2010–2019 (እ.አ.አ)
ምሳሌ እና ብርሃን ሁኑ
ኦክተውበር 2015


ምሳሌ እና ብርሃን ሁኑ

የአዳኙን ምሳሌ ስንከተል፣ የእኛ ድርሻ በሌሎች ሕይወት ውስጥ ብራሃን የመሆን እድል ይሆናል።

ወንድሞችና እህቶች፣ በድጋሚ ከእናንተ ጋር መሆን እንዴት መልካም ነው። እንደምታውቁት፣ አብረን ከነበርንበት ከሚያዚያ ጀምሮ፣ በሶስት ውድ ሐዋርያቶቻችን-- ፕሬዘዳንት ቦይድ ኬ ፓከር፣ ሽማግሌ ኤል ቶም ፔሪ እና ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ ስካት ሕልፈት አዝነናል። ወደ የሰማይ ቤታቸው ተመልሰዋል። እንናፍቃቸዋለን። ስለክርስቶስ መሰል ፍቅር ምሳሌዎቻቸው እና ለሁላችንም ለተዉት የሚያነሳሱ ትምህርቶች ምንኛ አመስጋኞች ነን።

አዲስ ለተጠሩት ሐዋርያቶች ማለትም ሽማግሌ ሮናልድ ኤ ራዝባንድ ፣ ሽማግሌ ጌሪ ኢ ስቲቨንሰን እና ሽማግሌ ዴል ጂ ረንለነድ ልባዊ የእንኳን በደህና መጣችሁን ምኞት እናቀርባለን። እነዚህ ለጌታ ስራ እራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ሰዎች ናቸው። ለተጠሩበት አስፈላጊ ቦታዎችን ለመሙላት በጣም ብቁ ናቸው።

በቅርቡ፣ ቅዱሳት መጽሐፍትን ሳነብና ሳሰላስል፣ ሁለት ምንባቦች ለየት ባለ ሁኔታ በውስጤ ቆዩ። ሁለቱም ለእኛ የተለመዱ ናቸው። የመጀመሪያው ከተራራው ላይ ትምህርት ነው፥ “መልካሙን ስራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።”1 ሁለተኛው ጥቅስ ስለመጀመሪያው ሳሰላስል ወደ አእምሮዬ የመጣ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ጢሞቴዎስ ከፃፈው ደብዳቤ ውስጥ ነው፥ “በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑት ምሳሌ ሁን እንጂ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።”2

የሁለተኛው ጥቅስ፣ በሰፊው፣ እንዴት የመጀመሪያውን ማከናወን እንደምንችል እንደሚያስረዳ አምናለሁ። በመለወጥ፣ በልግስና፣ በመንፈስ፣ በእምነትና በንፅህና ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመኖር የአማኞች ምሳሌዎች እንሆናለን። ይህን ስናደርግ፣ ብራሃናችን ሌሎች እንዲያዩት ይበራል።

እያንዳንዳችን የክርስቶስን ብርሃን በመቀበል ወደ ምድር መጣን። የአዳኙን ምሳሌ ስንከተልና እርሱ እንደኖረውና እዳስተማረው ሰንኖርና ስናስተምር፣ ያ ብርሃን በውስጣችን ይነዳል እንዲሁም ለሌሎች መንገዱን ያበራል።

ሐዋርያው ጳውሎስ ስድስት የአማኝ ባህሪዎችን ማለትም ብርሃናችን እንዲበራ የሚፈቅዱልንን ባህሪያት ዘረዘረ። እያንዳንዳቸውን እንመልከት።

የመጀመሪያ ሁለት ባህሪዎቹን በአንድ ላይ ልግለፅ--በቃልና በመለወጥ ምሳሌ መሆን። የምንጠቃማቸው ቃሎች ከፍ ሊያደርጉና ሊያነሳሱ ወይም ሊጎዱና ዝቅ ሊያደርጉ ይችላል። በዛሬው አለማችን ውስጥ በእያንዳንዱ መዞሪያ ላይ የተከበብን በሚመስል ሁኔታ ብዙ ጸያፍ ቃሎች አሉ። የፈጣሪዎችን ስሞች በተራ እና ግድ የለሽነት ሲጠሩ መስማትን ማስወገድ ከባድ ነው። ከባድ አስተያየቶች የቴሌቭዥን፣ የፊልሞች፣ የመጽሐፎችና የሙዚቃዎች የተለመዱ ነገሮች እየሆኑ የመጡ ይመስላሉ። በግድየለሽነት የሚደረጉ ንግግሮች ስድብ ያዘሉ አስተያየቶችና የንዴት ቋንቋዎች ናቸው። ለሌሎች ቋንቋችንን ንፁህ አድርገንና የሚያቆስሉ ወይም የሚያስቀይሙ ቃላቶችን በማስገድ በፍቅርና በክብር ማውራት አለብን። በመላ አገልግሎቱ ውስጥ በመቻቻልና በደግነት የተናገረውን የአዳኙን ምሳሌ እንከተል።

“እንደ የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር” የተተረጎመው በጳውሎስ የተገለፀው ቀጣዩ ባህሪይ ልግስና ነው።3 ተፅዕኖ መፍጠር የምንችልባቸው ብቸኛ የሆኑ፣ የታመሙና ተስፋ የቆረጡ ሰዎች እንዳሉ እተማመናለሁ። አዳኙ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋን እንዲሁም ለደካሞች ጥንካሬን አመጣ። የታመመውን ፈወሰ፤ ሽባውን እንዲራመድ አደረገው፣ መስማት የማይችለውን እንዲሰማ አደረገው። የሞተውን እንኳን ወደ ሕይወት አስነሳ። በመላ አገልግሎቱ ውስጥ ለሚፈልግ ሁሉ በልግስና እጁን ዘረጋ። የእርሱን ምሳሌ ስንከተል የራሳችንንም ጨምሮ ሕይወቶችን እንባርካለን።

በመቀጠል፣ በመንፈስ ምሳሌ መሆን አለብን። ለእኔ ያ ማለት በሕይወቶቻችን ውስጥ ደግነት፣ ምስጋና፣ ይቅር ባይነትና መልካም ፈቃደኝነት እንዲኖረን እንጥራለን ማለት ነው። እነዚህ መገለጫዎች በዙሪያችን ያሉትን ሰዎች የሚነካ መንፈስን ይሰጡናል። በብዙ ዓመታት ውስጥ እንደዚህ አይነት መንፈስ ካላቸው ቁጥር ስፍር ከሌላቸው ሰዎች ጋር የመገናኘት እድሎች ነበሩኝ። ከእነሱ ጋር ስንሆን ከእነሱ ጋር እንድንቀራረብ እና ምሳሌዎቻቸውን እንድንከተል የሚያደርገንን ለየት ያለ ስሜት እንለማመዳለን። የክርስቶስን ብራሃን ያመነጫሉ እንዲሁም ለእኛ ያለውን ፍቅር እንዲሰማን ይረዱናል።

ከንፁህና አፍቃሪ መንፈስ የሚመጣው ብርሃን በሌሎች እንደሚታይ ለማስረዳት ከብዙ ዓመታት በፊት የነበረውን ልምድ አካፍላችኋለሁ።

በዛ ሰዓት፣ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች በኢየሩሳሌም ከባለ ስላጣኖች ጋር የኢየሩሳሌም ማዕከል ስለሚገነባበት ቦታ የመሬት ሊዝ ስምምነት ለመፈራረም ተገናኙ። የተፈለገውን ፍቃድ ለማግኘት ቤተክርስቲያኗ ማዕከሉን በሚይዙ አባሎች ምንም አይነት ስብከት እንደማይደረግ መስማማት ነበረባት። ያ ስምምነት ከተደረገ በኋላ አንዱ ቤተክረስቲኗንና አባሎቿን በደንብ የሚያውቃት የእስራኤል ባለስልጣን ቤተክርስቲያኗ ስብከትን የሚከለክለውን ስምምነት እንደምታከብር እንደሚያውቅ ገለፀ። “ነገር ግን” አለ፣ እዛ ስለሚማሩት ተማሪዎች እየተናገረ፣ “በአይኖቻቸው ውስጥ ስላለው ብርሃን ምንድን ነው የምናደርገው?”4 ያ ለየት ያለ ብርሃን በሌሎች እንዲታወቅና እንዲደነቅ በውስጣችን ይብራ።

የእምነት ምሳሌ መሆን ማለት በጌታና በቃሎቹ እናምናለን ማለት ነው። አስተሳሰቦቻችንንና ተግባሮቻችንን የሚመራው እምነት ይኖረናል እናም እንንከባከበዋለን ማለት ነው። በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስና በሰማይ አባታችን ያለን እመነት በምናደርገው ነገር ሁሉ ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል። በእድሜያችን የግራ መጋባት፣ ህሊና ግጭቶችና በቀን ተቀን የሕይወት ብጥብጥ ውስጥ ዘለቄታ ያለው እምነት ለሕይወቶቻችን መልሕቅ ይሆናል። እምነትና ጥርጣሬ በአንድ አዕምሮ ውስጥ በአንድ ጊዜ እንደማይኖሩ አስታውሱ ምክንያቱም አንዱ ሌላውን ይገፋዋልና። በተደጋጋሚ የተነገረንን ነገር እደግማለሁ--የምንፈልገውን እምነት ለማግኘትና ለመጠበቅ ቅዱሳት መጽሐፍትን ማንበብና ማጥናት እንዲሁም ማሰላሰል አስፈላጊ ነው። በፀሎት አማካኝነት ከሰማይ አባታችን ጋር መነጋገር አስፈላጊ ነው። እነዚህን ነገሮች ችላ ማለት አንችልም ምክንያቱም ጠላቱና ጭፍሮቹ ድክመቶቻችንን፣ በአማኝነታችን ላይ ውድቀትን ሳይታክቱ እያሹ ናቸውና። ጌታን እንዲህ አለ፣ “በትጋት ከፈለግን፣ ሁሌም ከፀለይንና አማኞች ከሆንን፣ ሁሉም ነገሮች ለእኛ መልካምነት ይሰራሉ።”5

በመጨረሻም፣ ንፁህ መሆን አለብን፣ ይህም ማለት በሰውነት፣ በአዕምሮና በመንፈስ ንፁህ መሆን ማለት ነው። ሰውነታችን በክብር መያዝን የሚሻ የእግዚአብሔር ቤተ-መቅደስ መሆኑን እናውቃለን። አዕምሮአችን ከፍ ከፍ በሚያደርጉ እና ዘውዳዊ በሆኑ እንዲሁም ከሚበክሉ ነገሮች ነፃ በሆኑ አስተሳሰቦች መሞላት አለበት። እንደ ቋሚ ጓደኛ መንፈስ ቅዱስ እንዲኖርን ብቁ መሆን አለብን። ወንድሞችና እህቶች፣ ንፅህና የአዕምሮ ሰላምን ይሰጠናል እንዲሁም የአዳኙን ቃል-ኪዳኖች እንድንቀበል ብቁ ያደርገናል። እንደዚህም አለ፥ “ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።”6

በቃል፣ በንግግር፣ በልግስና፣ በመንፈስ፣ በእምነትና በንፅህና የአማኞች ምሳሌ እንደሆንን ስናረጋግጥ፣ ለዓለም ብርሃን ለመሆን ብቁ እንሆናለን።

ለሁላችሁም እንዲህ እላለሁ በተለይ ለእናንተ ወጣት ህዝቦች፣ በአፍቃሪው የሰማይ አባታችን ከተሰጡን መርሆችና መመሪያዎች አለም እየራቀ በመጣ ቁጥር፣ እኛ የተለየን ስለሆን ከተሰበሰቡት ሰዎች ተለይተን እንወጣለን። መልካም አለባበስ ስላለን ተለይተን እንወጣለን። ጸያፍ ቃሎችን ስለማንጠቀምና ሰውነቶቻችንን የሚጎዱ ንጥረ ነገሮችን ስለማንጠቀም እንለያለን። ተገቢ ያልሆኑና የበታች የሚያደርጉ ቃሎችን ስለምናስወግድ እንለያለን። ኢግብረገባዊ በሆኑና ዝቅ በሚያደርጉ እንዲሁም ከቤቶቻችንና ከሕይወቶቻችንን መንፈስን በሚያስወግዱ የሚዲያ ምርጫዎች አዕምሮአችንን ላለመሙላት ስንወስን እንለያለን። ከወንጌል መርሆች ጋር የሚስማማ የግብረገብነት ምርጫዎችንን ስናደርግ በትክክል ተለይተን እንወጣለን። ከብዙው ዓለም ጋር ልዩ የሚያደርጉን እነዛ ነገሮች እንዲሁ በጨለማ ዓለም ውስጥ በቀጣይነት የሚበራውን ያንን ብርሃንና መንፈስ ይሰጡኛል።

ልዩ መሆንና በተሰበሰቡ ሰዎች መካከል ተለይቶ መውጣት ብዙዉን ጊዜ ከባድ ነው። ሌሎች የሚያስቡትንና የሚሉትን መፍራት ተፈጥሯዊ ነው። እንደዚህ የሚሉት የመዝሙረ ዳዊት ቃሎች አፅናኞች ናቸው፥ “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?”7 ክርስቶስን የሕይወቶቻችን መአከል ስናደርግ፣ ፍርሃቶቻችን በአቋማችን ድፍረት ይተካሉ።

ለማንኛችንም ሕይወት ፍፁም አይደለችም፣ አንዳንድ ጊዜ የሚያጋጥሙን ፈተናዎችና ችግሮች ብርሃናችን እንዲደበዝዝ በማድረግ አድካሚ ሊሆኑ ይችላሉ። ይሁን እንጂ፣ በሰማይ አባታችን እርዳታ አማካኝነት፣ የሌሎችንም እርዳታ ጨምሮ በድጋሚም የገዛ መንገዳችንን የሚያበራውን ያንን ብርሃን እንደገና ማግኘት እንችላለን እንዲሁም ሌሎች የሚፈልጉትን ብርሃን እንሰጣለን።

ግልፅ ለማድረግ፣ ከብዙ አመት በፊት ያነበብኩትን ከምወዳቸው ግጥሞች መካከል ልብን የሚነኩትን ቃሎች አካፍላችኋለሁ።

በምሽት ውስጥ አንድ እንግዳ ሰውን አገኘሁ።

ፋኖሱ መብራቱን አቁሞ ነበር።

ቆምኩኝና እንዲያበራ ፈቀድኩለት።

የእርሱን ፋኖስ ከእኔ ላይ።

ከዛ አውሎ ነፋስ ተነሳ፣

እናም ዓለምን አናወጣት።

እናም ነፋሱ በሄደ ጊዜ

የእኔ ፋኖስ ጠፍቶ ነበር!

ነገር ግን እንግዳው ሰው ወደ እኔ ተመለሰ--

የእርሱ ፋኖስ አሁንም እየበራ ነበር።

ውዱን እሳት ያዘ

እናም የእኔን አበራልኝ!8

ወንድሞቼና እህቶቼ፣ የእኛ ብርሃን የመስጠት እድል በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን በእያንዳንዱ ቀን በዙሪያችን ነው። የአዳኙን ምሳሌ ስንከተል የእኛ ድርሻ በሌሎች ሕይወት ውስጥ ማለትም የገዛ የቤተሰብ አባሎችም ይሁኑ፣ ጓደኞች፣ የስራ ባልደረቦች፣ ተራ ትውውቆች ወይም እንግዳ ሰዎች፣ ለእነሱ ብርሃን የመሆን እድል ነው።

የሰማይ አባታችን ወንድ ወይም ሴት ልጆች ናችሁ ብዬ ለእያንዳንዳችሁ እናገራለሁ። ለተወሰነ ወቅት በዚህ ምድር ላይ ለመኖር፣ የአዳኙን ፍቅርና ትምህርት ለማንፀባረቅና በድፍረት ሁሉም እንዲያዩት ብርሃናችሁ እንዲበራ ለመፍቀድ ከእርሱ መገኛ መጥታችኋል ። በምድር ላይ ያ ወቅት ሲያበቃ፣ የራሳችሁን ድርሻ ከተወጣችሁ፣ የእናንተ ድርሻ ለዘላለም ከእርሱ ጋር ለመኖር የመመለስ ክብራማ በረከት ይሆናል።

የጌታ ቃሎች እንዴት ዳግም የሚያረጋግጡ ናቸው፤ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም።”9 እርሱ ምሳሌአችንና ጥንካሬአችን ነው። በጨለማ ውስጥ የሚበራ ብርሃን ነው።10 በድምፅ ጥላ ውስጥ ያለነው እያንዳንዳችን እርሱን ለመከተል ቃል እንግባ፣ ስለሆነም ለዓለም የሚበራ ብርሃን እንድንሆን ፀሎቴ ነው፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።