2010–2019 (እ.አ.አ)
ወደ ቤት በደህና መመራት
ኦክተውበር 2014


ወደ ቤት በደህና መመራት

ጥበብ ያለው እና ትክክለኛ የሆነውን ንድፍ ለመንደፍ እና ለመከተል ለዛ የማይቆም አቅጣጫ ጠቋሚ ወደ ሰማይ እናያለን፡ የሰማይ አባታችን የእኛን ቅን የሆነ ፀሎት ሳይመልስልን አያልፍም።

ወንድሞች፣ በጉባኤ መአከሉ ውስጥ እና በአለም ዙሪያ ባሉ ቦታዎች ውስጥ እንደ የክህነት ኃያል አካል ተሰብስበናል። ክብር ትንሽ ነገሮችን ለእናንተ ለማካፈል ባለኝ ሀላፊነት ክብር ተሰምቶኛል ግን ትሁት ሆኛለው። ይህንን በማደርግበት ሰአት የጌታ መንፈስ እንዲጎበኘኝ እፀልያለው።

ከሰባ አምስት አመት በፊት በየካቲት 14፣ 1939 (እ.አ.አ)፣ በሀምቡርግ ጀርመን ውሰጥ የህዝብ አመት በአል ተከብሮ ነበር። በሚገርም ንግግር፣ የህዝብ ብዛት እና ብሔራዊ መዝሙር እየተጫወተ ባለ ውስጥ፣ “አዲሱ የጦር መርከብ ቢስማርክ በኤልብ ወንዝ ውስጥ ተነሳ።” ይህ በጣም ኃይለኛ የሆነው መርከብ መንሳፈፈ አየር የሚያሳጣ የጋሻ እና የማሽን ምስል ነበር። ግንባታው ለ406 ሚሊሜትር 57 ሺህ የካርታ እቅዶችን፣ ባለ ሶስት የጠመንጃ ቤትን፣ የአየር መቃወሚያ ጠመንጃዎችን ጠይቋል። መርከቡ 28 ሺህ ማይሎች (45 ሺህ ኪሎ ሜትሮች) የኤሌክትሪክ ገመዶችን ፈጅቷል። ሰላሳ አምስት ሺህ ቶን የጋሻ ጠፍጣፋ ብረት ከፍተኛ ደህንነት ሰጠው። በእይታው ግርማ ሞገስ ያለው፣ በመጠኑ እጅግ ከፍተኛ፣ በአተኳኮስ ኃይሉ የሚገርም፣ ኃያሉ ግዙፍ የማይሰምጥ ተደርጎ ተወስዶ ነበር።

በግንቦት 24፣ 1941 (እ.አ.አ) ሁለቱ በጣም ኃይለኛ የጦር መርከቦች በብርቴን የባህር ኃይል ውስጥ ያሉት የዌልሱ ልዑል እና ሁዱ በጦርነት ከቢስማርክ እና የጀርመን ትንሽዬ የጦር መርከብ ፕሪነዝ ኢዩጌን ጋር ሲጋጠሙ የቢስማርክ ቀጠሮ እጣ ፋንታ ሁለት አመት ካለፈ በኋላ መጣ። በአራት ደቂቃ ውስጥ ቢስማርክ ሁዱን እና ከ1,419መርከበኞች ሶስት ወንዶች ሲቀሩ ሁሉም ወደ ጥልቁ አትላንቲክላካቸው። ሌላኛው የብርቴን የጦር መርከብ የዌልሱ ልዑል ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት እና ሸሸ።

ከሶስት ቀን በኋላ፣ ቢስማርክ እንደገና በአራት የብርቴን የጦር መርከቦች ተጠመደ። በድምር የsmnt የጦር መርከቦች፣ የሁለት የጦር ጀት ተሸካሚዎቸ፣ የ11 ትንንሽ የጦር መርከቦች እና የ21 አፈራራሾች የሆኑ የጥምረት ጥንካሬ ኃያሉን ቢስማርክ ለማስመጥ ለመጣር ብርቴኖች ሰበሰቡ።

በጦርነቱ ወቅት፣ ብዙ ሚሳኤሎች በቢስማርክ ውጫዊ አካል ላይ ትንሽ ጉዳት አደረሱበት። የማይሰምጥ ነበረን?ከዛ መተኮሻ የቢስማርክን መሪ ያገተውን እድለኛ ምቱን ተኮሰ። የመጠገን ሙከራ ፍሬ አልባ እንደሆነ አረጋገጠ። ለመተኮስ ዝግጁ በሆኑ ጥይቶች እና መርከበኞቹም በዝግጅት ላይ ሆነው፣ ቢስማርክ ቀስ ብሎ እና “በእረጅም ክብ መሽከርከር ብቻ ሆነ።” የጀርመን ኃያል የአየር ኃይል ከሚደረስበት ውጭ ነበር። የቤቱ ወደብ ደህንነት በጣም ቅርብ ነበር። ሁለቱም የተፈለገውን ደህንነት ሊያቀርቡ አልቻሉም። ምክንያቱም ቢስማርክ የታቀደን መስመር ይዞ ለመሽከርከር አቅም አጥቶ ነበር። ቢስማርክማሽከርከሪያ አልነበረም፤ እርዳታ አልነበረም፤ ወደብ አልነበረም።ፍፃሜው ደረሰ። የብርቴን ጥይቶች የጀርመን መርከበኞች ሲሸፍኑት ተተኮሱ እና አንድ ጊዜ የማይጠፋ የሚመስለውን መርከብ አሰመጡት። የአትላንቲክ የተራቡ መአበሎች መጀመሪያ ጎኑን መቱት ከዛም የጀርመንን የባህር ኃይል ኩራት ዋጡት። ቢስማርክ ጠፋ።1

ልክ እንደ ቢስማርክ እያንዳንዳችን የኢንጂነሪንግ ታምራት ነን። ይሁን እንጂ ፍጥረታችን በሰወ ጉብዝና የተገደበ አይደለም። ሰው በጣም ውስብስብ የሆኑ ማሽኖችን ሊሰራ ይችላል ነገር ግን ሕይወት ሊሰጣቸው ወይም በላያቸው ላይ የምክንያትን እና የፍርድን ኃይል ሊጭንባቸው አይችልም።እነዚህ በእግዚአብሔር ብቻ የሚሰጡ መለኮታዊ ስጦታዎች ናቸው።

ልክ እንደ መርከብ ወሳኝ መሪ፣ ወንድሞች የጉዞአችንን አቅጣጫ እንድንወስን ተሰጥቶናል። የጌታ ማማ ላይ መብራት የሕይወትን ባህር ላይ ስንጓዝ ለሁላችንም ያንፀባርቃል። አላማችን ወደ ምኞታችን ግብ እሱም የእግዚአብሔር የሰለስቲያል መንግሰት ወደሆነው በማይወላውል መንገድ ላይ መንዳት ነው። አላማ የሌለው ሰው መሪ እንደሌለው መርከብ ነው። ቤት ወደብ ላይ ሊደርስ የማይችል መርከብ ማለት ነው። ወደ እኛ ምልክቱ ይመጣል፥ መንገዳችሁን አቅዱ፣ ጉዞአችሁን አስተካክሉ መሪያችሁን አስተካክሉ እናም ቀጥሉ።

ልክ እንደ ኃያሉ ቢስማርክ ለሰው ልጅም ይሄው ነው። የሞተሩ እና የመቅዘፊያው ኃይል እምነት ከዛ አቅጣጫ ጠቋሚ፣ ከዛ ጉልበት ተጠቃሚ፣ ከዛ ከመሪው የሚመጣውን ኃይል ከሚመራው፣ ከእይታ ከተደበቀው፣ በመጠን ትንሽ ከሆነው ነገር ግን በጥቅም ላይ በጣም አስፈላጊ ከሆነው ውጪ ጥቅም የለውም።

አባታችን ፀኃይን፣ ጨረቃን እና ከዋክብትን- የሰማይ ህዋዎችን በባህር ላይ የሚጓዙትን ለመምራት ሰጠ። ለእኛ የሕይወትን ጎዳና ስንጓዝ ግልፅ የሆነ ካርታን ሰጠ እና ወደ የምኞታችን እጣ ፋንታ እንድንደስ መንገዱን ጠቆመ። አቋራጭ መንገዶችን፣ ገደሎችን፣ ወጥመዶችን ተጠንቀቁ ብሎ አስጠነቀቀ። ወደ ተሳሳተ መንገድ በሚመሩን ሰዎች፣ በእነዛ እዚ እና እዚያ በሚያታልሉት የሀጢያት ብልጭልጮች መታለል አንችልም። በምትኩ፣ ለመፀለይ እንቆማለን፤ ያንን ለነግሳችን ጥልቀት የሚያወራውን የአስተማሪያችንን “ኑ ተከተሉኝ” 2 የሚለውን በዝግተኛ እና ትንሽዬ ድምፅ ውስጥ ረጋ ያለ ጥሪ እንሰማለን።

ነገር ግን የማይሰሙት፣ የማይታዘዙት፣ የራሳቸውን የመንገድ ስሪት መራመድ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። ብዙውን ጊዜ ሁላችንንም ለሚከቡን ፈተናዎች እና አሳሳች ሆነው ለሚቀርቡት ነገሮች እጅ ይሰጣሉ።

እንደ ክህነት ተሸካሚነታችን፣ በአስቸጋሪ ሰአት ነው በምድር ላይ የተቀመጥነው። በየቦታው የግጭት ሞገድ በሚገኝበት ውስብስብ አለም ውስጥ ነው የምንኖረው። የፖለቲካ አስተሳሰብ የሀገርን መረጋጋት አፈራርሷል፣ የጨቋኝ መሪዎች ስልጣን ላይ መውጣት እና የመሀበረሰብ ክፍሎች ሁሌም የተመቱ መምሰል፣ የተከለከሉ እድሎች እና በወዳቂነት ስሜት ውስጥ መተው በዝቷል። በጆሯችን ውስጥ የሚያሰተጋባው የሰዎች ውሸት እና ሀጢያት ዙሪያችንን ከቦታል።

የእኛ ሀላፊነት የሰማይ አባታችን ላስቀመጠልን ክብራዊ በረከቶች ብቁ ሆነን መገኘት ነው። በምንሄድበት ቦታ ሁሉ ክህነታችን አብሮን ይጓዛል። በቅዱስ ቦታዎች እየቆምን ነውን? እባካችሁ፣ እራሳችሁን እና ክህነታችሁን ወደ አደጋ ቦታዎች በመሄድ ወይም ከእናንተ ወይም ከዛ ክህነት በማይጠበቁ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ በአደጋ ላይ ከማስቀመጣቹ በፊት፣ የሚያመጣውን ውጤት አስቡት።

በእግዚአብሔር ክህነት የተሸምን ሰዎች ልዩነት ማምጣት እንችላለን። የግል ንፅህናችንን ስንጠብቅ እና ክህነታችንን ስናከብር ሌሎች እንዲከተሉት ፅድቅ ምሳሌዎች እንሆናለን። ሐዋርው ጳውሎስ እንዲህ መከረ፣ “በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንፅህናም ለሚያምኑት ምሳሌ ሁን።”3 እንዲሁም የክርስቶስ ተከታች “በአለም ላይ እንደ ብርሀን”4 መሆን እንዳለባቸው ፃፈ።

ብዙዎችችሁ ፕሬዘደንት ኤን. ኤልደን ታነርን ለአራት የቤተክርስቲያን ፕሬዘደንቶች አማካሪ የነበሩትን ታስታውሳችኋላችሁ። እሳቸው በሕይወታቸው ውስጥ በኢንዱስትሪ ውስጥ ስራቸው፣ በካናዳ መንግስት ውስጥ አገለግሎታቸው እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የፅድቅ የማይወላውል ምሳሌን ሰጡ። ይህንን የተነሳሳ ምክር ሰጡን፥ “እንደ ወንጌል ትምህርቶች ከመኖር ውጪ ምንም ታላቅ ድስታን እና ውጤትን አያመጣልንም። ምሳሌ ሁኑ፤ ለመልካም ተፅዕኖ ፈጣሪ ሁኑ።”

እሳቸውም ቀጠሉ፥ “እያንዳንዳችን እግዚአብሐየር ለክህነት እና በስሙ የማገልገል ኃይል ብቁ ናቸው ብሎ ባመነባቸው አገልጋዮች ላይ ሾሞ ሲመርጥ ለአንዳንድ ስራዎች ቀድመን ተሸመናል። ሁል ጊዜ አስታውሱ ሰዎች ለአመራር እያዩአችሁ ነው እና የግለሰቦችን ሕይወት ለጥሩም ሆነ ለመጥፎ ለሚመጡት ሁሉ ትውልዶች የሚሰማ ተፅዕኖ እያደረጋቹባቸው ነው።” 5

በዛሬው አለም ውስጥ ታላቁ ኃይል በሰዎች ውስጥ እንደሚሰራው የእግዚአብሔር ኃይል እንደሆነ ባለን እውነታ ጠንክረናል። የሟቸነትን ባህር በደህንነት ለመጓዝ፣ የዘላለማዊውን የባህር ኃይል እሱም የታላቁ ዮሁዋን ምሪት እንፈልጋለን። የሰማይ እርዳታን ለማግኘት እንዘረጋለን፣ እንጠይቃለን።

በጣም ታዋቂ የሆነው ያልጠየቀው ሰው ምሳሌ የአዳም እና ሔዋን ወንድ ልጅ የቃኤል ነው። በችሎታ ኃያል ነገር ግን በፍቃደኝነት ደካማ የነበረው ቃኤል ስግብግብነትን፣ ምቀኝነትን፣ አለመታዘዝን እንዲሁም ወደ ደህንነት እና የዘላለም ሕይወት አምርቶት የነበረውን የግል መሪ በመግደል በመስበር ጋበዘ። ከመንፈሳዊ ነገሮች አለማዊ ነገሮችን አጥብቆ አሸ፤ ቃኤል ወደቀ።

በሌላ ጊዜ ውስጥ እና በክፉ ንጉስ፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ ተፈትኖ ነበር። በሰማይ መነሳሳት በመታገዝ፣ ዳንኤል በግድግዳው ላይ ያለውን ፅሁፍ ተረጎመ። ስለተሰተው ሽልማቶች- ነጉሳዊ ካባ፣ የወርቅ የአንገት ሀብል እና ፖለቲካዊ ኃይል ዳንኤል እንደዚህ አለ፣ “ስጦታህ ለአንተ ይሁን፣ በረከትህንም ለሌላ ስጥ።”6 የእግዚአብሔር ሳይሆን የአለም ነገሮችን የሚወክሉ ታላቅ የሀብት እና የኃይል ሽልማቶች ለዳንኤል ተሰጥቶ ነበር። ዳንኤል ተቃወመ እና አማኝ ሆኖ ቆየ።

በኋላ፣ ዳንኤል እግዚአብሔርን ሲያመልክ ምንም እንኳን እንደዚህ አይነት ድርጊት በአዋጅ ቢከለከልም፣ ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጣለ። የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች በሚቀጥለው ጠዋት ምን እንደተከሰተ ይናገራል፣“ዳንኤልም ከጉድጓድ ወጣ፣ በአምላም ታምኖ ነበርና አንዳችም ጉዳት አልተገኘበትም።”7 በወሳኝ አስፈላጊ ሰአት የዳንኤል ቀጥ ባለ መንገድ የማሽከርከር ቆራጥነቱ መለኮታዊ ጥበቃል አስገኘለት እንዲሁም የደህንነት ቅዱስ ቦታ ሰጠው። እንደዚህ አይነት ጥበቃ እና ደህንነት እኛም በዛ ቀጥ ያለ ወደ ዘላለማዊ ቤት ወደሚወስደን መንገድ ላይ ስናሽከረክር የእኛ ሊሆን ይችላል።

የታሪክ ሰአት፣ ልክ ጊዜ እንደሚለካ መሳሪያ፣ የጊዜን ማለፍ ይጠቁማል። አዲስ ተግባር የሕይወትን መድረክ ይይዛል። የቀናችን ችግር ያስፈራራናል። በአለም መላ ታሪክ ውስጥ ሴጣን የአዳኝን ተከታዮች ለማጥፋት ሳይደክም ሰርቷል። ልሽወዳው እጅ ከሰጠን፣ እኛም ልክ እንደ ኃያሉ ቢስማርክ ወደ ደህንነት የሚመራንን መሪ እናጣለን። በምትኩ፣ በዘመናዊ አኗኗር ውስብስብ ተከበን፣ ጥበብ ያለው እና ትክክለኛ የሆነውን ንድፍ ለመንደፍ እና ለመከተል ለዛ የማይቆም አቅጣጫ ጠቋሚ ወደ ሰማይ እናያለን፡ የሰማይ አባታችን የእኛን ቅን የሆነ ፀሎት ሳይመልስልን አያልፍም። የሰማይን እርዳታ በምንሻበት ወቅት፣ መሪያችን፣ እንደ ቢስማርክ ሳይሆን፣አይበላሽም።

በግል ጉዟችን ላይ ስንጓዝ፣ የሕይወትን ባህር በደህንነት እንጓዝ። በዙሪያችን ሀጢያት እና ፈተና ቢከበንም፣ እውነት እና አማኝ ሆነን ለመቆየት እንደ ዳንኤል ድፍረት ይኑረን። ምስክርነቶቻችን እንደ ያዕቆብ የኔፊ ወንድም እምነቱን ለማጥፋት ከሞከረ ጋር ሲጋፈጥ “ስለሆነም አልናወጥም”8 እንዳለው ጥልቅ እና ጠንካራ ይሁን።8

በእምነት መሪ መንገዳችንን እየመራ፣ ወንድምች፣ እኛም በደህንነት የቤት መንገዳችንን- ለዘለአለም ከእርሱ ጋር ለመኖር ወደ እግዚአብሔር ቤትየሚወስደውን መንገድ እናገኛለን። ለእያንዳንዳችን ይሄ ይሁን። በቅዱስ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም እፀልያለው፣ አሜን።