2010–2019 (እ.አ.አ)
ፍትህ፣ ፍቅር፣ እና ምህረት የሚገናኙበት
ኤፕረል 2015


ፍትህ፣ ፍቅር፣ እና ምህረት የሚገናኙበት

ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቃየው፣ የሞተው፣ እናም ከሞት የተነሳው፣ እኛን ከፍ ለማድረግ ነው።

ደህንነትን ከማይጠብቅ ገመድ፣ ካለቀበቶ፣ ወይም ተራራ ከማይወጣበት እቃ፣ ሁለት ወንድሞች፣ የ14 አመቱ ጅሚ እና የ19 አመቱ ጆን (እውነት ስማቸው አይደለም)፣ በተወለድኩበት በደቡብ ዮታ ውስጥ በስኖው ካንየን መናፈሻ ውስጥ የሚገኘውን ተራራ ለመውጣት ሞከሩ። በጣም አስቸጋሪ የሆነውን የተራራ መውጣት ትግላቸውን በሚጨርሱበት በተራራው ጫፍ አካባቢ፣ የሚያፈነግጥ ክፈፍ ተራራ ላይ ለመውጣት የሚፈፅሙበትን ትንሽ ሜትሮች እንዳይጨርሱ የሚከለክላቸው ነገር ተመለከቱ። ይህን አልፈው ለመሄድ አልቻሉም፣ ነገር ግን ከዚህም ለመውረድ አልቻሉም። በዚያም ያለረዳት ቀርተው ነበር። በጥንቃቄ ወደዚህ እና ወደዚያ ከሄዱ በኋላ፣ ጆን ታናሽ ወንድሙን ወደ ክፈፉ ላይ እንዲወጣ ለመግፋት እግሩን የሚያሳርፍበት ቦታ አገኘ። ነገር ግን ራሱን ወደዚያ ለማውጣት አልቻለም። የእጅ ወይም በእግር ለሚያሳርፍበት ቦታ ለማግኘት በሚጥርበት ጊዜ፣ ጡንቻው መሸምቀቅ ጀመረ። ፍርሀት መጣበት፣ እናም ለህይወቱም መፍራት ጀመረ።

ለብዙ ጊዜ በዚያ ለመቆየት ባለመቻሉ፣ ጆን ያለው እድል መዝለል እና የክፈፉን ጫፍ መያዝ ብቻ እንደሆነ ወሰነ። ውጤታማ ከሆነ፣ ታላቅ በሆነው የክንዱ ጥንካሬ ራሱን ወደ ደህንነት ጎትቶ ማውጣት ይችላል።

በራሱ ቃላት እንዲህ ብሏል፥

“ከመዝለሌ በፊት፣ ምንም እንኳን በድንጋይ በተሞላው ተራራ ላይ እንደማይገኝ ባውቅም፣ ወደ እኔ ለመዘርጋት የሚችል የዛፍ ቅርንጫፍ ለመፈለግ እንዲሄድ ጆንን ነገርኩት። ብቻዬን እንዲተወኝ ለማድረግ የፈለኩበት ማታለያ ነበር። መዝለሌ ውጤታማ ካልሆነ፣ ትንሹ ወንድሜ በመውደቅ ስሞት እንዳያየኝ ለማድረግ እችል ነበር።

“ከሚያየኝ ቦታ እንዲሄድ ትንሽ ጊዜ ከሰጠሁት በኋላ፣ ቤተሰቤ እንደምወዳቸው እንዲያውቁ እና ጅሚ በደህንነት ወደቤት እንዲደርስ የመጨረሻ ጸሎቴን አደረኩኝ፣ ከዚያም ዘለልኩኝ። ካለሁበት በሀይል ገፍቼ፣ የዘለልኩበት የክፍፉን ጫፍ እስከክርኔ ድረስ ለመንካት ችዬ ነበር። ነገር ግን እጆቼ ክፍፉን ሲመቱ፣ የነካሁት በጠፍጣፋው ድንጋይ ላይ ካለ አሸዋ በስተቀር ምንም ሌላ አልነበረም። በዚያ ላይ የምይዘው ምንም ነገር ሳይኖር የተንጠለጠልኩበትን ስሜት አስታውሳለሁ፣ ምንም ጫፍ፣ ምንም ከፍ ያለ ድንጋይ፣ ምንም የሚያዝ ነገር አልነበረም። ጣቶቼ ቀስ በቀስ በአሸዋው ላይ ሲንሸራተቱ ተሰማኝ። ህይወቴ እንዳለቀ አወቅኩኝ።

“ነገር ግን በድንገት፣ በበጋ እንደነበር መብረቅ አይነት፣ ሁለት እጆች በተራራው ጫፍ ላይ ከአንድ ቦታ መጥተው ከመጠናቸው በላይ በሆነ ጥንካሬና ውሳኔ እጆቼን ያዟቸው። ታማኙ ትንሽ ወንድሜ የውሸት ዛፍ ቅርንጫፍን ለመፈለግ አልሄደም። ምን ለማድረግ አላማ እንዳለኝ በመገመት፣ ካለበት አልተነቃነቀም ነበር። በጸጥታ፣ ሳይተነፍስም፣ ለመዝለል እንደምሞክር ሞኝ እንደሆንኩኝ በማወቅ ይጠብቅ ነበር። ስዘል፣ ያዘኝ፣ እናም እንድወድቅ አልፈቀደም። እነዚያ ጠንካራ የወንድም ክንዶች ያለእርዳታ በመውደቅ እሞትበት በነበርኩበት ላይ ተንጠልጥዬ ባለሁበት በዚያ ቀን ህይወቴን አዳነ”።1

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ዛሬ ፋሲካ ነው። ምንም እንኳን ሁልጊዜ ማስታወስ ቢገባንም (በየሳምንቱ የቅዱስ ቁርባን ጸሎታችን እንደምናስታውስ ቃል እንገባለን)፣ ይህም ከምንወድቅበት፣ እና ከወዳቂነታችን፣ ከሀዘኖቻችን እና ከኃጢያቶቻችን በወንድማዊ እጆች እና ክንዶች ከሞት ያዳነንን በልዩ የምናስታውስበት ከአመቱ ቀናት ሁሉ በላይ የተቀደሰ ቀን ነው። ይህን በጆን እና በጅሚ ቤተሰቦች የተነገረውን ታሪክ በመጠቀም፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ ምስጋናዬን አቀርባለሁ እናም ወደዚህ የመሩት በእግዚአብሔር መለኮታዊ እቅድ ውስጥ ላሉት ድርጊቶችንና “ኢየሱስ የሚያቀርብልንን ፍቅር”2 ትርጉም ለሚሰጡትም ምስጋና አቀርባለሁ።2

አለማዊ አስተያየትን በሚያፈቅሩ ህብረተሰቦቻችን ውስጥ ስለ አዳምና ሔዋን እና ወደ ሟችነት “ስለወደቁበት እድል” መናገር እንደ ተቀባይነት ያለው ፋሽን አይደለም። ይህም ቢሆን፣ የክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ በሙሉ ለመረዳት እና የተወለደበትን እና የህይወቱን ልዩ አላማ በብቁ ምስጋና ለማግኘት አለመቻላችን እውነት ነው – በሌላም አባባል፣ ውድቀት ካለው ውጤት ጋር ከኤድን የወደቁ አዳም እና ሔዋን እንደነበሩ ያለመረዳት ገናን ወይም ፋሲካን በእውነት ለማክበር ምንም መንገድ የለም።

ከዚያ በፊት በዚህች ምድር ምን እንደነበረ ምንም አላውቅም፣ ነገር ግን እነዚህ ሁለት ሰዎች በእግዚአብሔር መለኮታዊ እጅ እንደተፈጠሩ፣ የሰው ሞት ወይም የወደፊት ቤተሰብ ባልነበረበት በገነት ሁኔታ በብቻቸው እንደኖሩ፣ እናም በምርጫዎች ምክንያት የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመተላለፍ የአትክልት ስፍራን ለቀው እንዲሄዱ ቢያደርጋቸውም ከስጋዊ ሞት በፊት ልጆች ለመውለድ እንዲችሉ ያስቻላቸው እንደነበር አውቃለሁ።3 ለሁኔታቸው ተጨማሪ ሀዘን እና ረቂቅ በመስጠት፣ የተላለፉበት መንፈሳዊ ውጤትም ነበረው፣ ከእግዚአብሔር ፊት ለዘለአለም ወጥተው ነበርና። በዚያ በወደቀ አለም ውስጥ ስለተወለድን እና እኛ የእግዚአብሐርን ህግጋት ስለምንተላለፍ፣ አዳም እና ሔዋን እንደነበራቸው ቅጣት እኛም ተጋፍጠን ነበር።

ምን አይነት አስጨናቂ ሁኔታ ነው! ወደ መጨረሻ ሞት እየወደቁ፣ ወደ ዘለአለም ሀዘን እየወረዱ ያሉ በሰው ዘር ውስጥ የሚገኙ እያንዳንዱ ወንድ፣ ሴት እና ልጅ በሙሉ የሚያድናቸው ሳይኖር እየወደቁ ነበር። ህይወት እንዲህ እንዲሆን የተመደበ ነበርን? ይህ የሰው ዘር ህይወት አጋጣሚ ታላቅ መጨረሻ ነውን? እኛም እያንዳንዳችን የምንደገፍበትን እየፈለግን፣ የምንይዘውን ነገር ስንፈልግ፣ እኛን የሚይዝ ከማግኘት ከጣታችን ስር ከሚንሸራተት አሸዋ በስተቀር ምንም የሚያድነን ሳናገኝ በቀዝቃዛ ሸለቆ ላይ፣ ምንም ሀሳብ በሌለው ሁለንተና ውስጥ ተንጠልጥለን እንገኛለን? በህይወት ያለን አላማ ትርጉም የሌለው ህይወት፣ ወደምንችልበት ለመዝለል የምንሞክርበት፣ ለተመደበልን ሰባ አመት ለመኖር፣ ከዚያም ለመውደቅ፣ እናም ለዘለአለም በመውደቅ ለመቀጠል ብቻ ነውን?

የእነዛ ጥያቄዎች መልሱ ግልጽ እና ለዘለአለም አይደለም የሚል ነው። ከጥንት እና ከዚህ ዘመን ነቢያት ጋር፣ “ሁሉም ነገሮች የተደረጉት ሁሉን ነገሮች በሚያውቀው ጥበብ” በክል እንደሆነ እመሰክራለሁ።4 ስለዚህ፣ እነዚያ የመጀመሪያ ወላጆች ከገነት ከወጡ ጊዜ ጀምሮ፣ የሁሉም አባት እግዚአብሔር፣ የአዳም እና የሔዋንን ውሳኔ አስቀድሞ በማወቅ፣ የወደቁበት ውጤት ለዘለአለም ደስታ የታቀደበት እንደሆነ ለእነርሱ፣ እናም እስከ እኛ ዘመን ድረስም፣ እንዲያውጁላቸው የሰማይ መላእክትን ላከላቸው። በዘመን መካከል ለአዳም ኃጢያት ለመክፈል የሚመጣ አዳኝ፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅን፣ ሐዋሪያው ጳውሎስ እንደጠራውም ሌላ “አዳምን”5፣ መስጠቱ የመለኮታዊ አላማው ክፍል ነበር። ያም የኃጢያት ክፍያ በስጋዊ ሞት ላይ ፍጹም ድል ያገኛል፣ ይህም በአለም ላይ ላሉ ወይም ለተወለዱ ሰዎች በሙሉ ምንም ቅድመ ሁኔታ የማያስፈልገው ከሞት የመነሳት እድል ይሰጣል። በምህረትም ከአዳም እስከ አለም መጨረሻ ድረስ፣ ንስሀ በመግባት እና ለመለኮታዊ ትእዛዛት ታዛዥ በመሆን ቅድመ ሁኔታዎች፣ ለሁሉም ለግል ኃጢያቶቻቸው ምህረትን ይሰጣል።

እንደተሾመ አንዱ ምስክር፣ በዚህ ፋሲካ ጠዋት የናዝሬቱ ኢየሱስ የአለም አዳኝ፣ ያ “የመጨረሻው አዳም”፣6 የእምነታችን ጸሀፊ እና ፈጻሚ፣ የዘለአለም ህይወት አልፋና ኦሜጋ እንደሆነ አውጃለሁ። ጳውሎስ እንዳወጀው፣ “ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።”7 እናም ደግሞ የአባቶች አለቃ ነብዩ ሌሂ እንዳለው፥ “ሰዎች እንዲኖሩ … አዳም ወደቀ። እናም መሲሁ የሰው ልጆችን ከውድቀት ለማዳን በፍፃሜው ቀን ይመጣል።”8 ከሁሉም በላይ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ባስተማረበት በሁለት ቀን ስብከት ውስጥ የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢያት ያዕቆብ በግልጽ እንዳስተማረው፣ “በመተላለፍ የተነሳ ደግሞ ትንሣኤ ይመጣ ዘንድ አስፈልጓል።”9

ስለዚህ ዛሬ ባጋጠሙን ውድቀቶች ፣ በምናውቃቸው በእያንዳንዱ ሀዘኖች፣ ተስፋ ባስቆረጡን በማንኛቸውም፣ ባጋጠሙን በማንኛቸውም ፍርሀቶች ላይ በሙሉ ያለውን ድል፣ እንዲሁም ከሞት ለምንነሳበት እና ለኃጢያቶቻችን ምህረት ስጦታ እናከብራለን። ያም ድል ለእያንዳንዳችን የሚገኘው ከሁለት ሺህ አመታት በፊት በዚህ ሳምንት በኢየሩሳሌም በነበረው ድርጊት ምክንያት ነው።

በገትሰመኔ የአትክልት ስፍራ ከነበረ የመንፈስ ስቃይ ጀምሮ፣ በካልቨሪ መሰቀል በመቀጠል፣ እና ለእርሱ በተመደበው መቃብር ውስጥ በሚያስደንቀው የሰንበት ጠዋት ላይ የተፈጸመውን፣ ኃጢያት የሌለው፣ ንጹህ፣ እና ቅዱስ ሰው፣ እንዲሁም እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ፣ በዚህ አለም ታሪክ ውስጥ ማንም የሞተ ሰው አድርጎት የማያውቀውን አደረገ። በራሱ ሀይል፣ መንፈሱ እንደገና ከሰውነቱ በምንም እንዳትለያይ፣ ከሞት ተነሳ። ቅዱሳት መጻህፍት በራሱ ፈቃድ፣ የታሰረበትን የመቀበሪያ ጨርቁን አውልቆ፣ በፊቱ ላይ ተደርጎ የነበረውን የመቃብር ጨርቅ በጥንቃቄ “ለብቻው በአንድ ስፍራ [ጠምጥሞ]” አስቀመጠ።10

እነዚያም የሶስት ቀናት የኃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ ድርጊቶች ኢየሱስ ይህን በማድረግ ካጋጠማቸው ጋር፣ ይህም ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆኑ ጊዜዎችን፣ ተመሳሳይ የሌለው መስዋዕትን፣ በአለም ታሪክ ውስጥ ተደርጎ ከሚታወቀው የመለኮታዊ ፍቅር የሚያሳይ ውጤትን አንድ ላይ የሚያጣምር ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቃየው፣ የሞተው፣ እናም ከሞት የተነሳው፣ እንደ በጋ ቀን መብረቅ፣ ሁለት የእርዳታ እጆችን ወደ እኛ ለመዘርጋት፣ በሁለት የወንድም ክንዶች እኛን ለመያዝ፣ እናም ለእርሱ ባለን ታማኝነት ወደ ዘለአለም ህይወት እኛን ከፍ ለማድረግ ነው።

ምንም እንኳን በቆሰለ እግሩ ቢቆምም በዚህ ፋሲካ እርሱን እና ኢየሱስ አሁንም ድረስ በሞት ላይ ድል እንዲኖረው እርሱን ለእኛ የሰጠውን አብን አመሰግናለሁ። በዚህ ፋሲካ እርሱን እና በቆሰሉ የእጅ መዳፍና ፍንጅ የዘረጋ ቢሆንም ኢየሱስ መጨረሻ የሌለው ጸጋ ለእኛ እንዲዘረጋ ለእኛ ለሰጠው አብ ምስጋና አቀርባለሁ። በዚህ ፋሲካ እርሱን እና በላብ በቆሸሸው የአትክልት ስፍራ፣ ምስማር በተሰካበት መስቀል፣ እና በግርማዊው መቃብር ፊት ይህን ለመዘመር እንድንችል እርሱን ለሰጠን አብ ምስጋና አቀርባለሁ፥

እንዴት ታላቅ፣ እንዴት ግርማዊ፣ እንዴት ፍጹም፣

የቤዛነት ታላቅ ንድፍ፣

ፍትህ፣ ፍቅር፣ እና ምህረት የሚገናኙበት

በመለኮታዊ ስምምነት!11

ከሞት በተነሳው በቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።