2010–2019 (እ.አ.አ)
የቤተመቅደስ በረከቶች
ኤፕረል 2015


የቤተመቅደስ በረከቶች

ቤተመቅደስ ስንካፈል፣ የመንፈሳዊነት ስፋት እና የሰላም ስሜት ወደ እኛ ሊመጣ ይችላል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ሀሳባችን የአለም አዳኝ ወደሆነው በሚዞርበት በዚህ የፋሲካ ማለዳ ከእናንተ ጋር በመሆኔ ምን ያህል አመስጋኝ ነኝ። ለእያንዳንዳችሁ ፍቅሬን እና ሰላምታዬን አደርሳለሁ እና ቃላቶቼን የሰማይ አባት ያነሳሳ ዘንድ እፀልያለሁ።

በዚህ ኮንፈራንስ የቤተክርስቲያን ፕሬዘዳንት እንድሆን ድጋፍ ያገኘሁበት ሰባተኛ አመት ሆኗል። ስራ የበዛባቸው አመታት ነበሩ፣ በጥቂት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ብቻ ሳይሆን በማይቆጠሩ በረከቶች የተሞሉ ነበሩ። በጣም ከአስደሳች እና ቅዱስ በረከቶች መካከልለአዲስ ቤተመቅደሶችን ቡራኬ መስጠት እና ለቆዩት ቤተ መቅደሶች በድጋሚ ቡራኬን መስጠትነበር።

በጣም በቅርብ፣ አሁን ባለፈው ህዳር የሚያምረውን አዲስ የኤሪዞና ፎኒክስ ቤተመቅደስ ቡራኬ የመስጠት እድል ነበረኝ። ፕሬዘዳንት ዴይተር ኤፍ ኡክዶርፍ፣ ሽማግሌ ዳሊን ኤች ኦክስ፣ ሽማግሌ ሪቻርድ ጄ ማየንስ፣ ሽማግሌ ላይን ጂ ሮቢንስ፣ እና ሽማግሌ ኬንት ኤፍ. ሪቻርድስ አብረውኝ ነበሩ። ከቡራኬው በፊት ባለው ምሽት፣ከቤተመቅደስ አውራጃ 4000 የሚሆኑ ወጣቶቻችን በአስደናቂ የባህል ክብረበአል የሚያምር ትእይንት አቀረቡ። በቀጣዩ ቀን በሶስት ቅዱስ እና አነሳሽ ክፍለ ጊዜያት ለቤተመቅደሱ ቡራኬ ተሰጠ።

የቤተመቅደስ ግንባታዎች የቤተክርስቲያን እድገት በጣም ግልፅ ማሳያ ናቸው። በአሁኑ ወቅት 144 በአገልግሎት ላይ ያሉ ቤተመቅደሶች በአለም ላይ አሉን፣ 5 እንደገና እየተገነቡ እና ሌላ 13 አዲስ እየተሰሩ ነው። በተጨማሪም፣ ቀደም ብለው የተዋወቁ 13 ቤተመቅደሶች ግንባታ ከመጀመሩ በፊት በተለያየ የዝግጅት ደረጃ ላይ ናቸው። በዚህ አመት 2 ቤተመቅደሶችን እንደ ገና ቡራኬ ለመስጠት እና 5 ለመጨረስ የታቀዱ አዲስ ቤተመቅደሶችን ቡራኬ ለመስጠት እናስባለን።

ባለፉት ሁለት አመታት፣ ከዚህ በፊት እንደሚገነቡ የታወጁትን ቤተመቅደሶች በመፈጸም ላይ ጥረታችንን እያተኮርን እያለን፣ ለተጨማሪ ቤተመቅደሶች እቅዶችን አቁመን ነበር። በዚህ ጠዋት ግን በሚቀጥሉት ሶስት ቦታዎች ስለሚገነቡ ቤተመቅደሶች ለማስተዋወቅ እደሰታለሁ። አቢጃን፣ አይቨሪ ኮስት፣ ፖርት አኡ ፕሪንስ፣ ሄቲ፣ እና ባንኮክ ታይላንድ። በእነዚህ አካባቢዎች፣ እና ቤተመቅደሶች በሚገኙባቸው በማንኛውም በአለም አቀፍ ቦታዎች ለሚገኙ ታማኝ አባላት ምን አይነት አስደናቂ በረከቶች እየጠበኳቸው ነው።

ፍላጎትን መመዘን እና ለተጨማሪ ቤተመቅደሶች ቦታ መፈለግ ቀጣይነት ያለው ስራ ነው፣ ምክንያቱም የሚቻለውን ያህል ሁሉም አባላት ያለ ትልቅ የጊዜ እና የወጪ መስዋእትነት ቤተመቅደስ እንዲካፈሉ እንፈልጋለን። ከዚህ በፊት እንዳደረግነው፣ በዚህ ጉዳይ ውሳኔዎች ሲተላለፉ ለእናንተ እናሳውቃለን።

ቤተመቅደሶችን ሳስብ፣ በእነርሱ ውስጥ ስለምንቀበላቸው በረከቶች አስባለሁ። በቤተመቅደስ በሮች ስንገባ፣ የአለምን ጥፋት እና ግራ መጋባት ከኋላችን እንተዋለን። በዚህ ቅዱስ ቦታ ውስጥ፣ ውበት እና ስርአትን እናገኛለን። ለነብሳችን እረፍት እና ከህይወታችን ሀሳቦች ፋታን እናገኛለን።

ቤተመቅደስ ስንካፈል፣ የመንፈሳዊነት ስፋት እና የሰው ልብ ውስጥ ሊመጣ ከሚችል ከማንኛውም ሌላ ስሜት የሚልቅ የሰላም ስሜት ወደ እኛ ሊመጣ ይችላል። አዳኝ የተናገረውን እነዚህ ቃላት እውነተኛ ትርጉም እናገኛለን፤ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፣… ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።”1

ይሄ ሰላም የትኛውም ልብ ውስጥ ሊሰራጭ ይችላል—የተረበሹ ልቦች፣ በሀዘን የተቃጠሉ ልቦችን፣ ግራ መጋባት የሚሰማቸውን ልቦች፣ ለእርዳታ የሚማፅኑ ልቦችንም ቢሆን።

በቅርብ አንድ ወጣት ወንድ ልቡ ለእርዳታ በመማፀን ቤተመቅደስ ሲካፈል እራሴ አስተዋልኩ። ከብዙ ወራት በፊት በደቡብ አሜሪካ ሚስኦን ውስጥ ለማገልገል ጥሪ ተቀብሏል። ቢሆንም፣ ለረጅም ጊዜ ቪዛው ስለዘገየ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንዲያገለግ እንደገና ተመደበ። በዋናው ጥሪ ቦታ ላይ ማገልገል ባለመቻሉ ቢበሳጭም፣ በአዲሱ ጥሪው ጠንክሮ ሰራ፣ በአቅሙ የተቻለውን ያህል ለማገልገል በቁርጠኝነት ሰራ። ሆኖም፣ ወንጌል ከማካፈል ይልቅ ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ የበለጠ ፍላጎት ያላቸው በመሰለው ሚስኦኖች ባጋጠመው አሉታዊ ተሞክሮ ተስፋ ቆረጠ።

ከጥቂት አጭር ወራት በኋላ ይሄ ወጣት በከፊል ፓራላይዝ ባደረገው ከባድ የጤና ችግር ተሰቃየ፣ እና በህክምና ፍቃድ ወደ ቤቱ ተላከ።

ከትቂት ወራት በኋላ ወጣቱ ሙሉ በሙሉ ተፈወሰ፣ እና ፓራላይዙ ተወገደ። እንደገና እንደ ሚስኦናዊ ማገልገል እንደሚችል ተነገረው፣ ያም የየቀን ፀሎቱ በረከት ነበር። አናዳጁ ነገር ትቶት ወደመጣው ተመሳሳይ ሚስኦን መመልስ ነው፣ ያም የአንዳንድ ሚስኦናዊዎች ባህሪያት እና አመለካከቶች መሆን ካለባቸው ያያነሰ ንቁ እንደነበር የተሰማው ቦታ ተመልሶ እንደሚሄድ ነበር።

ቤተመቅደስ የመጣው እንደ ሚስኦናዊ ጥሩ ተሞክሮ ሊኖረው እንዲችል መፅናናት እና ማረጋገጫን ለመሻት ነበር። ይሄ የቤተመቅደስ ጉብኝት ወንድ ልጃቸው ያስፈለገውን እርዳታ ይሰጠው ዘንድ ወላጆቹም ፀልይው ነበር።

ክፍለጊዜውን ተከትሎ ወጣቱ ወደ ሰሌሽያል ክፍል ሲገባ፣ ወንበር ላይ ተቀመጠ እና ከሰማይ አባቱ ምሬትን ለማግኘት መፀለይ ጀመረ።

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ሰሌሽያል ክፍል የገባው ሌላው ወጣት ወንድ ስሙ ላንዶን ነው። ወደ ክፍሉ እየተራመደ ሲገባ፣ አትኩሮቱ ወዲያው ወንበር ላይ ወደተቀመጠው ወጣት ተስቦ ነበር፣ አይኖቹን ጨፍኗል እና በእርግጥም እየፀለየ ነው። ላንዶን ከወጣቱ ጋር መነጋገር እንዳለበት ያልተሳሳተ መነሳሳት ተቀበል። ላለመረበሽ በማመንታት፣ ለመጠበቅ ወሰነ። ብዙ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ እና ወጣቱ አሁንም በጸሎት ላይ ነበር፣ ላንዶን መነሳሳቱን ከዚያ በላይ ማስተላለፍ እንደማይችል አወቀ። ወደ ወጣቱ ጠጋ አለ እና በዝግታ ትከሻውን ነካው። ወጣቱ አይኑን ከፈተ፣ በመረበሹ ተደናገረ። ላንዶን በዝግታ እንዲህ አለ፣ “ከአንተ ጋር መነጋገር እንዳለብኝ ተሰማኝ፣ ለምን እንደሆነ በትክክል ባላውቅም።”

መነጋገር ሲጀምሩ፣ ወጣቱ የልቡን አውጥቶ ለላንዶን ነገረው፣ ስለ ሁኔታው እና ሚስኦኑን አስመልክቶ መፅናናት እና ብርታት ለመቀበል ስላለው ፍላጎት አብራራ። ላንዶን፣ ከአንድ አመት በፊት ከነበረው ስኬታማ ሚስኦን ተመልሶ የነበረ ነው፣ ስለእራሱ የሚስኦን ተሞክሮ ነገረው፣ ያጋጠሙትን ችግሮች እና ጭንቀቶች፣ ወደ ጌታ ለእርዳታ የዞረበትን ሁኔታ፣ እና የተቀበላቸውን በረከቶች ነገረው። ቃላቶቹ አፅናኝ እና አረጋጊ ነበሩ፣ እና ለሚስኦኑ ያለው ስሜት ተላላፊ ነበር። ቀስ በቀስ፣ ፍርሀቱ ጋብ ሲል፣ የሰላም ስሜት ወደ ወጣቱ መጣ። ፀሎቱ መመለሱን ሲያስተውል ጥልቅ አመስጋኝነት ተሰማው።

ሁለቱ ወጣት ወንዶች አብረው ፀለዩ፣ እና ላንዶን ለመሄድ ተዘጋጀ፣ ወደ እርሱ የመጣውን መነሳሳት በማዳመጡ በመደሰት። ለመሄድ ሲቆም፣ ወጣቱ ላንዶንን እንዲህ ጠየቀው፣ “የት ነበር ሚስኦንህን ያገለገልከው?” እስከዚህ ጊዜ፣ ያገለገሉበትን ሚስኦን ስም አንዳቸውም ለሌላው አላነሱም ነበር። ላንዶን የሚስኦንኑን ስም መልስ ሲሰጥ፣ በወጣቱ አይኖች ላይ እንባዎች መነጩ። ላንዶን ያገለገለው ሚስኦን ወጣቱ ከሚመለስበት ጋር አንድ ነው!

በቅርብ ለእኔ በመጣ ደብዳቤ፣ የወጣቱን የመጨረሻ ቃለት ላንዶን ለእኔ አካፈለኝ፤ “የሰማይ አባት እንደሚባርከኝ እምነት ነበረኝ፣ ነገር ግን ከእራሴ ሚስኦን ሰው እንዲረዳኝ ይልካል ብዬ በፍፁም አላሰብኩም። ሁሉም መልካም እንደሚሆን አሁን አውቄአለሁ።”2 የቀና ልብ ትሁት ጸሎት ተሰማ እና ተመለሰ።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በህይወታችን ፈተናዎች ይኖሩብናል፤ መከራዎች እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይኖሩብል። ወደ ቤተመቅደስ ስንሄድ፣ እዚያ የምንፈፅማቸውን ቃል ኪዳኖች ስናስታውስ፣ እነዚያን ፈተናዎች ለማለፍ እና መከራዎችን ለመቋቋም በተሻለ ሁኔታ እንችላለን። በቤተመቅደስ ሰላም ማግኘት እንችላለን።

የቤተመቅደስ በረከቶች ዋጋቸው ሊገመት አይችልም። በህይወቴ ሁል ቀን አመስጋኝ ከሆንኩበት አንዱ ተወዳጇ ሚስቴ፣ ፍራንሲስ፣ እና እኔ በቅዱሱ መሰዊያ ተንበርክከን ለዘለአለም የሚያስረንን ቃልኪዳን ስንገባ የተቀበልነው ነው። እርሷ እና እኔ እንደገና አንድ ላይ እንደምንሆን ባለኝ እውቀት ከማገኘው ሰላም እና መፅናናት የበለጠ ውድ በረከት ለእኔ የለም።

ቤተመቅደስ የማምለክ መንፈስ እንዲኖረን፣ ለእርሱ ትእዘዛዛት ታዛዥ እንድንሆን፣ እና የጌታችንን እና የአዳኛችንን፣ የኢየሱስ ክርስቶስን መንገድ በጥንቃቄ እንድንከተል የሰማይ አባታችን ይባርከን። እርሱ ቤዛችን እንደሆነ እመሰክራለሁ። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። እርሱ በዚያ በፋሲካ ማለዳ ከመቃብር የመጣው ነው፣ ለእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ የዘለአለም ህይወት ስጦታን አምጥቷል። በዚህ በሚያምር ቀን፣ ያንን የክንውን ክስተት ስናከብር፣ ለሰጠን ታላቅ እና ድንቅ ስጦታው የምስጋና ፀሎት እናቅርብ። ይሄ ይሆን ዘንድ፣ በቅዱስ ስሙ እፀልያለሁ፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ዮሀንስ 14፥27

  2. በቶማስ ኤስ. ሞንሰን እጅ የሚገኝ ደብዳቤ