2010–2019 (እ.አ.አ)
የአዋጁ ጠባቂዎች
ኤፕረል 2015


የአዋጁ ጠባቂዎች

በድፍረት በመቆም እና የጋብቻ፣ የወላጅነት እና የቤት ጠባቂ በመሆን የእግዚአብሔርን መንግስት በመገንባት እንርዳ።

የዚህ የልጃገረዶች እና የሴቶች ድንቅ ስብስብ አካል መሆን ምን አይነት መታደል እና አስደሳች ነው። በአንደነት እና በፍቅር እንደ ሴቶች በዚህ አመሻሽ ላይ በጋራ በመሰብሰባችን ምነኛ የተባረክን ነን።

ምስል
Old portrait of Marie Madeleine Cardon

በቅርብ ቀን ከቤተሰቦቿ ጋር በዳግም የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በ1850(እ.አ.አ) በጣልያን ውስጥ እንዲያገለግሉ በተጠሩት የመጀመሪያ ሚስዮኖች ስለተቀበለችውየመሪ ማደሊን ካርደንን ታሪክ አነበብኩኝ።ስትጠመቅ የ17 ወይም የ18 አመት ወጣት ሴት ነበረች። አንድ እሁድ፣ በጣልያን ሰሜናዊ ተራራዎች ላይየአምልኮት አገልግሎት በቤታቸው ውስጥሲያካሂዱ፣ የአካባቢው ቄሶችንየሚጨምርየተቆጡ የወንዶች ስብስብ በቤቱ ዙሪያ ከበው መጮኸ እና ሚስዮኖቹ ወደ ውጪ እንዲወጡ መጣራት ጀመሩ።አካላዊ ጥቃት ለማድረስ ፈልገው እንጂ፣ ወንጌሉን ለመማር ጓግተው አይመስለኝም።ሰዎቹን ለመጋፈጥ ወጣቷ መሪ ነበረች የወጣችው።

አረመኔ ጩኸታቸውን እና ሚሲዮኖቹን እንዲወጡ ማዘዛቸውን ቀጠሉ። መሪ መጽሐፍ ቅዱሷን በእጇ ወደ ላይ አነሳች እና እንዲሄዱ አዘዘቻቸው። ሚስዮኖቹ በጥበቃ ስር እንዳሉ እና ከፀጉራቸው አንዲት ፀጉር እንኳን መጉዳት እንደማይችሉ ነገረቻቸው።የገዛ ቃሎቿን አድምጡ፥“ሁሉም በመገረም ቆሙ። …እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነበር። እነዛን ቃሎች በአፌ ውስጥ አኖረ፣ ባይሆን ኖሮ አልናገራቸውም ነበር። ወዲያው ሁሉም ነገር ፀጥ አለ። ያኛው ጠንካራ አስፈሪ የወንዶች አካል ከደካማ፣ የሚንቀጠቀጥ ነገር ግን ፍርሃት አልባ ከነበረችው ልጃገረድ ፊት እረዳት አልባ ሆኖ ቆመ።”ቄሶቹ ሰዎቹን እንዲሄዱ ጠየቁ፣ እነሱም በፀጥታ በእፍረት፣ በፍርሃት እና በሃዘን ሄዱ።1

ያቺን ደፋር ወጣት ሴት እንደብዙዎቻችሁ ተመሳሳይ እድሜ ያላትን ከሰዎቹ ፊትለፊት በመቆም እና አዲስ የተገኘውን እምነቷን በድፍረት እና በታላቅ እምነት ስትጠብቅ መሳል አትችሉምን?

እህቶች፣ ጥቂቶቻችን የተቆጡ ሰዎች ሊያጋጥሙን ይችላሉ፣ ነገር ግን በዚህ አለም ውስጥ እየተካሄደ የሚገኝ ብዙ የምንወዳቸው እና መሰረታዊ የሆኑ ትምህርቶቻችን በጥቃት ላይ ያሉ ጦርነት አለ። ለየት ባለ ሁኔታ ስለ ቤተሰብ ትምህርት ነው እየተናገርኩ ያለሁት። የቤት ቅድስና እና የቤተሰብ አስፈላጊ አላማዎች በጥያቄ ላይ፣ በትችት እና በተቻለው መንገድ በጥቃት ላይ ይገኛሉ።

ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሂንክሊ “ቤተሰብ፥ ለአላም አዋጅ”ን ከ20 አመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያነቡ፣ ለዚህ ራዕያዊ ሰነድ ግልፅነት፣ ቀላልነት እና እውነት ዋጋ ሰጠነው እናም አመስጋኝ ሆንን።ከሚዲያ፣ ከኢንተርኔት፣ ከጠበብቶች፣ ከቲቪ እና ፊልሞች እንዲሁም ከህግ አውጪዎች ወደ እኛ የሚመጡትን የአለማችንን አዳዲስ ትምህርቶች ወይም ፍልስፍናዎች በምን አይነት መስፈርት እንደምንፈርድ ለማወቅ እነዚህን መሰረታዊ አዋጆች በዛሬ አለማችን ውስጥ ምን ያህል እንደምንፈልገው በዛ ሰአት ትንሽ ነበር የተረዳነው። የቤተሰብ አዋጅ የአለምን ፍልስፍናን ለመፍረድ እንደ መለኪያ ሆኖልናል እናም በእዚህ መግለጫ ውስጥ የተቀመጡት መርሆች ዛሬ እውነት እንደሆኑ ሁሉ ከ20 አመታትም በፊት በእግዚአብሔር ነብይ ሲሰጡን እውነት እንደነበሩ እመሰክራለው።

አንድ ግልፅ የሆነን ነገር ልጠቁም? ለማንም ሰው ሕይወት እንደታቀደው አይሄድም እናም ሁሉም ሴቶች አዋጁ የሚገልፀውን እንደማይለማመዱ በደምብ እናውቃለን። የጌታን መንገድ መረዳት እና ማስተማር እንዲሁም በተቻለን አቅም ያንን መንገድ ከግብ ለማድረስ መጣርም ጠቃሚ ነው።

እያንዳንዳችን በዕቅዱ ውስጥ የምንጫወተው ድርሻ አለ እናም እያንዳንዳችን በጌታ አይኖች ስር በእኩልነት ነው የምንታየው። አፍቃሪው የሰማይ አባት ፃድቅ ምኞታችንን እንደሚያውቅ እና በእምነት ቃል-ኪዳናቸውን ከሚጠብቁ ሰዎች ምንም ነገር ወደ ኋላ እንደማይዘው፣ ቃል-ኪዳኖቹን እንደሚጠብቅ ማወቅ አለብን። የሰማይ አባት ለእያንዳንዳችን ተልዕኮ እና ዕቅድ አለው፣ ነገር ግን የራሱ የጊዜ ሰሌዳም አለው።በዚህ ሕይወት ውስጥ ከባዱ ፈተና በጌታ የጊዜ አቆጣጠር ላይ እምነት ማድረግ ነው።ቃል-ኪዳን ጠባቂዎች፣ ለጋሾች እና ሕይወታችን በምንም አይነት መንገድ ቢጓዝም መንግስቱን የሚገነቡ ፃድቅ ሴቶች እንድንሆን የሚረዳንን አማራጭ የሆነ ዕቅድ በአዕምሮአችን ውስጥ መያዙ መልካም ሃሳብ ነው።

በዚህ በ20ኛው የቤተሰብ አዋጅ አከባበር ወቅት፣ ለሁላችንም የቤተክርስቲያን ሴቶች የ“ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅ” ጠባቂዎች እንድንሆን ጥሪ አቀርባለው።ልክ እንደመሪ ማደሊን ካርደን ሚስዮኖቹን እና አዲስ የተገኙትን እምነቶቿን በድፍረት አንደጠበቀች ሁሉ ምንም እንኳን አለም እነዚህ መርሆች ያረጁ፣ የሚገድቡ እና ጥቅም የሌላቸው መሆናቸውን በጆሮዎቻችን እየጮኸብን ቢሆንም ስለ ጋብቻ፣ ስለ ቤተሰቦች፣ ስለ ወንዶች እና ሴቶች መለኮታዊ ሚናዎች እንዲሁም ቤቶች እንደተቀደሱ ቦታዎች ስለመሆናቸው አስፈላጊነት የሚገልፁ የጌታን የተገለፁ ትምህርቶችን በድፍረት መጠበቅ ያስፈልገናል። እያንዳንዱ ሰው የጋብቻ ሁኔታቸው ወይም የልጆች ብዛት ምንም ይሁን ምን፣ በቤተሰብ አዋጅ ውስጥ ለተገለፀው የጌታ ዕቅድ ጠባቂዎች መሆን ይችላሉ።የጌታ ዕቅድ ከሆነ፣ የእኛም ዕቅድ መሆነ አለበት! ወደዚህ ሕይወት ከመምጣታችን በፊት የተስማማንበት እና የተቀበልነው ዕቅድ ነው።

በአዋጁ ውስጥ ፅኑ ጠባቂዎች ይፈልጋሉ ብዬ የማስባቸው ሶስት መርሆች ይስተማራሉ። የመጀመሪያው በወንድ እና በሴት መካከል ያለ ጋብቻ ነው። በቅዱሳት መጽሐፍ ውስጥ ይሄን ተምረናል፣ “ነገር ግን በጌታ ዘንድ ሴት ያለ ወንድ ወንድም ያለ ሴት አይሆንም።”2 የክህነት ሙሉ በረከቶችን ማግኘት ለሚፈልግ ማንኛቸውም ሰዎች፣ በጌታ ቤት ውስጥ የሚታተሙ፣ በፅድቅ በጋራ የሚሰሩ እና ለቃል-ኪዳናቸው ታማኝ ሆነው የሚቆዩ ባል እና ሚስት መኖር አለባቸው። ይህ ጌታ ለልጆቹ ያለው ዕቅድ ነው እናም ጌታ ያወጀውን ነገር ምንም አይነት የህዝብ ውይይት ወይም ትችት አይቀይረውም። ፅድቅ ጋብቻዎችን እንደ ምሳሌ መውሰዳችንን መቀጠል አለብን፣ ያንን በረከት በሕይወቶቻችን ውስጥ መሻት አለብን እናም ቀስ ብሎ ቢመጣም እምነት ሊኖረን ይገባል።የተለየ አመለካከት ላላቸው ሰዎች ፍቅር እና ርህራሄ እያሳየን ጌታ እንደተረጎመው የጋብቻ ጠባቂዎች እንሁን።

የጥበቃ ድምፃችንን የሚጠራው ቀጣዩ መርህ የእናቶችን እና የአባቶችን መለኮታዊ ሚናዎች ማክበር ነው። በዚህ ሕይወት ውስጥ ከፍ አድርገው እንዲያልሙ ልጆቻችንን በጉጉት እናስተምራለን። ሴት ልጆቻችን የሚያስቡትን ማንኛውንም ነገር የማሳካት እና የመሆን አቅሙ እንዳለቸው ማወቃቸውን ማረጋገጥ እንፈልጋለን። ማወቅ፣ መማር፣ ተሰጥኦ ያላቸው መሆን እንደሚወዱ እና ምናልባት ቀጣይ ሜሪ ኩሪ ወይም እላይዛ አር. ስኖ እንደሚሆኑ ተስፋ እናደርጋለን።

ወንድ እና ሴት ልጆቻችንን በዚህ ሕይወት ውስጥ ከአባት እና ከእናት የበለጠ ክብሮች፣ የበለጠ የተከበረ መሃረጎች እና የበለጠ ጠቃሚ ሚናዎች እንደሌሉ እናስተምራቸዋለን? ልጆቻችንን በዚህ ሕይወት ውስጥ ለተሻለ ነገር እንዲደርሱ ስናበረታታ እናቶች እና አባቶች በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ የሚጫወቱትን ሚናዎች እንዲያከብሩ እና እንዲያወድሱም ጭምር እንደምናስተምራቸው ተስፋ አደርጋለው።

ታናሽ ልጃችን አቢ፣ ለእናትነት ሚና እንደ ጠባቂ ለመቆም ለየት ያለ እድል አየች። አንድ ቀን ከልጆቿ ትምህርት ቤት ስለ ስራ ቀን ዘገባዎች በትምህርት ቤት ውስጥ እንደሚኖራቸው ማስታወቂያ አገኘች። ወላጆች ወደ ትምህርት ቤቱ መጥተው ስለ ስራዎቻቸው ማስተማር ከፈለጉ ማመልከቻ እንዲያስገቡ ተጋብዘው ነበር። አቢ ልጆቹን እናት ስለመሆን መጥታ ለማስተማር ማመልከቻ መላክ ተሰማት። ከትምህርት ቤቱ መልስ አልሰማችም እናም የስራ ቀኑ እየቀረበ ሲመጣ፣ ማመልከቻው ጠፍቶባቸው ይሆናል ብላ በማሰብ መጨረሻ ላይ ለትምህርት ቤቱ ስልክ ደወለች። አዘጋጆቹ አቢ በስራ ቀን ስልጠናው መጨረሻ ላይ መጥታ ንግግር እንድታደርግ የተስማሙ ሁለት አስተማሪዎችን ፈልገው አገኙላት።

ለልጆቹ በጣም በሚያስቅ አገላለፅ፣ አቢ ከብዙ ነገሮች መካከል እንደ እናት ስለ መድሃኒት፣ ስለ ስነ-ልቦና፣ ሰል ሐይማኖት፣ ስለ ትምህርት፣ ስለ ሙዚቃ፣ ስለ ስነ-ጽሑፍ፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ ገንዘብ አያያዝ፣ ስለ ማስጌጥ፣ ስለ የፀጉር ፋሽን፣ ስለ ሹፍርና፣ ስለ ስፖርት፣ ስለ ምግብ አበሳሰል እና ብዙ ነገሮችአዋቂ መሆን እንደሚጠበቅባት አስተማረቻቸው። ልጆቹ በጣም ነበር የተደነቁት። እያንዳንዱን ልጆች የአመሰግናለው ደብዳቤ በመፃፍ በየቀኑ ለሚቀበሉት የፍቅር ተግባር አገልግሎት ምስጋና በማቅረብ እናታቸውን እንዲያስታውሱ በማድረግ ጨረሰች። አቢ ልጆቹ እናታቸውን በሙሉ አዲስ ብርሃን እንደተመለከቱ እና እናት ወይም አባት መሆን ታላቅ ዋጋ ያለው መሆኑን እንዳዩ ተሰማት። በዚህ አመትም ለማካፈል አመልክታ ለስድስት ክፍሎች እንታቀርብ ተጋብዛ ነበር።

ምስል
Sister Oscarson's daughter, Abby, holding a portrait of her children

አቢ ስለ ልምዷ ይህን አለች፥ “በዚህ አለም ውስጥ ለአንድ ልጅ ወላጅ መሆን ሁለተኛ ስራ ወይም አንዳንድ ጊዜ ችግር ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰቡ ቀላል መስሎ ይሰማኛል። እያንዳንዶቹልጆችለወላጆቻቸው በጣም ጠቃሚ ቀዳሚ ነገሮችእንደሆኑ እንዲሰማቸው እፈልጋለው እና ምናልባት ወላጅ መሆን እንዴት ጠቃሚ እንደሆነ መንገር ወላጆቻቸው ለእነሱ የሚያደርጉትን ነገሮች ሁሉ እንዲያውቁ እና ለምን እንደሚያደርጉት እንዲያውቁ ይረዳቸዋል ብዬ አስባለው።”

ውድ ነብያችን፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን፣ ሴቶችን እና እናትነትን በተለይም የራሳቸውን እናት የማከበር ድንቅ ምሳሌ ናቸው። ምድራዊ እናታችንን በማስመልከት ይህን ብለዋል፥ “እያንዳንዳችን ይህን እውነታ ዋጋ እንስጠው፤ አንድ ሰው እናትን እረስቶ እግዚአብሔርን ማስታወስ አይችልም። አንድ ሰው እናትን አስታውሶ እግዚአብሔርን መርሳት አይችልም። ለምን? ምክንያቱም፣ እነዚህ ቅዱስ ሰዎች፣ እግዚአብሔር እና ምድራዊ እናታችን፣ በፍጥረት ውስጥ፣ በፍቅር ውስጥ፣ በመስዋዕትነት ውስጥ፣ በአገልግሎት ውስጥ ወላጆች እንደ አንድ ናቸው።”3

መቆም እና መጠበቅ ያለብን የመጨረሻው መርህ የቤት ቅድስና ነው። አንዳንድጊዜ ከፌዝ ጋር የሚነገርለትን ስያሜ መውሰድ እና ማጉላት ያስፈልገናል። ቤት ሰሪ የሚለው ስያሜ ነው። ሁላችንም ሴቶች፣ ወንዶች፣ ወጣቶቸ እና ልጆች ያላገባን ወይም ያገባን፣ ቤት ሰሪዎች ሆነን መስራት እንችላለን።“ቤታችንን” እንደ መጠለያ፣ ቅድስና እና ደህንነት ቦታዎች አድርገን “መስራት” አለብን። ቤቶቻችን የጌታ መንፈስ በታላቅ መትረፍረፍ የሚሰሙበት እና ቅዱሳት መጽሐፍ እና ወንጌል የሚጠኑበት፣ የሚማሩበት እና የሚኖሩበት መሆን አለባቸው። ሁሉም ሰዎች እራሳቸውን እንደ ፃድቅ ቤት ሰሪዎች ቢመለከቱ በአለም ውስጥ ምን አይነት ለውጥ ያመጣ ነበር። ቤትን በቅድስና ከቤተ-መቅደስ ቀጥሎ እንዳለ ቦታ እንጠብቀው።

እህቶች፣ በዚህ በኋለኛው ቀኖች ውስጥ ሴት ስለሆንኩኝ አመስጋኝ ነኝ። በአለም ውሰጥ ሌላ የሴቶች ትውልድ የሌላቸውን እድሎች እና ችሎታዎች አሉን። በድፍረት በመቆም እና የጋብቻ፣ የወላጅነት እና የቤት ጠባቂ በመሆን የእግዚአብሔርን መንግስት በመገንባት እንርዳ። ጌታ ዕቅዱን የምንጠብቅ እና የሚመጡትን ትውልዶች የእርሱን እውነቶች የምናስተምር ደፋር፣ ፅኑ እና የማንናወጥ ጦረኞች እንድንሆን ይፈልገናል።

የሰማይ አባት እንደሚኖር እና እያንዳንዳችንን እንደሚወደን እመሰክራለው። ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን እና ቤዛችንነው። ይህን ምስክርነት የምተውላችሁበኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. See Marie Madeline Cardon Guild, “Marie Madeline Cardon Guild: An Autobiography,” cardonfamilies.org/Histories/MarieMadelineCardonGuild.html; see also Marie C. Guild autobiography, circa 1909, Church History Library, Salt Lake City, Utah.

  2. 1 ቆሮንጦስ 11፥11.

  3. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን, “Behold Thy Mother,” Ensign, ጥር 1974, 32.