2010–2019 (እ.አ.አ)
መንፈስ ቅዱስ እንደ አጋራችሁ
ኦክተውበር 2015


መንፈስ ቅዱስ እንደ አጋራችሁ

በብቁነት የምንኖር ከሆነ፣ የመንፈስ ቅዱስ በረከት አንዳንዴ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ከእኛ ጋር ሊሆን ይችላል።

በዚህ የጌታ ቤተክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ በሰንበት ቀን ከእናንተ ጋር በመሆኔ አመስጋኝ ነኝ። እናንተ እንደተሰማችሁ ሁሉ ሲነገሩ የሰማናቸው ቃላትን እውነታ መንፈስ ሲመሰክር እኔም ተሰምቶኛል።

የዛሬ አላማዬ ከተጠመቅን በኋላ ለእያንዳንዳችን ቃል የተገቡት ስጦታዎች ይገቡናል ለማለት ፍላጎታችሁን እና ቁርጠኝነታችሁን መጨመር ነው። ማረጋገጫ በሚሰጠን ወቅት እነዚህን ቃላት ሰምተናል፤ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበል(ይ)።”1 ከዚያ ቅፅበት ጀምሮ፣ ህይወታችን ለዘለአለም ተቀየረ።

በብቁነት የምንኖር ከሆነ፣ የመንፈስ ቅዱስ በረከት አንዳንዴ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ከእኛ ጋር ሊሆን ይችላል። ከቅዱስ ቁርባን ፀሎት ያ ቃልኪዳን እንዴት እንደተሟላ ታውቃላችሁ፤ “የዘለአለም አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ዳቦ ለሚበሉት ነብሳት ሁሉ፣ የልጅህን ስጋ ለማሰብ ይበሉት ዘንድ፣ ላንተም ይመሰክሩ ዘንድ፣ የዘለአለም አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ የእርሱን ስም በላያቸው ለመውሰድ እና ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ፍቃደኞች ይሆኑ ዘንድ ትባርከው እና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሀለን አሜን።”

እና ከዛም ቃል ኪዳኑ ይመጣል፤ “መንፈሱም ሁልጊዜ ከእነርሱ ጋር ይሆን ዘንድ” (ት እና ቃ 20:77 ፤ አትኩሮት ተጨምሮበት)።

ሁልጊዜ መንፈሱ ከእኛ ጋር እንዲኖር ማለት የመንፈስ ቅዱስ ምሬት በየቀን ህይወቶቻችን መኖሩ ነው። ለምሳሌ፣ ክፋትን የማድረግ ፈተናን እንድንቋቋም በመንፈስ ልንገሰፅ እንችላለን።

በዚያ ምክንያት ብቻ፣ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎቻችን ውስጥ እግዚአብሔርን ለማምለክ ፍላጎታችን እንዲጨምረ ለምን የጌታ አገልጋዮች እንደሞከሩ ለመረዳት ቀላል ነው። በእምነት ቅዱስ ቁርባንን ከተካፈልን፣ በስሜት እና በድግግሞሽ እየጨመሩ ከሚመጡት ፈተናዎች እኛን እና የምንወዳቸውን ሰዎች መንፈስ ቅዱስ ሊጠብቅ ይችላል።

የመንፈስ ቅዱስ አጋርነት መልካም የሆነው ይበልጥ እንዲስበን እና የመፈተን ግዳጅ እንዲቀንስ ያደርጋል። ያ ብቻ መንፈስ ቅዱስ ሁሌ ከእኛ ጋር እንዲሆን ብቁ ለመሆን እንድንወስን ለማድረግ በቂ ነው።

መንፈስ ከክፋት በተቃራኒ እንደሚያጠነክረን ሁሉ፣ በእውነት እና ውሸት መካከል እንድንለይ ሀይልንም ይሰጠናል። ለውጥ የሚያመጣው እውነት የሚረጋገጠው ከእግዚአብሔር በሆነ መገለጥ ብቻ ነው። ሰዋዊ ምክንያታችን እና የአካላዊ ስሜቶቻችንን መጠቀም በቂ አይሆኑም። ጠቢባን እንኳን እውነትን ከሀይለኛ ማጭበርበር ለመለየት በሚቸገሩበት ጊዜ ላይ ነው የምንኖረው።

የአዳኝን ትንሳኤ የአዳኝን ቁስሎች በመንካት አካላዊ ማረጋገጫ ለፈለገው ሐዋርያው ቶማስ፣ መገለጥ የተሻለ ማረጋገጫ እንደሆነ ጌታ አስተማረው፣ “ኢየሱስም፣ ስለ አየኸኝ አምነሃል፣ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው” (ዮሐነስ20:29)።

እግዚአብሔር ዘንድ ወዳለው ቤት የሚጠቁሙት እውነታዎች በመንፈስ ቅዱስ ይረጋገጣሉ። ወደጫካው በሄድ አብ እና ልጁ ወጣቱ ዮሴፍ ስሚዝን ሲያናግሩት ማየት አንችልም። ቃል

መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ይገባኛል ለሚሉ የእግዚአብሔር ሴት እና ወንድ ልጆች የእውነት ማረጋገጫ ይመጣል። ውሸቶች በማንኛውም ጊዜ ለእኛ ሊቀርቡ ስለሚችሉ፣ ከጥርጣሬ ጊዜያት እንዲያድነን የእውነት መንፈስ ቋሚ ተፅእኖ ያስፈልገናል።

የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ አባል በነበሩበት ወቅት፣ መንፈስ ከእኛ ጋር እንዲሆን በቋሚነት እንድንሻ ጆርጅ ኪው ካኖን ገልፀዋል። እንዲህ ብለው ቃል ገቡ፣ እና እኔም ያንን ቃል እገባለሁ፣ ያንን መንገድ ከተከተልን፣ “የእውነት እጥረት በፍፁም አይኖርብንም”፣ “በፍፁም በጥርጣሬ እና ጨለማ ውስጥ አንሆንም”፣ እና “እምነታችን ጠንቃራ እና ደስታችን ሙሉ ይሆናል።”2

ያንን የመንፈስ ቅዱስ አጋርነት ለሌላ ምክንያትም እንፈልገዋለን። የምናፈቅራቸው ሰዎች ሞት ሳይጠበቅ ሊመጣ ይችላል። የምናፈቅራቸውን በምናጣ ጊዜ ተስፋ እና ምቾት የሚሰጠን የተወዳጁ የሰማይ አባት እና ትንሳኤን ያደረገው አዳኝ እውነታ የሆነው የመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ነው። ሞት በሚከሰትበት ወቅት ያ ምስክርነት ትኩስ መሆን አለበት።

ስለዚህ፣ ለብዙ ምክንያቶች፣ የመንፈስ ቅዱስ ቋሚ አጋርነት ያስፈልገናል። እንፈልገዋለን፣ ነገር ግን ለማግኘት ቀላል እንዳልሆነ ከተሞክሮአችን እናውቃለን። መንፈስን የሚያስከፉ ነገሮችን ሁላችንም በየቀን ህይወታችን እናስባለን፣ እንናገራለን፣ እናም እናደርጋለን። ልቦቻችን በልግስና ሙሉ ሲሆኑ እና “ቅድስና ያለማቋረጥ አስተሳሰባችንን ሲያስውብ” መንፈስ ቅዱስ የእኛ ቋሚ አጋር እንደሚሆን ጌታ አስተምሮናል። (ት. እና ቃ. 121:45)

ለመንፈስ አጋርነት ስጦታ ብቁ ለመሆን በሚያስፈልገው ከፍተኛ ደረጃ ትግል ላይ ላሉ ሰዎች፣ ይህንን ማበረታቻ አቀርባለሁ። የመንፈስ ቅዱስ ተፅእኖ የተሰማችሁ ጊዜያት ነበሩ። ዛሬ ተከስቶ ሊሆን ይችላል።

እነዚያን የመነሳሳት ወቅቶች ልክ አልማ እንዳብራራው የእምነት ዘር ተንከባከቡ(አልማ 32:28 ተመልከቱ)። እያንዳንዱን ትከሉት። በተሰማችሁ መነሳሻ ላይ ያንን ማድረግ ትችላላችሁ። አስራትን ለመክፈል ከሆነ፣ ክፈሉ። ማንኛውም ነገር ቢሆን፣ አድርጉት። እናም ማድረጋችሁን ቀጥሉ። ለመታዘዝ ፍቃደኛነታችሁን ስታሳዩ፣ እግዚአብሔር እንድታደርጉ የሚፈልገውን መንፈስ በበለጠ ስሜት ይልክላችኋል።

ስትታዘዙ፣ ከመንፈስ ስሜቶች በይበልጥ ይመጣሉ። ትክክለኛውን የመምረጥ ሀይላችሁ ይጨምራል።

ለድርጊት መነሳሻዎች ከእራሳችሁ ፍላጎት ይልቅ ከመንፈስ የመጡ መሆናቸውን ማወቅ ትችላላችሁ። ስሜቶቹ አዳኝ እና ህያው ነብያቶቹ እና ሐዋርያቶቹ ከተናገሩት ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ በድፍረት ለመታዘዝ ትመርጣላችሁ። ከዛም እንዲረዳችሁ ጌታ መንፈሱን ይልካል።

ለምሳሌ፣ በተለይ ከባድ በሚሰል ጊዜ፣ የሰንበት ቀንን ለማክበር መንፈሳዊ መነሳሻን ከተቀበላችሁ፣ ለመርዳት እግዚአብሔር መንፈሱን ይልካል።

አባቴ ለስራ ወደ አውስትራሊያ ሲሄድ ያ እርዳታ ወደእርሱ መጥቶ ነበር። በእሁድ ቀን ብቻውን ነበር፣ እናም ቅዱስ ቁርባንን ለመውሰድ ፈልጎ ነበር። ስለ ኋለኛው ቀን ቅዱሳን ስብሰባዎች መረጃ ሊያገኝ አልቻለም ነበር። ስለዚህ የእግር ጉዞ ጀመረ። ወዴት መታጠፍ እንዳለበት ለማወቅ በእያንዳንዱ መታጠፊያ ላይ ፀለየ። ለሰአት ያህል ከተጓዘ እና ከታጠፈ በኋላ፣ ደግሞ መፀለዩን አቆመ። በሆነ መንገድ ለመጠማዘዝ መነሳሻ ተሰማው። ብዙም ሳይቆይ በአቅራቢያ ካለው ከህንጻ ታችኛ ወለል ውስጥ ዝማሬ ይሰማው ጀመረ። በመስኮት ውስጥ ተመለከተ እና በነጭ ልብስ በተሸፈነ ጠረጴዛ እና የቅዱስ ቁርባን ማቅረቢያ አከባቢ ጥቂት ሰዎች ተቀምጠው ተመለከተ።

አሁን፣ ያ እምብዛም ላይሰማችሁ ይችላል፣ ነገር ግን ለእርሱ ድንቅ ነገር ነበር። የቅዱስ ቁርባንን ፀሎት ቃል ኪዳን መሟላቱን አወቀ፤ “ሁሌም ያስታውሱ እና የተሰጣቸውን ትእዛዛት ይጠብቁ ዘንድ፤ መንፈሱም ሁልጊዜ ከእነርሱ ጋር ይሆን ዘንድ” (ት እና ቃ 20:77)።

ያ የፀለየበት እና እግዚአብሔር እንዲያደርግ የፈለገውን መንፈስ እንደነገረው ያደረገበት አንድ ብቻ የምሳሌ ጊዜ ነው። ለአመታትም እነደዚው አደረገ፣ እናንተ እና እኔ እንደምናደርገው። ስለመንፈሳዊነቱ በፍፁም አያወራም። ለጌታ ጥቂት ነገሮችን በማድረግ ብቻ ቀጠለ።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሰዎች እንዲነግራቸው በሚጠይቁት ጊዜ ሁሉ፣ ያደርገው ነበር። ሰዎቹ 10 ወይም 50 ቢሆኑም ወይም ምንም ያህል ደክሞት ቢሆንም ያደርገው ነበር። መንፈስ እንዲያደርግ በገፋፋው ጊዜ ሁሉ ስለ አብ፣ስለልጁ፣ እና ሰለነብያት ምስክርነቱን አካፍሏል።

በቤተክርስቲያን ውስጥ የነበረው ከፍተኛ ጥሪ፣ በካስማ እርሻ ውስጥ አረም ያጸዳበት፣ እና የሰንበት ትምህርት ክፍል ያስተማረበት፣ የቦንቪል ካስማ ከፍተኛ አማካሪ ነበር። በአመታት ውስጥ፣ ባስፈለገው ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ አጋሩ በዛ ነበረው።

በሆስፒታል ክፍል ውስጥ ከአባቴ ጎን ቆሜ ነበር። እናቴ፣ የ41 አመታት ሚስቱ፣ አልጋ ላይ ተኝታለች። ለሰአታት ስንመለከታት ነበር። የህመም መስመሮች ከእርሷ ፊት ላይ ሲወገዱ ማየት ጀመርን። የእጆቿ ጣቶች፣ ጭብጥ ብለው የነበሩት፣ ፈታ አሉ። ክንዶቿ በጎኗ ላይ ሆኑ።

የካንሰር የአስርተ አመታት ህመሞች እያበቁ ነበር። በፊቷ ላይ የሰላም እይታን ተመለከትኩ። ጥቂት አጭር ትንፋሾችን ወሰደች፣ ከዛ አቃሰተች፣ እናም ከዛ ጋደም አለች። ሌላ ትንፋሽ ይኖራል ብለን ቆመን ጠበቅን።

በመጨረሻም፣ በዝግታ አባቴ እንዲህ አለ፣ “ትንሽዋ ልጅ ወደ ቤት ሄደች።”

እምባ አላፈሰሰም። ያም የሆነበት ምክንያት እርሷ ማን እንደነበረች፣ ከየት እንደመጣች፣ ምን መሆን እንደቻለች፣ እና የት እንደምትሄድ መንፈስ ቅዱስ ግልፅ ምስልን ከሰጠው ቆይቷል። ስለሰማይ አባት፣ የሞት ሀይልን ስለሰበረው አዳኝ፣ እና ከሚስቱ እና ቤተሰቡ ጋር የተካፈለው የቤተመቅደስ መታተምን እውነታ መንፈስ ብዙ ጊዜ መስክሮለታል።

መልካምነቷ እና እምነቷ እንደ ድንቅ የቃልኪዳን ልጅነት ወደምትታወስበት እና በክብር ወደ ቤት እንኳን ደህና መጣሸ የምትባልበት የሰማይ ቤት ለመመለስ ብቁ እንዳደረጋት መንፈስ ካረጋገጠለት ቆይቷል።

ለአባቴ፣ ያ ከተስፋም በላይ ነበር። መንፈስ ቅዱስ ያንን እውን አድርጎለታል።

አሁን፣ የእርሱ ቃላት እና ስለሰማይ ቤት የነበረው የአእምሮ ምስል ጣፋጭ ስሜት፣ ሰው በማጣቱ የሚኖር የባል ደመናማ ፍርድ መሆኑን ጥቂቶች ሊናገሩ ይችላሉ። ነገር ግን ማወቅ በሚቻለው መንገድ የዘለአለም እውነታን ያውቃል።

እርሱ በጉርምስናበ ሙሉ ህይወቱ ውስጥ ስለአካላዊ አለም እውነታን ሲፈልግ የነበረ ሳይንቲስት ነበር። በአለም ዙሪያ በእኩዮቹ ያስከበረውን የሳይንስ መሳሪያዎች በበቂ ሁኔታ ተጠቅሟል። አብዛኛው የኬሚስትሪ ስራዎቹ የመጡት በአእምሮው አይኖች ውስጥ ቅንጣቶች ሲንቀሳቀሱ ከማየት እና ከዛም እይታውን በቤተሙከራ ውስጥ በመሞከር በማረጋገጥ ነበር።

ነገር ግን ለእርሱ እና ለእኛም በጣም ትርጉም የነበረውን እውነትን ለማግኘት የተለየ መንገድ ተከተለ። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ብቻ ሰዎችን እና ክስተቶችን እግዚአብሔር ልክ እንደሚያያቸው መመልከት እንችላለን።

ያ ስጦታ ሚስቱ ከሞተች በኋላም በሆስፒታል ውስጥ ቀጠለ። ወደቤት ለመውሰድ የእናቴን ነገሮች ሰበሰብን። ወደ መኪና ለመውጣት ስንሄድ አባቴ በመንገዱ ያገኛቸውን ነርስ እና ዶክተር ሁሉ እየቆመ አመሰገነ። ብቻችንን በሀዘን ውስጥ ለመሆን መውጣት እንደነበረብን የተሰማኝን አስታውሳለሁ።

እርሱ የተመለከተው መንፈስ ቅዱስ ያሳየውን ነገሮች ብቻ እንደነበር አሁን አስተውያለሁ። ፍቅሩን ለመንከባከብ እነዚያን ሰዎች እግዚአብሔር እንደላካቸው መላእክት ነበር የተመለከታቸው። እነርሱ እራሳቸውን እንደ ጤና ባለሙያ ይመለከቱ ይሆናል፣ አባቴ ግን ያመሰገናቸው በአዳኝ ፈንታ ስለሰሩ ነበር።

በወላጆቼ ቤት ስንደርስም የመንፈስ ቅዱስ ተፅእኖ አብሮት ቀጠለ። በሳሎን ውስጥ ለጥቂት ደቂቃዎች ተነጋገርን። አባቴ ወደ ቅርቡ መኝታ ክፍል ውስጥ ለመግባት ሄደ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ፣ ወደ ሳሎን በእርምጃ ተመለሰ። አስደሰች ፈገግታ ይታይበት ነበር። ወደእኛ ተራመደ እና በዝግታ እንዲህ አለ፣ “ሚልድረድ ብቻዋን ወደመንፈስ አለም ትደርሳለች ብዬ ሰግቼ ነበር። በግርግር ውስጥ የጠፋች ይመስላት ይሆናል ብዬ አሰብኩ።”

ከዛም እርሱ በደመቀ መልኩ እንዲህ አለ፣ “አሁን ፀልዬ ነበር። ሚልድረድ ሰላም እንደሆነች አውቃለሁ። እርሷን ለማግኘት እናቴ እዛ ነበረች።”

አያቴ፣ የልጇ ሚስት ስተደርስ እርሷን ለማግኘት እና ከእርሷ ጋር ለመደሰት እዚያ መሆኗን ለማረጋገጥ አጭር እግሮቿ ሲራመዱ፣ እያሰበ በፈገግታ ሲናገር አስታውሳለሁ።

አሁን፣ አባቴ የጠየቀበት እና ያንን ምቾት ያገኘበት አንዱ ምክንያት ከልጅነቱ ጀምሮ በእምነት በመፀለዩ ነበር። ምቾት እና መመሪያን ወደልቡ ለመስጠት የሚመጡትን መልሶች መቀበልን ተለማምዶ ነበር። የፀሎት ልምድ ከማኖሩም በተጨማሪ፣ ቅዱሳን መጽሐፍቶችን እና የህያው ነብያትን ቃላቶች ያውቅ ነበር። ስለዚህ የመንፈስ ሹክሹክታዎችን ያስተውል ነበር።

የመንፈስ አጋርነት ለእርሱ ከምቾት እና መመሪያም በላይ ነበር። በኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢአት ክፍያ አማካኝነት እርሱን ለውጦታል። ያንን መንፈስ ሁሌ ከእኛ ጋር እንዲሆን ያለውን ቃልኪዳን ስንቀበል፣ ከስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ለሆነው የዘለአለም ህይወት የሚያስፈልገውን ንፅህና አዳኝ ሊሰጠን ይችላል (ት. እና ቃ. 14:7 ተመልከቱ)።

የአዳኝን ቃላት ታስታውሳላችሁ፤ “እንግዲህ ትእዛዜ ይህች ናት፣ በምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ ንሰሃ ግቡ፣ እናም ወደ እኔ ኑ፣ እናም መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ትቀደሱ ዘንድ፤ በመጨረሻው ቀን በፊቴ ያለእንከን ትቆሙ ዘንድ በስሜ ተጠመቁ።” (3ኛ ኔፊ 27:20)።

እነዚያ ትእዛዛት ከጌታ ከሆኑት እነዚህ ቃልኪዳኖች ጋር አብረው ይመጣሉ፤

“እናም አሁን፣ እነሆ እንዲህ እላችኋለሁ፣ በፍትህ ለመስራት፣ በትህትና ለመጓዝ፣ በቅድስና ለመፍረድ ወደ መልካም በሚመራው መንፈስ ላይ እምነታችሁን አድርጉ፤ እናም ይሄ የእኔ መንፈስ ነው።

“እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ አእምሮአችሁን ከሚያበራው፣ መንፈሴን ለእናንተ አካፍላለሁ፣ ነብሳችሁንም በደስታ ይሞላል” (ት እና ቃ 11:12–13)።

አብ እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ፣ ትንሳኤን ያደረገው ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን እንደሚመራ፣ ቶማስ ኤስ ሞንሰን የክህነት ቁልፎችን ሁሉ እንደያዙ፣ እና ያ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እናም ትሁት አባሎቹን እንደሚመራ እና እንደሚደግፍ ምስክርነቴን አካፍላችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Handbook 2: Administering the Church (2010), 20.3.10።

  2. George Q. Cannon, in “Minutes of a Conference,” Millennial Star, May 2, 1863, 275–76 ተመልከቱ።