 የሚጠጉትን የተሰበሰቡ ህዝቦች ሁሉም አንድ በአንድ መጥተው እስከሚያልቁ ድረስ እጆቻቸውን ወደ ጎኑ እንዲልኩና በእጆቹና በእግሮቹ ላይ ያለውን የሚስማር አሻራ እንዲነኩት ጋበዛቸው።15

“እናም ሁሉም በሄዱ እናም ለየራሳቸውም በመሰከሩ ጊዜ በአንድነት እንዲህ ሲሉ ጮሁ፥

ሆሳዕና! የኃያሉ አምላካችን ስም የተባረከ ይሁን! እናም በኢየሱስ እግር ስር ወደቁ፣ እናም አመለኩት።”16

የክርስቶስ ትንሳኤ የእርሱ ኑሮ እራሱን የቻለና ዘላለማዊ እንደሆነ ያሳያል። ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው፤ እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።”17

“ነፍሴን ደግሞ አነሳት ዘንድ አኖራታለሁና፣ ስለዚህ አብ ይወደኛል።

“እኔ በፈቃዴ አኖራታለው እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ስልጣን አለኝ፣ ደግሞም ላነሳት ስልጣን አለኝ።”18

አዳኙ ለሕይወት በምግብ ላይ ወይም በውሀ ላይ ወይም በመተንፈሻ አየር ላይ ወይም በማንኛውም በሌላ ንጥረ-ነገር፣ ኃይል፣ ወይም ሰው ላይ ጥገኛ አይደለም። እንደ ሁለቱም ያህዌህና መሲህ፣ ያለና የሚኖር ታላቁ እኔ ነኝ፣ በራሱ የሚኖርም አምላክ ነው።19 በቀላሉ እርሱ ነው፣ እንዲሁም ለዘላለም ይሆናል።

በሀጢያት ክፍያውና በትንሳኤው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሁልንም አይነት ውድቀት አሸንፏል። አካላዊ ሞት ጊዜያዊ ይሆናል፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ሞት እራሱ መጨረሻ አለው፣ ሁሉም ለመፈረድ ወደ እግዚአብሔር ፊት፣ ቢያንስ ለጊዜው፣ ይመለሳሉ። በእርሱ ሁሉንም ነገሮች የማሸነፍ ኃይልና ለእኛ የዘለአለም ሕይወት መስጠት የመጨረሻ እምነትና መተማመን ሊኖረን ይችላል።

“ሞት በሰው በኩል ስለመጣ፣ ትስሳኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና።

“ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።”20

ሽማግሌ ኒል ኤ ማክስዌል ባሏቸውም፥ “ክርስቶስ ሞት ላይ የተቀዳጀው ድል የሰዎችን ከባድ ውስብስብ አስቁሞታል። አሁን ግላዊ ከባድ ውስብስቦች ብቻ ነው ያሉት፣ እናም ከዚህም እራሱ ከጠቅላላ መጥፋት ያዳነንን የእርሱን ትምህርቶች በመከተል መዳን እንችላለን።”21

የፍትህን አስገዳጂነት በማሟላት፣ ክርስቶስ አሁን በፍትህ ቦታ ላይ ይገኛል፤ ወይም እርሱ ፍቅር እንደሆነ ሁሉ፣ ፍትህ ነው ማለት እንችል ይሆናል።22 እንዲሁም፣ ፍፁም ፍትህ አምላክ ከመሆኑም ባሻገር፣ ፍፁም መሐሪ አምላክ ነው።23 ስለዚህም፣ አዳኙ ሁሉንም ነገር ትክክል አደረገው። በሟች ሕይወት ውስጥ፣ እንዲሁም ሞት፣ ያለ ኢፍታዊነት ዘላቂ አይደለም፣ ማክንያቱም እርሱ ሕይወትን በዳግም መልሷልና። ምንም አይነት ቁስለት፣ አካለ-ጎዶሎነት፣ ክህደት፣ ወይም ትንኮሳ በመጨረሻ ላይ በእርሱ ፍትህና ምህረት ምክንያት ሳይከፈል አይቀርም።

በተመሳሳይ ገለፃ፣ ሁላችንም ለሕይወቶቻቸን፣ ለምርጫዎቻችን፣ እናም ለተግባሮቻችን፣ እንዲሁም ለአስተሳሰቦቻችን ለእርሱ ተጠያቂነት አለብን። ከውድቀቱም ሁላችንንም ስላዳነ፣ ሕይወቶቻችን በእውን የእርሱ ናቸው። እርሱም አንዲህ በማለት አወጀ፥

“እነሆ ወንጌልን ሰጥቻችኋለሁ እናም ለእናንተ የሰጠኋችሁ ወንጌሌም ይህ ነው ወደ አለም የመጣሁት የአባቴን ፈቃድ ለመፈፀም ነው ምክንያቱም አባቴ ልኮኛልና።

“አባቴም በመስቀል እሰቀል ዘንድ ልኮኛል እናም ከዚያም በኋላ በመስቀል ላይ ተሰቀልኩ እንዲሁ ሰዎችን ሁሉ ወደ ራሴ አመጣ ዘንድ እኔ ለሰዎች እንደተሰቀልኩ በአብ አማካኝነት ይነሱ ዘንድ በእኔ ፊት ለመቆም ይችሉ ዘንድ መልካምም ይሁኑ መጥፎ በስራቸው እንዲፈረድባቸው እነርሱን ለማሳመን በመስቀሉ ላይ ተሰቀልኩኝ።”24

የትንሳኤን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የናዝሬቱ ኢየሱስን እውነተኛ ማንነትና ታላቁን የሕይወት ፍልስፍና ውድድሮችንና ጥያቄዎችን በመቅረፍ ረገድ ያበረከተውን አስተዋፅኦ ለአንዴ አስቡት። ኢየሱስ በእውነት ትንሳኤ ካደረገ፣ እርሱ መለኮታዊ ፍጡር መሆኑ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይከተለዋል። ማንም ተራ ሟች የሆነ ሰው ከሞት በኋላ ወደ ሕይወት እነደገና ለመምጣት በራሱ ኃይል የለውም። እርሱ ትንሳኤ ስላደረገ፣ ኢየሱስ አናፂ፣ አስተማሪ፣ ራቢ፣ ወይም ነቢይ ብቻ አልነበረም። ምክንያቱም እርሱ ትንሳኤ ስላደረገ፣ ኢየሱስ አምላክ መሆን ነበረበት፣ እንዲሁም የአብ አንድያ ልጅ።

ስለዚህ፣ ያስተማረው ሁሉ እውነት ነው፤ እግዚአብሔር አይዋሽም።25

ስለዚህ፣ እርሱ እንዳለው፣ የምድር ፈጣሪ ነበር። 26

ስለዚህ፣ እርሱ እንዳስተማረው፣ መንግስተ ሰማይና ሲዞል እውን ናቸው።27

ስለዚህ፣ ከእርሱ ሞት በኋላ የጎበኘው የመንፈስ አለም አለ።28

ስለዚህ፣ እርሱ በድጋሚ ይመጣል፣29 እና “በግል በምድር ላይ ነግሳል።30

ስለዚህ፣ ለሁሉም ትንሳኤና የመጨረሻ ፍርድ አለ።31

የክርስቶስን የትንሳኤ እውንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ አንድያ ልጁን ለአለም ቤዛነት ስለሰጠው ስለ አባት እግዚአብሔር ሙሉ ኃያልነት፣ ሁሉን አዋቂነት፣ እና ሩህሩህነት ያሉት መጠራጠሮች ምክንያት አልባ ናቸው። ስለ ሕይወት ትርጉምና አላማ ያሉት መጠራጠሮች መሰረት አልባ ናቸው። በእርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ደህንነት የሚመጣበት ብቸኛው ስም ወይም መንገድ ነው። የክርስቶስ ፀጋ እውን ነው፣ ሁለቱንም ይቅርተኝነትንና ማንፃትን ንስሀ ለሚገባው ሀጢያተኛ በጋራ በመስጠት። እምነት በእውነት ከአስተሳሰብ ወይም ከስነ-ልቦናዊ ፈጠራ በላይ ነው። የመጨረሻና አለም አቀፋዊ እውነታ አለ፣ እንም በእርሱ እንደተማረው እውነታ ላይ የሚመሰረትና የማይቀየር የግብረ-ገብ አቋም አለ።

የእርሱን ማንኛውንም አይነት ህግና ትዕዛዛት የመጣስ ንስሀ አስቸኳይ ጉዳይ ነው። የአዳኙ ታምራቶች እውን ናቸው፣ የእርሱ ደቀመዝሙሮች ልክ እንደ እርሱ ተመሳሳይ ነገሮችን፣ እንዲሁም ታላላቅ ስራዎችን ያደርጉ ዘንድ እንደሰጣቸው ቃል-ኪዳን እውን መሆን ሁሉ።32 የእርሱ ክህነት ካለምንም ጥርጥር “ወንጌልን የሚያስተዳድር እናም የእግዚአብሔርን እውቀት ቁልፍ ጭምሮ፣ የንጉስ ጋዛቱን ሚስጥራት ቁልፍ የሚይዝ። ስለዚህም፣ በዛ ስነ-ስርአቶች ውስጥ፣ የመለኮታዊ ኃይል የሚገለፅበት።”33 ትክክለኛ ኃይል ነው። የክርስቶስን የትንሳኤ እወንነት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ምንም እንኳን የቆዳ ትሎች ሰውነታችንን ቢያፈራርሱትም ቅሉ፣ ሞት የእኛ መጨረሻ አይደለም። ነገር ግን በስጋችን እግዚአብሔርን እናየዋለን።34

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን ስለ ሮበርት ብላችፎርድ ከ 100 አመታት በፊት እግዚአብሔርና ጎረቤት በሚለው መፅሀፉ ውስጥ በኃይል ሲያጠቃ የነበረው የክርስትያን እምነቶችን ለምሳሌ እንደ እግዚአብሔር፣ ክርስቶስ፣ ፀሎት፣ እና አለሟችነት የሚሉትን ስለመቀበሉ ተናገሩ። እርሱ በድፍረት እውነታውን እንዲህ ሲል አሰቀመጠ፣ ‘ሁሉንም ሙሉ በሙሉና በቁርጠኝነት ማንም ክርስቲያን ምንም ታላቅና ችሎታ ያለው ቢሆንም እንኳን ክርክሬን እንደማይመልስልኝ ወይም አቋሜን እንደማይወዘውዝ ለማረጋገጥ የወጣሁትን ነገሮች ማረጋገጤን እናገራለው።’ እውነተኛ እውቀት ማግኘት አይቻልም በሚል ግድግዳዎች እራሱን ከበበ። ከዛ የሚያስገርም ነገር ተከሰተ። የእርሱ ግድግዳዎች በድንገት ወደ አፈር ተመለሱ። ወደ ተቃወመውና ወዳፌዘበት እምነት በዝግታ ሲመለስ ተሰማው። በባህሪው ይህንን ታላቅ ለውጥ ምንድን ነው መንስኤ ያደረገው? ሚስቱ ሞታለች። በተሰበረ ልብ፣ ሟች የሆነው እርሷነቷ ወደተኛበት ክፍል ገባ። በጣም ይወድ የነበረውን ፊት በድጋሚ ተመለከተ። ከክፍሉ ሲወጣም፣ ለጓደኛው እንደዚህ አለ፥ እርሷ ነች፣ እናም ግን እርሷ አይደለችም። ሁሉም ነገር ተቀየረ። በፊት እዛ የነበረው ነገር ተወሰደ። አንድ አይነት አይደለችም። ነፍስ ካልሆን ምን ሊሄድ ይችላል?’”35

ጌታ በእውን ሞቶ እንደገና ተነስቷልን? አዎ። “የሐይማኖታችን መሰረታዊ መርህዎች የሐዋርያቶችና የነብያቶች ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሞተ፣ እንደተቀበረ፣ እና በሶስተኛውም ቀን እንደተነሳ፣ እንዲሁም ወደ ሰማይ እንዳረገ የሚመሰክሩት ናቸው፤ እናም ሁሉም ስለኛ ሐይማኖት የሚመለከቱ ሌላ ነገሮች በሙሉ የዛ አካል ቅጥያዎች ብቻ ናቸው።”36

የተተነበየለት የኢየሱስ ልደት ሲቃረብ፣ ምንም እንኳን ብዙዎች ቢጠራጠሩም፣ ከጥንት ኔፊያውያንና ላማናውያን መካከል ያመኑ ነበሩ። ከጊዜ በኋላ የውልደቱ ምልክት ደረሰ-ቀንና ማታ እንዲሁም ቀን ካለ ምንም ጨለማ-ከዛ ሁሉም አወቁ። አሁንም እንኳን፣ በክርስቶስ ትክክለኛ ትንሳኤ የተወሰኑት ያምናሉ፣ እና ብዙዎች ይጠራጠራሉ ወይም አያምኑም።37 ነገር ግን የተወሰኑት ያውቃሉ። ከጊዜ በኋላ፣ ሁሉም ያያል እንዲሁም ያውቃል፤ በእርግጥ፣ “በእርሱ ፊት ሁሉም ጉልበት ይንበረከካል፣ እናም ሁሉም ምላስ ይናዘዛል።”38

እስከዛ ድረስ፣ ብዙ የአዳኙን የትንሳኤ ምስክሮችን፣ ልምዳቸውና ምስክርነታቸው በአዲስ-ኪዳን ውስጥ የሚገኙውን፣ ከሌሎቹ መካከል፣ የጴጥሮስንና የአስራሁለቱ ጓደኞቹ እና ውድ፣ ንፁ የመቅደላሚት ማርያም ምስክርነቶችን አምናለው። በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኙትን ምስክርነቶች አምናለው፣ የሐዋርው ኔፊ ስማቸው ካልተጠቀሰ በተትረፈረፈው ምድር ውስጥ ከነበሩ ህዝቦች ጋር፣ ከሌሎቹ መካከል። እንዲሁም የዮሴፍ ስሚዝንና የሲድኒ ሪገደንን፣ ከብዙ ምስክርነት በኋላ የዚህ የመጨረሻው ዘመን ታላቁ ምስክር ብለው ያወጁትን፣ “በሕይወት አለ! እኛ አይተንዋልና”39 የሚለውን ምስክርነት አምናለው። በእርሱ ሁሉንም በሚያይ አይን ስር በመሆን፣ እኔ እራሴ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከሞት የተነሳ አዳኝ እንደሆነ እንደ ምስክር እቆማለው። ከእርሱ የትንሳኤ እውነታዎች የሚከተሉትን ሁሉንም እመሰክራለው። የዛን ተመሳሳይ ምስክርነት ጥብቅ አቋምንና መፅናናትን ተቀበሉ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እፀልያለው፣ አሜን።