2010–2019 (እ.አ.አ)
ብዙ፣ ተባዙ፣ እናም ምድርንም ግዟት
ኤፕረል 2015


ብዙ፣ ተባዙ፣ እናም ምድርንም ግዟት

የሰማይ አባት እንደ እርሱ እንሆን ዘንድ እንድንበዛ፣ እንድንባዛ፣ እና ምድርን እንድንገዛ ሀላፊነት ሰጥቶናል።

የታበርናክል ዘማሪዎች፣ ለአለም አዳኝ ፤እሰጣችሁት አስደሳች መታሰቢያ ስላቀረባችሁት አመሰግናችኋለሁ።

አብ አንድያ ልጅን ሰውን በመልካቸው እንዲፈጥሩ በጠራበት በዚያ ቀን፣ እንዲህ በማለት ልጆቹን ባረከ፣ ’’ብዙ፣ ተባዙ፣ ምድርንም ሙሏት፣ ግዟትም፤ የባህርን አሶች፣ የሰማይን ወፎች፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዟቸው።’’1 በዚህም የሟችነት ጉዞአችን በመለኮታዊ ሀላፊነት እና በረከት ተጀመረ። ለማደግ እና እንደ እርሱ እንሆን ዘንድ፣ እንድንበዛ እና እንድንባዛ እናም እንድንገዛ አፍቃሪው አብ ሀላፊነት እና በረከት ሰጠን።

ወንድሞች እና እህቶች፣በዚህ ከሰዓት ስለሶስቱ መለክታዎ የፍጥረት ፀባያችን አንዳንድ ሀሳቦቼን ከእናንተ ጋር ሳካፍል ፀልታችሁ እና እምነታችህ ከእኔ ጋር እንዲሆን እጋብዝችሃለሁ። ፀሎቴም የአባታችን ሰራን የሆነውን፣ ጉዞአችንን በስኬታማነት እንድንጓዝበት እና መለኮታዊ እጣ ፈንታችንን እንድናገኝ መለኮታዎ ፀባያችንን የማሳድግ ቅዱስ ሀላፊነታችንን በሙሉ እንድንረዳና እንድናሟላ ነው።

መጀመሪያ፣ እግዚአብሔር እንድንባዛ አዘዘን

አንዳንዴ ችላ የሚባለው የመባዛት አስፈላጊ ክፍል የእግዚአብሔርን መንግስት ወደ ምድር የሚያመጣው ነው። አዳኝ እንዳስተማረው፥

“እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለእኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።

“በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።

“ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀመዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።”2

በክርስቶስ ስንኖር ነው እናም ሌሎችን ወደ እርሱ እንዲመጡ በመርዳት “[በራሳችን] ላይ [የእርሱን] ስም [ስንወስድ እናም]…እስከ መጨረሻም [ስናገለግለው]”3 እንባዛለን።

በጊዜያችን፣ ህያው ነቢያት እና ሐዋሪያት በችሎታዎቻችን እና በእድሎቻችን መሰረት በደህንነት ስራ በሙሉ እንድንሳተፍ እያንዳንዳችንን ለመጋበዝ ድምጻቸውን ከፍ አድርገዋል።

ብዙ ፍሬ የሚያመጣው የመመለሱ የመጀመሪያ ቦታም “በልቡ የሚራራ እናም የዋህ” መሆን ነው።4 ከዚያም መንፈስ ቅዱስ ለሚያነሳሳው ተቀባይ በመሆን እና የገባናቸው ቃል-ኪዳናት በሙሉ በማክበር ወደ ክርስቶስ በሙሉ ልብ ለመምጣት እንችላለን።5 የልግስና ስጦታን ለመፈለግና ለመቀበል እናም የራሳችንን ቤተሰቦች፣ ቀዳሚ አያቶች፣ እና አባላት የሆኑ እና ያልሆኑ ጎረቤቶቻችንና ጓደኞቻችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲቀበሉ ለመጋበዝ እንችላለን።

በልግስና መንፈስ ማገልገል ሀላፊነት ሳይሆን ደስታ ነው። ፈተናዎች እምነት የመገንባት እድሎች ይሆናሉ። እኛም “በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገር የእግዚአብሔር [መልካምነት] ምስክር በመሆን [ለመቆም]… እስከ ሞት ምድረስ…” እንችላለን።6

ሁላችንም በደህንነት ስራ በሙሉ መሳተፍ ይገባናል እናም እንችላለን። አዳኝ የሚቀጥለውን ሀላፊነት ከተስፋ ቃል ጋር ሰጥቶናል፥ “እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።”7

ሁለተኛ፣ እግዚአብሔር እንድንባዛ ትእዛዝ ሰጥቶናል

ስጋዊ ሰውነቶቻችን የእግዚአብሔር በረከቶች ናቸው። የተቀበልናቸውም “የሰውን አለሟችነት እና የዘለአለም ህይወት ማምጣት”8 የሆነውን የሰማይ አባትን ስራ ለማሟላት ነው። ሰውነት መለኮታዊ ችሎታችንን ለማግኘት የምንችልበት መንገድ ነው።

ሰውነት የሰማይ አባት ታዛዥ የመንፈስ ልጆች የምድር ህይወትን እንዲቀምሱ የሚያስችል ነው።9 ልጆች መውለድ ሌሎች የእግዚአብሔር የመንፈስ ልጆች የምድር ህይወትን የሚደሰቱበትን እድል ይሰጣቸዋል። ወደ ስጋዊነት የተወለዱት በሙሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ካከበሩ የማደግ እና ከፍ የመደረግ እድል አላቸው።

በወንድ እና በሴት መካከል የሚደረግ ጋብቻ የመባዛት ሀላፊነትን ለማሟላት እግዚአብሔር የሾመው ድርጅት ነው። የአንድ ጾታ ግንኙነት የሚባዛ አይደለም።

በቤተ-መቅደስ የሚተሳሰርና የመተሳሰር ቃልኪዳን የሚከበርበት ህጋዊ ጋብቻ ወላጆችን እና ልጆቻቸውን ከሁሉም የሚሻል የፍቅር አጋጣሚን እና ፍሬአማ ለሆነ ህይወት የሚያዘጋጅ እድል ይሰጣቸዋል። ይህም ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል-ኪዳን የሚኖሩበት በፍጹም የሚስማማ ቦታ ያቀርብላቸዋል።

ለእኛ ባለው ፍቅር ምክንያት፣ የቃል-ኪዳን ጋብቻንና ልጅ የመውለድ በረከቶች ያላገኙ ወይም ማግኘት የማይችሉ ወይም የነዚያን በረከቶች በሙሉ ለመደሰት ራሳቸው ባላደረጉት ምክንያት የማይችሉ፣ በጌታ ሰዓት የሰማይ አባት ለታማኝ ልጆቹ በሙሉ እነዚህን በረከቶች የሚደሰቱበትን መንገድ ሰጥቷል።10

ህያው ነቢያት እና ሐዋሪያት ወደ ዘለአለማዊ ጋብቻ ቃልኪዳን ለመግባት እድል ላላቸው በሙሉ በጥበብ እና በእምነት ወደ ፊት እንዲገፉ ምክር ሰጥተዋል። በአለማዊ ፍላጎት ምክንያት ወይም ባለቤታችን ይሆናል ወይም ትሆናለች ብለን የምንጠብቅ ከፍተኛ ሆኖ ተመራጭ የሚሆኑት በሙሉን ብቁ እንዳይሆኑ በሚያደርግ ሁኔታ የዚያን ቅዱስ ቀን ማዘግየት አይገባንም።

በዘለአለም ጋብቻ ቃልኪዳን ለተሳሰሩት እና ቃልኪዳናቸውን በመጠበቅ በኩል ፍሬአማ ለሆኑት የተሰጠውም የተስፋ ቃል አጥፊው የዘለአለም ግንኙነታቸውን መሰረት ለማዳከም ሀይል በምንም እንደማይኖረው ነው።

ሶስተኛ፣ እግዚአብሔር ምድርን እንድንቆጣጠር ሀላፊነት ሰጠን

ምድርን መቆጣጠር እና የሚኖሩት ነገሮች ሁሉ ላይ ስልጣን መኖር ማለት እነዚህ ነገሮች የእግዚአብሔርን ፍላጎት እንዲያሟሉ እና የልጆቹን አላማዎች እንዲያገለግሉ መቆጣጠር ማለት ነው።11 መቆጣጠርም ሰውነታችንን ለመቆጣጠር መቻል ማለት ነው።12 የእነዚህ ነገሮች እርዳታ እንደሌለው የአደጋ ሰለባ መሆን ወይም እነዚህን ከእግዚአብሔር ፍላጎት ውጪ መጠቀምን እነዚህ አይጨምሩም13

የምድር ነገሮችን የመቆጣጠር ችሎታን ማሳደግ የሚጀመረው የሰውነት ደካማነታችንን እና በክርስቶስና በኃጢያት ክፍያው በኩል ለእኛ የሚገኘውን ሀይል በማወቅ ትህትና ይጀምራል። “ክርስቶስ እንዳለው፥ በእኔ እምነት ካላችሁ እኔ ያስፈልጋል የምለውን ማንኛውንም ነገር ለመስራት ስልጣን ይኖራችኋል።”14 ይህም ሀይል ለእኛ የሚገኘው ለትእዛዛቱ ታዛዥ ለመሆን ስንመርጥ ነው። ችሎታችንን የምንጨምረው የመንፈስ ስጦታዎችን በመፈልግ እና ችሎታዎቻችንን በማሻሻል ነው።

በብዙ የአፍሪካ ቤተሰቦች በሚገኙበት በዝቅተኛ ሁኔታዎች ውስጥ ነበር ያደኩት። ከእነዚህ ጉዳዮች ራሴን ከፍ የማድረግ ችሎታን ያገኘሁት በሚያስቡልኝ ወላጆቼ እርዳታ፣ ጥሩ ትምህርት በመፈለግ እና በማግኘት ነው። ወደፊት ምን እንደምሆን ያለኝ የወደፊት እይታም ለእድገቴ አስፈላጊ ነበር። በኋላም፣ እንደ ወጣት ባልናሚስት፣ ባለቤቴና እኔ በዳግም የተመለሰውን ወንጌል አገኘን፣ ይህም ህይወታችንን በመንፈሳዊ መመሪያ በታላቅ መባረኩን ቀጠለ። እንደ እያንዳንዱ ቤተሰብ፣ ፈተናዎች ነበሩን። ነገር ግን ወደ ጌታ ለእርዳታ ስንመለከት፣ ሰላም እና መፅናኛ የሚያመጣ መልስ አግኝተናል፣ እናም በእነዚህ ስሜቶች አንጥለቃለቅም።

ዛሬ የሰው ዘር የሚያጋጥማቸው ፈተናዎች፣ እንዲሁም ግብረገባዊ አለመሆን፣ የወሲባዊ ነገር ማሳያዎች፣ ጦርነት፣ የአየር ብክለት፣ ሱስ፣ እና ድህነት፣ የሚበዛው በአለም ውስጥ ያሉት አብዛኛዎች በምርጫቸው ወደ እግዚአብሔር ፍላጎት ሳይሆን “ወደ ዲያብሎስ እና ስጋዊ ፍላጎት”15 ስለዞሩ ነው። “ፅድቁን ለመመስረት ጌታን አይፈልጉም፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው በገዛ መንገዱ፣ እናም የጣኦት ቁሳቁስ በሆነው፣ አምሳያውም የአለም በሆ ነው… ምስል ይጓዛል።”16

ነገርግን፣ እግዚአብሔር ልጆቹን በሙሉ የዚህን ህይወት ፈተናዎች እንዲያሸንፉ እና እንዲጸኑ በእነዚህ ቃላቶች ይጋብዛል፥

“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ አለምንና ሰዎችን ስጋ ከመልበሳቸው በፊት የፈጠርኩኝ እኔ ነኝ።

“…ወደ እኔ ብትመለስ፣ እና ድምጼንም ብታደምጥ፣ እና ብታምን፣ እና ለተላለፍካቸውም ነገሮች ንስሀ ብትገባ፣ እና...[በ]አንድያ ልጄ ስም፣ …በውሀ ብትጠመቅ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም ይሰጥሀል፣ እና ሁሉንም ነገሮችን በእርሱ ስም ጠይቅ፣ እና የምትጠይቀውን ማንኛውም፣ ይህም ይሰጥሀል።”17

መለኮታዊ ችሎታቸውን የሚያውቁና በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል የሚገኙትን ሀይል በሙሉ ልባቸው የሚመኩ ታማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በተፈጥሮ ድካማቸው ይጠናከራሉ እናም “ሁሉንም ነገሮች ለማድረግ ይችላሉ።”18 ብዙዎችን በጠላት እስር ውስጥ እንዲገቡ ያደረገውን የክፉን ማታለያ ለመቋቋም ችሎታ ይኖራቸዋል። ጳውሎስ እንዳስተማረው፥

“…ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።”19

“እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።”20

የሰማይ አባት እንደ እርሱ እንሆን ዘንድ እንድንበዛ፣ እንድንባዛ፣ እና ምድርን እንድንገዛ ሀላፊነት ሰጥቶናል። እያንዳንዳችን፣እንደግል ምርጫችን፣ እንደ እርሱ በመሆን እንድናድግም እርዳታ ሰጥቶናል። መለኮታዊ ፍጥረታችን አይታ በመመራት፣ መለኮታዊ ልዩ መብታችንን በሙሉ እየተቀበልን፣ እና መለኮታዊ እጣፈንታችንን እንድናሟላ ህይወታችንን እንድንኖር እጸልያለሁ።

የአብ እግዚአብሔርን እና የውድ ልጁ፣ የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስን እውነታነት፤ ስለግርማዊው የደህንነት እቅድ፤ እና ዛሬ በምድር ላይ ባሉት በህያው ነቢያት፣ እንዲሁም በቶማስ ኤስ ሞንሰን፣ ላይ ስላሳረፈው ቁልፎች እመሰክራለሁ። የበረከቶቹን ሙላት ለመቋደስ ሀይል እንዲኖረን የምጸልየው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።