2010–2019 (እ.አ.አ)
ምስክሩ
ሚያዝያ 2014


ምስክሩ

በጣም ለማወቅ የሚጠቅማችሁን እነዛን እውነቶች ላካፍላችሁ እመኛለው።

የጦርነት ወይም የብዥታ ጊዜያቶች ትኩረታችንን በእውነት ትርጉማ ባላቸው ነገሮች ላይ ስል የማድረግ መንገድ አለው።

ሁለተኛው የአለም ጦርነት ለኔ ትልቁ የመንፈስ ግራ መጋባት ጊዜ ነበር። እየተዳፋ ባለ ምስክርነት ብቻና ለበለጠ ነገር አስፈላጊነት እየተሰማኝ፣ በብሪግሀም ከተማ፣ ዩታ፣ የሚገኘውን በቤቴን ተውኩኝ። በኢ ሺማ ደሴት፣ የኦኪናዋ፣ ጃፓን ደቡባዊ ክፍል ላይ ተመድቤ በነርኩበት ሰአት፣ ከመጠራጠርና ከብዥታ ጋር ታገልኩኝ። የወንጌልን የግል ምስክርነት ለማግኘት ፈለኩኝ። ማወቅ ፈለኩኝ!

በአንድ እንቅልፍ አልባ ምሽት ወቅት፣ ድንኳኔን ትቼ ግድግዳ ለመስራት አሸዋ በተሞሉና በተደራረቡ ባለ 50 ጋሎን የነዳጅ ሲሊንደሮች የመሬት ውስጥ መጠለያ ውስጥ ገባሁ። ጣሪያ አልነበረም፣ እናም ለዛ በዝግታ ገባው፣ በኮከብ የተሞላችውን ሰማይ ቀና ብዬ አየሁ፣ እናም ለመፀለይ ተንበረከኩኝ።

ቢያንሰ የዐረፍተ-ነገር አጋማሽ ላይ ተከሰተ። የተከሰተውን ነገር ለናንተ ለመግለፅ ብሞክር እንኳን አልችልም። መግለፅ ከምችለው ኃይል በላይ ነው፣ ነገር ግን በዛ ምሽት ከ65 አመታት በፊት ግልፅ እንደነበረ ሁሉ ዛሬም ግልፅ ነው። በጣም የራስ፣ በጣም የግል መገለፅ እንደሆነ አወቅኩኝ። በመጨረሻም ለራሴ አወቅኩኝ። ለእኔ ስለተሰጠኝ፣ በእርግጠኝነት አውቅኩኝ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ፣ በዝግታ ከመሬት ውስጥ መጠለያ ውስጥ ወጣውና ወደ አልጋዬ ሄድኩኝ። ቀሪውን ምሽት ደስታና አድናቆት እየተሰማኝ አሳለፈኩኝ።

የሆነ ለየት ያልኩኝ ሰው ነኝ ብዬ ከማሰብ ባሻግር፣ እንደዚህ አይነት ነገር ወደኔ ከመጣ፣ ለማንም ሰው መምጣታ እንደሚችል አሰብኩኝ። ያንን አሁንም አምናለው። በተከተሉት አመታት ውስጥ፣ እንደዚህ አይነት ልምድ በአንድ ወቅት የምንከተለው ብርሀንና የምንሸከመው ክብደት እንደሆን ለመረዳት ችያለው።

90 ለሚጠጉ የሕይወት አመታትና ከ50 በላይ ለሚሆኑ እንደ አጠቃላይ ባለስልጣን አመታት ስለ ተማርኳቸውና ስለ ተለማመድኳቸው ነገሮች፣ በጣም ለማወቅ የሚጠቅማችሁን እነዛን እውነቶች ላካፍላችሁ እመኛለው። ብዙዎቹ ለማወቅ የቻልኳቸው ነገሮች ማስተማር ከማንችላቸው ነገሮች ነገር ግን መማር ከምንችላቸው ዝርዝር ውስጥ ይወድቃሉ።

እንደ በጣም ጠቃሚ ነገሮች፣ የዘላለም ጥቅም ያለው እውቀት በግል ፀሎትና በማሰላሰል አማካኝነት ብቻ ይመጣል። እነዚህ፣ ከፆምና መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጋር አንድ ላይ በመሆን፣ ግንዛቤዎችንና ራዕዮችን እናም የመንፈስ ቅዱስ ሹክሹክታዎችን ይጋብዛሉ። መርህ በመርህ ላይ በምንማርበት ጊዜ ከላይ የሚመጣ ምሪት ያቀርብልናል።

ራዕዮቹ “በዚህ ሕይወት ውስጥ በጥረት የምናገኘው ምንኛውም አይነት የጉብዝና መርህ፣ በትንሳኤ ጊዜ አብሮን እንደሚነሳ” እንዲሁን “እውቀትና ጉብዝና በትጋትና በታዛዥነት አማካኝነት እንደሚገኙ”(ት. እናቃ. 130:18–19) ቃል ይገባሉ።

ለማወቅ የቻልኩት አንድ ዘላለማዊ እውነታ እግዚአብሔር ህያው መሆኑን ነው። አባታችን ነው። የእርሱ ልጆች ነን። “በዘላለም አባት፣ በእግዚአብሔር፣ እናም በልጁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እናም በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን” (የእምነት አንቀፆች 1፥1)።

ከሁሉም ሊጠቀማቸው ይችል ከነበራቸው መአረጎች፣ “አባት” ተብሎ መጠራቱን መረጠ። አዳኙ አዘዘ፣ “ስለዚህ እነዲህ ብላችሁ ፀልዩ፣ በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ” (3 ኔፊ 13፥9፤ እንዲሁም ማቴዎስ 6፥9 ተመልከቱ)። በዚህ ሕይወት ውስጥ የበለጠ የሚጠቅመውን ነገር እየተረዳን ስንመጣ “አባት” የሚለው የስሙን አጠቃቀም ሁሉም የሚማሩት ትምህርት ይሆናል።

ክህነት የተቀደሰ እድል ነው፣ አማኝነት ላይ በመመርኮዝ፣ የዘላለም በረከት መሆን ይችላል። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ካሉት የሁሉም እንቅስቃሴዎች መሰረታዊ መጨረሻ አንድ ወንድ ከሚስቱና ከልጃቸው ጋር በቤት ውስጥ ደስተኛ መሆን መቻላቸው ነው።

ያላገቡት ወይም ልጆች የማይኖራቸው ሰዎች ከሚሹት የዘላላም በረከቶች አልተወገዱም ነገር ግን፣ ለአሁኑ፣ ከመድረሻቸው ውጪ ሆኖ ነው ያለው። በረከቶች ሁልጊዜ እንዴትና መቼ እራሳቸውን እንደሚያቀርቡ አናውቅም፣ ነገር ግን ዘላለማዊ የመጨመር ቃል-ኪዳን ቅዱስ ቃል-ኪዳኖችን ለሚገባና ለሚጠብቅ ለማንኛውም አማኝ ግለሰብ አይካድም።

የእናንተ የሚስጥር መሻቶችና ለቅሷማ ተማፅኖዎች የአባትንና የልጁን የሁለቱንም ልብ ይነካል። ሕይወታችሁ ሙሉና ምንም አስፈላጊ የሆነ በረከት ከእናንተ እንደማይጠፋ ከእነርሱ ግላዊ ማረጋገጫዎች ይሰጧችኋል።

እንደ የጌታ አገልጋይ፣ በተሸምኩበት ክፍል ውስጥ በመተግበር፣ በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ላላችሁት በሰአቱ በናንተ ላይ የማያርፍ ለድህንነታችሁና ለክብራችሁ የሚያስፈልግ ምንም ነገር እንደማይኖር ቃል እሰጣችኋለው። አሁን ባዶ የሆኑ ክንዶች የሞላሉ፣ በተሰበሩ ህልሞችና መሻት አሁን የሚያሙ ልቦች ይፈወሳሉ።

ሌላኛው ላውቀው የቻልኩት እውነታ መንፈስ ቅዱስ እውን መሆኑን ነው። ከአምላኮች ዕራስ ሶስተኛው አባል ነው። ተልዕኮው እውነትንና ጽድቅን መመስከር ነው። የሰላምና የተስፋ ስሜቶችን ጨምሮ እራሱን በብዙ መንገዶች ይገልፃል። እንዲሁም መፅናናትን፣ ምሪትንና እርምትን ሲያስፈልጉ ያመጣል። በሕይወታችን ሙሉ የመንፈስ ቅዱስ ጓደኝነት የሚጠበቀው በጽድቅ አኗኗራችን ነው።

የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሚሰጠው በወንጌል ስነ-ስረአት አማካኝነት ነው። ስልጣን ያለው ሰው እጆቹን በቤተክርስቲያኑ አዲስ አባል ላይ በመጫን እንደነዚህ አይነቱን ቃሎች ይናገራል፥ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበል።”

ይህ ስነ-ስርአት በራሱ ማየት በሚቻል መልኩ አይቀይረንም፣ ነገር ግን አነሳሾችን የምናዳምጥና የምንከተል ከሆነ፣ የመንፈስ ቅዱስን በረከቶች እንቀበላለን። እያንዳንዱ የሰማይ አባታችን ወንድና ሴት ልጆች የሞሮኒን ቃል-ኪዳን እውንነት ማወቅ ይችላሉ፥ “የሁሉንም ነገር እውነታ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ታውቁታላችሁ” (ሞሮኒ 10፥5)።

በሕይወቴ ያገኘሁት ከሰማይ የመጣ እውነታ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነቴ ነው።

ወሳኙና ለምናደርገው ሁሉ መሰረት የሆነው፣ በመላ ራዕዮች መልህቅ በሆነው፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የምናገለግልበት ስልጣን በሆነው፣ የጌታ ስም ነው። በእያንዳንዱ የሚቀርብ ፀሎት፣ በትንሽ ልጆች እንኳን፣ በኢየሱስ ክርሰቶስ ስም ነው የሚያልቀው። እያንዳንዱ በረከቶች፣ እያንዳንዱ ስነ-ስርአቶች፣ እያንዳንዱ ሹመቶች፣ እያንዳንዱ መደበኛ ተግባሮች የሚከናወኑት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው። የእርሱ ቤተክርስቲያን ነው፣ ለእረሱ ነው የሚጠራው--የኋለኛው ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን (ት. እና ቃ. 115፥4)።

በመጽሐፈ ሞርሞን ውሰጥ ታላቅ አለ ኔፋውያን “ወደ አብ [በጌታ] ስም እየፀለዩ ነበር።”

“ምን እንድሰጣችሁ ትፈልጋላችሁ?

“እናም እንዲህ አሉት፥ ይህንን ቤተክርስቲያን የምንጠራበትን ስም እንድትነግረን እንፈልጋለን፤ ምክንያቱም ይህንን በተመለከተ በህዝቡ መካከል ፀብ አለና።

“እናም ጌታም እንዲህም አላቸው፥ እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ህዝቡ ስለዚህ ነገር ለምን ያጉረመርማል እንዲሁም ይጣላል?

“ስሜ የሆነውን፣ የክርስቶስን ስም መልበስ እንዳለባቸው ቅዱሳን መጻሕፍትን አላነበቡምን? በዚህ ስም በመጨረሻው ዘመን ትጠሩበታላችሁና፤

“እናም ስሜን በራሱ ላይ የወሰደ፣ እናም እስከመጨረሻው በዚህ የፀና በመጨረሻው ዘመን እርሱ ይድናል።…

“ስለዚህ፣ ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ በስሜ አድርጉት፤ ስለዚህ ቤተክርስቲያኗን በስሜ ጥሯት፤ እናም ወደ አብ በስሜ ፀልዩ እርሱም ለእኔም ሲል ቤተክረስቲያኗን ይባርካታል” (3 ኔፊ 27፥2–7)።

የእርሱ ስም ነው፣ ኢየሱስ ክረስቶስ፣ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” (የሐዋርያት ስራ 4፥12)።

ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፥ በቤተክርስቲያን ውስጥ ማን እንደሆነ እናውቃለን። እርሱ የአባት አንድያ ልጅ ነው። እርሱ ማለት የተገደለውና እንደገና የሚኖረው ማለት ነው። ከአባት ጋር አማላጃችን ነው። “አስታውሱ፣ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በክርስቶስ፣ አዳኝ በሆነው በአለቱ መሰረታችሁን መገንባት እንዳለባችሁ፤ (ሔለማን 5፥12)። በሕይወት መአበል ውስጥ እኛንና ቤተሰቦቻችንን የሚይዝና የሚጠብቅ መልህቃችን ነው።

በእያንዳንዱ እሁድ በአለም ዙሪያ የማንም ዜግነትና ቋንቋ ተናጋሪዎች በሚሰበሰቡበት ቦታ፣ ቅዱስ ቁርባኑ በተመሳሳይ ቃላቶች ነው የሚበረከው። የክርስቶስን ስም በራሳችን ላይ ወስደናል እናም ሁሌም እናስታውሰዋለን። ያ በላያችን ላይ ታትሟል።

ነብዩ ኔፊ እንዲህ አወጀ፣ “ስለክርስቶስ እንናገራለን፣ በክርስቶስ እንደሰታለን፣ ስለክርስቶስ እንሰብካለን፣ ስለክርስቶስ ትንቢት እንናገራለን፣ እናም በትንታችን መሰረት እንፅፋለን፣ ስለዚህ ልጆቻችን ለኃጢአታቸው ስርየት ትኛውን መንገድ መመልከት እንዳለባቸው ያውቁ ዘንድ” (2 ኔፊ 25፥26)።

እያንዳንዳችን ወደራሳችን የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የግል ምስክርነት መምጣት አለብን። ከዛ ያንን ምስክርነት ከቤተሰባችንና ከሌሎች ጋር እናካፍላለን።

በዚህ ሁሉም ውስጥ፣ የጌታን ስራ በግሉ ለማደናቀፍ የሚሻ ተቃዋሚ እንዳለ እናስታው። የምንከተለውን መምረጥ አለብን። የእኛ ጥበቃ በአማኝነት ከአዳኙ ጎን እንደምንቆይ በማረጋገጥ በግል እርሱን ለመከተል እንደመምረጥ ቀላል ነው።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ ዮሐንስ ለአዳኙና ለትምህርቶቹ እራሳቸውን ለማዘጋጀት ያልቻሉ የተወሰኑ እንደነበሩ መዘገበ፣ እናም “ከዚህም የተነሳ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ወደኋላ ተመለሱ፣ ወደፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።

“ኢየሱስም ለአስራሁለቱ፣ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ።

“ስምዖን ጴጥሮስ፣ ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ።

“እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም” (ዮሐንስ 6፥66–69)።

ጴጥሮስ በያንዳንዱ የአዳኙ ተከታዮች መማር የሚቻለውን ነገር አገኘ። ለኢየሱስ ክርስቶስ በአማኝነት መስዋዕት ለመሆን፣ እንደ አዳኛችን እንቀበለዋለን እናም ትምህርቶቹን ለመኖር ባለን ኃይል እንሰራለን።

ከዛ ሁሉ ከኖርኩባቸውና ካስተማርኩባቸው እንዲሁም ካገለገልኩባቸው አመታት በኋላ፣ በአለም ዙሪያ ከተጓዝኳቸው ከሚሊዮኖች ማይሎች በኋላ፣ ልምድ ከቀሰምኩባቸው ነገሮች ሁሉ፣ ማካፈል የምችለው አንድ ታላቅ እውነታ አለ። የእኔ የአዳኙ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነቴ ነው።

ዮሴፍ ስሚዝና ሲድኒ ሪግደን ከቅዱስ ተሞክሮ በኋላ የሚከተለውን መዘገቡ፥

“እናም አሁን፣ ስለ እርሱ ከተሰጡት ከብዙ ምስክርነቶች በኋላ፣ ይህ ስለ እርሱ የምንሰጠው፣ የሁሉም መጨረሻ ምስክርነት ነው፥ እርሱ ሕያው ነው!

“እኛ አይተነዋልና” (ት. እና ቃ. 76፥22–23)።

ቃላቸው ቃሎቼ ናቸው።

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለው እንዲሁም አውቃለው። እርሱ የአባት አንድያ ልጁ ነው፣ እናም “በእርሱ፣ እናም በእርሱ ስር፣ እናም የእርሱ፣ አለሞች እየተፈጠሩ ነው እንዲሁም ነበር፣ እናም በውስጡ ያሉት ህዝቦች የእግዛብሔር ወንድና ሴት ልጆች ናቸው” (ት. እና ቃ. 76፥24)።

አዳኙ ሕያው እንደሆነ ምስክርነቴን እሰጣለው። ጌታን አውቀዋለው። የእርሱ ምስክር ነኝ። ለሁሉም የሰማይ አባት ልጆች የከፈለውን ታላቅ መሰዋትነትና ያለውን ዘላለማዊ ፍቅር አውቃለው። ለየት ያለውን ምስክርነቴን በሙሉ ትህትናዬ ነገር ግን በፍፁም እርግጠኛነት እመሰክራለው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።