2010–2019 (እ.አ.አ)
ወደ እምነት መመለስ
ኤፕረል 2015


ወደ እምነት መመለስ

ሁላችንም በየግል ጉዞአችን በኢየሱስ ክርስቶስ እምነታችንን ማጠንከር እና ደስታን ማግኘት እንችላለን

በዚህ የፋሲካ ጠዋት፣ ፕሬዘዳንት ሞንሰን፣ በህይወት የሚኖር ነብያችንን ድምፅ በመስማታችን በጣም አመስጋኝ ነን። ቃላቶችህ ለኛ ዋጋ አላቸው፣ ምክሮችህም ጨምሮ፤ “በመንገዳችሁ ደስታን አግኙ”1 እና “እንደ እምነታችሁ የወደፊታችሁም ብሩህ ነው።”2

በዚህ አመት ልጆች ደስታቸውን እና በኢየሱስ ክርስቶስ የእምነታችው ብሩህነትን ይህን መዝሙር በመዘመር እየካፈሉ ነው “አዳኜ እንደሚወደኝ አውቃለሁ።”3 እውነታውን ይዘምራሉ፤ “ህያው እንደሆነ አውቃለሁ!... ልቤን ለእርሱ እሰጣለሁ።” ልክ እንደ ልጆቹ መዝሙር፣ ።

በቅርብ በሴቶች መረዳጃ አንድ ወጣት እናት ስለ የንግግር ጉዞዋ አንዱን ክፍል ስታካፍል ሰማሁ። ወንጌልን ካስተማሯት ወላጆቿ ጋር በቤተክርስቲያን ውስጥ አድጋለች።የልጆች ክፍልን፣ የወጣት ሴቶች ክፍልን፣ እናም ሴሚነሪ ክፍልን ተካፍላለች፡፡ እውነታዎችን መማር እና ማግኘት ትወዳለች። ለምን እንደሆነ ማወቅ የማያቋርጥ ጥያቄዋ ነበር። ሽማግሌ ሩሴል ኤም. ኔልሰን እንዲህ አሉ፣ “ጌታ የሚጠይቅን አእምሮ ብቻ ማስተማር ይችላል።”4 እና ይህች ወጣት ሴት መማር የምትችል ነበረች።

ከሁለተኛ ደረጃ በኋላ ዩኒቨርስቲ ገባች፣ ከሚስኦን ከተመለሰ ሰው ጋር በቤተመቅደስ ታተመች፣ እና በሚያምሩ ልጆች ተባርካ ነበር።

በመጠየቅ መንፈስ፣ ይች እናት ጥያቄዎችን መጠየቅ ቀጠለች። ነገር ግን ጥያቄዎቹ በመክበድ ሲያድጉ፣ መልሶቹም እንደዚያው ነበሩ። እና አንዳንድ ጊዜ መልሶች አልነበሩም---ወይም ሰላም የሚያመጡ መልሶች አልነበሩም። ቀስ በቀስ መልሶችን ለማግኘት ስትሻ፣ የበለጠ ብዙ ጥያቄዎች ተነሱ እና የእምነቷን ዋና መሰረቶች መጠራጠር ጀመረች።

በዚህ ግራ በሚያጋባ ጊዜ፣ በዙሪያዋ የነበሩት እንዲህ አሏት፣ “በእኔ እምነት ተመርኮዢ፣” እርሷ ግን እንዲህ አሰበች፣ “አልችልም። አልገባችሁም፤ ከእነዚህ ጉዳዮች ጋር አልተያያዛችሁም።” እርሷ እንዲህ አብራራች፣ “ጥርጣሬ ከሌላቸው ጋር መልካም እርዳታዬን ላካፍል ፍላጎት ነበረኝ፣ እነርሱ ወዳጅነታችውን ለእኔ ካካፈሉ።” እና ብዙዎች አደረጉት።

እንዲህ አለች፣ “ወላጆቼ ልቤን ያውቃሉ እና ነጻነትን ፈቀዱልኝ። እኔ ለእራሴ ለማወቅ እየጣርኩ እያለሁ እነርሱ እኔን መውደድን መረጡ።” በተመሳሳይ፣ የዚህች ወጣት እናት ኤጲስ ቆጶስ በብዛት አገኛት እና በእርሷ ያለውን መተማመን ነገራት።

የአጥቢያ አባላትም ፍቅርን ለመስጠት አላመነቱም፣ እና አብራ መካተቷ ተሰማት። አጥቢያዋ ፍፁም ፊትን የማሳያ ቦታ አልነበረም፣ የእንክብካቤ ቦታ ነበር።

“አስደሳች ነበር፣” እርሷ እነዲህ ታስታውሳለች፣ “በዚህ ወቅት ከሞቱት አያቶቼ ጋር እውነተኛ ግንኙነት ተሰማኝ። ለእኔ እየጣሩ እና መሞከሬን እንድቀጥል እያሳሰቡኝ ነበር። ‘በምታውቂው ላይ ትኩረት እድርጊ’ እያሉ እንደነበር ተሰማኝ።”

በቂ የድጋፍ ሂደት ቢኖርም፣ ተሳትፎዋ ቀነሰ። እንዲህ አለች፣ “እራሴን ከቤተክርስቲያን የለየሁት በመጥፎ ባህሪ ምክንያት፣በመንፈሳዊ ድክመት፣ ትእዛዛትን ላለማክበር ምክንያት እየፈለኩ፣ ወይም ቀላል መውጫን ፈልጌ አይደለም። ‘በእውነት ምንድነው የማምነው?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ እንደሚያስፈልገኝ ተሰምቶኝ ነው።”

በዚህ ጊዜ አከባቢ ተመሳሳይ ስሜቶችን ከሚጋራው የእናት ትሬዛን ፅሁፍ ከያዘው መጽሐፍ አነበበች። በ1953 ደብዳቤ፣ እናት ትሬዛ እንዲህ ፃፉ፤ “ሁሉም ነገሮች የሞቱ ያህል አስቀያሚ ጨለማ ነገር ውስጤ አለና፣ እባካችሁ ስራውን እንዳላበላሽ እና ጌታችን እራሱን እንዲያሳይ በተለይ ለእኔ ፀልዩልኝ። ስራውን ከጀመርኩ ጀምሮ ይብዛም ይነስ ልክ እነዚህ ነው የቆየው። ብርታት እንዲሰጠኝ ጌታን ጠይቁ።”

ኤጲስቆጶስ ፔሪየር እንዲህ መለሱ፤ “ውድ እናት፣ እንደምታስቢው ያህል ጨለማ ውስጥ አይደለሽም፣ እግዚአብሔር ይመራሻል። መከተል የሚገባን መንገድ ሁሌም በእንዴ ግልፅ ላይሆን ይችላል። ለብርሀን ፀልዪ፤ በጣም በፍጥነት አትወስኚ፣ ሌሎች የሚሉትን አድምጪ፣ ምክንያተቸውን አስቢበት። ሁልጊዜም የሆነ የሚረዳን ነገር ታገኚያለሽ። … በእምነት በፀሎት እና በምክንያት በመመራት ትክክለኛ ፍላጎት በቂ አለሽ።”5

ያለ ሁሉም መልሶች እና በሁሉም ነገሮች ግልፅነት ሳይኖር እናት ትሬዛ እምነታቸውን መኖር ከቻሉ፣ ምናልባት እርሷም እንደምትችል ጓደኛዬ አሰበች። በእምነት አንድ ቀላል ደረጃ ወደፊት ከዛ ሌላ መውሰድ ትችላለች። ባመነችበት እውነታዎች ላይ ማተኮር እና እነዚያ እውነታዎች አእምሮዋን እና ልቧን እንዲሞሉ ማድረግ ትችላለች።

መልሳ ስታስብ፣ እንዲህ አለች፣ “ምስክርነቴ እንደተጠራከመ አመድ ሆኗል። ሁሉም ነዷል። የቀረው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።” እርሷ ቀጠለች፣ “ነገር ግን ጥያቄ ሲኖራችሁ እርሱ ጥሎአችሁ አይሄድም። ማንም ሰው ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ሲሞክር፣ በሩ በሰፊው ክፍት ነው። ፀሎት እና ቅዱስ መጽሐፍት በጣም አስፈላጊ ሆኑ።”

እምነቷን መልሶ ለመገንበት የቅድሚያ ደረጃ በመሰረታዊ የወንጌል እውነታዎች መጀመር ነበር። የልጆች መዝሙር መጽሐፍ ገዛች እና የመዝሙሮቹን ቃላት ማንበብ ጀመረች። ለእርሷ እሴቶች ነበሩ። የተሰማትን ክብደት ለማንሻ እምነት ፀለየች።

ለጥርጣሬ ምክንያት የሚሆን አርፍተ ነገር ሲገጥማት፣ ማቆም እንደምትችል፣ ሙሉ ምስሉን መመልከት፣ እና ወንጌልን ግላዊ ማድረግን ተማረች። እንዲህ አለች፣ “እጠይቃለሁ፣ ይሄ ለእኔ እና ቤተሰቤ ትክክለኛው መንገድ ነው? አንዳንዴ እራሴን እንዲህ ጠይቃለሁ፣ ለልጆቼ የምፈልገው ምንድነው? የቤተመቅደስ ጋብቻ እንዲኖራቸው እንደምፈልግ አስተዋልኩ። ያኔ ነው እምነት ወደ ልቤ ተመልሶ የመጣው።”

ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ እንዲህ አሉ፣ “ትህትና፣ እምነት፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ተፅእኖ ሁልጊዜም ለእውነት እያንዳንዱ የመጠይቅ ክፍሎች ናቸው።”6

መጽሐፈ ሞርሞን እንዴት እንደሆነ ጥያቄ ቢኖራትም፣ በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ የምታውቃቸውን እውነታዎች መካድ አልቻለችም። አዳኝን የበለጠ ለመረዳት የአዲስ ኪዳን ጥናት ላይ ትኩረት አደረገች። “ነገር ግን ቀስ በቀስ፣” አለች፣ “ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና የሐጢያት ክፍያው ሳነብ የተሰማኝን በመውደዴ ምክንያት እራሴን ወደ መጸሐፈ ሞረሞን ውስጥ ተመልሼ አገኘሁት።”

እንዲህ አጠቃለለች፣ “በዚያ መጸሐፍ ካሉት እውነታዎች ጋር የራሳችሁ መንፈሳዊ ተሞክሮ ሊኖራችሁ ይገባል፣” እና እርሷ ያ አላት። እንዲህ አብራራች፣ “በሞዛያ ውስጥ አነበብኩ እና ፍጹም ምሬት ተሰማኝ። ‘በእግዚአብሔር እመኑ፤ እርሱ እንደሆነ፣ እና ሁሉንም ነገሮች እንደፈጠረ እመኑ፤… ሁሉም ጥበብ እንዳለው እና በሰማይም እና በምድር ሁሉም ሀይል እንዳለው እመኑ፤ ጌታ የሚረዳውን ነገሮች ሁሉ ሰው እንደማይረዳ እመኑ።’ 7

በዚህ ወቅት እንደ የልጆች ክፍል ፒያኖ ተጫዋች እንዳገለግል ጥሪ መጣ። “ምቹ ነው፣” አለች። “ልጆቼ በልጆች ክፍል እንዲሆኑ እፈልግ ነበር፣ እና አሁን ከእነሱ ጋር መሆን እችላለሁ። እና ገና ለማስተማር ዝግጁ አልነበርኩም።” ስታገለግል፣ በዙሪያዋ ካሉት በቀጣይነት እንዲህ ተሰማት፤ “ነይ፣ በየትኛውም ደረጃ ላይ ብትሆኚ እንፈልግሻለን፣ እና እዛም እናገኝሻለን። መስጠት የምትችዪን ያህል ስጪን።”

የልጆችን መዝሙር በመጫወት፣ በብዛት ለእራሷ እንዲህ አሰበች፤ “የምወዳቸው እውነታዎች እኚውና። ምስክርነቴን አሁንም ማካፈል እችላለሁ። የማውቃቸው እና የማምናቸውን ነገሮች እናገራለሁ። ፍፁም የሆነ የእውቀት አቅርቦት ባይሆንም፣ ነገር ግን የእኔ አቅርቦት ይሆናል። ትኩረት የማደርግበት በእኔ ውስጥ ይስፋፋል። ወደ ወንጌል መሰረት መመለስ እና የግልጽነት ስሜት መሰማት አስደሳች ነው።”

በዚያ እሁድ ጠዋት፣ ይቺን ወጣት እህት የጉዞ ታሪኳን ሳዳምጥ፣ ሁላችንም በአዳኛችን አለት ላይ መሰረታችንን መገንባት እንዳለብን አስታወስኩ።8 የሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ ምክርንም አስታወስኩ፤ “የምታውቁትን አጥብቃችሁ ያዙ እና ተጨማሪ እውቀት እስኪመጣ ጠንክራቹ ቁሙ።”9

በትምህርቷ ወቅት፣ ከልብ ስንሻ እና ትእዛዛትን ስንኖር ጥያቄዎቻችን እንደሚመለሱ በሙሉ ልብ አወኩኝ። እምነታችን ከጊዜው ምክንያት ገደብ በላይ ሊደርስ እንደሚችል አስታወስኩ።

እና፣ ኦህ፣ ይህችን ወጣት እናት በመውደድ እና በማገዝ እንደከበቧት ለመሆን ምነኛ እፈልጋለሁ። ፕሬዘዳንት ዴይተር ኤፍ ኡክዶርፍ እንዳሉት፤ በደቀመዛሙርትነት መንገድ ስንጓዝ ሁላችንም “የእግዚአብሔርን ብርሀን የምንሻ መንፈሳዊ ተጓዦች ነን። ሌሎች ስላላቸው የብርሀን መጠን ወይም ስለሌላቸው አንወቅስም፤ በዛ ፈንታ፣ ሁሉም ብርሀን ግልጽ፣ ብሩህ፣ እና እውነት እየሆነ እስኪያድግ እንንከባከባለን እና እናበረታለን።”10

የፕራይመሪ ክፍል ልጆች ሲዘምሩ “የልጅ ፀሎት፣” እንዲህ ይጠይቃሉ፤ “የሰማይ አባት፣ በእርግጥ አለህ? እና የሁሉንም ልጅ ጸሎት ትሰማለህ እና ትመልሳለህ?”11

እኛም ልንገረም እንችላለን፣ “የሰማይ አባት በእውነት አለ?” መልሱ ፀጥ ባለ እና ቀላል ማረጋገጫ ሲመጣ፣ እንደ ጓደኛዬ-- ደስታ ይሆናል። የእርሱ ፍላጎት የእኛ ሲሆን እነዚያ ቀላል ማረጋገጫዎች እንደሚመጡ እመሰክራለሁ። እውነት ዛሬ በምድር ላይ እንደሆነ እና የእርሱ ወንጌል በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሚገኝ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን, “Finding Joy in the Journey,” Ensign or Liahona, ህዳር 2008, 85.

  2. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን, “Be of Good Cheer,” Ensign or Liahona, ግንቦት 2009, 92.

  3. “I Know That My Savior Loves Me,” in I Know My Savior Lives: 2015 Outline for Sharing Time (2014), 29.

  4. ራስል ኤም. ኔልሰን, in M. Russell Ballard, “What Came from Kirtland” (Brigham Young University fireside, ህዳር  6, 1994); speeches.byu.edu.

  5. In Mother Teresa: Come Be My Light; The Private Writings of the Saint of Calcutta, ed. Brian Kolodiejchuk (2007), 149–50; punctuation standardized.

  6. ጄፍሪ አር. ሆላንድ, “Be Not Afraid, Only Believe” (evening with Elder Jeffrey R. Holland, Feb. 6, 2015); lds.org/broadcasts.

  7. ሞዛያ 4፥9.

  8. ሔላማን 5፥12.

  9. ጄፍሪ አር. ሆላንድ, “Lord, I Believe,” Ensign or Liahona, May 2013, 94.

  10. ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ, “Receiving a Testimony of Light and Truth,” Ensign or Liahona, Nov. 2014, 22.

  11. “A Child’s Prayer,” Children’s Songbook, 12.