2010–2019 (እ.አ.አ)
የሚያዩ አይኖች እና የሚሰሙ ጆሮዎች
ኦክተውበር 2015


የሚያዩ አይኖች እና የሚሰሙ ጆሮዎች

አይናችንን እንዲሁም ጆራችንን ክፍት ካደረግን፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በህይወታችን ውስጥ ሲሰራ እንድናይ መንፈስ ቅዱስ ይባርከናል።

በስጋዊ አገልግሎቱ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን “ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ ... ብዙ ሕዝብ ተከተሉት”1 እስከሚባልበትድረስ ኢየሱስ ታላቅ የመፈወስ ታዕምራቶችን ሰራ እናም በስልጣን እና ሀይል አስተማረ።

ሲፈውስ ያዩት እና ሲያስተምር የሰሙት አንዳንዶች ካዱት። ሌሎችም ለጊዜ ተከተሉት፣ ነገር ግን ከእርሱ ጋር መሄድን አቆሙ።2 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በፊታቸው ነበር፣ ነገር ግን እርሱ ማን እንደሆነ በእርግጥም አላዩትም። አይናቸው ታውሮ ነበር፣ እናም ዞር ለማለት መረጡ። ስለእነርሱን ኢየሱስ እንዲህ አለ፥

“የእኔ ወደሆኑት መጣሁና፣ የራሴ የሆኑትም አልተቀበሉኝም።”3

“…ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል።”4

ነገር ግን እርሱን የህይወታቸው ማእከል ያደረጉ፣ ታማኝ ሐዋርያቶቹን ጨምሮ፣ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ነበሩ። በአለም መምታታቻዎች፣ ስላስተማራቸው ነገሮች ግራ በመጋባት፣ እንዲሁም በፍርሀት ቢታገሉም፣ በእርሱ አመኑ፣ እርሱን ወደዱ እናም ተከተሉት።

ስለእነርሱም ኢየሱስ እንዲህ አለ፥ “ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።”5

ልክ በጌተሰመኔ እና በካልቨሪ ከመሰቃየቱ በፊት፣ ኢየሱስ ይህን አስደናቂ ቃል ኪዳን ለሐዋሪያቱ ሰጠ፥ “በእኔ የሚያምን፣ እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።”6

ኢየሱስ ይህን ቃል ኪዳን አሟላ፥ ከበዓለ ኀምሳ ከተባለው ቀን ጀምሮ፣ ደቀመዛሙርቱ በእሳት እና በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተባርከው ነበር።7 በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት፣ ንስሀ መግባት፣ እና ታዛዥነት በኩል፣ መንፈስ ቅዱስ የእነርሱ ጓደኛ ሆነ፣ ልባቸውን ቀየረ፣ እናም በሚታገስ የእውነት ምስክርነት ባረካቸው።

እነዚህ ስጦታዎች እና በረከቶች የጌታ ደቀመዛሙርትን አጠናከሩ። የኖሩበት ዘመን አደገኛ እና የሚያደናግር ቢሆንም፣ የሚያዩ አይኖች እና የሚሰሙ ጆሮዎች የመንፈስ ስጦታ ተቀበሉ። በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በኩል፣ ነገሮች እንደሚገኙበት እውነትን ተመልከቱ፣ በልዩም ስለጌታ ኢየሱስ ክርስቶች እና በመካከላቸው ስለነበረው ስራ፣ መመልከት ጀመሩ።8 መንፈስ ቅዱስ እንዲብራሩ አደረጋቸው፣ እናም የጌታን ድምጽ በግልጽ ማዳመጥ ጀመሩ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በልባቸው ውስጥ ሰመጠ።9 የማይነቃነቁና ታዛዥ ሆኑ።10 ወንጌልን በድፍረት እና በሀይል ሰበኩ እናም የእግዚአብሔርን መንግስት ገነቡ።11 በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደስታ ነበራቸው።

በዘመን መካከል ከነበሩት ታማኝ ወንዶችና ሴቶች ጋር አንድ የምንሆንባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። በመካከላችን፣ የታመመው የሚፈወስበት፣ ከኃጢያት የሚያጸዳን፣ ልባችንን የሚቀይር፣ እና የእግዚአብሔር ልጆች ደህንነትን በመጋረጃው ሁለት ጎኖች ላሉት እንዲገኝ የሚያደርግ አይነት፣ የታዕምራት ስራዎችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰራበት ዘመን ውስጥ እየኖርንም ነን። በጊዜአችንም ህያው ነቢያት እና ሀዋሪያት፣ የክህነት ሀይል፣ የመንፈስ ስጦታዎች፣ እና የደህንነት ስርዓቶች መለኮታዊ በረከቶች ይገኛሉ።

ጊዜአችን አደገኛ ጊዜ – የታላቅ ክፉት እና መፈተኛ ጊዜ፣ ግራ የመጋባት እና የሁካታ ጊዜ ነው። በእነዚህ አደገኛ ጊዜዎች ውስጥ፣ በምድር የሚገኙት የጌታ ነቢይ፣ እንዲሁም ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ የተጎዱትን ነፍስ እንድናድን፣12 በብርታት ለእውነት እንድንቆም፣, 13 እና የእግዚአብሔርን መንግስት እንድንገነባ ጥሪ ሰጥተውናል።14 ምንም አይነት መንፈሳዊነት ወይም እምነት ወይም ታዛዥነት ቢኖረንም፣ ወደፊት ላለው ስራ ብቁ አይሆንም። ታላቅ መንፈሳዊ ብርሀን እና ሀይል ያስፈልገናል። አዳኝ በህይወታችን ውስጥ ሲሰራ በግልጽ የሚያይ አይኖች እና በልባችን ውስጥ በጥልቅ ድምጹን የሚሰሙ ጆሮውች ያስፈልገናል።

ይህ አስደናቂ በረከት የሚመጣው ልባችንን ስንከፍት እና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ትምህርቱን፣ እና ቤተክርስትያኑን በህይወታችን ስንቀበል፣ በእውነት ስንቀበል፣ ነው።15 ፍፁማን መሆን አይጠበቅብንም፣ ነገር ግን መልካም መሆን እና መሻሻል አለብን። በወንጌል እቅድ እና ግልጽ እውነት ለመኖር መጣር ያስፈልገናል። የክርስቶስን ስም በራሳችን ላይ ከወሰድን፣ በእርሱ ባለን እምነት ንስሀ ከገባን፣ ትእዛዛቱን ካከበርን፣ እና እርሱን ሁልጊዜም ካስታወስን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ምህረት እና ጸጋ በሙል የመንፈስ ቅዱስ ጓደኝነትን እናገኛለን።

ቀጥተኛ ታዛዥነት መንፈስን ወደልባችን ያመጣል። በቤታችን ውስጥ በእምነት እንጸልያለን፣ ቅዱሳት መጻህፍትን እንፈትሻለን፣ እና ሰንበትን ቅዱስ አድርገን እንጠብቃለን። በቤተክርስቲያንችን ውስጥ ቅዱስ ቁርባንን እንቀበላለን እናም ከሰማይ አባታችን ጋር በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን እንገባለን። በቅዱስ ቤተመቅደሶች ውስጥ በመጋረጃው ሌላ ጎን ላሉት ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን ወኪል በመሆን በቅዱስ ስርዓቶች እንሳተፋለን። በቤተሰቦቻችን እና በጌታ በተሰጡን ስራዎች፣ ሸከማቸውን በመቀነስ እና ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ በመጋበዝ ሌሎችን እንረዳለን።

ወንድሞችና እህቶች፣ እነዚህን ነገሮች ካደረግን፣ መንፈስ ቅዱስ እንደሚመጣ አውቃለሁ! በመንፈስ እናድጋለን እናም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ተሞክሮዎችን እናገኛለን፣እናም እርሱም ጓደኛችን ይሆናል። ወደክርስቶስ ከተመለከትን እና አይኖቻችንን እና ጆሮዎቻችንን ከከፈትን፣ መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ ክርስቶስ ስራን በህይወታችን እንድንመለከት፣ በእርሱ ያለንን እምነት በማረጋገጫ እና በመረጃ በማጠናከር ይባርከናል። ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን እግዚአብሔር እንደሚያያቸው፣ በፍቅር እና በርህራሄ፣ ለማየት እንችላለን። በቅዱሳት መጻህፍት እና በህያው ነቢያት ቃላት ውስጥ፣ በመንፈስ ሹክሹክታ፣ የአዳኝን ድምጽ ለመስማት እንችላለን።16 በነቢዩ እና በእውነት እና ህያው ቤተክርስቲያኑ መሪዎች ላይ የእግዚአብሔር ሀይል አርፎ እናያለን፣ እናም በእርግጥ ይህ የእግዚአብሔር ቅዱስ ስራ እንደሆነም እናውቃለን።17 ራሳችንን እና በአካባቢያችን ያለውን አለም አዳኝ እንደሚያደርገው ለማየት እና ለመረዳት እንችላለን። ሐዋርያው ጳውሎስ “የክርስቶስ ልብ”18 ብሎ የጠራውን ለማግኘት እንችላለን። የሚያዩ አይኖች የሚሰሙ ጆሮዎች ይኖሩናል፣ እናም የእግዚአብሔርን መንግስት እንገነባለን።

ህይወት አስቸጋሪ፣ ግራ የሚያጋባ፣ የሚያሳምም፣ እና ተስፋ የሚያስቆርጥ ሊሆን ይችላል። በመንፈስ ቅዱስ ጓደኝነት፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ብርሀን ግራ የሚያጋባውን፣ የሚያሳምመውን፣ እና ጨለማውን እንደሚበትን ምስክርነቴን እሰጣችኋለሁ። በሚያስደንቅ ሁኔታ ወይም ቀስ በቀስ ቢሆንም፣ ያ ግርማዊ የመንፈስ ሀይል የሚፈውስ ፍቅር እና መፅናኛ ንስሀ ወደሚገባው፣ የተጎዳ ነፍስ ያቀርባል፤ ጭለማን በእውነት ብርሀን ይበትናል፤ እናም ተስፋ መቁረጥን በክርስቶስ ተስፋ ያስወጣል። እነዚህ በረከቶች ሲመጡ እናያለን፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት በኩል ኢየሱስ ክርስቶስ በህይወታችን ውስጥ እየሰራ እንደሆነ እናውቃለን። ሸከማችንም “[በቤዛችን] ደስታ [ይዋጣል]።”19

ከብዙ አመቶች በፊት እናቴና አባቴ የነበራቸው ተሞክሮ የአይኖች ማየት እና የጆሮዎች መስማት አስፈላጊነት እና ሀይል በምሳሌ ያሳያሉ። በ1982 (እ.አ.አ) ወላጆቼ በፊሊፒንስ ዳቫኦ ሚስዮን እንዲያገለግሉ ተጠርተው ነበር። እናቴ ደብዳቤውን ስትከፍት እና የት እንደተመደቡ ስታይ፣ ለአባቴ “አይሆንም! ልትደውልላቸው ይገባል እና ወደ ፊሊፒንስ ለመሄድ እንደማንችል ንገራቸው። አስም እንዳለብህ ያውቃሉ” አለችው። አባቴ በአስም ለብዙ አመቶች ተሰቃይቶ ነበር፣ እናም እናቴ ለእርሱ በጣም አስባ ነበር።

ከትንሽ ምሽቶች በኋላ በለሊት 8:30 ላይ እናቴ አባቴን ከእንቅልፍ አስነሳችና እንዲህ አለች፣ “መርልን፣ ያን ድምጽ ሰማኸው?”

“አይ፣ ምንም ድምጽ አልሰማሁም።”

“እኔ አንድ አይነት ድምጽ ሶስት ጊዜ በዚህ ምሽት እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ፣ ‘ለምንድን ነው የምትረበሺው? እርሱ አስም እንዳለበት እንደማውቅ አታውቂምን? እርሱን እንከባከበዋለሁ፣ እናም አንቺንም እንከባከባለሁ። በፊሊፒንስ ውስጥ ለማገልገል እራሳችሁን አዘጋጁ።’”

ምስል
መርሊን እና ሄለን ክላርክ

እናቴና አባቴ በፊሊፒንስ ውስጥ አገለገሉ እናም አስደናቂ ተሞክሮዎች ነበራቸው። መንፈስ ቅዱስ ጓደኛቸው ነበር፣ እናም ተባርከውና ተጠብቀው ነበር። አባቴ በአስም ምንም ችግር አላጋጠመውም ነበር። አባቴ በሚስዮን አመራር ውስጥ እንደ መጀመሪያ አማካሪ አገለገለ፣ እናም እርሱና እናቴ ብዙ መቶ ሚስዮኖች እና ብዙ ሺህ ታማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱሳንን ለአውራጃዎች እና ካስማዎች በሚንዳናኦ ደሴት ውስጥ መምጣት እንዲዘጋጁ አደረጉ። በሚያዩ አይኖች እና በሚሰሙ ጆሮዎች ተባርከው ነበር።

ወንድሞችና እህቶች፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነትን እሰጣለሁ። እርሱ ህያው ነው። አዳኛችን እና ቤዛችን ነው። እርሱን በህይወታችን ውስጥ ከተቀበልን እና በወንጌሉ ግልጽ እና ቀላል እውነቶች ከኖርን፣ የምንፈስ ቅዱስ ጓደኝነትን እንደምንደሰትበት አውቃለሁ። የሚያዩ አይኖች እና የሚሰሙ ጆሮዎች ውድ ስጦታ ይኖረናል። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።