2010–2019 (እ.አ.አ)
ለጻድቅ ምክንያት ለማገልገል እዚህ ነን
ኦክተውበር 2015


ለጻድቅ ምክንያት ለማገልገል እዚህ ነን

በጻድቅ ምክንያት እንደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጀግና መልእክተኞች ለማገልገል እንምረጥ።

እንደ ሊሳ በልብ ንጹህ ከሆኑ፣ በግል ፈተናቸው መካከልም፣ ጌታን ከሚያፈቅሩ እና ከሚያገለግሉት አይነት ታማኝ ሴቶች መካከል በመሰብሰባችን ምስጋና ይሰማኛል። የሊሳ ታሪክ እርስ በራስ መፈቃቀር እና አንዳችን የሌላችንን የመንፈስ ወብት ለመመልከት እንድንችል እንዲያስታውሰን ያደርጋል። ጌታ እንዳስተማረው፣ “የነፍሶች ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ እንደሆነ አስታውሱ።”1 8 ወይም 108 አመታችን ብንሆንም፣ እያንዳንዳችን “[በእርሱ] ፊት ውድ” ነን።2 ይወደናል። የእግዚአብሔር ሴት ልጆች ነን። በፅዮን ውስጥ እህቶች ነን። መለኮታዊ ፍጥረት አለን፣ እናም የምናከናውነው ግርማዊ ስራ አለን።

ባለፈው በጋ ሴት ልጆች ካሏት ተወዳጅ እናት ጋር ተገናኘሁ። ወጣት ሴቶቻችን ምክንያት፣ እንዲሁም ዋጋ ያለቸው መሆኑ እንዲሰማቸው የሚረዳቸው አንድ ነገር፣ እንደሚያስፈልጋቸው ሀሳቧን ከእኔ ጋር አካፈለች። በዚህ ህይወት ውስጥ ባለን መልኮታዊ አላማ መሰረት በመስራት የግል እና መለኮታዊ ዋጋችንን ለማወቅ እንደምንችል አውቃ ነበር። እነዚህም አስደናቂ ዘማሪዎች ይህን አላማ የሚያስተምሩ ቃላት ዘምረዋል። በፈተና እና ችግር ውስጥ፣ በፍርሀት እና በስቃይ ውስጥም፣ ጀግና ልብ አሉን። ሚናችንን ለማከናወን ወስነናል። ጻድቅ ምክንያትን ለማገልገል ነው በዚህ ያለነው።3 እህቶች፣ በዚህ ምክንያት ውስጥ ዋጋ ያለን ነን። እናስፈልጋለን።

ይህ የምናገለግለው ጻድቅ ምክንያትም የክርስቶስ ምክንያት ነው። ይህም የደህንነት ስራ ነው።4 ጌታ እንዳስተማረው፣ “ይህም ስራዬ እና ክብሬ ነው - የሰውን ሟች አለመሆን እና ዘለአለማዊ ህይወት ማምጣት።”5 ክርስቶስ የተሰቃየበት፣ ከእናንዳንዱ ቆዳ ቀዳዳው ደም የፈሰሰበት፣ እና በፍጹም ፍቅር ህይወትን የሰጠበት ምክንያት እኛ ነን። የእርሱም ምክንያት መልካም ዜና፣ “…ምስራች … እርሱም፣ እንዲሁም ኢየሱስ፣ ለአለም ሊሰቀልና የአለም ኃጢአቶችን ሊሸከም፣ እናም አለምንም ሊቀድስና፣ ከርኩሳትም ሊያጸዳ ወደ አለም እንደመጣ፣… በእርሱም አማካይነት …ሁሉ ይድኑ ዘንድ…።”6 አዳኛችን “መንገዱን አስመልክቷል እናም መርቷል።”7 የእርሱን ምሳሌ ስንከተል፣ እግዚአብሔርን ስናፈቅር፣ እና እርስ በራስ በደግነት እና በርህራሄ ስናገለግል፣ “በእግዚአብሔር ፊት በመጨረሻው ቀን”8 በንጹህነት እንደምንቆም እመሰክራለሁ። ከአብ እና ወልድ ጋር አንድ ለመሆን እንድንችል በእርሱ ጻድቅ ምክንያት ለማገልገል እንመርጣለን።9

ነቢዮ ሞርሞን እንዳወጀው፣ “በዚህ በሟች ሰውነታችን የምናከናውነው ስራ አለን፤ በዚያም የፅድቅ ጠላት የሆነውን ሁሉ እናጠፋለን፣ እናም ነፍሳችንን በእግዚአብሔር መንግስት እናሳርፋለን።”10 የመጀመሪያው የድሮ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች እና ፈር ቀዳጆች በጀግንነት እና በልብ ውሳኔ ታማኝነት በዳግም የተመለሰውን ወንጌል ለመመስረት እና የከፍተኛነት ስርዓቶች የሚከናወኑበት ቤተመቅደሶች ለመገንባት ወደፊት ገፉ። የአሁን ዘመን ፈር ቀዳጆቹም፣ ማለትም እናንተና እኔ፣ ደግሞም “ለሰዎች ነፍሳት መዳን በ[ጌታ] የወይን አትክልት ስፍራ ውስጥ ለማገልገል”11 በእምነት ወደፊት እንገፋለን። እናም፣ ፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ እንዳስተማሩት፣ “ሁሉን ቻይ ድንቅ ስራውን ልባቸው በአለም ቤዛ ፍቅር በተሞሉት ራስ ወዳድ ባልሆነ [አገልግሎት] ወደፊት ሲገፋ የወደፊቱ እንዴት አስገራሚ ነው።”12 ከድሮ፣ የአሁን ዘመን፣ እና የወደፊት ትውልድ ታማኝ እህቶች ጋር በደህንነት ስራ በመጣመር እንሰራለን።

ከመወለዳችን በፊት፣ “ልጆቹ ወደ ፍጹምነት እና በመጨረሻም መለኮታዊ እጣ ፈንታቸውን እንደ ዘለአለም ህይወት ወራሾች የሚሆኑበትን ስጋዊ ሰውነት እና ምድራዊ ልምዶች የሚያገኙበትን”13 የሰማይ አባት እቅድ ተቀበልን። ስለዚህ ቅድመ ህይወት ቃል ኪዳን፣ ሽማግሌ ጆን ኤ. ውድስቶው እንደገለጹት፥ “ወዲያው እና በዚያም፣ ለራሳችን አዳኞች ለመሆን ብቻ ሳይሆን… ለሰው ዘር ቤተሰብ በሙሉ አዳኞች ለመሆን ተስማማን።” ከጌታ ጋር አብረን የምንሰራ ሆንን። የእቅዱ መሳካት የአብ ስራ፣ እናም የአዳኝ ስራ ብቻ ሳይሆን የእኛም ስራ ሆነ። ለእኛ፣ ከሁሉም ትሁት የሚያደርገው፣ ከሁሉም ቻይ ጋር የደህንነት ዘለአለማዊ እቅድ አላማን ለማከናወን ያለ ተባባሪነት ነው።”14

በዚህ በሟችነት እንደገና አዳኝን በደህንነት ስራ ለማገልገል ቃል ገብተናል። በዚህ ቅዱስ የክህነት ስርዓት በተሳተፍ፣ በእግዚአብሔር አገልግሎት በሙሉ ልብ፣ ሀይል፣ አዕምሮ እና ጉልበት ለመስራት ቃል ገብተናል።15 መንፈስ ቅዱስን ተቀብለናል እናም በጥረታችን የእርሱን አመራር እንፈልጋለን። ጻድቅነት በአለም ውስጥ የሚስፋፋው እግዚአብሔር እንድናደርግ የሚፈልገንን ስንረዳና ይህንንም ስናደርግ ነው።

በባስ ማቆሚያ ቦታ ቆመው ሳሉ አንድ የህፃናት ክፍል ልጅ ለጓደኛዋ፣ “ወደ ቤተክርስትያን ከእኔ ጋር መምጣት ይገባሻል!” ያለችውን አውቃለሁ።

ሴት ጓደኛሞች በወጣት ሴቶች ክፍል ውስጥ እጅ ለእጅ ተያይዘው እና እርስ በራስ ለመረዳዳት ቃል ሲገቡ እና ከዚያም በሱስ ምክንያት የምትሰቃይን ወጣት ሴት የሚረዱበት ትክክለኛ መንገድ ሲያቅዱም አይቻለሁ።

የወንጌልም መሰረታዊ መርሆችን ለልጆቻቸው ለማስተማር እና ምሳሌ ለልጆቻቸው ለማሳየት፣ እና በዚህም እንደ ሔላማን ልጆች በችግሮች እና ፈተናዎች በጀግንነት እና በታማኝነት ለመቆም ይችሉ ዘንድ ወጣት እናቶች ጊዜአቸውን፣ ችሎታቸውን፣ እና ሀይላቸውን በሙሉ ሲሰጡ ተመልክቻለሁ።

ምናልባት ለእኔ ከሁሉም ትሁት የሚያደርግ ቢኖር በንጹህ ምስክር ከምናደርጋቸው ሁሉ በጣም አስፈላጊ የሚሆነው ለጋብቻና ለቤተሰብ መዘጋጀታችን ነው ብላ አንድ ሴት ያወጀችውን መስማት ነበር። ይህም እርሷን ያጋጠማት ባይሆንም፣ ቤተሰብ የደህንነት ስራ ዋና ክፍል እንደሆነ ታውቅ ነበር። “መለኮታዊው የደህንነት እቅድ የቤተሰብ ግንኙነቶች ከመቃብር በላይ እንዲቀጥሉ ያስችላል።”16 የአብን እቅድ እና የእግዚአብሔርን ክብር የምናከብረው እነዚያን ግንኙነቶች በአዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ጋብቻ ስናጠናክር እና ልዑል ስናደርግ ነው። እድሉ ሲመጣ፣ ያን ቅዱስ ቃል ኪዳን በጌታ ቤት ውስጥ ለማድረግ እና ለመጠበቅ እንችል ዘንድ ንጹህ እና ምግባረ መልካም ህይወት ለመኖር እንመርጣለን።

ሁላችንም በህይወታችን ጊዜያትን እና ዘመናትን እንለማመዳለን። ነገር ግን በትምህርት፣ በስራ፣ በህብረተሰብ ውስጥ፣ እና በልዩም በቤት ውስጥ ብንሆንም፣ እኛ የጌታ ወኪል ነን እናም በእርሱ ስራ ላይ ነው ያለነው።

በደህንነት ስራ ውስጥ፣ ለማመዛዘን፣ ለትችት፣ ወይም ለማውገዝ ምንም ክፍል የለም። ስለእድሜ፣ ስለልምድ፣ ወይም ስለህዝብ ሙገሳ አይደለም። ይህ ቅዱስ ስራ የጌታን ስራ በእርሱ መንገድ ለማከናወን የተሰበረ ልብ፣ የተዋረደ መንፈስ፣ እና መለኮታዊ ስጦታዎችን እና ልዮ ችሎታዎችን የምናዳብርበት ነው። ይህም በጉልበታችን ለመንበርከክ እና ፣ “አባት ሆይ፣ እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን፣ ግን ባንተ ፍላጎት” ለማለት ትህትና ሲኖር ነው።17

በጌታ ጥንካሬ፣ “ሁሉንም ነገሮች ለማድረግ” እንችላለን።18 የእርሱን ምሬት በጸሎት፣ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ፣ እና በመንፈስ ቅዱስ ሽኩሹክታ ውስጥ በቀጣይነት እንሻለን። ስሜት የሚነካ ሀላፊነትን የተጋፈጠችው አንድ እህት እንዲህ ጻፈች፣ “አንዳንዴ የቤተክርስቲያኗ የጥንት ታሪክ ውስጥ ያሉ እህቶች፣ ልክ እንደኛ፣ በምሽት ላይ ጭንቅላታቸውን በትራስ ላይ ጥለው ‘ነገ ምንም ቢያመጣም፣ አንተ በዚያ ውስጥ እንዳልፍ ትርዳኛለህን?’ የማይፀልዩ እንደነበር አስባለሁ።” ከዚያም እንዲህ ጻፈች፣ “ከበረከቶች አንዱ አንዳችን ለሌላችን መገኘታችን እና በዚህም ውስጥ አብረን መሆናችን ነው!”19 ጉዳያችን ምንም ቢሆንም፣ በደህንነት ጎዳና ላይ የትም ብንሆንም፣ ለአዳኝ ባለን የልብ ውሳኔ አንድ ነን። በአገልግሎቱም እርስ በራስ እንደጋገፋለን።

ምስል
ኤላ ሆስኪንስ የግል እድገታቸው ፈጸሙ

በቅርብ፣ በአንድ መቶ አመታቸው የአውራጃቸውን ወጣት ሴቶች በግል እድገታቸው እንዲረዱ ጥሪ ስለተቀበሉ እህት ኤላ ሆስኪንስ ሰምታችሁ ይሆናል።20 ከሁለት አመት በኋላ፣ በ102 አመታቸው፣ እህት ሆስኪንስ የወጣት ሴቶች የእውቅና ሽልማትን አገኙ። ወጣት ሴቶች፣ የአውራጃው እና የካስማው ወጣት ሴቶች አመራር፣ እና ቤተሰብ አባላት ስኬታቸውን ለማክበር ተሰበሰቡ። የእድሜ፣ ድርጅት፣ እና የጋብቻ ሁኔታ ግደብ በታማኝ አገልግሎት ውስጥ ተዋጠ። ወጣት ሴቶች ለእህት ሆስኪንስ፣ ስላስተማሯቸው፣ ለእርሳቸው ጻድቅ ምሳሌ፣ ምስጋና አቀረቡ።እንደእርሳቸው ለመሆን ፈለጉ። ከዚያም በኋላ፣ እህት ሆስኪንስ፣ “እንዴት ይህን አደረጉት?” ብዬ ጠየኩኝ።

በቅፅበት እንዲህ መለሱ፣ “በየቀኑ ንስሀ እገባለሁ።”

በጌታ መንፈስ ሙሉ ሆነው በንጹህ ብርሀን ከሚያበሩ ጨዋ ሴት፣ በድቅድስና ውብት ብሩህ ለመሆን፣ ከጌታ ጋር ለመቆም እና ሌሎችን ለመባረክ፣ ንጹህ መሆን እንዳለብን እንዳስታውስ ተደርጌአለሁ። ንጹህነት በክርስቶስ ጸጋ በኩል፣ ከሀጂነትን ትተን እና እግዚአብሔን በሀይል፣ አዕምሮ፣ እና ጥንካሬ ለማፍቀር በመምረጥ፣ የሚቻል ነው።21 ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳስተማረው፣ “ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።”22 ማንኛችንም ፍጹም አይደለንም። ስህተቶች አድርገናል። ነገር ግን ለመሻሻል እና “የ[ክርስቶስን] ስም [በልባችን] ውስጥ ሁልጊዜም ተጽፎ ለማግኘት”23 ንስሀ እንገባለን። በንጹህ ልብ፣ በጌታ ስም ስናገለግል፣ የጌታን ፍቅር እናንጸባርቃለን እና ሌሎችንም የሰማይን ምልክት እንሰጣለን።

በጻድቅ ምክንያት እንደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጀግና መልእክተኞች ለማገልገል እንምረጥ። አብረን እንቁም እና “በልባችን ውስጥ ባለ መዝሙር፣ በወንጌል በመኖር፣ ጌታን በማፍቀር፣ እና መንግስቱን በመገንባት ወደፊት እንግፋ።”24 በዚህ ክቡር ስራ ውስጥ የእግዚአብሔርን ንጹህ ፍቅር ለማወቅ እንደምንችል እመሰክራለሁ። እውነተኛ ደስታን ለመቀበል እና የዘለአለምን ክብሮች ሁሉ ለማግኘት እንችላለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።