2010–2019 (እ.አ.አ)
በእግዚአብሔር አይኖች በኩል
ኦክተውበር 2015


በእግዚአብሔር አይኖች በኩል

ሌሎችን በውጤታማነት ለማገልገል፣ በወላጅ አይኖች በኩል፣ በሰማይ አባት አይኖች በኩል፣ ማየት ያስፈልገናል።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ትላንትና እኔን እንደ አስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል በመደገፋችሁ አመሰግናችኋለሁ። ይህ ምን ያህል ትርጉም እንዳለው ለመግለጽ ከባድ ነው። በህይወቴ ውስጥ ለሚገኙት ሁለት አስደናቂ ሴቶች፥ ባለቤቴ፣ ሩት፣ እና የእኛ ውድ፣ ውድ ሴት ልጅ፣ አሽሊ፣ ለሰጡኝ የድጋፍ ምርጫ ልዩ ምስጋና ይሰማኛል።

ጥሪዬ ጌታ በዚህ ዘመን መጀመሪያ ውስጥ ለተናገራቸው እውነትነት ብቁ መረጃ ይሰጣል። “የወንጌሌ ሙላት በደካሞች እና በተራ ሰዎች አማካይነት በነገስታት እና በገዢዎች ፊት እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ይታወጅ ዘንድ ተሰጥቷቸዋል።”1 እኔ ከእነዚህ ደካሞች እና ተራ ሰዎች አንዱ ነኝ። ከአስር አመቶች በፊት፣ በምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንደ ኤጲስ ቆጶስ ስጠራ፣ ከእኔ ትንሽ በእድሜ እና በጥበብ የሚበልጥ ወንድሜ በስልክ ደወለልኝ። እንዲህ አለ፣ “ጌታ የጠራህ አንተ ባደረግከው በማንኛውም ምክንያት እንዳልሆነ ማወቅ አለብህ። በአንተ በኩል፣ አነተ ያደረካቸው ምንም ሳይቆጠሩ ነው። ጌታ በአንተ አማካኝነት ለማድረግ ለሚፈልገው ነው የጠራህ፣ እናም ይህም የሚሆነው አንተ በእርሱ መንገድ ካደረግከው ብቻ ነው።” ከታላቅ ወንድሜ የመጣው ይህ ጥበብ ዛሬ ከሁሉም በላይ እንደሚሰራ አውቃለሁ።

በሚስዮን አገልግሎት ውስጥ እርሱ ወይም እርሷ ጥሪዋ ስለ እርሱ ወይም ስለእርሷ እንዳልሆነ፣ ግን ይህም ስለጌታ ስራ፣ እና ስለሰማይ አባት ልጆች እንደሆነ ሲረዳ ወይም ስትረዳ፣አስደናቂ ነገር ይደርሳል። እኔ ይህም ለሐዋርያ አንድ አይነት እንደሆነ ይሰማኛል። ይህ ጥሪ ስለእኔ አይደለም። ይህም ስለጌታ፣ እና ስለሰማይ አባት ልጆች ነው። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሀላፊነት ወይም ጥሪ ምንም ቢሆንም፣ በችሎታ ለማገልገል፣ የምናገለግላቸው ሰዎች በሙሉ “የሰማይ ወላጆች የተወደዱ የመንፈስ ሴት እና ወንድ ልጆች [እንደሆኑ]፣ እናም ይህ ስለሆነም፣ … መለኮታዊ ተፈጥሮ እና ፍጻሜም [እንዳላቸው”2 ማወቅ ያስፈልጋቸዋል።

በፊት በነበረኝ ስራዬ፣ በሽተኛዎቼ በጣም የታመሙ፣ በልብ መውደቅ እና መቀየር የሰለጠንኩኝ የልብ ዶክተር ነበርኩኝ። ባለቤቴ በቀልድ የእኔ ታካሚ መሆን የመጥፎ የህክምና አመለካከት ነው ትለኝ ነበር። ቀልዱን ወደ ጎን በማድረግ፣ ብዙ ሰዎች ሲሞቱ ተመልክቻለሁ፣ እናም ነገሮች መልካም አለመሆን ሲጀምሩ በስሜት መራቅ ለመጀመር ችሎታ አገኘሁ። በዚህ መንገድ፣ የሀዘን ስሜት እና ተስፋ መቁረጥን እቀንሳለሁ።

በ1986 (እ.አ.አ) ቻድ የሚባል ወጣት ልጅ ልቡ እየደከመ መጣ እናም ልቡን በቀዶ ጥገና ለመቀየር ቻለ።ለአስር አመት ከግማሽ በደንብ ይኖር ነበር። ቻድ ጤና ለመሆን የሚችለውን ሁሉ አደረገ እናም በሚችለው ያህል በመደበኛ ህይወት ኖረ። በሚስዮን አገለገለ፣ ሰራ፣ እናም ለወላጆቹ ታማኝ ልጅ ነበር። የህይወቱ መጨረሻ አመቶች ግን ፈተና የነበራቸው እናም በብዙ ጊዜ ወደ ሆስፒታል የሚገባና የሚወጣ ነበር።

አንድ ምሽት፣ ልቡ መስራት አቁማ ወደ አደጋ መረጃ ክፍል ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ነበር። ከእኔ ጋር አብረው የሚሰሩት እና እኔ የደም መሰራጫው እንዲሰራ ለማድረግ ለብዙ ጊዜ ሞከርን። በመጨረሻም፣ ቻድ እንደገና ሊነቃ እንደማይችል ግልጽ ሆነ። ውጤት የሌለውን ጥረታችንን አቆምን፣ እናም ሞቷል ብየ አሳወቅኩኝ። የሚያሳዝን እና ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢሆንም፣ የስራ ጸባዬን ቀጠልኩኝ። ለራሴም እንዲህ አሰብኩኝ፣ “ቻድ ጥሩ እንክብካቤ ነበረው። ሊያገኝ ከሚችለው ህይወት በላይ ነበር ለብዙ አመቶች ለመኖር የቻለው።” ወላጆቹ ወደ ሆስፒታሉ አደጋ መረጃ ክፍል ሲገቡ እና የሞተው ልጃቸው በመኝታው ላይ ተዘርግቶ ሲመለከቱት፣ ከስሜት ራሴን የማርቅበት መንገድ ተሰበረ። በዚያ ጊዜ፣ ቻድን በእናቱ እና በአባቱ አይኖች ተመለከትኩኝ። ለእርሱ የነበራቸውን ታላቅ ተስፋ እና ጥበቃ፣ ለትንሽ ተጨማሪ ጊዜ እና ለትንሽ የተሻለ ሁኔታ እንዲኖር የነበራቸውን ፍላጎች ተመለከትኩኝ። ይህን በመረዳት፣ ማልቀስ ጀመርኩኝ። ምጸታዊ በሆነ የሀላፊነት ቅያሬ እና በደግነት ስራ፣ የቻድ ወላጆች እንዴት እንዳፅናኑኝ አልረሳም።

አሁን በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በውጤታማነት ሌሎችን ለማገልገል በወላጅ፣ አይኖች፣ በሰማይ አባት አይኖች፣ በኩል መመልከት እንዳለብን ተረዳሁ። በዚህ ብቻ ነው እውነተኛው የነፍስ ዋጋ ምን እንደሆነ ለማወቅ የምንችለው። በዚህ ብቻ ነው የሰማይ አባት ለልጆቹ በሙሉ ያለውን ፍቅር ለመሰማት የምንችለው። በዚህ ብቻ ነው አዳኝ ለእነርሱ ያለውን የመንከባክብ ሀሳብ ለመሰማት የምንችለው። እነርሱን በእግዚአብሔር አይኖች በኩል ካላየን በስተቀር፣ ከሚያዝኑት ጋር ለማዘን እና መፅናናት የሚያስፈልጋቸውን ለማፅናናት ያለንን የቃል ኪዳን ሀላፊነት በሙሉ ለማሟላት አንችልም።3 ይህ የተዘረጋ አስተያየት ስለሌሎች ተስፋ መቁረጥ፣ ፍርሀት፣ እና የልብ መሰበር ልባችንን ይከፍታል። ነገር ግን፣ ልክ የቻድ ወላጆች እኔን ከብዙ አመቶች በፊት እንዳደረጉት፣ የሰማይ አባት እኛን ይረዳል እናም ያፅናናል። በፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ሁልጊዜ እንዲደረግ በሚያበረታቱት የማዳን ሀላፊነት ለማከናወን እንድንችል፣ የሚያዩ አይኖች፣ የሚሰሙ ጆሮዎች፣ እና የሚያውቅ እና የሚሰማው ልብ ያስፈልገናል።4

በሰማይ አባት አይኖች ስናይ ብቻ ነው “በክርስቶስ ንጹህ ፍቅር”5 ለመሞላት የምንችለው። በየቀኑም ከእግዚአብሔር ጋር ይህን ፍቅር ለማግኘት መለመን ይገባናል። ሞርሞን እንደገሰጸው፣ “ስለሆነም የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ሁሉ ላይ በሚያፈሰው በዚህ ፍቅር ትሞሉ ዘንድ በኃይል ከልባችሁ ወደ አብ ፀልዩ።”6

በልቤ በሙሉ የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታይ ለመሆን እፈልጋለሁ።7 እርሱንም አፈቅራለሁ። እርሱንም እወዳለሁ። ስለህያው እንነትነቱም እመሰክራለሁ እርሱ የተቀባው፣ መሲህ፣ እንደሆነም እመሰክራለሁ። መመዛዘን የማይቻለው ምህረት፣ ርህራሄ፣ እና ፍቅር ምስክሩም ነኝ። በ 2000 (እ.አ.አ)፡ሐዋሪያት “ኢየሱስ ህያው ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር የማይሞት ልጅ እንደሆነ። … እርሱ የአለም ብርሀን፣ ህይወት፣ እና ተስፋ”8እንደሆነ በመሰከሩበት ላይ የራሴንም ምስክር እጨምራለሁ።8

በ 1820 (እ.አ.አ) አንድ ቀን በኒው ዮርክ ጥሻ ውስጥ፣ ከሞት የተነሳው ጌታ፣ ከእግዚአብሔር የሰማይ አባታችን ጋር፣ ልክ ጆሴፍ ስሚዝ ነበር እንዳለው፣ ወደ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደመጡ እመሰክራለሁ። የክህነት ቁልፎች የሚያድኑ እና ከፍ የሚያደርጉ ስርዓቶችን ለማከናወን በምድር ላይ ዛሬ አሉ። ይህን አውቃለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥23

  2. “ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” Liahona፣ ህዳር 2010፣ 129፤ በፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ በመስከረም 23፣ 1995 (እ.አ.አ)፣ በሶልት ሌክ ከተማ፣ ዩታ ውስጥ እንደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባ ንግግራቸው ክፍል ያነበቡት።

  3. አብርሐም 18፥8–10ተመልከቱ።

  4. ለምሳሌ፣ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “To the Rescue,” Liahona፣ ሀምሌ 2001፣ 57–60፤ “Our Responsibility to Rescue፣” Liahona፣ ጥቅምት 2013፣ 4–5። ፕሬዘደንት ሞንሰን ይህን ሀሳብ በመስከረም 30፣ 2015 (እ.አ.አ)፣ ለአጠቃላይ ባለስልጣኖች በሰጡት መልእክት ውስጥ፣ በሚያዝያ 2009 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ አጠቃላይ ባለስልጣኖችን እና የክልል ሰባዎችን በሚያሰለጥኑበት ጊዜ የሰጡትን መልእክት ለተሰበሰቡት በትኩረት እንዲያስታውሱ ለማድረግ ነው።

  5. ሞሮኒ 7፥47

  6. ሞሮኒ 7፥48

  7. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18:27–28ተመልከቱ፥

    “እናም አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርቴ ይሆናሉ፣ እናም በላያቸው ላይ ስሜን ይወስዳሉ፤ እናም አስራ ሁለቱም ዓላማ በተሞላ ልብ ስሜን በላያቸው ለመውሰድ ፈቃድ ያላቸው ናቸው።

    “እናም አላማ በተሞላ ልብ ስሜን በላያቸው ላይ ሊወስዱ ፈቃድ ካላቸው፣ ወደ አለም ሁሉ በመሄድ ወንጌሌን ለፍጥረታት ሁሉ ለማወጅ ተጠርተዋል።”

  8. “ህያው ክርስቶስ፥ የሐዋሪያት ምስክርነት፣” Liahona፣ ሚያዝያ 2000፣ 3። ይህን በዚህ በመጥቀስ፣ በዚህ መረጃ ላይ፣ በእነዚያ ሐዋሪያት የተሰጠውን ያን አንድ አይነት ምስክርነት ምስክርብ በመስጠት፣ በምስል ፊርማዬን መጨመሬ ነው።