2010–2019 (እ.አ.አ)
ወንጌልን በደስታ መኖር
ኦክተውበር 2014


ወንጌልን በደስታ መኖር

ትክክለኛ የእግዚያብሔር ተፈጥሮ እና ማንነት ትእዛዛቱን ስትረዱ፣ እራሳችሁን እና የመኖራችሁን መለኮታዊ አላማ በተሻለ መንገድ ትረዳላችሁ።

የተወደዳችሁ እህቶቼ፣ውድ ጓደኞቼ እና የተባረካችሁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሌላኛውን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ አጠቃላይ ጉብኤ ስንጀምር ከእናንተ ጋር ለመሆን እድሉን ስላገኘሁ ክብር ይሰማኛል። በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ አመራር እና አስራ ሁለት ሀዋሪያት ሁሉንም አጠቃላይ ባለስልጣናት አጠቃላይ የኦግዝለሪ መሪዎች ጋር ይገናኛሉ። ቀሪው ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ጉባዔ ክፍለ ጊዜ ቅዳሜ እና እሁድ ይቀጥላል። የመጀመሪያ አመራርን ወክዬ ለቤተክርስቲያን ሴቶች ንግግር እንዳቀርብ ስለጠየቀኝ ለነብያችን ቶማስ ኤስ. ሞንሰን በጣም ምስጋና አለኝ።

ልናገር የምችለውን ነገር እያሰላሰልኩ ሳለ፣ ሃሳቤ ሕይወቴን ወደ ቀረፀቺው እና በምድራዊ ፈተና ወደ ረዳችኝ ሴት ወደ ህዋላ ተመለሰ።ከአስርት አመታት በፊት ቤተሰቧን ወደ የሞርሞን ቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ለመውሰድ የወሰነቺው የሴት አያቴን አመሰግናለሁ። ስሟ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ሲተረጎም “የዘላለም እህት” ለሚሆነው፣ ለትልቋ ያላገባች ጀርመናዊዋ ሴት፣ እህት እዊግ ምስጋና አለኝ።ይህንን ብርታታዊ እና አስገራሚ ግብዣ ለሴት አያቴ ያቀረበቺላት አሷ ነበረች።

እና፣ በርግጥም፣ ወጣትነቴን ብሩህ በማድረጓ፣ እንደ እናት የወጣት ቤተሰባችንን ከባድ ሸክም ስለተሸከመች፣ እነደ ሚስት አብራኝ በመሆን፣ እና ልጆቻችንን፣ የልጅ ልጆቻችን የምትወድ እና የምታስደስታቸው ለሚስቴ ሀሪየት ዘለአለማዊ አመስጋኝ ነኝ በመልካምም በክፉም ጊዜ በቤታችን ውስጥ ጥንካሬያችን ነበረች። በሚያቋት ሁሉ ህይወት ውስጥ የፀሀይ ብርሀን ታመጣለች።

በመጨረሻም፣ ለሁላችሁም በጣም አመስጋኝ ነኝ፣ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት ብዙ ነገር የምታደርጉ ሚሊየን የምትሆኑ ታማኝ እህቶች። በአካባቢያችሁ የሚገኙትን ለማነሳሳት፣ ለመንከባከብ፣ እና ለመባረክ ለምታደርጓቸው ቁጥር ለሌላቸው ነገሮችም እናመሰግናችኋለን።

የእግዚአብሔር ሴት ልጆች

በብዙ የእግዚአብሔር ሴት ልጆች መሀል በመገኘቴ ደስተኛ ነኝ። “I Am a Child of God,” የሚለውን መዝሙር ስንዘምር ስንኞቹ ወደ ልባችን ይዘልቃሉ። የሰማይ ወላጆቻችን ልጆች የመሆናችንን እውነታ ማሰላሰል1---በማንነት፣ አላማ እና እጣፈንታ ትርጉም ይሞላናል።

ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ልጅ መሆናችሁን ማስታወስ መልካም ነው። ይሄ እውቀት በህይወታችሁ በጣም አስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ይሸከማችኋል እና ድንቅ ነገሮችን እንድትፈጽሙ ያነሳሳችኋል። በመሆኑም፣ የዘለአለማዊ ወላጆች ሴት ልጅ መሆን እናንተ በራሳችሁ ጥረት ያገኛችሁት ወይም የምታጡት ያለመሆኑን ማስታወስም አስፈላጊ ነው። መቼም እና ሁሌም የእግዚአብሔር ሴት ልጅ ሆናችሁ ነው የምትቀጥሉት። የሰማይ አባታችሁ ለእናንተ ትልቅ ብርታት አለው፣ ነገር ግን መለኮታዊ ማንነታችሁ ብቻ መለኮታዊ ውርስ የእናንተ መሆኑ አያረጋግጥም። እግዚአብሔር እዚህ የላካችሁ ማሰብ ከምትችሉት በላይ ታላቅ ለሆነ ወደፊት ነው።

እግዚአብሔር ለታማኞች የገባው የበረከቶች ቃል የከበሩ እና የሚያነሳሱ ናቸው። ከእነዚያም ውስጥ፤“ዙፋን፣ መንግስታት፣ መለኮት፣ እና ሀይል፣ ግዛት፣ በሁሉም ከፍታ እና እርቀት።”2 እና ለእነዚህ ማሰብ ለሚዳግቱ በረከቶች ለመብቃት መንፈሳዊ ውልደት ወይም “የእግዚአብሔር ልጅ አባልነት ካርድ” በቂ አይደለም።

እንዴት ነው የምናገኛቸው?

አዳኝ በእኛ ጊዜ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሰቷል፤

“ህጌን ካልፈጸማችሁ በስተቀር ይህን ክብር አታገኙም።

“ወደ መዳን የሚመራው መግቢያ ቀጥታ እና መንገዱ ጠባብ ነው። .

“… ስለዚህ፣ ህጌን ተቀበሉ።.”3

ለዚህ ምክንያት፣ በደቀመዝሙር ጉዞ ላይ ስለመጓዝ እንናገራለን።

ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ስለመታዘዝ እንናገራለን።

በሙሉ ልባችን፣ ሀሳብ እና ነብሳችን ወንጌልን በደስታ ስለ መኖር እንናገራለን።

እኛ የማናውቀው አንድ ነገር እግዚአብሔር ያውቃል

ግን ለአንዳንዶቻችን፣ ለእግዚአብሔር ትእዛዛት መታዘዝ ሁሌ የሚያስደስት መስሎ አይሰማንም። ልክ በሰሀን ያለ ጤናማ ነገር ግን የማይወደድ አትክልት ፊት እንደ ተቀመጠ ልጅ መነሳሳት እኛም የምንቀርባቸው፣ ከባድ የሚመስሉ ትእዛዛት ይኖራሉ። በተሻለ ወደ የሚወዱ እንቅስቃሴዎች ለመሄድ ጥርሳችን እንነክሳለን እና እራሳችንን እናስገድዳለን።

በእርግጥም በእነደዚህ አይነት ጊዜያት እራሳችንን እንዲህ ስንተይቅ እንገኛለን፣ “የእውነት ለእግዚአብሔር ትእዛዛት በሙሉ መታዘዝ አለብን?”

ለእዚህ ጥያቄ ምላሼ ቀላል ነው፤

እኛ የማናውቀውን ነገር እግዚአብሔር ያውቃል ብዬ አስባለሁ! ለመረዳት ከእኛ አቅም በላይ የሆኑ ነገሮችን! የሰማይ አባታችን ልምዱ፣ ጥበቡ፣ እና እውቀቱ ከእኛ በእጅጉ የበለጠ ታላቅ ዘለአለማዊ ነው። 4ያም ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን እርሱ ለዘለአለም ወዳጅ፣ ሩህሩህ፣ እና ሟች ያለሆነ እና ዘለአለማዊ ህይወትን ለማምጣት አንድ የተባረከ አላማ ላይ ያተኮረ ነው።5

በሌላ አነጋገር፣ እርሱ ለእናንተ ምርጥ የሆነውን ማወቅ ብቻም አይደለም፤ ለእናንተ ምርጥ የሆነውን እንድትመርጡ በጣም ይፈልጋል

ይህንን በልባችሁ የምታምኑ ከሆነ-- የሰማይ አባታችን ታላቅ አላማ ልጆቹን ማዳን እና ማክበር እና እንዴት ማድረግ ደሞ እንዳለበት በደምብ የሚያውቅ መሆኑን በእውነት ካመናችሁ፣ ከባድ የሚመስሉትን ጨምሮ ትእዛዛቱን መከትል እንዳለብን ትርጉም አይሰጥም?

እንደማስበው የፈተናው ክፍል፣ እርሱ ያዘጋጀውን ከባድ እና ቀጥተኛ መጠይቅ ካላሟላን በስተቀር፣ እግዚአብሔር ሁሉንም በረከቶቹን ላለመስጠት በታላቅ ዳመና ውስጥ በሰማይ ቆልፏል ብለን እናስባለን። ትእዛዛት በፍጹም እንደዚያ አይደሉም። በእውነታው፣ የእኛ ፍራቻ፣ ጥርጣሬ፣ እና ሀጢያት እንደ ዣንጥላ በረከቶቹ ወደ እኛ እንዳይደርሱ እየከለከሉ ነው እነጂ የሰማይ አባታችን ሁሌም በረከቶችን በእኛ ላይ እያዘነበ ነው።

የሰማይ በረከት ፍሰትን መቀበል እንችል ዘንድ፣ ትእዛዛቱ የፍቅር መመሪያዎች እና ዣንጥላውን ለመዝጋት መለኮታዊ እርዳታ ናቸው።

የእግዚአብሔር ትእዛዛት የመልካም ሀሳብ ረጅም ዝርዝር ብቻ እንዳልሆኑ መቀበል ያስፈልገናል። ከኢንተሬት የሚገኙ የህይወት መሪዎች ወይም የማበረታቻ ጥቅሶች አይደሉም። “ ሰላምን በዚህ አለም እና በሚመጣው አለም ዘለአለማዊ ህይወት”6 ለማምጣት የተሰጡ፣ በዘለአለማዊ እውነት ላየተመሰረቱ፣ መለኮታዊ ምክሮች ናቸው።

ስለዚህ ምርጫ አለን። በአንድ ጎኑ፣ ሁሌም በሚቀያየር ሀሳብ እና አጠራጣሪ አካሄድ ያለ የአለም ሀሳብ ይገኛል። በሌላ ጎን፣ እግዚአብሔር ለልጆቹ የገባው ዘለአለማዊ ጥበብ፣ ጽኑ ቃል ኪዳን፣ እና ወደ እሱ እይታ በክብር፣ ፍቅር እና ንግስና ሚመልሱ ተወዳጅ መመሪያዎቹ ይገኛሉ።

ምርጫው የእናንተ ነው!

የውቅያኖሶች፣ አሸዋ እና የማያልቁ ከዋክብት ፈጣሪ በየቀኑ ወደ እናንተ እየደረሰ ነው! ለደስታ፣ ሰላም እና የዘለአለም ህይወት ታላቅ የሆነ ምሬት እያቀረበ ነው!

ለነኛ ታላቅ ለሆኑ በረከቶችለመብቃት፣ እራሳችሁን ትሁት ማድረግ፣ እምነታችሁን መለማመድ፣ የክርስቶስን ስም በላያችሁ በመውሰድ፣ በቃልም በስራም እርሱን በመሻት፣ እና “በሁሉም ሰአት እና ነገሮች፣ እና በሁሉም ቦታ የእግዚአብሔር ምስክሮች መሆን አለባችሁ።” 7

የመታዘዝ ምክንያት

ትክክለኛ የእግዚያብሔር ተፈጥሮ እና ማንነት ትእዛዛቱን ስትረዱ፣ እራሳችሁን እና የመኖራችሁን መለኮታዊ አላማ በተሻለ መንገድ ትረዳላችሁ። በዚህ ሁኔታ ትእዛዛቱን ለመከተል ያላችሁ መነሳሳት ይለወጣል እናም ወንጌልን የበለጠ በደስታ ለሞኖር በጣም የልባችኁ ፍላጎት ይሆናል።

ለምሳሌ፣ ቤተክርስትያን መሄድን፣ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ለ መጨመር፣ ሰላምን ለማግኘት ፣ ሌሎችን ለማነፅ፣ መንፈስ ቅዱስን ለመሻት አናም ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ያላቸውን ቃልኪዳን ለማደስ እንደሆነ የሚያስቡ ሰዎች እንዲሁ ቤተክርስቲያን ተካፍለው ከሚሄዱት እጅግ በተሻለ ልምድ ይባረካሉ። እህቶች፣ የሰንብት ስብሰባችንን መካፈል በጣም ጠቃሚ ነው፣ ነገር ግን የሰማይ አባታችን የበለጠ የሚጨነቀው ስለኛ ምን ያህል ቤተክርስቲያን መተናል የሚለው ሳይሆን ስለ እምነታችን እና ንሰህችን እንደሆነ በጣም እርግጠኛ ነኝ።

ይሄ ሌላ ምሳሌ ነው፤

ባል የሌላት የ ሁለት ትናንሽ ልጆች እናት በቅርቡ ኩፍኝ ወጣባት። በእርግጥ፣ ልጆችዋም መታመማቸው ብዙም አልቆየም። ለራሷ አና ለትናንሽ ልጆችዋ እንክብካቤ የማድረግ ስራ ብቻውን ለወጣት እናት በጣም ብዙ የሚባል ያህል ነው ።እናበውጤቱም፣ ወትሮውን እንከን የሌለው ንፁሁ ቤት የነበረው የተመሰቃቀለ እና ድብልቅ ልቅ ያለ ቤት ሆነ። የቆሸሹ ሳህኖች በዕቃ ማጠቢያ ገንዳ ላይ ተከምረው፣ እንዲሁም የቆሸሹ ልብሶች በየቦታው ላይ ተከምረዋል።

ልጆች ለመያዝ እየተቸገረች ሳለች— እራሷ መሸከም እየፈለገች — በሯተንክዋክዋ። የጉብኝት አስተማርዎችዋ ነበሩ። የወጣት እናት ጉዳት ማየት ችለው ነበር።. ቤቷን፣መአድ ቤቷን ማየት ይችሉ ነበር።የልጆቹንለቅሶ መስማት ይችሉ ነበር።

አሁን፣ እነዚህ እህቶች የተመደበላቸውን የወር ጉብኝት ብቻ ጭንቀታቸው ቢሆን ኖሮ፣ ለናትየው አንድ ሰሃን ጣፋጭ ብስኩት ያቀብሉዋት ነበር፣ ባለፈው ሳምንት የሴቶች መረዳጃ እንዳልመጣች አና አስዋን ከጎናቸው እንዳጧት በመግለፅ፣ ምናልባት እንዲ በማለት፣“ማድረግ የምንቺለው ነገር ካለ አሳውቂኝ”ከዚያ በደስታ መንገድ ላይ ወደ ቤት እየሄዱ ይሆናል፣ የወሩ የጉብኝት ትምህርታቸው በ100 ፐርሰንት ጨርሰው ነበር።

እንደ እድል ሆኖ፣ እነዚህ እህቶች ትክክለኛ ደቀመዛሙርት ነበሩ። እህቶቻቸው የእነሱ ብዙ መክሊቶች እንደሚያስፈልጋችው እና በሥራ ላይ ማዋል እንዳለባቸው ተገነዘቡ። የፈራረሰውን አፀዱ፣ ብርሃንን እና ግልፅነትን ወደ ቤት አመጡ።አናም ግዋደኛቸውን በጣም አስፈላጊ ሸቀጣ ሸቀጦችን እንዲያመጡ ጠሩ። በስተመጨረሻ ስራቸውን ጨርሰው ሲሰናበቱ፣ ያቺን ወጣም አናት እስከ እምባዋ ጥለዋት ነበር የሄዱት— የምስጋና እና የፍቅር እምባ።

ከዚያ ጊዜ በኋላ፣ የወጣት እናት የጉብኝት ትምህርት አመለካከት ተቀየረ። እንዲህ አለች “ሰዎች የሚጎበኙኝ እኔ ጋር እንዲመጡ ስለተመደቡ ብቻ እንዳልሆነ”“አውቃለሁ”።

አዎን፣ የጉብኝት አስተማሪዎች ወርሃዊ ጉብኝቶችን በማድረግ ታማኝ መሆን አለባቸው፣ አንዱንም ሳይቀሩ “ለምን” ከዚህ ትዕዛዝ ጀርባ እግዝኣብሄርን እና ባልንጀሮቻቸውን እንዲወዱ።

የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ስንንካባከብእናም የኛን መንግስቱን ለመገንባት ድርሻ የምናደርገውን ዝርዝር በማየት፣ የደቀ መዛሙርታዊነትን ጠቃሚ አካልን እናጣለን። የሰማይ አባታችንን ትዕዛዛት በደስታበመኖር የሚመጣውን እድገት እናጣለን።

በደቀመዝሙር መንገድ መራመድ መራራ ተሞክሮ ሊሆን አይገባም። “ከጣፋጮችም በላይ ጣፋጭ ነው።”8 ወደ ታች የሚጫነን ሸክም አይደለም። ደቀ መዛሙርትነት መንፈሳችንን ያነሳል አናም ልቦቻችንንያበራል።በ እምነት ፣ ተስፋ እና ፍቅር ያነሳሳናል። በሐዘን ጊዜያት በጭለማ እና በመንፈስ እርካታ ጊዜያት መንፈሶቻችንን በ ብርሃን ይሞላል።

መከኮታዊ የሆነ ኃይልና ዘላቂ የሆነ ደስታን ይሰጠናል።

ወንጌልን በደስታ መኖር

በወንጌል ውስጥ ያላችሁ እህቶቼ፣ እድሜያችሁ 8 ሆነም 108፣ በእውነት እንድታውቁ እና እንድትረዱ የምፈልገው አንድነገርአለ።

ተወዳችኋል።

እናንተ ለሰማይ ወላጆቻችሁ ውድ ናችሁ።

የብርሀን እና ህይወት ዘለአለማዊ ፈጣሪ ያውቃችኋል! ስለ እናንተ ያውቃል። ይወዳችኋል!

አዎ፣ እግዚአብሔር ዛሬ በዚህች ቀን እና ኁሌም ይወዳችኋል።

መጥፎ ልማዳችሁን እና ድክመታችሁን እስክታሸንፉ ድረስ እናነተን ለመውድድ እየጠበቀ አይደለም። ትግሎቻችሁንሙሉ በመረዳት ይወዳችኋል። ከልብ በመነጨ እና ሙሉ ተስፋ ባለው ፀሎት ወደ እሱ እንደምትመጡ ያውቃል። ሚያድግ ጨለማ መሀል ቢሆንም እንክዋን—የፈዘዘ ብርሃን እና እምነት የያዛችሁበትን ጊዜያት ያውቃል። ሚጠበቅባችሁን ነገር ባላደረጋችሁ እና በወደቃችሁ ጊዜያት የተሰማችሁን ፀፀት ያውቃል። እናም አሁንም ይወዳችኋል።

አናም የእናንተን ውጤታማነት እግዚአብሔር ያቃል፤ ለእናንተ ትንሽ መስለው ቢታዩም፣ እያንዳንዱን ያስባል እንዲሁን ይንከባከባቸዋል። እራሳችሁን ለሌሎች በማቅረባችሁ ይወዳችኋል። እራሳችሁ ችግር ውስጥ ሆናችሁ እንኩዋን ለሌሎችን በመድረሳችሁ እና ከባድ ሸክሞቻቸውን በመሸከም በማገዛችሁ ይወዳችኋል።

ስለናንተ ሁሉ ነገር ያውቃል። በግልፅ ያያችኋል—እንደማንነታችሁ ያቃችኋል። እናም ዛሬ እና ሁለም— ይወዳችኋል።

ብትኳኳሉ፣ ብትለብሱ፣ ፀጉር ብታስገጡ እናም በቆንጆ ሁኔታ ጥፍራችሁን ብትሠሩ እግዚያብሄርን የሚያስጨንቀው ይመስላችኋል? በማህበረ ድህረ ገፅ ላይ ባላችሁ ተከታዮች ብዛት ላይ ተመርኩዞ ለእናንት የሚሰጠው ዋጋ የሚቀይር ይመስላችኋ? አንዳንዶች ጓደኞቻችሁ ካልሆኑ ወይም በፊስ ቡክ እና ትዊተር የማይከተሏችሁ ከሆኑ እናንተ እንድትጨነቁና ትክዝ እንድትሉ የሚፈልግ ይመስላችኋልን? የውጪው የሚማርክ ውበት ወይም ዝነኝነት ዩንቨርስን ለፈጠረው የእናንተ ዋጋ ላይ ትንሽ ልዩነት የሚፈጥር ይመስላችኋል?

ዛሬ በዚች ቀን ያላችሁንማንነታችሁን ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን የከበረ እና ብርሃን ለመሆን ላላችሁ አቅም አና ፍላጎትይወዳችኋል።

ማሰብ ከምትችሉት በላይ፣ መድረሻችሁን እንድታሳኩ—ወደ ሠማይ ቤታቹ በክብር እንድትመለሱ ይፈልጋል።

ይህንንየማሳክያውመንገድየራስንራስወደድመሻቶንአናየማይረቡ ምኞቶችን በመስእዋት እና በአገልግሎት መሰውያው ላይ በመተካት ነው። እህቶች፣በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ኃይል ላይ እምነታችሁን ጣሉ; ህግጋቱን አና ትእዛዛቱን ጠብቁ። በሌላ አባባል---- ወንጌልን በደስታ ኑሩ።

የታደሰ አና የሰፋ ውብ የእግዚአብሔርንፍቅር በህይወታች ውስጥ ተሞክሮ እንድታገኙ፤ እና የእግዚአብሔር ትእዛዛትን ለመማር እምነትን፣ ውሣኔን እንድታገኙ የኔ ፀሎት ነው።

እንደዚ ስታደርጉ፣ ምርጡን ማንነታችሁን--- ትክክለኛ ማንነታችሁን ታገኛላችሁ በማለት ቃል ገባለሁ ። የፃድቆች ሁሉ ጌታየዘላለም እግዚአብሔር ሴት ልጅ መሆን በእውነት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ። ይህንን ምመሰከርላችሁ አና በረከቴን ምተውልችሁ አንደ የጌታ ሐዋርያ ነው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።