2010–2019 (እ.አ.አ)
ቤታችንን በብርሃን እና በእውነት መሙላት
ኤፕረል 2015


ቤታችንን በብርሃን እና በእውነት መሙላት

እኛ እና ቤተሰቦቻችን የአለምን ጫናዎች ለመቋቋም፣ በብርሃን እና በወንጌል እውነት መሞላት አለብን።

እነኚህን ቤተሰቦች ያንን ቅዱስ እውነት ሲያስተምሩ ሳይ ልቤ በመንፈስ ይሞላል፣ “ቤተሰብ ከእግዚያብሄር ነው።” የሚያነሳሳ መዝሙር በብርሃን እና በእውነት እየሞላን የመንፈስን ሹክሹክታ ሊያሰሙን ከሚችሉ መንገዶች አንዱ ነው።1

ምስል
Woman with 1 can of soda that is crushed and one that is not.

ከብዙ አመታት በፊት በነበረኝ ተሞክሮ ምክንያት በብርሃን እና በእውነት መሞላት በተለይ ለኔ ጠቃሚ ሆኗል። የወጣት ሴቶች አጠቃላይ ቦርድ አባላት በመንፈሳዊ ጠንካራ ቤተሰቦችን እና ቤቶችን ስለመፍጠር ያስተማሩበት ስብሰባ ላይ ተገኘሁ። ይህንን በእይታዊ ለማሳየት፣ የወጣት ሴት መሪ ሁለት የለስላሳ ጣሳዎችን ከፍ አድርጋ ያዘች። በአንድ እጇ ባዶ የነበረውን ጣሳ ይዛለች በሌላ እጇ ደግሞ ያልተከፈተ እና ሙሉ ለስላሳ ያለውን ይዛለች። መጀመሪ፣ ባዶውን ጣሳ በእጇ ጨመቀችው፤ መጨማደድ ጀመረ ከዛም በጫናው ስር ወደቀ። ቀጥሎ፣ በሌላ እጇ፣ ያልተከፈተውን ጣሳ ጨመቀችው። ፀንቶ ቆየ። እንደ ባዶው ጣሳ አልተጨማደደም ወይም አልወደቀም—ምክንያቱም ተሞልቶ ነበርና።

ይህንን መግለጫ ከግል ህይወታችን እና ቤታችን እና ቤተሰቦቻችን ህይወቶች ጋር አመሳሰልን። በመንፈስ እና በወንጌል እውነት ስንሞላ፣ የከበቡንን እና በተቃርኖ የሚገፉንን የውጪው አለም ሀይሎች ለመቋቋም ሀይል አለን። ነገር ግን፣ በመንፈሳዊነትን ካልተሞላን፣ የውጪውን ጫናዎች ለመቋቋም ውስጣዊ ጥንካሬ የለንም እና ሀይሎች በተቃርኖ ሲገፉን መውደቅ እንችላለን።

እኛ እና ቤተሰቦቻችን የአለምን ጫናዎች ለመቋቋም፣ በብርሃን እና በወንጌል እውነት መሞላት እንዳለብን ሴጣን ያውቃል። ስለዚህ እውነቱን ለማድከም፣ ግራ መጋባትን በመፍጠር እና የወንጌልን እውነት ለማጥፋት እናም ከእውነቱ እኛን ለመለየት በአለው ሀይል ሁሉንም ያረጋል።

ብዙዎቻችን ተጠምቀናል እናም ሚናው የነገሮችን ሁሉ እውነት መግለፅ እና ማስተማር የሆነውን፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ተቀብለናል።2 ከዛ ስጦታ እድል ጋር እውነትን የመሻት፣ የምናውቀውን እውነት መኖር፣ እና እውነቱን ማካፈል እና የመከላከል ሀላፊነት ይመጣል።

በብርሀን እና በእውነት ለመሞላት የምንፈልግበት አንድ ምርጥ ቦታ በቤቶቻችን ውስጥ ነው። በስንኙ ቃላት የሰማነው መዝሙር ይህን ያስታውሰናል፣ “እሱ እኛ እንድንሆን የሚፈልገውን እንድንሆን እንዲረዱን እግዚያብሄር ቤተሰቦችን ሰጠን።” 3 ወንጌልን ለመማር እና ለመኖር ለመርዳት ቤተሰብ በምድር ላይ የጌታ መሳሪያዎች ናቸው። በምንፈሳው አንዳችን አንዳችንን ለማጠንከር ለመርዳት ቅዱስ ከሆነ ሀላፊነት ጋር ወደ ቤተሰባችን መጣን።

ጠንካራ ዘላለማዊ ቤተሰቦች እና በመንፈስ የተሞሉ ቤቶች በቀላሉ የሚፈጠር አይደለም። ታላቃ ጥረትን ይወስዳሉ፣ ግዜን ይወስዳሉ፣ እናም እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ድርሻውን ወይም ድርሻዋን ማድረግን ይወስዳል። እያንዳንዱ ቤት የተለየ ነው፣ ነገር ግን አንድ ግለሰብ የትም ቦታ እውነቱን ካሻ ልዩነት መፍጠር ይችላል።

በፀሎት እና ቅዱሳን መፅሀፍትን እና በህይወት ያሉ ነብያትን ቃላት በማንበብ እና በማሰላሰል መንፈሳዊ እውቀታችንን እንድናሳድግ በተከታታይ ሁኔታ ተመክረናል። ፕሬዘዳንት ዲይተር  ኤፍ ኡክዶርፍ በአጠቃላይ ጉባኤ ንግግሩ ላይ ስለ ብርሃን እና እውነት ምስክር መቀበል እንዲህ አለ፤

“ የዘላለም እና ሀያሉ አምላክ……. በተሰበረ ልብ እና በተዋረደ መንፈስ ለቀረቡት ይናገራል።

“ ህልሞች፣ በራዕዮች፣ በሀሳቦች እና በስሜቶች ይናገራቸዋል።”

ፕሬዘዳንት ኡክዶርፍ ሲቀጥል፤“ እግዚያብሄር ስለናንተ ይጨነቃል። የግል ጥያቄዎቻችሁን ያዳምጣል እናም ይመልሳል። የፀሎቶቻችሁ መልሶች በራሱ መንገድ እና በራሱ ጊዜ ይመጣሉ፣ እናም ስለዚህ፣ የሱን ድምፅ ለማዳመጥ መማር አለባችሁ።”4

ይህንን ምክር የአንድ ቤተሰብ ታሪክ ያብራራዋል።

ከጥቂት ወራት በፊት ኤልዛቤት ስታሄሊ ወከር የምትባለውን የወንድ ቅድመ አያቴ እህትን ምስክርነት አነበብኩ። በልጅነቷ ከቤተሰብዋ ጋር ከስዊዘር ላንድ ወደ አሜሪካ ኤልዛቤት ተሰደደች።

ኤልዛቤት ካገባች በኋላ፣ እሷ እና የእሷ ባለቤቷ እና ልጆቿ በናቫዳ ጠረፍ አቅራቢያ የፖስታ መሳሪያዎች አቅርቦት የሚሰጥ ሱቅ በሚያስተዳድሩበት አካባቢ ይኖሩ ነበር። ቤታቸው ለተጓዦች የማቆሚያ ቦታ ነበር። ሁሌም ቀን እና ማታ ለተጓዦች ምግብ ለማብሰልና ለማገልገል ዝግጁ መሆን ነበረባቸው። ከባድ ነበር፣ አድካሚ ስራ፣ እናም ትንሽ እረፍት ነበራቸው። ነገር ግን ኤልዛቤት ታላቁ ያስጨነቃት የነበረው ከሚያገኟቸው ሰዎች ጋር ያለው ጭውውት ነበር።

መፅሀፈ ሞርሞን እውነት እንደነበር፣ ነብዩ ዮሴፍ ስሚዝ ያደረገውን ነገር እንዲያደርግ ፍቃድ ተሰቶት እንደነበር፣ እናም የእሱ መልዕክት የህይወት እና የመዳን እቅድ እንደነበር መሆኑን እስካሁን ድረስ እንደቀልድ አድርጋ እንደወሰደችው እልዛቤት ተናገረች።

ከሚቆሙት ተጓዦች አንዳንዶቹ ጥሩ አንባቢዎች፣ የተማሩ፣ ጎበዞች ነበሩ እናም በጠረጴዛዋ ዙሪያ የነበረው ወሬ ዮሴፍ ስሚዝ መፅሀፈ ሞርሞንን እራሱ እንደፃፈው እና ገንዘብ ለማግኘት መፅሀፉን የበተነ “አታላይ አጭበርባሪ” እንደነበር ነበር። የትኛውም ነገር የማይመስል፣ ሞርሞኒዝም ሞኝነት እንደነበረ ነበር ያስመሰሉት።

ይሄ ሁሉ ወሬ ኤልዛቤትን የተገለለች እና ብቸኛነት እንዲሰማት አደረጋት። እሷን ለማናገር ሰው የለም፣ ፀሎቶቿን ለማድረግ እንኳን ሰዓት የለም፣ እየተራመደች ሳለች ብትፀልይም። ሀይማኖቷን የሚሳለቁትን ሰዎች አንድ ነገር ለማለት በጣም ፈርታ ነበር። እንዲህ አለች እውነት መናገራቸውን መገመት ነበረብኝ፣ ብትሞክር ኖሮ እምነቷን መከላከል እንደማትችል እንደነበር ተሰማት።

ምስል
Pioneer Family in front of a log home

በኋላ፣ ኤልዛቤት እና ቤተሰቧ መኖረያ ቀየሩ። ኤልሳቤት ኤንዲህ አለች ለማሰብ ብዙ ሰዓት ነበራት እናም ሁሌም ትረበሽ አልነበረም። ብዙ ጊዜ ወደ ምድር ቤት ትወርድና ያስቸግራት ስለነበረው ነገር፣ — እንኛ ጎበዝ በሚመስሉ ሰዎች ስለ ወንጌሉ እና ስለ ዮሴፍ ስሚዝ እና ስለ መፅሀፈ ሞረሞን ሞኝ መሆን ስለ ተነገሩት ታሪኮች ወደ ሰማይ አባት ትፀልያለች።

አንድ ምሽት ኤልዛቤት ህልምን አየች። እንዲህ አለች “ ዝቅ ባለ ኮረብታ ስር ባለ የጋሪ መንገድ ላይ የቆምኩ ይመስለኛል። ከተራራው ግማሽ ላይ አንድ ሰው ወደ ታች እየተመለከተ ሲናገር አየሁ፣ ወይም ተንበርክኮ ከመሬት ጉድጓድ ውስጥ እየተማረ ላለ ወጣት ልጅ እየተናገረ ይመስላል። የወጣቱ ልጅ እጆች ከጉድጓድ ውስጥ የሆነ ነገር ላይ ለመድረስ በሚመስል መልኩ ተዘርግተው ነበር። ልጁ ተንበርክኮ ከነበረበት ከጉድጓድ የተነቀለ የሚመስል የድንጋይ ክዳን መመልከት ቻለ። ብዙ ሰዎች በመንገዱ ላይ በነበሩበት ነገር ግን አንዳቸውም ከኮረብታው ላይ ባሉት ሁለት ሰዎች ላይ ፍላጎት ያላቸው አይመስሉም። ወዲያው እንድነቃ ያደረገኝ በጠንካራ ሁኔታ እንድገረም ካደረገኝ ህልም ጋር ተያይዞ የመጣ አንድ ነገር ነበር፤--- ህልሜን ለማንም መናገር አልቻልኩም ነገር ግን በዛች ሰሌዳውን ባገኘባት ሰዓት መላዕክ ሞሮኒ ልጅ ዮሴፍን መመሪያ እየሰጠው ነው ማለት ነው በዬ የተደሰትኩ መሰለኝ።

በፀደይ 1893 ወቅት፣ ኤልዛቤት ለቤተ መቅደስ ምረቃ ወደ ሶልት ሌክ ከተማ ሄደች። ገጠመኟን እንዲህ ገለፀች፤ “በህልሜ ውስጥ አይቼ እንደነበረው ተመሳሳይ ምስልን አየሁ። እነደሚመስለኝ ባለ ቀለም የመስታወት መስኮት ነበር። እራሱን የኮሞራ ኮረብታ እንዳየሁ ያህል ነው እርግጠኛ የመሆን ስሜት የተሰማኝ። ከዚህ የተሸለ እውነት አይመስልም። በህልሜ መላዕክት ሞሮኒ ለዮሴፍ ስሚዝ ሰሌዳዎቹን ሲሰጠው ያለውን ምስል እንዳስመለከኝ የእርግጠኝነት ስሜት ተሰማኝ።”

ምስል
Old portrait of Elizabeth Staheli

ከዚህ ህልም ብዙ አመት በኋላ እና 88 አመት ሊሞላት ሲል ከመሞትዋ የተወሰኑ ወራቶች በፊት፣ ኤልዛቤት ሀይለኛ መነሳሳትን ተቀበለች። “ ልክ አንድ ሰው ለኔ እንደተናገረኝ ያህል ሀሳቡ ወደ እኔ በግልፅ ማጣ…… ‘መስክርነትሽን መሬት ውስጥ አትቅበሪው።”5

ከትውልዶች በኋላ፣ የኤልዛቤት ልጅ ልጆች ከእሷ ምስክርነት ጥንካሬን መምዘዝን ቀጠሉ። ልክ እንደ ኤልዛቤት፣ አጥብቀን የያዝነውን እውነት የሚሳለቁ እና የሚቃወሙ ብዙ ተጠራጣሪዎች እና ተቺዎች ባሉበት አለም ውስጥ ነው ያለነው። ግራ የሚያጋቡ ታሪኮች እና የሚጋጩ መልእክቶችን ልንሰማ እንችላለን። ልክ እንደ ኤልዛቤት፣ አሁን የለንን የትኛውንም ብርሃን እና እውነት ጠንክሮ ለመያዝ የተሻለንን ማድረግ አለብን፣ በተለየ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ። የፀሎቶቻችን መልሶች በአስደናቂ መልኩ ላይመጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን ታለቅን ብርሃን እና እውነትን ለመሻት ፀጥ ያሉ ጊዜያትን መፈለግ አለብን። እናም ስንቀበለው፣ እሱን መኖር፣ ማካፈል፣ እና መከላከል ሀላፊነታችን ነው።

በእዳኝ ብርሃን እና እውነት ልቦቻችንን እና ቤቶቻቸውን ስንሞላ፣ በማንኛውም ሆኔታ ውስጥ ፅኑ ለመሆን ውስጣዊ ጥንካሬን እንደምናገኝ ምስክርነቴን እተውላችኋለሁ። በእየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “The Family Is of God,” in 2014 Outline for Sharing Time: Families Are Forever (2013), 28–29.

  2. ሞሮኒ 10፥5 ተመልከቱ

  3. “The Family Is of God.”

  4. Dieter F. Uchtdorf, “Receiving a Testimony of Light and Truth,” Ensign or Liahona, Nov. 2014, 21.

  5. See Elizabeth Staheli Walker, “My Testimony, Written for My Children and Their Children after I Am Gone,” 1939, 22–26, University of Nevada, Las Vegas, Special Collections; punctuation, capitalization, and spelling standardized.