2010–2019 (እ.አ.አ)
ምርጫን መጠበቅ፣ የሀይማኖት ነፃነትን መጠበቅ
ኤፕረል 2015


ምርጫን መጠበቅ፣ የሀይማኖት ነፃነትን መጠበቅ

የታማኝ ምርጫችን ጥቅም የእኛ የእምነት ምርጫ ላይ የተመረኮዘ ነው።

ይህ የፋሲካ እሁድ ነው፤ የአዳኝን ኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ እና ለሁሉም የሰው ልጅ ትነሳኤ ምስጋና እና ክብርን የማስታወሻ ቀን ነው። እናመልከዋለን፣ ለእምነታችን ነፃነት፣ ስለመሰባሰብ ነፃነት፣ ስለ መናገር ነፃነት፣ እናም በእግዚያብሄር የተሰጠን የምርጫ መብት እናመሰግናለን።

ስለ ምንኖርበት የመጨረሻው ቀን ነብያቶች አስቀድመው እንደተናገሩት፣ ማን እነደሆንን እና ምን እንደምናምን ብዙ ግራ መጋባቶች አሉ። አነዳንዶች “የሀሰት ከሳሾች ናቸው… [እናም] መልካም የሆኑትን የሚንቁ።”1 ሌሎች ክፋትን መልካም፣ እና መልካም ክፋት የሚሉ፤ [እናም] ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ያደርጋሉ።” 2

በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ለእንነታችን እመዴት መመለስ እንዳለባቸው ምርጫዎችን ሲያደርጉ፣ የምርጫ ምግባር እግዚያብሄር ለልጆቹ ያለው እቅድ ጠቃሚ መሆኑን መርሳት አይገባንም። ከሟችነት ህይወት በፊት በሰማይ መማክርት የቀረበልን፣ ያ ዘላለማዊ እቅድ፣ የመምረጥ ስጦታን ያጠቃልላል።3

በታላቁ መማክርት ላይ፣ ሰይጣን ተብሎ የሚታወቀው፣ ሉሲፈር፣ የእግዚያብሄርን እቅድ ለመቃወም ምርጫውን ተጠቀመ። እግዚያብሄርን እንዲህ አለ፥ “ ምክንያቱም ስጣን በኔ ላይ ስለተቃወመ፣ እናም የሰዎችን ምርጫ ለማትፋት ስለፈለገ፣ እኔ፣ ጌታ እግዚያብሄርን፣ ሰጥቼዋለሁ፣ … ወደ ታች እንዲጣል አድርጌዋለሁ።”4

እናም ደግሞ የሰማይ ሰራዊት አንድ ሶስተኛው በምርጫቸው የተነሳ ከእኔ ፊታቸውን አዞሩ።”5

በውጤቱም፣እቅዱን ለመቃወም የመረጡ እና ሉሲፈርን የተከተሉ የሰማይ አባት የመንፈስ ልጆች መለኮታዊ መድረሻቻን አጡ።

ኢየሱስ ክርስቶስ ምርጫውን በመጠቀም፣ እንዲህ አለ፤

“ይሄው እዚህ ነኝ፣ ላከኝ።”6

“ፍቃድህ ይፈፀም፣ ክብር ለዘላለም የአንተ ይሁን።”7

ኢየሱስ የሰማይ አባት እቅድን ለመደገፍ ምርጫውን ከተለማመደ በኋላ ብቻ ነው አባት እንደ እኛ አዳኝ የለየው እና የቀባው፣ ለሁሉም ቤዛዊ መስዕዋት ለመፈፀም አስቀድሞ የመረጠው። በተመሳሳይ፣ ተዕዛዛትን ለመጠበቅ ምርጫችንን ከተለማመድን በኋላ ብቻ ነው በእርግጥ ማን እንደሆንን በሙሉ ሁኔታ መረዳት የምንችለው እና የሰማይ አባታችን ለእኛ ያለውነን በረከቶች የምንቀበለው— አካልን መኖርን፣ ማደግን፣ ደስታን መለማመድ፣ ቤተስብ መኖርን፣ እናም የዘላለምን ህይወት መውረስ እድልን ጨምሮ።

ትዕዛዛትን ለመጠበቅ፣ በግለሰብ በየጊዜው በሚቀያየሩ ግፊቶች ከክርስቶስ መሪነት አቅጣጫ እንዳንቀይር ፍቃድ ያለውን የቤተክርስቲያን ትምህርት ማወቅ አለብን።

አሁን የምንደሰትባቸው በረከቶች ያሉት ከዚህ ህይወት በፊት በሰራነው ምርጫ ምክንያት ነው። ይነኚህን ቃላቶች ለሚሰሙት ወይም ለሚያነቡት ሁሉ፣ ማንም ብትሆኑ እና ያለፈው ነገራችሁ ምንም ቢሆንም፣ ይህንን አስታውሱ፤ ያንን ተመሳሳይ ምርጫ በድጋሚ ለማድረግ እና እሱን ለመከተል ብዙ አልረፈደም።

በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት፣ በሀጢያት ክፍያው በማመን፣ ለሀጢያቶቻችንን ንስሀ በመግባት፣ በመጠመቅ፣ ከዚያ በኋላ መለኮታዊ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እንቀበላለን። ይህ ስጦታ እውቀትን እና መረዳትን፣ ለመማር እና ምስክርነት ለማግኘት ምሬትን እና ጥንካሬን፣ ሀይልን፣ እናም ሀጢያትን ለማሸነፍ መንፃትን፣ እናም በመከራዎች ውስጥ ታማኝ ለመሆን መፅናናትን እና ብርታትን ያመጣል። እነኚህ የማይነፃፀሩ የመንፈስ በረከቶች ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ነፃነታችንን እና ሀይላችንን ያሳድጋሉ፣ ምክንያቱም “የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።”8

በዚህ በመጨረሻው ቀናቶች በመንፈስ አርነት መንገድ ስንራመድ፣ የታማኝ ምርጫችን ጥቅም የእኛ የእምነት ምርጫ ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ልንረዳ ይገባል። ሴጣን ይህ ነፃነት የእኛ እንዲሆኑ እንደማይፈልግ እስቀድመን እናውቃለን። የምርጫ ስነምግባርን ለማጥፋት በሰማይ ሞከረ፣ አሁን በነፃነት ላይ— ለእኛ መንፈሳዊ ህይወት እና መዳን ምንድን እና ለምንድን ነው ጠቃሚ የሆነው።

እኛ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መተማመን እና መከላከል ያለብን የእምነት ነፃነት አራት የማእዘን ድንጋዮች አሉ።

የመጀመሪያው የማመን ነፃነት ነው። ማንም ሰው መወቀስ፣ መሰደድ፣ ወይም ስለ እግዚያብሄር ባለው ወይም ባላት እምነት በግለሰብም ወይም በመንግስትም ጥቃት መድረስ የለበትም። የእምነት አርነትን በተመለከተ መጀመሪያ የወጣው እምነታችን አዋጅ እንዲህ ይላል፤

“እንደዚ አይነት ህጎች ካልተቀረፁ እና ነፃ የህሊና ተግባርን ለግለሰብ ካለተረጋገጠ በቀር፣ የትኛውም መንግስት በሰላም አይኖርም. …

“… የሲቪል ዳኞች ወንጀልን ማገድ አለባቸው፣ ነገር ግን ህሊናን መቆጣጠር በጭራሽ የለባቸውም፤ … [ወይም] የነፍስን ነፃነት መጨቆን የለባቸውም።”9

ይህ መሰረታዊ የእምነት ነፃነት ከዚያ ጀምሮ በዩናይትድ ህዝቦች በሰው መብት አዋጅ ውስጥ እና በሌሎች ህዝቦች እና በአለም አቀፍ የሰዎች መብት ሰነዶች እውቅና አግኝቷል።10

ሁለተኛው የእምነት አርነት የመአዘን ድንጋይ እምነታችንን እና ምናምናቸውን ነገሮች ከሌሎች ጋር የማካፈል ነፃነት ነው። ጌታ አዘዘን፣ “በቤታችሁ ስትቀመጡ … [ወንጌልን] ለልጆቻችሁ ማስተማር አለባችሁ።”11 ለሃዋሪያቱም እንዲህ አላቸው፣ “ ወደ አለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።”12 እንደ ወላጆች፣ የሙሉ ጊዜ ሚሲዮናዊዎች፣ እናም አባል ሚሲዮናዊዎች፣ የጌታን ትምህርት በቤታችን እና በአለም ዙሪያ ለማስተማር በእምነት ነፃነት ላይ እንሞረከዛለን።

ሶስተኛው የእምነት አርነት የመአዘን ድንጋይ የሀይማኖት ድርጅት መመስረት እና ከሌሎች ጋር በሰላም ማምለክ ነው። አስራ አንደኛው የእምነት አንቀፅ እንዲህ ያውጃል፣ ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚያብሄርን ኅሊናችን እንደሚመራን የማምለክ መብት እንዳለን እናረጋግጣለን፣ እናም ሁሉም ሰዎች እንዴትም፣ የትም፣ ወይም ምንም የፈለጉትን እንዲያመልኩ እንደዚህ አይነት መብት እንዳላቸው እንቀበላለን። አለም አቀፍ የሰው መብት ሰነዶች እና ብዙ አገር አቀፍ መተዳደሪያ ደንቦች ይህንን መመሪያ ይደግፉታል።

አራተኛው የእምነት አርነት የመአዘን ድንጋይ እንደ እምነታችን የመኖር ነፃነት — በቤት እና በማምለኪያ ቦታ ብቻ ሳይሆን13 ነገር ግን በህዝብ ቦታዎች ላይ እምነታችንን የመተግበር ነፃነት። ጌታ በግላችን እንድንጸልይ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ወደ ፊት በመሄድ “ መልካሙን ስራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ [የእናንተ]ብርሃን እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።”14

አንዳንዶች ሰዎች እምነታችንን ወደ ህዝብ አደባባይ ስናመጣ ይቀርብላቸዋል፣ እናም አስተሳሰባቸው እና ድርጊቶቻቸው በማህበረሰብ ውስጥ ቻይነትን የሚጠይቁ እነኛው ተመሳሳይ ሰዎች በአብዛኛውን ጊዜ አስተሳሰባቸው እና ድርጊቶቻቸው ላይ ቻይነትን ለሚመኙት ቻይነትን ለመስጠት በጣም ቀርፋፎች ናቸው። ለሀይማኖት አስተሳሰቦች አጠቃላይ ክብር እጥረት ለሀይማኖቶች እና ለተቋማት መህበራዊ እና ፖለቲካዊ አለመቻቻልን በፍጥነት እያበላሸ ነው።

ለአለማዊ መርሆች እጅ ለመስጠት፣ የሀይማኖት ነፃነታችንን አሳልፈን እንድንሰጥ፣ እናም ምርጫችንን እንድናጋልጥ ያደገ ግፊትን ስንጋፈጥ፣ መፅሀፈ ሞረሞን ስለ ሀላፊነቶቻችን ምን እንደሚያስተምረን አስቡበት። በመፅሀፈ አልማ ውስጥ በህዝቡ ላይ ንጉስ ለመሆን፣ በቤተክርስቲያን ያላቸውን መብት እና ጥቅም ለመከልከል የፈለገ “እጅግ አጭበርባሪ” እና “ክፉ ሰው” ስለሆነው አምሊካይ እናነባለን።15 ትክክል ነበር ብለው ለተሰማቸው ድምፃቸውን እንዲያነሱ በንጉስ ሞዛያ ተምው ነበር።16 ስለዚህ፣ “እያንዳንዱ ሰው እንዳስተሳሰቡ በአምሊካይ የሚደግፉ ይሁን ወይም የሚቃወሙ፣ አንዱ ከሌላው የተለየ አካል በመሆን በታላቅ ፀብና በአስገራሚ ጥል በምድሪቱ ላይ ሆኑ።”17

በዚህ ውይይት ላይ፣ የቤተክርስቲን አባላት እና ሌሎች በአንድ ለመሆን፣ አንደነትን መንፈስን ለማየት፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ስር ለመውደቅ እድል ነበራቸው። “እንዲህ ሆነ የህዝቡ ድምፅ በአምሊካይ ላይ ሆነ፣ እርሱም በህዝቡ ላይ አልተደረገም ነበር።”18

የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን ትክክል ለሆነው ድምፃችንን ከፍ ለማድረግ የእኛ አይነት ፍላጎት ካላቸው የሀይማኖት ሰዎች ጋር አብሮ የመስራት ሀላፊነት አለብን። አባሎች ለቤተክርስቲያን እንደሚናገሩ ይግባኝ ማለት ወይም ይመለከተኛል ሳይሉ፣ ሁላችንም፣ በአቅማችን እንደ ዜጋ፣ በፀና እምነት እና ፍቅር የግል ምስክርነታችንን ለማካፈል ተጋብዘናል — “እያንዳንዱ ሰው እንደአስተሳሰቡ።”19

ዮሴፍ ስሚዝ እነዲህ አለ፤

“ለፕሮስፒቴሪያን፣ ለባብቲስት ወይም በየትኛውም የሀይማኖት ወገን ውስጥ ላለ ሰው[ ሞርሞንም ]፤ የኋለኛውን ቀን ቅዱሳን ለተመሳሳይ መመሪያ ለሚጨቁን በሮማን ካቶሊኮች ላይ፣ ወይም የትኛውም ያልታወቀ የሌላ የሀየማኖት ወገን እናም እራሳቸውን ለመከላከል በጣም ደካማ ለሆኑት በሰማይ ፊት ለመሞት ዝግጁ መሆኔን ለማወጅ ደፋር ነኝ።

“የአርነት ፍቅር ነው ነፍሴን የሚያነሳሳው— የሲቪል እና የሀይማኖቶች አርነት ለሰው ዘር ሁሉ።”20

ወንድሞች እና እህቶች፣ እነኚህን የተከበሩ ነፃነቶች እና መፍቶች ለራሳችን እና ለልጅ ልጆቻችን ለመከላከል ሀላፊነት አለብን። እናንተ እና እኔ ምን ማድረግ እንችላለን?

መጀመሪያ፣ ማወቅ እንችላለን። በመንደራችሁ ውስጥ በሀይማኖት ነፃነት ላይ ግጭት ሊኖራቸው የሚችሉ ነገሮችን ተጠንቀቁ።

ሁለተኛ፣ በግል አቅማችሁ፣ ለሀይማኖት ነፃነት ጥረታቸውን የሚያካፍሉትን ተቀላቀሏቸው። የሀይማኖት ነፃነት ለመከላከል በአንድ ላይ ስሩ።

ሶስተኛ፣ ለምታምኑት ነገር መልካም ምሳሌ ለመሆን ህይወታችሁን ኑሩ— በቃል እና በተግባር። ሀይማኖታችንን የምንኖርበት መንገድ ሰለ ሀይማኖታችን ልናወራው ከምንችለው በጣም በተሻለ ሁኔታ ጠቃሚ ነው።

የአዳኛችን ዳግም መምጫ እየቀረበ ነው። በዚህ ታላቅ ምክንያት ላይ አንዘግይ። የነፃነትን አርማ ከፍ አድርጎ ያነሳውን እነኚህን ቃላት በመጻፍ የነጻነት አርማን ከፍ ያደረገውን ሻምበል ሞሮኒን እስታውሱ፥ “አምላካችንን፣ ሀይማኖቶቻችንን፣ እና ነፃነታችንን፣ እና ሰላማችንን፣ እናም ሚስቶቻችንን፣ እና ልጆቻችንን ለማስታወስ።”21 የህዝቡን መልስ እናስታውስ፥ ምርጫቸውን በመለማመድ፣ እነሱ ለመተግበር በቃልኪዳን በመግባት “አንድ ላይ እየሮጡ መጡ።”22

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች፣ አትራመዱ! ሩጡ! መንፈስ ቅዱስ በመከተል እና የሱን ፍቃድ እንድናደርግ እግዚያብሄር የሰጠንን ነፃነቶች በማድረግ የነፃነትን በረከቶች ለመቀበል ሩጡ።

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይ አባታችንን ፍቃድ ለማድረግ ምርጫውን እንደተጠቀመ ልዩ የሆነውን ምስክርነቴን እሰጣችኋለህ።

ስለ አዳኛችን፣ እንዲህ እንዘምራለን፣ “ውዱን ደሙን በነፃ አፈሰሰ፤ ህይወቱን በነፃ ሰጠ።” 23 እናም ስላደረገው፣ በዋጋ የማይተመን በሀጢያት ክፍያው ሀይል እና በረከቶች አማካኝነት “ነፃነት እና የዘላለም ህይወት ለመምረጥ” በዋጋ የማይተመን እድል አለን።24 በነፃነት ዛሬ እና ሁሌም እርሱን ለመከተል እንምረጥ፣ በቅዱሱ ስሙ፣ በኢየሱስ በክርስቶስ ስም እፀልያለሁ፣ አሜን።