2010–2019 (እ.አ.አ)
አዎን፣ እንችላለን እናም እናሸንፋለን!
ኤፕረል 2015


አዎን፣ እንችላለን እናም እናሸንፋለን!

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምስክርነታችንን አፅንተን መያዝ አለብን። ከዚያም የየቀኑን ከክፉ ጋር የለንን ጦርነት እናሻንፋለን።

ውድ ወንድሞች፣ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ሁሉ ላላችሁ የእግዚአብሔርን ስልጣን ለተሸከማችሁት ለእናንተ ለመናገር ባለኝ እድል ትሁት ሆኛለሁ።

ፕሬዘዳንት ቶማስ  ኤስ. ሞንሰን በአንድ ወቅት እነዲ አሉ:

“አንዳንዴ አለም ለመኖር አስፈሪ ቦታ ሊሆን ይችላል።የህብረተሰቡ የግብረገብ ዋጋዎች በፍጥነት በሚያውክ ሁኔታ እየተበላሽ ይመስላል። ማንም ሰው — ወጣትም ይሁን ወይም አዛውንት ወይም በመካከለኛ እድሜ ላይ ያለ — ሊጎዳው እናም ሊያጠፋው አቅም ካላቸው ነገሮች መጋለጥን ማስወገድ ይቻላል።

“… ነገር ግን ተስፋ መቁረጥ የለብንም። … እኛ ሀጢያት ላይ ጦርነት እያስነሳን ነው።… ማሸነፍ የምንችለው እና የምናሸንፍው ጦርነት ነው።ይህንንም ጦረነት ለማድረግ የሰማይ አባታችን የሚያስፈልጉንን መሳሪያዎች ሰጥቶናል።” 1

ሁላችንም፣ ወጣትም ወይም አዛውንት፣ በፕሬዘዳንት ሞንሰን ከጠቀሰውን ጦርነት ጋር በየቀኑ እንጋፈጣለን። ጠላት እና የእርሱ መላእክቶች እኛን ሊያምታቱ እየሞከሩ ነው።አላማቸው ዘላለማዊ ውርሳችንን እንድንረሳ ለማድረግ ከጌታ ጋር ከገባነው ቃልኪዳን ጋር እንድንለያይ እኛን ለማበረታታት ነው። በታላቁ መማክርት ጉባኤ ላይ እቅዱ ሲቀርብ ከእኛ ጋር ስለነበሩ የሰማይ አባታችን ለእኛ እና ለልጆቹ ያለውን እቅድ ጠንቅቀው ያውቁታል።ድክመቶቻችንን እና ፀባየ ድክመቶቻችንን ለመጠቀም ይሞክራሉ፣ በእነኚህ በማታለል “የጨለማው ጭጋግ…… አይን የሚያሳውሩ፣ እናም የሰው ልጆችን ልብ የሚያጠጥሩ፣ እናም ወደ ሰፊው ጎዳና እነርሱን የሚያስቱና መርተው የሚያጠፉ ናቸው።”2

ተቃርኖን ብንጋፈጥም ፕሬዘዳንት ሞንሰን እነዳስተማሩት፣ ይህ ማሸነፍ የምንችለው እና የምናሸንፍው ጦርነት ነው። ይህንን ለማድረግ ጌታ በእኛ አቅም እና ቁርጠኝነት ይተማመናል።

ቅዱሳን መጻህፍት በጥላቻ ግዜ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ጦርነታቸውን ስለአሸነፉ ምሳሌዎች ይዘዋል። ከነዚህም ምሳሌዎች ውስጥ አንዱ በመጸሀፈ ሞርሞን ውስጥ ሻምበል መሮኒ ነው። ይህ አስደናቂ ወጣት ልጅ ጠቦች እና ጦርነቶች የኔፋውያንን ህዝብ በሙሉ በህይወት የመኖር ስጋት ላይ ባደረጉበት ጊዜያት እውነቱን ለመከላከል ብርታት ነበረው። ሀላፊነቶቹን በመወጣት ውስጥ ድንቅ ቢሆንም፣ ሞሮኒ ትሁት መሆንን ቀጠለ።ይህ እና ሌሎች ጸባዮች በዚያን ጊዜ አስገራሚ፣ በእግዚአብሔር እጆች መሳሪያ እነዲሆን አደረገው። ነቢዩ አልማ እንዳወጀው፣ ሰዎች ሁሉ እነደሞሮኒ ከነበሩ፣ “የሲኦል ሀይል እራሱ ለዘላለም ይናወጥ ነበር፣[ እናም] ዲያቢሎስም በሰው ልጆች ልብ ላይ ስልጣን በጭራሽ ባይኖረው ነበር።”3 ሁሉም የሞሮኒ ባህሪያት የመጡት እርሱ በእግዚያብሄር እና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ4 ባለው ታላቅ እምነት እና የእግዚአብሔርን እና የእርሱን ነብያት ድምጽ ለመከተል ካለው ቁርጠኝነት የተነሳ ነው።5

በምሳሌያዊ አነጋገር፣ በህይወታችን ውስጥ ከክፋት ተፅእኖ ጋር ያለትን ጦርነቶች ለማሸነፍ ዛሬ ሁላችንም እራሳችንን ወደ ዘመናዊው ሻምበል ሞሮኒ መቀየር አለብን። እራሱን ወደ ዘመናዊ ሻምበል ሞሮኒ የለወጠ በጣም ታማኝ የሆነ ወጣት ዲያቆን አውቃለሁ። ምንም እንኳን የወላጆቹን እና የቤተክርስቲያን መሪዎችን ምክር ለመከተል ምንም ያህል ቢሞክርም፣ እምነቱ እና ቁርጠኝነቱ በዚህ የወጣትንት እድሜው በየቀኑ ተፈትኗል። አንድ ቀን ወደ የክፍል ጓደኞ ሲቀርብ፣ በጣም በአስቸጋሪና ምቾት በማይሰጥ ሁኔታ ላይ ተገርሞ ነበር— ጓደኞቹ በሞባይል ስልካቸው ላይ የራቁት ምስሎችን ይመለከቱ ነበር። በዛችው ቅፅበት፣ ይህ ወጣት በጣም ጠቃሚ የነበረውን መወሰን ነበረበት— የሱን ተወዳጅነትን ወይንም እምነቱን እና ፅድቅን የመኖር ቁርጠኝነትን። በጥቂት ሰከንዶች ውሰጥ፣ በብርታት ተሞልቶ እናም ሲያደርጉት የነበረው ትክክል እንዳልነበረ ለጓደኞቹ ነገራቸው። በተጨማሪም፣ ሲያደርጉ የነበሩትን ማቆም እንዳለባቸው አለበለዚያ ለሚያደርጉት ነገር ባሪያ እንደሚሆኑ ነገራቸው። የህይወት አንዱ አካል እንደሆነ እና ምንም ችግር የለውም በማለት፣ አብዛኛውን የክፍል ጓደኞቹ በምክሩ ተሳለቁበት። ነገር ግን ከመካከላቸው አንዱ የወጣቱን ምክር ሰምቶ እያደረገ የነበረውን ለማቆም ወስኖ ነበር።

የዚህ ዲያቆን ምሳሌ ቢያነስ በአንዱ የክፍል ጓደኛው ላይ መልካም ተፅእኖ ነበረው። ያለ ጥርጥር፣ በዛ ውሳኔ የተነሳ እሱና ጓደኛው መሳለቅ እና ረብሻ ደርሶባቸዋል። በሌላ መንገድ፣ አልማ ለህዝቦቹ እንዲህ “ከክፉዎች ውጡ እናም ተለዩ፣ እናም የጎደፉ ነገሮቻቸውን አትንኩ እላችኋለሁ” ሲል የሰጣቸውን ተግሳፅ ተከትለዋል።6

For the Strength of Youthየሚለው በራሪ ወረቀት ላይ እነዲህ የሚል ምክር ከቀዳሚ አመራር ለቤተክርስቲያኗ ወጣቶች ይይዛል፥“ለምትወስኑዋቸው ውሳኔዎች ሃላፊነት አለባችሁ። ምንም እንኳን ቤተሰብባችሁ እናም ጓደኞቻችሁ ነፃ ምርጫቸውን መልካም ባልሆኑ መንገዶች ቢጠቀሙም፣ እግዚአብሔር ያውቃችኋል እና መልካም ምርጫን እንድትመርጡ ይረዳችኋል። ብቻችሁንም መቆም ቢሆንም፣ ለምታምኑት ነገር የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለመታዘዝ ፀንታችሁ ቁሙ። ይህንን በምታደርጉ ጊዜ፣ ሌሎች እንዲከተሉ ምሳሌን ታስቀምጣላችሁ።”7

መልካም በክፋት ላይ ያለው ጦርነት በህይወታችን ሙሉ ይቀጥላል፣ የጠላት እቅድ ሁሉኑም ሰው እንደ እርሱ መከረኛ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው። ሴጣን እና መላእክቶቹ ሀሳቦቻችን ግራ እንዲጋቡ እና ሀጢያት እነድንሰራ በመፈተን በሀይል ይቆጣጠሩናል። መልካም የሆነውን ሁሉ ያበላሹታል። ምንም እንኳን፣ እኛ ከፈቀድንላቸው ብቻ በእኛ ላይ ሀይል እንደሚኖራቸው መረዳት ጠቃሚ ቢሆንም።

ቅዱሳን መፃህፍት ያንን ፍቃድ ለጠላት ስለሰጡት እና በውጤቱን በስተመጨረሻ ግራ ስለተጋቡት እና ስለጠፉትም፣ እንደ ኔሆር፣ ኮሪሆር እና ሼረምን አይነት ብዙ ምሳሌዎችን ይይዛል። ለዚህ አደገኛ ንቁ መሆን አለብን። በአለም በቀላሉ ተቀባይነት ያላቸው እና ከኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ትምህርት እና እውነተኛ መመሪያዎች ጋር በሚፋለሱት ታዋቂ መልእክቶች ግራ እንድንጋባ እራሳችንን መፍቀድ የለብንም። አብዛኛውን እነኚ አለማዊ መልእክቶች የሚወክሉት ሀጢያትን ከማስተባበል የህብረተሰቡ ሙከራ የዘለለ አይደሉም። በስተመጨረሻ፣ መልካም ሆነ መጥፎ፣ ሁሉም እነድስራችን ሊፈረድብን ከክረስቶስ ፊት ይቆማሉ።8 እነኚ አለማዊ መልእክቶች ሲያጋጥሙን፣ መልካምን ለመምረጥ ታላቅ ብርታት እና የሰማይ አባታችን እቅድ ጠንካራ እውቀት እንዲኖረን ይጠበቅብናል።

ጌታን የምናሻው እና ሁሉንም እምነታችንን በእርሱ ካደረግን እና በእርሱ ካመንን ትክክለኛውን ለመምረጥ ሁላችንም ጥንካሬን መቀበል እንችላለን። ነገር ግን፣ ቅዱሳን መፃህፍት እንደሚያስተምሩት፣ የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ ሊኖራችሁ ይገባል፣ እናም ጌታ፣ በማያልቀው ምህረቱ፣ “በመንፈስ ቅዱስ ሀይል እውነቱን ይገልፅላችኋል። እናም የሁሉንም ነገሮች እውነታ በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ታውቁታላችሁ።”9

ይህ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ያገኛችሁት እውቀት ምስክርነታችሁ በላይ አይደለም፣ እውቅ የሆነው ከአለም የምንሰማቸው መልእክቶች ቢኖሩም ይህም ደግሞ እምነታችንን እና በመጨረሻው ቀናት በተመለሰው ወንጌል ትምህርት ለመከተል ቁርጠኝነታችንን ያጠነክራል። ምስክርነታችን እኛን ለማጥቃት ባለው ሙከራ ላይ ከጠላት ክፉ ፍላፃ ለመከላከል ጋሻችን ይሆናሉ።10 ይህም በዛሬው አለም ውስጥ ካለው ጭለማ እና ግራ መጋባት ውስጥ ሊመራን ይችላል።11

እንደ ወጣት ምስኦናዊ ሳገለግል ይህንን መርህ ተማረኩ። እኔ እና አጣማሪዬ የቤተክርስቲያንኗ ትንሷ በሆነችውና በራቀችው ቅርንጫፍ ውሰጥ እያገለገልን ነበር። በከተማው ያሉትን ሰዎች ሁሉ ለማናገር ሞከርን። በደንብ ተቀበሉን፣ ነገር ግን ቅዱሳን መፃህፍት ላይ መከራከርን እናም ስለምናስተምረው እውነት ሙላት በተመለከተ ተጨባጭ ማስረጃን እኛን መጠየቅ ይወዳሉ።

እኔ እና አጣማሪዬ ተፈትነን የሆነ ነገርን ለህዝቡ ለማረጋገጥ በሞከርንበት ሰአት ሁሉ፣ የእግዚያብሄር መንፈስ ከኛ እንደራቀ እና ሙሉ ለሙሉ የመጥፋት እና ግራ የመጋባት ስሜት እንደተሰማን አስታውሳለሁ። እኛም ምስክርነታችንን በበለጠ ጠንካራ ሁኔታ ከምናስተምረው የወንጌል እውነቶች መስመር ማስያዝ እንዳለብን ተሰማን። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ፣ በሙሉ ልቦቻችን መስክርነታችንን ስንሰጥ፣ ፀጥ ያለ የማረጋገቻ ሀይል፣ ከመንፈስ ቅዱስ የመጣ፣ ክፍሉን ሲሞላው እና ግራ ለመጋባት እና ለክርክር የሚሆን ቦታ እንዳልነበር አስታውሳለሁ። ከልብ የሆንውን እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙር ምስልርነትን ሀይል ግራ የማጋባት፣ የማታለል ወይም የመካድ እቅም ያለው ምንም የክፉ ሀይል እንደሌለ ተማርኩኝ።

አዳኝ እራሱ እንዳስተማረው፣ አለም ላይ መልካም ተፅእኖ ለማድረግ አቅማችንን እንድናጣ ፣ ጠላታችን እንደ ስነዴ ሊያበጥረን ይሻል።12

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ዛሬ በአለም ዙሪያ በተሰራጨው ታላቅ የግራ መጋባት ወጀብ እና ጥርጣሬዎች የተነሳ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምስክርነታችንን አፅንተን መያዝ አለብን። ከዚያ እውነትን እና ፍትህን የመከላከል አቅማችን በታላቁ ይጨምራል። እኛም የየቀኑን ከክፉ ጋር ያለንን ጦርነት እናሻንፋለን፣ በህይወት ፈተና ከመውደቅ ይልቅ፣ የአስተማሪን ስነ-ስርአቶችን ሌሎች በአግባቡ እንዲኖሩ እናደርጋለን።

በቅዱሳን መፅሃፍት ትምህርት ውስጥ የሚገኘውን ደህንነት እንድታገኙ ሁላችሁንም እጋብዛችኋልሁ።ካፕቴን ሞሮኒ በእግዚያብሄር ያለውን እምነት እና የእውነቱን ምስክርነቱን ከቅዱሳን መፅሃፍት ውስጥ ከሚገኘው እውቀት እና ጠበብ ጋር እራሱን አዛመደ። በዚህ መንገድ፣ ከጌታ በረከቶችን እንደሚቀበል እናም ብዙ ድሎችን እነደሚቀዳጅ አመነ፣ እሱም፣ በእርግጥ ተከሰተ።

አሁን ባሉ ነብያት ብልህ ቃላቶች ደህንነት እንድታገኙ ሁላችሁንም እጋብዛችኋልሁ። ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንደዚህ አሉ: “ እኛ ለእግዚያብሄር ክህነት የተሾምነው ልዩነት መፍጠር እንችላለን። የግል ንፅህናችንን ስንጠብቅ እና ክህነታችንን ስናከብር፣ ሌሎች እንዲከተሉ ፃድቅ ምሳሌ እንሆናለን …. የበለጠ ክፉ እየሆን ላለው አለም መልካምን እንጨምራለን።”13

በኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ ላይ እምነታችሁን እንድታደርጉ ሁላችሁንም እጋብዛችኋልሁ። በእርሱ መስዋዕት አማካይነት የጊዜያችንን ጦርነቶች በሙሉ ለማሸነፍ ብረታትን ማግኘት እንችላለን፣ በአስቸጋሪ ነገሮቻችን፣ በችግሮች፣ እናም በፈተናዎች ጊዜያትም ቢሆን እንኳን። በእርሱ ፍቅር እና እኛን ለማዳን ባለው ሀይል እንመን። ክርስቶስ እራሱ እንዲህ አለ:

“እኔ መንገድና፣ እውነት ህይወትም ነኝ: በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ” 14

“እኔ የአለም ብርሃን ነኝ፤ ለሚከተለኝ የህይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገረ። ” 15

በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዧችሁ፤ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ።16

የእነኝህን እውነታዎች ምመሰክረው በተከበረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።