2010–2019 (እ.አ.አ)
እንድገና እስከምንገናኝ ድረስ
ሚያዝያ 2014


እንድገና እስከምንገናኝ ድረስ

የየቀኑ ስራዎቻችንን ስናከናውንም ባለፉት ሁለት ቀናት የነበረን የመንፈስ ስሜት ከእኛ ጋር ይቆይ፣ እናም የጌታን ስራ ሁልጊዜም እያደረግን እንገኝ።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ይህ እንዴት አስደናቂ ጉባኤ ነበር። ያነጋገሩን ወንዶች እና ሴቶች ቃላት ስናዳምጥ በመንፈስ ተመግበናል። መዘምራኖቹ አስደናቂ ነበሩ፣ መልእክቶችም በመንፈስ ቅዱስ መነሳሻ ስር የተዘጋጁና የተቀረቡ ነበሩ፣ እናም ጸሎቶቹም ወደሰማይ እንድንቀርብ አድርገውናል። አብረን ስንሳተፍም በሁሉም መንገዶች ከፍ ከፍ ብለላን።

የጉባኤ መልእክቶች ኤንሳይን እና ሊያሆና መፅሔቶች ውስጥ በሚታተሙበት ጊዜ እነዚህን ለማንበብ ጊዜ እንደምናሳልፍ ተስፋ አለኝ፤ ምክንያቱም እነዚህ የእኛ የጥንቃቄ ግምገማና ጥናት ያስፈልጋቸዋልና።

በዚህ ጉባኤ ከአገልግሎት ለተለቀቁት ወንድሞች እና እህቶች ከልብ የሚመጣውን ምስጋና ሳቀርብ እናንተ ከእኔ ጋር እንደምታቀርቡት አውቃለሁ። በደንብ አገልግለዋል እናም በጌታ ስራም ታላቅ ተሳታፊዎች ነበሩ።

እጆችን በማንሳት፣ ለአዲስ ሀላፊነት የተጠሩትን ወንድሞችንም ደግፈናል። እነርሱን እንኳን ደህና መጣችሁ እንላለን እናም በጌታ ስራ ከእነርሱ ጋር አብረን ለማገልገል ጉጉት እንዳለን እንዲያውቁም እንፈልጋቸዋለን።

ያዳመጥናቸውን መልእክቶች ስናሰላስልባቸው፣ ከዚህ በፊት ካደረግነው በተሻለ ለማድረግ ውሳኔ ይኑረን። እምነታቸው እና መሰረታዊ መርኋቸው ከእኛ ጋር አንድ ላልሆኑት ደግ እና አፍቃሪ እንሁን። አዳኝ ወደዚህች ምድር ለሁሉም ወንዶችና ሴቶች የፍቅር እና በጎ ፈቃድን መልእክት ይዚ ነው የመጣው። ሁልጊዜም የእርሱን ምሳሌ እንከተል።

በአለም ብዙ አስቸጋሪ ፈተናዎች አሁን ያጋጥሙናል፣ ነገር ግን የሰማይ አባታችን ስለእኛ እንደሚያስብ ማረጋገጫ እሰጣችኋለሁ። እምነታችንን በእርሱ ላይ ስንጥል እርሱም ይመራናል እናም ይባርከናል እናም ምንም ችግሮች ቢያጋጥሙንም እርሱ ይረዳናል።

የሰማይ በረከቶች ከእያንዳንዳችን ጋር ይሁኑ። ቤቶቻችን በፍቅር እና ትህትና እናም በጌታ መንፈስ ይሞሉ። በጠላት ጥቃት ጊዜ እንዲጠብቀን የወንጌል ስክራችንን በየጊዜው እንመግብ። የየቀኑ ስራዎቻችንን ስናከናውንም ባለፉት ሁለት ቀናት የነበረን የመንፈስ ስሜት ከእኛ ጋር ይቆይ፣ እናም የጌታን ስራ ሁልጊዜም እያደረግን እንገኝ።

ይህ ስራ እውነት እንደሆነ፣ አዳኝ ህያው እንደሆነ፣ እና በዚህች ምድር ላይ ቤተክርስቲያኑን እንደሚመራና እንደሚያስተዳድር እመሰክራለሁ። እግዚአብሔር የዘለአለም አብ ህያው እንደሆነ እና እንደሚያፈቅረን ምስክርነቴን እሰጣችኋለሁ። እርሱም በእርግጥ አባታችን ነው፣ እናም እርሱም ግለሰባዊና እውነተኛ ነው። እርሱ ወደ እኛ ምን ያህል ለመቅረብ ፈቃደኛ እንደሆነ፣ እኛን ለመርዳት ምን ያህል ለማድረግ ፈቃደኛ እንደሆነ፣ እናም ምን ያህል እንደሚያፈቅረን እንረዳ።

ወንድሞቼና እህቶቼ፣ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።፡የእርሱ የሰላም ቃል ኪዳን አሁንና ሁልጊዜም ከእናንተ ጋር ይሁን።

በስድስት ወር በኋላ እስከምንገናኝ ድረስ ደህና ሁኑ እላችኋለሁ፣ እናም ይህንም የማደርገው በጌታችን እና አዳኛችን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።