2010–2019 (እ.አ.አ)
ትዕዛቱን ጠብቁ
ኦክተውበር 2015


ትዕዛቱን ጠብቁ

ታላቅ ደስታን ለማግኘት እንዴት መኖር እንዳለብን እኛን የፈጠረን እና የሚወደን እርሱ ፍፁም በሆነ መልኩ ያውቃል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ በድጋሚ ከእናንተ ጋር መሆኑ እንዴት መልካም ነው። በዚህ ምሽት በሰማናቸው ቃላቶች ተነሳስተናል። እኔ እራሱ በምለው ነገር ላይ እመራ ዘንድ እፀልያለሁ።

የዛሬ ምሽት መልዕክቴ ቀጥተኛ ነው። እሱም ይሄ ነው፥ ትዕዛዛትን ጠብቁ።

የእግዚአብሔር ትዕዛዛት እኛን ሊያጨናንቁን ወይም ለደስታችን እንቅፋቶች ሊሆኑብን አይደለም የተሰጡን። ልክ የዚህ ተቃራኒ ነው ትክክለኛው። የፈተረንና የሚወደን እግዚአብሔር የሚቻለውን ታላቅ ደስታ ለማግነት ሕይወቶቻችንን እንዴት አድርገን መኖር እንደሚገባን ፍፁም በሆነ መልኩ ያውቃል። ከተከተልናቸው በዚህ አደገኛ በሆነው ምድራዊ ሕይወታችን ውስጥ የሚጠቁሙንን ምሪቶች ሰጥቶናል። የታዋቂውን መዝሙር ቃሎች እናስታውሳለን፥ “ትዕዛዛቱን ጠብቁ፤ በዚህ ደህንነት አለና፤ በዚህ ሰላም አለና።”1

የሰማይ አባታችን እኛን ከመውደዱ ተነሳ እንዲህ ብሏል፥ አትዋሽ፤ አትስረቅ፤ አታመንዝር፤ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፤ ወዘተ።2 ትዕዛዛቶቹን እናውቃቸዋለን። ትዕዛዛቱን ስንጠብቅ፣ ሕይወታችን ደስተኛ፣ የበለጠ የሚያረካና ያነሰ ውስብስብ እንደሚሆን ይገባዋል/ይረዳል። ፈተናዎቻችንና ችግሮቻችን ለመሸከም ቀላል ይሆናሉ እንዲሁም ቃል የገባልንን በረከቶች እንቀበላለን። ነገር ግን ህግጋትንና ትዕዛዛትን ሲሰተጠን፣ እንዲሁም ለመቀበል ወይም ላለመቀበል እንድንመርጥ ይፈቅድልናል። በእነዚህ ነገሮች ላይ ያሉን ውሳኔዎቻችን እጣ ፈንታችንን ይወስኑታል።

እያንዳንዳችን እንደ እግዚአብሔር የመጨረሻ ግብ በሰማይ አባትና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ መገኛ የዘላለማዊ ሕይወት እንደሚኖረን እተማመናለሁ። ስለሆነም በሕይወታችን ውስጥ ወደዚህ ታላቅ ግብ የሚያመሩንን ምርጫዎች ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ፣ተቀናቃኙ ለእኛ ውድቀት ጠንክሮ እንደሚሰራ እናውቃለን። እሱና ጭፍሮቹ ፃድቅ ምኞታችንን ለመግታት እየባዘኑ ነው። እኛም በበኩላችን በውሳኔዎቻችንና ግባችንን ለማሳካት ባለን ጥረት የማንባዝን ከሆነ፣ ለዘላለም መዳናችን አስከፊና ዘላቂ የሆኑ ጥቃትን ይወክላሉ። ሐዋርያው ጴጥሮስ እንዲህ ሲል አስጠነቀቀን፥ “በመጠን ኑሩ ንቁም፣ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና።”3

ምንም እንኳን በሕይወታችን ውስጥ ከፈተና ንፁህ የምንሆንበት ጊዜ ባይኖርም፣ እናንተ ወጣት ወንዶች በተለየ ሁኔታ ተጠቂ በምትሆኑበት እድሜ ላይ ነው ያላችሁት። የአፍላ እድሜ ብዙውን ጊዜ ያለመረጋጋት፣ የጥቅም አልባነት ስሜት የሚሰማበት፣ በአቻዎቻችሁ ውስጥ ቦታን የማግኘት እና የመመሳሰል ጥረት የምታደርጉበት አመቶች ናቸው። ጓደኞች እንዲሆኗችሁ በምትመኟቸው ሰዎችተቀባይነትን ለማግኘት አቋማችሁን አውርዳችሁ አብዛኛዎቹን ሰዎች ለመከተል ትፈተኑ ይሆናል። እባካችሁ ጠንካሮች ሁኑ እንዲሁም የዘላላም በረከቶችን እንዳታገኙ ለሚገድባችሁ ማንኛውም ነገር የነቃችሁ ሁኑ። እዚህ እና አሁን የምታደርጉት ምርጫዎች ለዘላለም ጠቃሚዎች ናቸው።

1ኛ ቆሮንጦስ ይህን እናነባለን፥ “በዓለም ቁጥር የሌለው የቋንቋ ዓይነት ይኖራል።”4 ግፊት በሚያደርጉ፣ በሚያሳስቱ፣ ዝቅ በሚያደርጉ፣ ውስብስብ በሆኑና ግራ በሚያጋቡ ድምፆች ተከበናል። እነዚህ ጮክ ያሉ ድምፆች ናቸው ብዬ መጨመር እፈልጋለሁ። ድምፁን ዝቅ እንድታደርጉ እንዲሁም በአንፃሩ ወደ ደህንነት በሚመራችሁ በዝግታው፣ ትንሽዬ ድምፅ ተፅዕኖ እንዲደረግባችሁ እመክራችኋለሁ። የሆነ የክህነት ስልጣን ያለው ሰው ከተጠመቃችሁ በኋላ እጆቹን በራሳችሁ ላይ ጭኖ የቤተክርስቲያኗ አባልነታችሁን ፥ “መንፈስ ቅዱስ ተቀበል”5 ብሎ ማረጋገጡን አስታውሱ። ለዛ እውነትን ለሚመሰክረው ለየት ላለ ድምፅ ልባችሁን እንዲሁም ነፍሳችሁንም ጨምሮ ክፈቱ። ነብዩ ኢሳይያስ ቃል እንደገባው፣ “መንገድህ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ።”6 በደህና የሚያቆየንን ይህንን አፅናኝ፣ መሪ ድምፅ እንሰማ ዘንድ ሁሌም እራሳችንን እናመቻች።

ትዕዛዛት የቀናችን ወረርሽኞች ብዬ ለምለው መንገዱን ስለከፈተ ችላ በሉት። የተወሰኑት ለመጥቀስ ያክል፣ የመቻቻል ወረርሽኝን፣ የእራቁት ምስል ወረርሽኝን፣ የአደንዛዥ ዕፆች ወረርሽኝን፣ የኢግብረ ገብነት ወረርሽኝንና የውርጃ ወረርሽኝን ያካትታሉ። ቅዱሳት መጽሐፍቶች ጠላታችን “የእነዚህ ነገሮች ሁሉ አመንጪ”7 እንደሆነ ይነግሩናል። “ሰዎችን ሊያሳስትና ሊያሳውር ያለ የሁሉም ውሸቶች አባት”8 እንደሆነ እናውቃለን።

በዚህ ምድራዊና ወደ ፊት በሚመጣው ሕይወት ውስጥ ዘላለማዊ ደስታችሁን የሚወስድባችሁን ነገር እንድታስወግዱ እለምናችኋለሁ። ጠላቱ የምትፈቅዱለት ከሆነ በእሱ ማታለሎችና ውሸቶች ወደ ምትጠፉበት በአንሸራታቹ ቁልቁለት ላይ ይወስዳችኋል። መቆም እንደማትችሉ እስከምታውቁ ድረስ በዛ አንሸራታቹ ቁልቁለት ላይ እንዳላችሁ አታውቁም። የጠላቱን መልዕክቶች ሰምታችኋል። በማታለል መልኩ እንዲህ ይጣራል፥ ይሄኛው ብቻ ምንም ችግር የለውም፤ ሁሉም ሰው ደግሞ እያደረገው ነው፤ የድሮ ሰው አትሁን፤ ጊዜዎች ተለውጠዋል፤ ማንንም አይጎዳም፣ ሕይወትህ የራስህ ነው። ጠላቱ ያውቀናል እንዲሁም ችላ ለማለት የሚያስቸግሩንን ፈተናዎች ያውቃቸዋል። ለእንደዚህ አይነቶቹ ወሸቶችና ፈተናዎች እጃችንን መስጠት እናስወግድ ዘንድ እራሳችንን ሁሌ መጠበቅ እንዴት ጠቃሚ ነው።

እውነትን በሚያጣምሙ፣ መልካሙንና ጥሩዉን በሚያጠፉ እና በዓለም ሰው ሰራሽ ፍልስፍናዎች ለመተካት በሚሞክሩ ሁሌም በሚጨምረው የግፊትና የማታለያ ተፅዕኖ ውስጥ ተከበን አማኝና እውነተኛ ሆነን ስንኖር ታላቅ ድፍረት ያስፈልጋል። ትዕዛዛት በሰው ተፅፈው ቢሆን ኖሮ፣ ስሜትን ተከትሎ ወይም በህግ ወይም በሌላ መንገድ ቢቀየሩ ለሰዎች ተገዢ ይሆኑ ነበር። ትዕዛዛቶች፣ ይሁን እንጂ፣ ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸው። ነፃ ምርጫችንን በመጠቀም ወደ ጎን መተው እንችላለን። ይሁን እንጂ፣ እነሱን ካለመታዘዝና ከመስበር የሚመጡትን ውጤቶች መቀየር እንደማንችለው ሁሉ፣ እነሱንም መቀየር አንችልም።

የእኛ የዚህ ሕይወት ታላቅ ደስታ የሚመጣው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ስንከተልና ህጋጋቶቹን ስናከብር እንደሆነ እንናስተውል። በኢሳይያስ ምዕራፍ 32፣ ቁጥር 17 ላይ የሚገኙትን ቃሎች እወዳቸዋለሁ። “የጽድቅም ስራ ሰላም፣ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።” እንደዚህ አይንት ሰላም፣ እንደዚህ አይነት ማረጋገጫ መምጣት የሚችለው በጽድቅ አማካኝነት ብቻ ነው።

ከሃጢያት ጋር ስንጋፈጥ ትንሽ እንኳን ጠጋ ለማለት መፍቀድ አንችልም። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በማፍረስ “ትንሽዬ ብቻ” መለማመድ እንደምንችል በማመን እራሳችንን መፍቀድ አንችልም፣ ምክንያቱም ሃጢያቱ እራሳችንን ነፃ ለማውጣት እጅግ በሚያመው የብረት ዘንግ ሊይዘን ይችላልና። ከአደንዛዥ ዕፆች፣ ከአልኮል፣ ከእራቁት ምስልና ከኢግብረ ገብነት የሚመጡት ሱሶች፣ እውንና ከታላቅ ትግልና ብዙ እርዳታ ውጪ ለመስበር በጣም ከባድ የሚሆኑ ናቸው።

ማናችሁም በሕይወታችሁ ውስጥ ሃጢያትን የፈቀዳችሁ ብትኖሩ፣ ለመመለሻ መንገድ እንዳለ አረጋግጥላችኋለሁ። ሂደቱ ንስሃ ይባላል። ምንም እንኳን መንገዱ ከባድ ቢሆንም፣ የዘላለም መዳናችሁ በእሱ ላይ የተመረኮዘ ነው። ጥረታችሁን የበለጠ የሚሻ ሌላ ምን ነገር አለ? በሙሉ ንስሃ ለመግባት የሚያስፈልጉትን ደረጃዎች ለመውሰድ እዚህና አሁን እንድትወስኑ እማጸናችኋለሁ። ይህንን ቶሎ ባደረጋችሁ ጊዜ ኢሳይያስ የተናገረውን ሰላም፣ ጸጥታና መታመን ቶሎ ትለማመዳላችሁ።

ከትንሽ ጊዜ በፊት ከባሏ ጋር ትዕዛዛትን በመስበር በሂደቱ ውስጥም ቤተሰባቸው ሊፈርስ የነበረ፣ ከደህንነት መንገድ ወጥተው የነበሩ ሴትን ምስክርነት ሰማሁኝ። እያንዳንዳቸው መጨረሻ ላይ በሱስ ተፅዕኗቸው ውስጥ መመልከት ሲችሉና ሕይወታቸው እንዴት ደስተኛ እንዳልነበረ እንዲሁም የሚወዱትን ሰዎች እንዴት እየጎዷቸው እንደሆነ ሲገነዘቡ መለወጥ ጀመሩ። የንስሃው ሂደት ዝግተኛና የሚያም ነበር፣ ነገር ግን በክህነት መሪዎች እንዲሁም በቤተሰብና በታማኝ ጓደኞች እርዳታ አማክኝነት ወደ መንገዳቸው ተመለሱ።

የዚህችን እህት የንስሃን የፈውስ ኃይል ምስክርነት ትንሽዬ ክፍል አካፍላችኋለው፥ “እንዴት አንድ ሰው ከጠፉት በጎችና በሃጢያት ከተያዙት አንዱ ከመሆን አሁን ከሚሰማን ወደዚህ ሰላምና ደስታ ይሄዳል? መልሱ…ፍፁም በሆነው ወንጌል፣ ፍፁም በሆነው ልጁና ለእኔ ባደረገው መስዋትነቱ ምክንያት ነው። … ጨለማ በነበረበት አሁን ብርሃን አለ። ተስፋ መቁረጥና ህመም በነበረበት ደስታና ተስፋ አለ። በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት እውን የሆነውን በንስሃ ብቻ በሚመጣው ለውጥ መተባርከናል።”

አዳኛችን ለእናንተ እና ለእኔ ያንን የተባረከ ስጦታ ሊሰጠን ሞተ። ምንም እንኳን መንገዱ ከባድ ቢሆንም፣ ቃል-ኪዳኑ እው ነው። ጌታ ንስሃ ለሚገቡት ሰዎች እንዲህ በማለት ተናገረ፥

“ሀጢአታችሁ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።”9

“ከእንግዲህ ወዲህ [አላስባቸውምና]።”10

በመላ ሕይወታችን ውስጥ ቅዱሳት መጽሐፍትን በማጥናትና በመፀለይ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል እውነታዎችን በማሰላሰል ጠንካራ ምስክሮችን መመገብ ያስፈልገናል። የወንጌል፣ የአዳኝና የሰማይ አባታችን ምስክርነቶች ስር ሲሰዱ፣ የምናደርገውን ነገር በሙሉ ተፅዕኖ ያደርጋሉ።

ሁላችንም በዚህ ቀንና ጊዜ ለአላማ ወደ ምድር የተላክንና ሌሎችን እንድናገለግልና የእግዚአብሔርን ስራዎች በዚህ ምድር ላይ እንድንተገብር የእግዚአብሔር ክህነት የተሰጠን የሰማይ አባታችን ውድ ወንድ ልጆች እንደሆንን እመሰክራለሁ። ያንን ክህነት ለመሸከም ብቁ ሆነን ለመገኘት ሕይወታችንን እንድንኖር ታዘናል።

ወንድሞቼ፣ ትዕዛዛቱን እንጠብቅ! ከጠበቅን ድንቅና ክብራማ ነገሮች ይጠብቁናል። ይሄ በረከታችን ይሆን ዘንድ በአዳኛችንንና በቤዛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እፀልያለሁ፣ አሜን።