2010–2019 (እ.አ.አ)
የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ የተባደረኩ እና ደስተኞች ናቸው
ኦክተውበር 2015


የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ የተባደረኩ እና ደስተኞች ናቸው

በጌታ የተመሰረቱት መሰናክሎች ከክፉ እና አጥፊ ተፅእኖዎች የተጠበቀ ወደብን ይፈጥሩልናል።

ከተወሰነ ጊዜ በፊት፣ አውስትራሊያን ስጎበኝ፣ በአረፋ መሰል ማእበሉ ወደሚታወቀው የሚያምር የፈረስ ጫማ ቅርፅ ወዳለው ባህረ ሰላጤ ተጓዝኩ። በባህሩ ዳር ስራመድ፣ ልክ ከባህረ ሰላጤው ውጪ በሚያበቃው ታላቅ ወጀብ እና በዳርቻው አከባቢ ባሉት ትንንሽ ወጀቦች ተመስጬ ነበር።

መንሸራሽሬን ስቀጥል፣ የአሜሪካ ቀዛፊዎችን ቡድን አገኘሁ። ጮክ ብለው ያወራሉ እና ወደ ባህሩ ያመላክታሉ፣ በእርግጥም ስለሆነ ነገር ተበሳጭተዋል። ችግሩ ምን እንደሆነ ስጠይቃቸው፣ ከባህረ ሰላጤው ውጪ ወዳለው ትላልቅ የወጀብ መነሻዎች ጠቆሙኝ።

“ወደዛ ተመልከት፣” ከእነርሱ አንደኛው በንዴት አናገረኝ። “መሰናክሉን ማየት ትችላለህ?” አሁን የበለጠ በቅርበት ስመለከት፣ በመላው የባህረ ሰላጤው ዙሪያ የተዘረጋውን፣ በታላቆቹ ወጀቦች መነሻ አቅራቢያ መሰናክል መመልከት ቻልኩ። መሰናክሉ ከከባድ ወንፊታማ መረብ የተሰራ እና ከውሀው በላይ ባሉ መንሳፈፊያዎች የሚደገፍ ይመስላል። እነደቀዛፊዎቹ ከሆነ፣ እስከ ባህር ወለሉ ድረስ ሁሉ የወረደ ነው።

አሜሪካዊው ቀዛፊ ቀጠለ፣ “እዚህ ያለነው እነዚህ ትልቅ ወጀቦች ላይ ለመቅዘፍ በህይወት ዘመን አንዴ በሆነ ጉዞ ነው። በባህረ ሰላጤው በራሱ በሚነሱት ትንንሽ ወጀቦች ላይ መቅዘፍ እንችላለን፣ ነገር ግን መሰናክሉ በትልልቅ ወጀቦች ላይ መቅዘፍን የማይቻል አድርጎብናል። መሰናክሉ እዛ ለምን እንዳለ የምናውቀው ነገር የለም። የምናቀው ነገር ቢኖር ጉዞአችንን አበላሽቶብናል።”

አሜሪካዊ ቀዛፊዎቹ ይበልጡን ሲበሳጩ፣ የእኔ ቀልብ በቅርብ ወደነበረ ሌላ የአከባቢው ሰው የሆነ ቀዛፊ ዞረ። እየጨመረ በመጣው ስለመሳናክሉ የነበረው መነጫነጭ ትእግስቱን ያስጨረሰው ይመስላል።

በመጨረሻም፣ ተነሳ እና ወደ ቡድኑ ተራምዶ መጣ። ምንም ነገር ሳይናገር፣ ከጀርባ ቦርሳው አቅርቦ የሚያሳይ መነፅር አወጣ እና ለአንዱ ቀዛፊ ሰጠው፣ ወደ መሰናክሉ በመጠቆም። በመነፅሩ እያንዳንዱ ቀዛፊዎች ተመለከቱ። የእኔ ተራ ሲደርስ፣ በማጉያው እርዳታ አማካኝነት፣ በፊት ማየት ያልቻልኩትን ነገር ማየት ቻልኩ፤ የእንስሳ የጀርባ ክንፎች--- ትልልቅ አሳነባሪዎች በባህረ ሰላጤው ሌላኛ ጎን አቅራቢያ ሲመገቡ።

ቡድኑ በፍጥነት ዝም ተሰኙ። ሽማግሌው ሰው አጉሊ መነፅሩን መልሶ ወሰደ እና ለመሄድ ዞረ። ያን ሲያደርግ፣ ፈፅሞ የማልረሳቸውን ቃላት ተናገረ። “ስለመሰናክሉ ብዙም ወቃሾች አትሁኑ። ከመበላት እየጠበቃችሁ ያለው ብቸኛው ነገር እሱ ነው” ብሎ ተናገረ።

በእዛ የሚያምር ባህር ዳርቻ ቆመን፣ እይታችን በቅፅበት ተቀየረ። ጥብቅ እና ገደብ የሚመስለው---መዝናናትን እና በትልቅ ወጀቦች ላይ የመሆንን ደስታን የቀነሰ የመሰለን መሰናክል--- በጣም የተለየ ነገር ሆነ። ልክ ከወለል በታች ስለተጋፈጠው አደጋ ባለን አዲስ መረዳት፣ አሁን መሰናክሉ ጥበቃ፣ ደህንነት፣ እና ሰላም ሰጪ ሆነ።

እኔ እና እናንተ የህይወትን መንገድ ስንጓዝ እና በህልማችን ስንገፋ፣ የእግዚአብሔር ትእዛዛት እና መርሆዎች---ልክ እንደ መሰናክሉ--- አንዳንዴ ለመረዳት የሚያስቸግሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ጥብቅ እና የማይለቁ መስለው ይቀርቡ ይሆናል፣ ሌሎች በመከተል ላይ ያሉትን የአዝናኝ እና የደስታ የሚመስሉ መንገዶችን የሚዘጋ ሊመስል ይችላል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደገለፀው፣ውስን በሆነ እይታ፣ “በመስታውት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን፣”1 እናም ከወለሉ በታች የተደበቁትን ታላቅ አደጋዎች እንኳን በአብዛኛው ማስተዋል አንችልም።

ነገር ግን “ሁሉንም ነገሮች የሚረዳ”2 እነዚያ አደጋዎች በትክክል የት እናዳሉ ያውቃል። እነዚያን አደጋዎች እንድናስወግድ--ከመንፈሳዊ አውሬዎች እና ከሀጢያት መንጋጋዎች የተጠበቁ የህይወት ምንገዶቻችንን ለማስተካከል፣ በትእዛዙ እና ተወዳጅ ምሬቱ መለኮታዊ አቅጣጫን ይሰጠናል።33

ለእኛ ያቀረበውን መንገድ ለመከተል እና ለእኛ የሰጠንን ትእዛዛት ለመጠበቅ በየቀኑ የተቻለንን በማድረግ---ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር እናሳያለን። በይበልጥም ያንን እምነት እና ፍቅር ይምናሳየው ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ምክንያቱን እና ውሰዱ የሚለንን የተለየውን መንገድ ሙሉ ለሙሉ ሳንረዳ ባሉት ሁኔታዎች ውስጥ ነው። ልክ ከውጪ ሹል ጥርስ ያላቸው የአውሬ ምንጋዎች እንዳሉ ካወቅን በኋላ በመሰናክል ውስጥ መንገዱን ለመከተል መወሰን በአንፃሩ ቀላል ነው። ማየት የምንችለው ሁሉ በሌላኛው ጎን ያሉ ልብ አንጠልጣይ እና አስጎምጂ ወጀቦች ሲሆኑ በመሰናክል ውስጥ እራሳችንን ለመጠበቅ ይበልጥ አስቸጋሪ ነው። እና አሁንም፣ በእነዚያ ጊዜያት---እምነታችንን ለመለማመድ፣ በእግዚአብሔር ላይ ለመታመን፣ እና ለእርሱ ያለንን ፍቅር ለማሳየት በምንመርጥበት ጊዜ፣ ያኔ ነው የምናድገው እና የበለጠ የምንጠቀመው።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ አናኒያስ በክርስቶስ የሚያምኑትን ለማሰር ስልጣን ያለውን ስዖልን ለመፈለግ እና ለመባረክ የተሰጠውን የጌታ ትዕዛዝ አልተረዳም ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ስላከበረ፣ ለሐዋርያው ጳውሎስ መንፈሳዊ ውልደት ድርሻ ነበረው።4

በጌታ ስንታመን፣ እምነታችንን ስንለማመድ፣ ትእዛዛቱን ስንጠብቅ፣ እና ለእኛ የቀረፀውን መንገድ ስንከተል፣ በበለጠ ጌታ እኛ እንድንሆን የሚፈልገውን አይነት ሰው እንሆናለን። ይሄ መሆን---የልብ መለወጥ---ነው በጣም አስፈላጊው። ኤልደር ዳሊን ኤች ኦክስ እንዳስተማሩን፤ ለአንድ ሰው በእንቅስቃሴ ብቻ ማለፉ በቂ አይደለም። የወንጌል ትእዛዛት፣ ስርአቶች እና ቃል ኪዳኖች በሰማይ መዝገብ ለመደረግ የተዘረዘሩ ጥርቅሞች አይደሉም። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሰማይ አባት እንድንሆን የሚፈልገውን እንዴት እንደምንሆን የሚያሳየን እቅድ ነው።”5

ስለዚህ እውነተኛ መታዘዝ፣እራሳችንን ሙሉ ለሙሉ መስጠት እና መቼም ቢሆን እራሳችን መሆን ከምንችለው በላይ እርሱ የተሸለ እንደሚያደርገን በመረዳት በሰላምም ሆነ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች መንገዳችንን እርሱ እንዲቀርፅ መፍቀድ ነው።

እራሳችንን ለእርሱ ፍላጎት ስናስረክብ፣ ሰላም እና ደስታችን ይጨምራል። ንጉስ ቢንያም እንዳስተማረው የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ “በጊዜአዊም ሆነ በመንፈሳዊ ነገሮች ሁሉ” “የተባረኩ እና ደስተኛ” ናቸው።6 እግዚአብሔር እኛ ደስታ እንዲኖረን ይፈልጋል። ሰላም እንዲኖረን ይፈልጋል። ስኬታማ እንድንሆን ይፈልጋል። በደህንነት እንድንሆን እና በዙሪያችን ካሉ ምድራዊ ተፅእኖዎች እንድንጠበቅ ይፈልጋል።

በሌላ መልኩ ሲቀመጥ፣ የጌታ ትእዛዛት በቀጣይ ከእግዚአብሔር ጋር እንኖር ዘንድ በዚህ ህይወት ውስጥ ለመፅናትመማር ያሉብንን ጥቂት ውስብስብ የውሀ ውስጥ መሰናክሎችን አያካትትም። በምትኩ፣ በጌታ የቀረቡት መሰናክሎች ከክፋት እና ወደ ጥልቅ ጥፋት ይከቱን ከነበሩት አሳሳች ተፅእኖዎች የራቀ የደህንነት ወደብ ይፈጥርልናል። የጌታ ትእዛዛት የተሰጡት ከፍቅር እና እሳቤ በመነጨ ነው፤ በሚቀጥለው ህይወት ደስታ እና ደህንነታችን እንደሆኑት ሁሉ፣ በዚህም ህይወት ደስታችን የታቀዱ ናቸው።7 ማድረግ ባለብን ነገሮች መንገድ ይጠቁማሉ እና በይበልጥም መሆን ያለብንን ይጠቁሙናል።

መልካም እና እውነት በሆኑት ነገሮች ሁሉ እንደሆነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ምርጥ ምሳሌ ይነሳል። ልጁ ለአባቱ ትእዛዝ እራሱን ሲሰጥ ነበር የዘላለም ታለቅ የመታዘዝ ድርጊት የተፈፀመው። ከቀረበለት ሌላ መንገድ ይጓዝ ዘንድ--- ፅዋው እንዲያልፍ በጥልቅ ትህትና በመጠየቅ---ክርስቶስ አባቱ እንዲወስድ ለፈለገው መንገድ እራሱን ሰጠ። የማይገመት መከራ እና ስቃይን በተወጣበት እና የአባቱ መንፈስ ሲለየው ሙሉ ለሙሉ በራሱ በተተወበት በጌተሰማኒ እና ጎልጎታ የሚያመራ መንገድ ነበር። ነገር ግን ያ መንገድ በሶስተኛው ቀን በባዶ መቃብር፣ “ተነስቷል!”8 በሚሉ እርሱን በሚወዱት ሰዎች ጆሮ እና ልብ ውስጥ የተደወሉ ጩኸቶች ተቋጨ። በዘለአለም ሁሉ ላሉ የእግዚአብሔር ልጆች በእርሱ የሀጢአት ክፍያ ውስጥ የተመሰረተውን የማይገመት ደስታ እና ምቾትንም ያካትታል። የእርሱ ፍላጎት የአባቱ በሆነው ፍላጎት እንዲዋጥ በመፍቀድ፣ ክርስቶስ የዘለአለም ሰላም፣ የዘለአለም ደስታ እና የዘለአለም ህይወትም እይታ ለእኛ ሰጠን።

የተወዳጁ እግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን እመሰክራለሁ። እኛ ደስተኛ እና የተጠበቅን እና የተባረክን እንደንሆን እንደሚፈልግ እመሰክራለሁ። ለእዚያም ፍፃሜ፣ ወደ እርሱ የሚመራንን መንገድ ቀርፆልናል እና በመንገዱም እንዲጠብቁን መሰናክሎችን አዋቅሯል። ያንን መንገድ ለመከተል የተቻለንን ስናደርግ፣ እውነተኛ ደህንነት፣ ደስታ እና ሰላም እናገኛለን። እና ለእርሱ ፍላጎት ስንሰጥ፣ እንድንሆን የሚፈልገውን እንሆናለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።