2010–2019 (እ.አ.አ)
አባክኙን ልጅ ጥበቃ
ኤፕረል 2015


አባክኙን ልጅ ጥበቃ

እናንተ እና እኔ በሕይወታችን ውስጥ የጠፉትን ሰዎች እንዴት በጥሩ ሁኔታ መቅረብ እንዳለብን እንድናውቅ እራዕይ እንቀበል።

አዳኙ ምድራዊ አገልግሎቱን የፈውስ እና የማዳን ኃይሉን በማስተማር አሳለፈ። በአንድ ወቅት በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሉቃስ ምዕራፍ 15 ላይ ከሃጢያተኞች ጋር ስለበላ እና ጊዜ ስላሳለፈ በእርግጥ ተተቸ (ሉቃስ 15፥2 ተመልከቱ)። አዳኙ ይህንን ትችት መንገዳቸውን ላጡት ሰዎች እንዴት መመለስ እንዳለብል ሁላችንንም ለማስተማር እንደ አጋጣሚ ተጠቀመው።

ለተቺዎቹ ሁለት ጠቃሚ ጥያቄዎችን በመጠየቅ መልስ ሰጠ፥

“መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?” (ሉቃስ 15፥4)።

“አስር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት መብራት አብርታ ቤትዋን ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?” (ሉቃስ 15፥8)።

ከዛ አዳኙ ስለ የአባካኙን ልጅ ምሳሌ አስተማረ። ይህ ምሳሌ ስለ 100 በጎች ወይም ስለ 10 ድሪሞች አይደለም፤ ስለ አንድ የጠፋ ውድ ልጅ ነው። በምሳሌው አማካኝነት፣ አዳኙ የቤተሰብ አባል መንገዱን ወይም መንገዷን ሲስት ወይም ስትስት እንዴት መመለስ እንዳለብን ምን ያስተምረናል?

አባካኙ ልጅ የእሱን ውርስ አሁን እንደሚፈልግ ለአባቱ ነገረው። የቤቱን እና የቤተሰቡን ደህንነት ትቶ የአለምን ነገር ለማባረር መሄድ ፈለገ (ሉቃስ 12፥12–13 ተመልከቱ)። እባካችሁን በአዳኙ ምሳሌ ውስጥ አባትዬው ለልጁ ውርሱን በመስጠት ፍቅር በተሞላበት ሁኔት እንደመለሰለት አስተውሉ። እውነት ነው አባትዬው ልጁን እንዲቆይ ለማሳመን የሚቻለውን ነገር ሁሉ ማድረግ መቻል ነበረበት። ይሁን እንጂ፣ ጎልማሳው ልጅ ምርጫውን ከመረጠ በኋላ፣ ጠቢቡ አባት ለቀቀው። ከዛ አባትዬው ቅን የሆነ ፍቅርን አሳየ እናም ተመለከተው እናም ጠበቀው (ሉቃስ 15፥20 ተመልከቱ)።

ቤተሰቤ ተመሳሳይ ልምድ አጋጥሞታል። ሁለቱ አማኝ ወንድሞቼ፣ ድንቋ እህቴ እና እኔ በምሳሌያዊ ወላጆች ነበር ያደግነው። ወንጌልን በቤታችን ውስጥ ነበር የተማርነው፣ በስኬታማ ሁኔታ ወደ ወጣትነት እድሜ ደረስን እናም አራታችንም ከባለቤቶቻችን ጋር በቤተ-መቅደስ ውስጥ ነበር የታተምነው። ይሁን እንጂ፣ በ1994 እህታችን ሱዛን፣ በቤተክርስቲያኗ እና በአንዳንድ ትምህርቶቿ ደስተኛ ሳትሆን ቀረች። የቤተክርስቲያኗን ቀደምት መሪዎችን በሚያንጓጥጡ እና በሚተቹ ሰዎች ተፅዕኖ ደረሰባት። በሕይወት ባሉ ነብያት እና ሐዋርያት ላይ ያላትን እምነት እንዲደበዝዝ ፈቀደች። ከጊዜ በኋላ ጥርጣሬዋ እምነቷን አሸነፈው እና ቤተክርስቲያኗን ለመለየት መረጠች። ሱዛን ታሪኳን ሌሎችን ይረዳል ብለን ተስፋ በማድረግ እንዳካፍል ፈቅዳልኛለች።

ወንድሞቼ እና እኔ እንዲሁም ባሏ የሞተባት እናታችን በጣም አዘንን። እምነቷን እንድትተው ምን ሊያደርጋት እንደቻለ መገመት አቃተን።

ወንድሞቼ እና እኔ እንደ ኤጲስ ቆጶሶች እና የምልአተ ጉባኤ ፕሬዘደንቶች በመሆን አገልግለናል፣ እናም ከዋርድ እና ምልአተ ጉባኤ አባሎች ዘጠና ዘጠኞቹን ትተን አንዱን ፍለጋ ስንሄድ የውጤትን ደስታ ተለማምደናል። ይሁን እንጂ፣ በእህታችን ጉዳይ ላይ እሷን ለማዳን እና እንድትመለስ ለመጋበዝ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ የበለጠ እየሸሸች እንድትሄድ ነበር ያደረጋት።

እንዴት ለእሷ ምላሽ መስጠት እንዳለብን ለማወቅ የሰማይን ምሪት ስንሻ፣ የአባካኙ ልጅ ምሳሌ ላይ ያለውን የአባትዬውን ምሳሌ መከተል እንዳለብን ተገለፀልን። ሱዛን የራሷን ምርጫ አድርጋለች እናም በምርጫዋ ልንተዋት ይገባል። ነገር ግን ለእሷ ያለንን ቅን ፍቅር ሳታውቅ እና ሳይሰማት መሆን የለበትም። እናም ስለሆነ በታደሰ ፍቅር እና ደግነት ተመለከትን እናም ጠበቅን።

እናቴ ሱዛንን ማፍቀር እና ለእሷመጨነቋን አላቆመችም። እናቴ ቤተ-መቅደስ በተካፈለች ቁጥር፣ የሱዛንን ስም ተስፋ ሳታጣ በፀሎት ስም ዝርዝር ውስጥ ትከተዋለች። በካሊፎርኒያ ውስጥ ለሱሳን በቅርበት የሚኖሩት ታላቅ ወንድሜ እና ሚስቱ በሁሉም የቤተሰብ ክስተት ጋበዟት። በሱዛን የልደት ቀን በየአመቱ በቤታቸው ውስጥ እራት አዘጋጁ። ሁሌም ከእሷ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው እና ለእሷ ያላቸውን እውነተኛ ፍቅር ማወቋን አረጋገጡ።

ታናሽ ወንድሜ እና ሚስቱ በዩታ ለሚገኙት የሱዛን ልጆች ደረሱላቸው እና ተንከባከቧቸው እናም ወደዷቸው። ልጆቿ ለቤተሰብ ስብሰባዎች ሁሌም መጋበዛቸውን አረጋገጡ እና የሱዛን የልጅ ልጅ መጠመቂያዋ ሰአቱ ሲደርስ ወንድሜ ስነ-ስርዓቱን ለመፈፀም እዛ ነበር። እንዲሁም ሱዛን ያልተዋት አፍቃሪ የቤት ለቤት እና የጉብኝት አስተማሪዎች ነበሯት።

ልጆቻችን ወደ ሚስዮን ሲሄዱ እና ሲያገቡ ሱዛንም ተጋብዛ ነበር እናም ይህን የቤተሰብ በዓሎች ተካፍላለች።ሱዛን እና ልጆቿ ከእኛ ገር እንዲሆኑ እና ከሁሉም በላይ እንደምንወዳቸው እና የቤተሰቡ አካል እንደሆኑ ለማሳወቅ የቤተሰብ ክስተቶችን ለመፍጠር ጥረናል። ሱዛን በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ድግሪ ስትቀበል፣ በምርቃቷ ጊዜ ለመደገፍ ሁላችንም እዛ ነበርን። ምርጫዎቿን በሙሉ መቀበል ባንችልም እሷን በእርግጥምመቀበል እንችል ነበር። ወደድናት፣ ተመለከትናት እና ጠበቅናት።

በ2006(እ.አ.አ)፣ ሱዛን ቤተክርስቲያኗን ከተወች 12 አመታት ካለፉ በኋላ፣ ልጃችን ኬቲ ከባሏ ጋር የህግ ትምህርት እንዲካፈል ወደ ካሊፎረኒያ ተጓዘች። ከሱዛን ጋር በአንድ ከተማ ውስጥ ነበሩ። እነዚህ ወጣት ጥንዶች ለእርዳታ እና ለግዳፍ አክስታቸውን ሱዛንን ተመለከቱ እናም ወደዷት። ሱዛን የሁለት አመቷን የልጅ ልጃችንን ሉሲን ተንከባከበቻት እና ሱዛን ሉሲን በምሽት ፀሎቶቿ እየረዳቻት እራሷን አገኘች። ኬቲ አንድ ቀን ስልክ ደውላልኝ ሱዛን ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሳ ትመጣለች ብዬ እገምት እንደሆነ ጠየቀችኝ። እንደምትመጣ እንደተሰማኝ እና ትዕግስተኛ መሆናችንን መቀጠል እንዳለብን አረጋገጥኩላት። ሌላ ሶስት አመታት እንዳለፉ፣ ቀጣይነት ባለው ፍቅር፣ ተመለከትን እና ጠበቅን።

ከስድስት አመታት በፊት በዚህ ቅዳሜ እና አሁድ ባለቤቴ ማርሺያ እና እኔ በዚህ የስብሰባ መአከል ውስጥ የፊት ለፊት መደዳ ላይ ተቀምጠን ነበር። በዛ ቀን እንደ አዲስ አጠቃላይ አመራር ልሾም ነበር። ሁልጊዜ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ግንኙነት ያላት ማርሺያ እንደዚህ የሚል ማስታወሻ ፅፋልኝ ነበር፣ “ለሱዛን የመመለሻ ጊዜዋ ነው መሰለኝ።” ወጥቼ ለሱዛን ስልክ ደውዬ የዛን ቀን አጠቃላይ ጉባኤውን እንድታይ እንድጋብዛት ልጄ ኬቲሃሳብ አቀረበች።

በእነዚህ ታላቅ ሴቶች ተነሳስቼ ወደ መግቢያው ሄጄ ለእህቴ ደወልኩላት። የድምፅ መልዕክቷን አገኘሁና የዛን ስብሰባ የአጠቃላይ ጉባኤ ክፍል እንድታይ ብቻ ጋበዝኳት። መልዕክቱን አገኘችው።ለደስታችን፣ የጉባኤውን ሁሉንም ክፍሎች ለማየት የሆነ ነገር ተሰማት። በቀደምት አመታት ውስጥ ከወደደቻቸው ነብያት እና ሐዋርያት ሰማች። ከዚህ በፊት ሰምታ የማታውቃቸውን አዳዲስ ስሞች እንደ ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ እና ሽማግሌዎች ማለትም ቤድናር፣ ኩክ፣ ክርስቶፈርሰን እና አንድርሰን አገኘች። በዚህ እና በሌሎች ከሰማይ የመጡ ልምዶች ወቅት፣ እህቴ ልክ እንደ አባካኙ ልጅ፣ ወደ እራሷ መጣቸ (ሉቃስ 15፥17 ተመልከቱ)። የነብያቶች እና የሐዋርያቶች ቃሎች እንዲሁም የቤተሰቧ ፍቅር እንድትዞር እና ወደ ቤት ተመልሳ እንድትራመድ ገፋት። ከ15 አመት በኋላ የጠፋችው ልጃችን እና እህታችን ተገኘች። ምልከታው እና ጥበቃው ተፈፀመ።

ሱዛን ይህንን ክስተት ልክ በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ ሌሂ እንደገለፀው ገለፀችው። የብረት ዘንጉን ለቀቀችው እና እራሷን በጨለማ ውስጥ አገኘችው (1 ኔፊ 8፥23 ተመልከቱ)። እምነቷ በክርስቶስ ብርሃን እንደገና እስከሚነቃ ድረስ እና ጌታ እና ቤተሰቦቿ እየሰጧት ያለው ነገር በአለም ውስጥ እያየች ባለው ነገር ላይ አጉልቶ እስኪያበራ ድረስ እንደጠፋች እንዳላወቀችውገለፀች።

ባለፉት ስድስት አመታት ተአምር ተከስቷል። ሱዛን የመጽሐፈ ሞርሞን የታደሰ ምስክርነት አላት። የቤተ-መቅደስ መግቢያ ተቀብላለች። በቤተ-መቅደስ ውስጥ እንደ ስነ-ስርዓት ሰራተኛ አገልግላለች እናም አሁን በዋርዷ ውስጥ የወንጌል ትምህርት ክፍልን ታስተምራለች። የሰማይ መስኮቶች ለልጆቿ እና ለልጅ ልጆቿ ተከፍተዋል እናም አስቸጋሪ ውጤቶች ቢኖሩትም እንዳልሄደች ነው የሚሰማው።

ብዙዎቻችሁ ልክ እንደ ኒልሰን ቤተሰቦች ለጊዜው መንገዳቸውን የሳቱ የቤተሰብ አባሎች ሊኖራችሁ ይችላል። 100 በጎች ላላቸው፣ የአዳኙ ምክር ዘጠና ዘጠኙን ትተው አንዱን ለማዳን እንዲሄዱ ነው። አስር ድሪም ላላቸው እና አንዱ ለጠፋባቸው የእርሱ መመሪያ እስከምታገኙት ድረስ እንድትፈልጉት ነው። የጠፋው የወንድ ወይም የሴት ልጃቹ ሲሆን፣ ወንድማችሁ ወይም እህታችሁ ስትሆን እና እሱ ወይም እሷ ለመሄድ ስትመርጥ፣ ለምድረግ ከምንችለው ነገሮች ሁሉ በኋላ፣ ያንን ሰው በሙሉ ልባችን እንደምንወድ እና እንደምንመለከት፣ እንድመንፀልይ በቤተሰባችን ውስጥ ተምረናል፤ እና የጌታ እጅ እስከሚገለፅም እንጠብቃለን።

ምናልባት በዚ ሄደት ውስጥ ጌታ ያስተማረኝ በጣም ጠቃሚ የሆነው ትምህርት የተከሰተው እህቴ ቤተክርስቲያኗን ትታ ከሄደች በኋላ በነበረን የቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ውስጥ ነበር።አንድ ላይ ሰናጠና ልጃችን ዴቪድ ሉቃስ 15ን አያነበበ ነበር። የአባካኙል ልጅ ምሳሌ ሲያነብ፣ የዛን ቀን ከዚህ በፊት ከሰማሁት በተለየ ሁኔታ ሰማሁት። በሆነ ምክንያት ሁልጊዜ እቤት ከቆየውን ልጅ ጋር ነበር ግንኙነት የሚሰማኝ። በዚያ ጠዋት ዴቪድ ሲያነብ በተወሰነ መልኩ አባካኙ ልጅ እኔ እንደሆንኩኝ ተገነዘብኩኝ። ሁላችንም የእግዚአብሔር ክብር ጎድሎናል (ሮሜ 3፥23 ተመልከቱ)። ሁላችንም ለመዳን የአዳኙንየኃጢያት ክፍያ እንፈልጋለን። ሁላችንም ጠፍተናል እናም መገኘት አለብን። ይህ ራዕይ በዛን ቀን እህቴ እና እኔ የአዳኙን ፍቅር እና የሃጢያት ክፍያውን እንደምንፈልግ እንዳውቅ ረዳኝ። ሱዛን እና እኔ በእርግጥ በአንድ አይነት ወደ ቤት መመለሻ መንገድ ላይ ነበርን።

በምሳሌ ውስጥ አባቱ አባካኙን ልጅ ሰላም ያለበትን የሚገልጹት የአዳኝ ቃላትኃይለኛ ናቸው፣ እና እነዚህምእኔ እና እናንተ ወደ ሰማይ ቤታችን ስንመለስ ከአብ ጋር የሚኖረን አጋጣሚ አገላለፆች እንደሚሆኑ አምናለው። ስለሚያፈቅር፣ ስለሚጠብቅ እና ስለሚመለከት አባት ያስተምሩናል።እነዚህ የአዳኙ ቃሎች ናቸው፥“እርሱም ገና ከሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው” (ሉቃስ 15፥20 ተመልከቱ)።

እናንተ እና እኔ ሌሎችን በሕይወታችን ውስጥ የጠፉትን ሰዎች እንዴት እንደምንቀርብ ለማወቅ እናም፣ አስፈላጊ ሲሆንም፣ አባካኙን ስናፈቅር፣ ስንመለከት እና ስንጠብቅ የሰማይ አባታችን እና የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕግስት እናፍቅር እንዲኖረን ራዕይ እንቀበል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።