Skip main navigation
ሚያዝያ 2014 | ይፈለጋል፥ እጆችና ልቦች ስራውን ለማፋጠን

ይፈለጋል፥ እጆችና ልቦች ስራውን ለማፋጠን

ሚያዝያ 2014 አጠቃላላ ጉባኤ

የሰማይ አባታችንን ድንቅ ስራ ለማፋጠን የእርዳታ እጆችን እና ልብን ማቅረብ እንችላለን።

ውድ እህቶች፣ እንዴት እንደምወዳችሁ! ያንን የያምር ቪዲዮ ስንመለከት፣ በዛ በቃልኪዳኑ መንገድ ላይ የራሳችሁ እጅ ለእርዳታ ሲደርስ ተመለከታችሁ? አንድ እጅ ስለነበራት እና ያንን እጅ ቤተሰቦቿን እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖችን እና የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑትን ለመርዳት ስለተጠቀመችበት ስለ አንድ ብርን ሰለምትባል የመጀመሪያ ክፍል ትንሽ ሴት ልጅ እያሰብኩኝ ነበር። ቆንጆ እይደለችምን?እናንተም እንደእሷ ናችሁ! እህቶች፣ የሰማይ አባታችንን ስራ ለማፍጠን እጆችን እና ልብን ማቅረብ እንችላለን።

ልክ በቅዱስ መጽሐፍት ውስጥ እንዳሉ አማኝ እህቶቻችን፣ እንደ ሄዋን፣ ሳራ፣ ማርያም እና ሌሎችም ማንነታቸውን እና አላማቸውን እንዳወቁት እህቶች፣ ብርን የእግዚአብሔር ሴት ልጅ እንደሆነች ታውቃለች።1 እኛም እራሳችን የእኛን እንደ ተወዳጅ የእግዚአብሔር ሴት ልጆች መለኮታዊ ውርሳችንን እና እርሱ ለእኛ ስላለው ጠቃሚ ስራ ማወቅ እንችላለን።

አዳኝ አስተማረ፣ “ ማንም ሰው ፈቃዱን ቢፈጽም፣ ትምህርቱን ያውቃል።”2 “ከእርሱ ጋር የሆነ ቀን መኖር እንችል ዘንድ” ምን ማድረግ አለብን?3 ኢየሱስ ክርስቶስን የዘላለም ህይወትን ለመቀበል ምን ማድረግ እንዳለበት ከጠየቀው ወጣት ሀብታም ታሪክ መማር እንችላለን።

ክርስቶስም መለሰለት፣ “ ወደ ህይወት መግባት ከፈለግክ፣ ትዛዛቶችን ጠብቅ።”

ወጣቱም የትኛውን መጠበቅ እንዳለበት ጠየቀው። ኢየሱስም ሁላችንም የምናውቃቸውን አስርቱን ትዕዛዞች አስታወሰው።

ወጣቱም መለሰ፣ “ እነዚህን ነገሮች ከልጅነቴ ጀምሮ ጠብቄያለው፥ ምን ይጎድለኛል?”

ኢየሱስም አለ፣ “ፍጹም ከሆንክ፣ ያለህን ሂድና ሽጥ እና ለድሆች ስጥ እና በሰማይ ሀብት ይኖርካል፥ እና ና እና ተከተለኝ።”4

ኢየሱስ የስራው አካል እንዲሆን ጠራው- የደቀመዝሙር ስራ። የእኛም ስራ አንድ ነው። “ የአለምን ነገሮች ወደ ጎን መተው አለብን፣ እና የእኛ ቃልኪዳኖች ላይ መጣበቅ አለብን፣”5 እና ወደ ክርስቶስ ኑ እና ተከተሉት። ያንን ነው ደቀመዝሙሮች የሚያደርጉት!

አሁን እህቶች አዳኝ ለወጣቱ ሀብታም ፍጹም ስለመሆን ስለተናገረው ስለእድገታችን መጥፎ ስሜት አይሰማን ። በዚህ አገላለጽ ውስጥ ፍጹም የሚለው ቃል ከግሪክ ቃል “ሙሉ” ከሚለው የተተረጎመ ነው። በቃልኪዳኑ መንገድ ወደ ፊት በተቻለን አቅም ለመጓዝ በምንሞክርበት ወቅት፣ በዚህ ህይወት ውስጥ የበለጠ ሙሉ እና ፍጹም እንሆናለን።

ልክ በኢየሱስ ጊዜ ውስጥ እደነበረው እንደ ወጣቱ ሀብታም ሰው፣ አንዳንድ ጊዜ ተስፋ ለመቁረጥ እና ወደ ኋላ ለመመለስ እንፈተናለን ምክንያቱም ምናልባት ለብቻችን ማከናወን እንደማንችል እናስባለን። እናም ልክ ነን! የተጠየቅነውን ከባድ ነገሮች ካለ እገዛ ማከናወን አንችልም። እርዳታ የሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ አማካኝነት፣ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት፣ እና በሌሎች የእርዳታ እጆች ነው።

አንድ ያላገባች አማኝ አህት በቅርብ በሀጢያት ክፍያው አማካኝነት የእርዳታ እጆቿን በካንሰር የሞተችው እህቷ ትታቸው የሄደችውን አራት ልጆቿን ለማሳደግ ጥንካሬ እንዳገኘች መሰከረች። ሽማግሌ ኒል ኤ ማክስዌል እንዲህ ሲሉ አስታውሳለው፥ “ቤተክርስቲያኑዋ ማድረግ የነበረባት ሁሉም ቀላል ነገሮች ተደርገዋል።”6 በዚህ ዘመን ወደዚህ ምድር የተላካችሁበት ምክንያት በማንነታችሁ እና ምን ለማከናወን በመዘጋጀታችሁ ነው! ምንም እንኳን ሰይጣን ስለማንነታችን እንድናስብ ሊገፋፋን ቢሞክርም የእኛ እውነተኛ ማንነት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ነው!

ሞርሞን “ሁሉም ልቦቸ ሲደነድኑ… እና በሌሂ ልጆች መሀከል እንደዛ አይነት ታላቅ ክፋት ባልነበረበት ጊዜ የኖረው” እውነተኛ ደቀመዝሙር ነበረ።7 በእዛ ጊዜ እንዴት መኖር ትወዱ ነበር? የድፈፍረት ቃሉን በምናነብበት ጊዜ፣ ሞርሞን በትክክል ማን እንደነበር እንማራለን “እነሆ፣ እኔ የኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ደቀመዝሙር ነኝ።”8

ሞርሞንን አትወዱትምን? እሱ ማን አንደነበረ እና ተልዕኮው ምን እንደነበር ያውቅ ነበር እንዲሁም እሱን በከበበው መጥፎ ነገር አልተረበሸም ነበር። በእርግጥም፣ ጥሪውን እንደ ስጦታ ነበር የተመለከተው።9

የሁልጊዜ ለጌታ የእኛን የደቀመዝሙርነት ስጦታ “እነሆ እኔ የኢየሱስ ክርስቶሰ ደቀመዝሙር ነኝ!” የሚለውን በቃልና በተግባር በማወጅ ለመስጠት መጠራት እንዴት ደስ እንደሚል አስቡት፣

ፕሬዘደንት ፓከር ለአንድ ውድ የነብዩን ምግብ የማከማቸት ምክርን በመከተሏ ስለተሳለቁባት ሴት የነገሩትን ታሪክ እወደዋለው። የተቻት አንዱ ሰአቱ በጣም አስፈላጊ ከሆነ የእሷ የምግብ ጎተራ ተወስዶ ለሌሌች እንደሚሰጥ ሀሳብ አቀረበ። የእሷ ቀላልና የታሰበበት መልስ እንደ ትክክለኛ ደቀመዝሙር፣ “ቢያንስ የማመጣው ነገር ይኖረኛል” የሚል ነበር።10

የቤተክርስቲያኑን ሴቶች እወዳቸዋለው። ጥንካሬአቸውን አይቻለው። እምነታቸውን አይቻለው። የሚሰጥ ነገር አላቸው፣ እና ለመስጠትም ፍቃደኞች ናቸው። ይህንን የሚያደርጉት ባለመገለጽ ወይም በድብቅ ነው፣ ወደ ራሳቸው ሳይሆን ወደ ሚያመልኩት እግዚአብሄር ቀልባቸውን እየሰበሰቡ፣ እንዲሁም ስለሚቀበሉት ነገር ምንም ሳያስቡ ነው።11 ያንን ነው ደቀመዝሙሮች የሚያደርጉት።

በቅርብ በ7 አመቷ ቤተሰቦቿ ከቤተክርስቲያን የቀሩ፣ በየሳምንቱ ለብቻዋ አደገኛውን የቤተክርሰቲያን መንገድ እንድትጓዝ የተዋትን አንድ የፊሊፒንስ ወጣት ሴት አገኘሁ። በ14 አመቷ እንዴት ለቃልኪዳኖቿ ታማኝ ሆና እንደምትቆይ “በክህነት ሀይል ጥንካሬ የተባረከ” ቤት ውስጥ የወደፊት ቤተሰቧን ለማሳደግ ብቁ መሆን እንዴት እንድትችል እንደወሰነች ተናገረች።12 የአሁን ወይም የወደፊት ማጠንከሪያ አሪፉ መንገድ ለእግዚአብሄር እና እርስ በእርስ የገባነውን ቃልኪዳኖች መጠበቅ ነው።

ያም ደቀመዛሙርቶች የሚያደርጉት ነው!

አንድ የጃፓን ታማኝ እህትና ባሏ የኛን ሚስንዮን ለመጎብኘት ኮሪያ መጥተው ነበር። የኮርያ ቋንቋ አትናገርም ነበር እንዲሁም የእንግልዝኛ ቋንቋ የመናገር ችሎታዋ ዝቅተኛ ነበር፣ ነገር ግን ለየት ያለውን ስጦታዋን እና የእርዳታ እጆቿን የጌታን ስራ ለመስራት ፈቃደኛ ልብ ነበራት። ሚስዮኖቻችንን ቀላል የኦሪጋሚ ቁራጭ - የሚከፈት እና የሚዘጋ አፍ እንዴት እንደሚሰራ አስተማረቻቸው። ከዛ በኋላ የምታውቀውን ትንሽ የእንግሊዝኛ ቃላቶች ተጠቅማ ሚስዮኖቹን ወንጌልን ለማካፈል አፋቸውን እንዲከፍቱ አስተማረቻቸው- የማይረሱት ትምርት።

በአዕምሮአችሁ እኔ እና እናንተ አብረን ከቤተክርስቲያኑ ብዙ ሚልዮን እህቶች እና ወንድሞች ጋር በደፋርነት ወደፊት በመሄድ፣ አዳኝ ያደርግ እንደነበረው እንደ ደቀመዛሙርቶች ስናገለግል እና ስናፈቅር ተመልከቱ። “ለእናንተ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆን ማለት ምን ማለት ነው?”

የሞርሞን የእርዳታ እጆች የሚለው ጃፖኒዎች እና ካኒተራዎች በመቶ ሺዎች በሚጠጉ ጊዜያዊ የአገልግሎት እድሎች ውስጥ በተሳተፉ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙሮች ተለብሷል። ነገር ግን እንደ ዝግጁ ደቀመዝሙሮች የምናገለግልበት ብዙ መንገዶች አሉ። ከእኔ ጋር አንዳንድ ከደህንነት ስራ ጋር በተያያዘ መንፈሳዊ እርዳታ ያስፈልገናል የሚል ምልክት አስቡ።

 • እርዳታ ይፈለጋል፥ እናቶች ልጆቻቸውን በብርሀን እና በእውነት ለማሳደግ

 • እርዳታ ይፈለጋል፥ ሴት ልጆች፣ እህቶች፣ አክስቶች፣ የአክስ የአጎት ልጆች፣ እና የሴት አያቶች እንደ አሰልጣኞች እንዲያገለግሉ እና የእርዳታ እጅ በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ እንዲሰጡ

 • እርዳታ ይፈለጋል፥ የመንፈስ ቅዱስ መነሳሻን የሚያዳምጡ እና በሚያነሳሳበት የሚሰሩ

 • እርዳታ ይፈለጋል፥ በየቀኑ በቀላል እና በትትንሽ መንገዶች በወንጌል የሚኖሩ

 • እርዳታ ይፈለጋል፥ የቤተሰብ ታሪክ እና የቤተ-መቅደስ ሰራተኞች ቤተሰቦችን ለዘለአለም ሊያገናኙ

 • እርዳታ ይፈለጋል፥ መልካሙን ዜና-የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የሚያካፍሉ ሚስዮናውያኖች

 • እርዳታ ይፈለጋል፥ መንገዳቸውን የሳቱትን የሚያገኙ አዳኞች

 • እርዳታ ይፈለጋል፥ ለእውነት እና ለትክክል በጥንካሬ የሚቆሙ የቃል-ኪዳን ጠባቂዎች

 • እርዳታ ይፈለጋል፥ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀመዝሙሮች

ከአመታት በፊት ሽማግሌ ኤም ራስል ባላርድ ለቤተክርስትያን እህቶች እንዲደረግ የጠየቁበትን ጥሪ እንዲህ አስተላልፈዋል፥

“በአሁኑ እና ጌታ እንደገና በሚመጣበት ጊዜ ውስጥ፣ በሁሉም ቤተሰብ ውስጥ፣ በሁሉም ዋርድ ውስጥ፣ በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ፣ በሁሉም ሀገር ውስጥ በቅድስና ወደፊት ወጥቶ እና በቃላቸው እና በድርጊታቸው ‘እኔ ይሀው ላከኝ።’ የሚሉ ሴቶችን ይፈልጋሉ።

የእኔ ጥያቄ፣ ‘ከነዛ ሴቶች መካከል አንዷ ትሆናላችሁን?’ ነው።”13

ሁላችንም በግልጽ “አዎ!” ብለን እንመልሳለን ብዬ ተስፋ አደርጋለው። በህጻን ልጆች መዝሙር ቃላቶች እዘጋላው፥

እኛ የቃልኪዳን [እህቶች] ነን ከመስጠት ስጦታ ጋር።

ወንጌልን በምንኖረው አኗኗር እናስተምራለን።

በያንዳንዱ ቃላት እና ተግባር እንመሰክራለን፥

ኢየሱስ ክርስቶስን እናምናለን እንዲሁም እናገለግላለን።14

እንደ እውነተኛ ደቀመዝሙሮች፣ ፈቃደኛ ልባችንን እና የእርዳታ እጆቻችንን የእርሱን ስራ ለማፋጠን እናበርክት። ብርን አንድ እጅ ብቻ ያላት መሆኑ ምንም አይደለም። ፍጹም እና የተፈጸምን አለመሆናችንም ምንም አይደለም። እህትነታችን ከዚህ በፊት ይኖሩ ወደነበሩት ታማኝ እህቶች በትውልድ አልፎ ይደርሳል። አብረን፣ እንደ እህቶች እና በዳግም የተመለሰ የክህነት ቁልፎች ካሏቸው ከህያው ነቢያት፣ ባለራዕያት፣ እና ከገላጮች ጋር አብረን በአንድነት፣ እንደ ደቀ መዛሙር፣ የደህንነት ስራን ለማፋጠን የልብ እና የእጅ ፈቃል እንዳላቸው እንደ አገልጋዮች ለመራመድ እንችላለን። ይህን ስናደርግ፣ እንደ እርሱ እንሆናለን። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማጣቀሻወችን ያሳዩማጣቀሻወችን መደበቅ

  ማስታወሻ

  1. See “Brynn,” lds.org/media-library/video/2011–01–007-brynn.

  2. ዮሀንስ 7:17.

  3. “I Am a Child of God,” Hymns, no. 301; or Children’s Songbook, 2–3.

  4. ማቴዎስ 19:16–22ተመልከቱ.

  5. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25:10, 13.

  6. Neal A. Maxwell, “The Old Testament: Relevancy within Antiquity” (address to Church Educational System religious educators, Aug. 16, 1979), 4; si.lds.org.

  7. ሞርሞን 4:11–12.

  8. 3 ኔፊ 5:13.

  9. ሞሮኒ 7:2ተመልከቱ.

  10. In Boyd K. Packer, “The Circle of Sisters,” Ensign, Nov. 1980, 111.

  11. 2 ኔፊ 26:29–30ተመልከቱ.

  12. “Love Is Spoken Here,” Children’s Songbook, 190–91.

  13. M. Russell Ballard, “Women of Righteousness,”Ensign, Apr. 2002, 70;Liahona, Dec. 2002, 39.

  14. “Holding Hands around the World,”Friend, July 2002, 44–45;Liahona, Oct. 2003, F12–13.