2010–2019 (እ.አ.አ)
አፅናኙ
ኤፕረል 2015


አፅናኙ

ህያዉ ክርስቶስ ልናፅናና ቃል ላለብን ሰዎች አፅናኙን፣ መንፈስ ቅዱስ እንደሚልክ ምስክርነቴን እሰጣለሁ።

የተወደዳችሁ እህቶቼ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል የመሆንን በረከት ለእናነተ ማካፈል ለኔ ደስታ ነው። በመዝሙር፣ በፀሎቶች፣ እንዲሁም በሚያነሳሱ ስብከቶች አማካኝነት እሱን በዛሬው ምሽት አስታውሰነዋል። በጣም ከምናደንቃቸው የአዳኝ ባህሪያት ከሆኑት አንዱ የሱ መጠን የሌለው ርህራሄ ነው።

እንደሚያውቃችሁ እና እንደሚያፈቅራችሁ ተሰምቷችኋል። በአጠገባችሁ ላሉት ያለውን ፍቅርንም ተሰምቷችኋል። እህቶቻችሁ፣ እና የሰማይ አባት የመንፈስ ሴት ልጆች ናቸው። ለእናንተ እንደሚጨነቀው ለእነርሱም ይጨነቃል። የሚሰማቸውን ሀዘን ሁሉ ይረዳል። ሊታደጋቸው ይፈልጋል።

ዛሬ ምሽት ለእናንተ ያለኝ መልእክት መጽናናትን ለሚፈልጉ መፅናናትን ለመስጠት እንደምትችሉ እና በዚያም አስፈላጊ ክፍል መሆን እንዳለባችሁ ነው። የእርዳታ ፀሎቶችን እንዴት እንደሚመልስ የበለጠ ብታውቁ የእናንተን ሚና የበለጠ መጫወት ትችላላችሁ።

ብዙዎች ለእርዳታ፣ የሀዘናቸውን፣ ብቸኝነት፣ እና የፍርሀት ሸክም በመሸከም ውስጥ እርዳታን ለማግኘት ለሰማይ አባት ይፀልያሉ። የሰማይ አባት እነኛን ፀሎቶች ይሰማል እናም አስፈላጊነታቸውንም ይረዳል። እሱና የእሱ ተወዳጅ ልጅ፣ ትንሳኤ ያረገው እየሱስ ክርስቶስ፣ እርዳታን ቃል ገብተዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ጣፋጭ ቃሉን ሰጠ፤

“እናንተ ደካሞች ሸከማችሁ የከበደ ሁሉ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።

ቀንበሬንም በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።

ቀንበሬም ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነው።”1

የእርሱ ታማኝ አገልጋዮች በህይወት ውስጥ መሸከም ያለባቸው ሸክሞች በሀጢያት ክፍያው ቀላል ተደርገዋል። የሀጢያት ሸክም ሊወሰድ ይችላል። ነገር ግን የሟችነት ህይወት ፈተናዎች ለመልካም ሰዎች አሁንም ከባድ ሸክሞች መሆን ይችላሉ።

በምትወዷቸው መልካም ሰዎች ህይወት ውስጥ ፈተናዎችን አያታችኋል። እነሱን ለመርዳት መሻት ተሰምቷችኋል። ለእንሱ ላላችሁ የርህራሄ ስሜት ምክንያት አለ።

እናንተ በቃል ኪዳን ያላችሁ የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ናችሁ። ወደ እርሱ ቤተክርስቲያን ስትመጡ ታላቅ ለውጥ በልባችሁ ውስጥ ይጀምራል። ቃልኪዳን ገብታችኋል፣ እናም ዋና ተፈጥሮአችሁን መቀየር የጀመረውን ቃል ኪዳን ተቀብላችኋል።

አልማ፣ በሞረሞን ውሃ ላይ በተናገራቸው ቃላት፣ የገባችሁት ለእናንተ እና በዙሪያችሁ ላሉ ምን ማለት እንደሆነ ገለፀ። እናንተ የገባችሁትን ቃል ኪዳን ሊገቡ ላሉት ስዎች እየተናገረ ነበር፣ ጌታ ለእናንተ የገባውን ቃል ኪዳን እነሱም ተቀበሉ።

“እነሆ የሞርሞን ውሃ ይህ ነው፣(ለዚህም ነው የተጠሩት) እናም አሁን፣ እናንተ ወደ እግዚያብሄር በአንድ አላማ ለመምጣት እንደፈለጋችሁ፤ እናም ህዝቡ ትባሉ ዘንድ፣ እናም አንዳችሁ የአንዳችሁን ሸከም ለመሸከም ፍቃደኞች በመሆን እንዲቀላችሁ ታደርጉ ዘንድ፣

“አዎን፣ እናም ከሚያዝኑት ጋር ለማዘን ፈቃደኞች ትሆኑ ዘንድ፣ እናም መጽናናትን ለሚፈልጉ ካጽናናችኋቸው፤ እናም በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገር የእግዚያብሄር ምስክር በመሆን ተቆሙ ዘንድ፣ እናም በጌታ ትድኑ ዘንድ እስከ ሞትም ድረስ እንኳን በሁሉም ቦታ ትኖሩ ዘንድ፣ እናም ዘላለማዊ ህይወት ይኖራችሁ ዘንድ፣ እናም በፊተኛው ትንሳኤ ከሚገኙት ጋርም ትቆጠራላችሁ።”2

የሀዘን ሸክም እና አስቸጋሪ ነገርን ተሸክሞ ወደ ፊት ለመሄድ እየተቸገረ ያለ ሰውን የመርዳት ፍላጎት ስሜት ያላችሁ ለዛ ነው። ሸክማቸው ቀላል ለማድረግ እና እንዲፅናኑ አመቺ በማድረጉ ላይ ጌታን ለመርዳት ቃል ገብታችኋል። መንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስትቀበሉ እነኛን ሸክሞች ለማቅለል የመርዳትን ሀይል ተሰጥቷችሁ ነበር።

አዳኝ ሊሰቀል ሲል ሸክሞችን በማቅለል የረዳበት መንገድን ገለፀ እና ሊሰቀል በሆነ ጊዜ ለመሸከም ጥንካሬን ሰጣቸው። ደቀ መዛሙርቱ እንደሚያዝኑ ያውቅ ነበር። ስለ ወደ ፊታቸው እንደሚፈሩ ያውቅ ነበር። ለመቀጠል ባላቸው አቅም ላይ እርግጠኛ ያለመሆን ስሜት እንደሚሰማቸው ያውቅ ነበር።

ስለዚህ ለእኛ እና ለእርሱ ደቀ መዛሙረት ሁሉ የሰጠንን ቃል ኪዳን ሰጣቸው፤

“እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አፅናኝ ይሰጣችኋል፡

እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ልቀበለው የማይችል የእውነት መንፈስ ነው፣ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቁታላችሁ።3

ከዚያም በኋላ ቃል ገባ

አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አፅናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የንገረኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።

“ሰላምን እተውላችኋለሁ፡ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፡ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እነደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።””4

በዚህ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ብቻ በጸሎት ሸክሞቻቸው ይቀል ዘንድ ሲማጸኑ በነበሩት በእግዚአብሔር ልጆች ህይወት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የመላክ ቃል ኪዳን ሲሟላ አይቻለሁ። እያንዳንዱ ሸክሞች የመቅለል ተዐምር የመጣው ጌታ ቃል በገባው መንገድ ነው። እሱ እና የሰማይ አባት መንፈስን ቅዱስን እንደ አጽናኝ ላኩት።

ሶስት የቤተሰብ ትውልዶች በወጣት ልጅ ሞት ሲያዝኑ ነበር። ሁለቱ በሰፊ ቤተሰቦች ውስጥ ጠና ባሉ ሁለት አባወራዎች ሞት በጣም እያዘኑ ነበር። ሶስተኛው እና በጣም የቅርቡ በድንገት አደጋ በሞተው ህጻን ልጅ ነበር።

ጌታ ሸክሞችን ሲያቀል እና እንዴት እንደሚያደርግ ተመለከትኩ። እናንተ በአብዛኛውን ግዜ በህይወታችሁ —“ከሚያዝኑት ጋር እንደምታዝኑ እና መጽጽናናትን ለሚያስፈልጋቸው መጽጽናናት እንደምትሆኑት” እኔም ቃል ኪዳን እንደገባ የጌታ አገልጋይ ሆኜ እዛ ተገኘሁ።5

ይህ እውነት እንደ ሆነ ስላወቅኩኝ፣ የህፃኑን ልጅ ወላጆች ከቀብሩ ስነ-ስርዓት በፊት ከወላጆቹ ጋር እንድገናኝ አያቶቹ ሲጋብዙኝ፣ ደስታና ሰላም ተሰምቶኝ ነበር።

ጌታ እንዲያፅናናቸው እንዴት መርዳት እንዳለብኝ ለማወቅ ፀለይኩ። በእኛ ሳሎን ውስጥ ከእነርሱ ጋር ተቀመጥኩ። በቀዝቃዛው ምሽት ክፍሉን በእሳት ማሞቂያው ላይ በትንሽ እሳት ሞቅ አድርጌዋለሁ።

እንደምወዳቸው እንድነግራቸው ምሬት ተሰማኝ እናም ጌታ ለእነርሱ ያለውን ፍቅር እንደሚሰማኝን ነገርኳቸው። በጥቂት ቃላትም ከእነርሱ ጋር እንደማዝን ነገር ግን ጌታ ብቻ የእነሱን ሀዘን በፍጹም ለመሰማት እንደሚችል ልነግራቸው ሞከርኩኝ።

እነዚያን ጥቂት ቃላት ከተናገርኩኝ በኋላ፣ በፍቅር ስለስሜታቸው እነዲያወሩ መፍቀድ እንዳለብኝ ተሰማኝ።

አብረን በተቀመጥንበት እንድ ሰዓት ውስጥ፣ እኔ ካወራሁት በጣም የላቀ አወሩ። መንፈስ ቅዱስ እየነካቸው እንደነበር ከድምጻቸውም ከአይናቸውም ሁኔታ በመነሳት ይሰማኝ ነበር። በትንሽ የምስክር ቃላት የተፈጠረውን እና እንዴት እንደተሰማቸው ተናገሩ።

ለእያንዳንዱ የክህነት ቡራኬ ስሰጣቸው በፀሎቴ ውስጥ እዛ ስለነበረው ስለ መንፈስ ቅዱስ ተፅእኖ ምስጋናን ሰጠው። አፅናኙ መፅናናትን እና ያደገ ጥንካሬን ይዞ መጥቶ ነበር።

በዛ ምሽት፣ የጌታ ስራዎች በእኛ ሰዎች ሸክሞችን እንዴት እንደሚያቀል በተግባር አየሁ። በመፀሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሱ ህዝቦች በሀይለኛ አሰሪዎች በተሰጣቸው የስራ ብዛት ለጥቂት ተጨፍልቀው እንደነበር ታስታውሳላችሁ።

አብዛኛውን የምንወዳቸው እና የምናገለግላቸው እንደሚያደርጉት ሰዎቹ እረፍትን ለማግኘት ተማጸኑ። እውነት እንደሆነ የማቀው መዝገብ ይህ ነው፤

“እናም ደግሞ በትከሻችሁ ላይ ያለውን ሸክም አቃልልላችኋለሁ፣ በጀርባችሁም እንኳን ሊሰማችሁ እንዳይቻላችሁ፤ በባርነት በነበራችሁ ጊዜም ቢሆን፣እናም ይህንን የማደርገው ከዚህ በኋላ ለእኔ ምስክርነት እንድትቆሙ ነው፤ እናም እኔ ጌታ እግዚያብሄር በእውነት በመከራቸው ጊዜ ህዝቤን እንደምጎበኝ ታውቁ ዘንድ ነው።

እናም አሁን እንዲህ ሆነ በአልማ እና በወንድሞቹ ላይ የሆነው ሸክም ቀለለላቸው፣ አዎን፣ ሸክማቸውን ማቅለል እንዲችሉ እናም በደስታና በትግስት ለጌታ ፈቃድ እንዲሰጡ ጌታ ብርታትን ሰጥቷቸዋል።”6

ያንን ተዐምር ብዙ ጊዜ አይቼዋለሁ። እነሱን ጌታ ሲያጠነክር በመርዳት የሌሎችን ሸክሞች በተሻለ እናቀላለን። ለዛ ነው ጌታ ሌሎችን ለማጽናናት በሁሉ ጊዜ እና በሁሉ ቦታ የሱ ምስክር እንድንሆን ያዘዘን።

በዛ ምሽት የህፃኑ አባት እና እናት በሳሎኔ ውስጥ የአዳኝን መስክርነት ገለጡ። ሁላችንም ተፅናንተን ነበር። ወላጆቹ ተጠናክረው ነበር። የሀዘን ሸክሙ አልጠፋም፣ ነገር ግን ሀዘንን መሸከም እንዲችሉ ተደርገው ነበር። እምነታቸው ጨመረ፣ ጥንካሬያቸው በጠየቁት ጊዜ እና ሲኖሩት ማደጉን ይቀጥላል።

ሸክሙን በዛ ምሽት እንዲሸከም ኢዮብን ያጠነከረው ያ የጌታ እና የሀጢያት ክፍያው የመንፈስ ምስክርነት ነበር፤

“እኔን ግን የሚቤዠኝ ህያው እንደሆነ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እነዲቆም፤

“ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፤ በዚያን ጊዜ ከስጋዬ ተለይቼ እግዚያብሄርን እንዳይ አውቃለሁ። 7

የመንፈስ ምስክርነት ነበር እንዲጸና ጥንካሬ የሰጠው።በመከራቸው ውስጥ በታማኝነት ካለፉ በኋላ ለታማኞች የሚመጣውን ሀሴት ለማየት በለቅሶ ውስጥ እና ከሰዎች የመፅናናት እጥረት ውስጥ አለፈ።

ለኢዮብ እውነት ነበረ። በረከቶች በዚህ ህይወት ውስጥ ይመጣሉ። የኢዮብ ታሪክ በእዚህ ተዐምር ይፈፀማል፤

“እግዚያብሄርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን ለእዮብ ባረከ

“እንደ እዮብ ሴቶች ልጆችም ያሉ የተዋቡ ሴቶች በሀገሩ ሁሉ አልተገኙም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ውርስ ሰጣቸው።

“ከዚያም በኋላ እዮብ መቶ አርባ አመት ኖረ፤ ልጆቹን እና የልጅ ልጆቹንም እስክ አራት ትውልድ ድረስ አየ።

“እዮብ ሸምግሎ እድሜም ጠግቦ ሞተ።”8

እዮብ እንዲካተቱ በታቀደው የህይወት ፈተናዎች የረዳው በሀጢአት ክፍያ መንፈስ ምስክርነት ነበር። አባት የሰጠን የደስታ እቅድ አካል ነው። ወደ ቤት ለመሄድ ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆንም ልጁ ባረገው ቤዛነት መስዋትነቱ በኩል እንዲያቀርብ ፈቀደለት።

የጌታውን ደቀ መዛሙርት በጉዟቸው እንዲያፅናናቸው እና እንዲያጠነክራቸው አባት እና ልጅ መንፈስ ቅዱስን ላኩ።

የትንሹ ልጅ ቀብር ስነ-ስርዓት የሚካሄድበት የማምለኪያ ህንፃ ደጅ ስደርስ ይህንን የመፅናናት ተዐምር አየሁ። አንድ ቆንጆ ወጣት ሴት አስቆመቸኝ። እራስዋን ስታስተዋውቅ ፈገግ በማለት። የመጀመሪያ ልጇ በቅርብ እነደሞተ አብራራች። ከቻለች፣ በቀብሩ ስርዓት ለመፅናናትን እና ለማዘን ነው የመጣችው።

ወደ ቀብር የመጣቸው በእራሷ መፅናናት ፈንታ። የመጀመሪያ ልጇን በቅርብ እንደሞተ ነገረችኝ። የምታምር ሴት ልጅ አቅፋ ነበር። ወደምታምረው ልጅ መመልከትን ከእርሷ ተማርኩ። የልጅቷን እናት እንዲህ ብዬ ጠየኩ፣ስሟ ማን ነው? ፈጣኑ እና አስደሳቹ መልሷ እንዲህ ነበር “ስሟ ሀሴት ይባላል። ሀሴት ሁሌም ከሀዘን በኋላ ነው የሚመጣው።”

ምስክርነቷን ለኔ እያካፈለች ነበር። መፅናናቷ እርግጥ ከሆነው ብቸኛው ምንጭ እንደሆነ ማየት እችላለሁ። እግዚያብሄር ብቻ ነው ልቦችን የሚያውቀው፣ እናም በእውነት “ እንዴት እንደሚሰማችሁ አውቃለህ” ሊል የሚችለው እሱ ብቻ ነው። ነገር ግን ለእነርሱ የጌታን ፍቅር እና መጨነቅ እንደሚሰማን መናገር እንችላለን እና መመስከር አለብን።

እንደ ደቀመዝሙርነታችሁ፣ ለሰማይ አባታችን ልጅ ሰላም እና ደስታ ጊዜ ስታመጡ፣ ምን ያህል ደስታ እንደሚሰማው በከፊል ብቻ ማወቅ እችላለሁ።

ጌታ እኛን፣ የእርሱን ደቀ መዛሙርት፣ አንዳችን የአንዳችንን ሸክም ለመሸከም እንደጠየቀን ምስክርነቴን እሰጣለሁ። ጌታ በሐጢያት ክፍያው እና በትንሳኤው አማካኝነት የሞትን ሀይል እንደሰበረው ምስክርነቴን እሰጣለሁ። ህያው ክርስቶስ ለማፅናናት ቃል ለገቡት መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክ ምስክርነቴን እሰጣለሁ።

እንደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር አባል ለሀያ አመት በነበረችበት ጌዜ በሙሉ በልሷል ላይ በምታደርገው ጌጥ ላይ ስለነበረው እውነት ሁላችሁም፣ እኔ እንደሆንኩኝ፣ ምስክሮች ናችሁ፣ “ልግስና አትወድቅም።”9 የእነዚህ ቃላት ሙሉ ትርጉም ምን እንደሆነ አሁንም አላውቅም። ነገር ግን እርዳታ የሚፈልጉትን ለመርዳት ስትሞክር ይህን ተመልክቻለሁ። ቅዱሳት መጻህፍት ይህን እውነት ይነግሩናል፥ “ልግስና የክርስቶስ ንጹህ ፍቅር ነች።”10

የእርሱ ፍቅር አይወድቅም፣ እናም በልባችን ውስጥ “ከሚያዝኑት ጋር ለማዘን… እና መፅናናት የሚያስፈልጋቸው ለማፅናት” የሚሰማንን በምንም አናቆምም።11 ወይም በተስፋ የሚሰጠው ሰላምም ለእርሱ ብለን ሌሎችን ስናገለግል በምንም አይተዉንም።

እንደ ምስክሩ፣ ህያው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እና አፅናኙ መንፈስ ቅዱስን የደከሙትን ጉልበቶች ለማጠናከር እና የሚንዘላዘለውን እጅ ለማንሳት ለመርዳት ለምታደርጉት ሁሉ አመሰግናችኋለሁ።12 እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ደቀመዛሙር ለረዱኝ እና ለባረኩኝ በህይወቴ ለሚገኙ ሴቶችም በልቤ በሙሉ አመሰግናለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።