2010–2019 (እ.አ.አ)
ለምን ቤተክርስቲያኗ
ኦክተውበር 2015


ለምን ቤተክርስቲያኗ

የአባቱን ስራ ለመፈጸም የራሱን ቤተክርስቲያን፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን፣ ለምን እንደመረጠ ቆም ብሎ ማሰብ አስፈላጊ ነው።

በህይወቴ በሙሉ፣ አጠቃላይ ጉባኤ በጣም የሚያስደስት መንፈሳዊ ክንውን ነበር፣ እና ቤተክርስቲያኗም ጌታን ለማወቅ የሚኬድባት ቦታ ነበረች። ራሳቸውን ሀይማኖታዊ ወይም መንፈሳዊ እንደሆኑ የሚያምኑ ሰዎች እንዳሉ እና በቤተክርስቲያን መሳተፍን እና እንዲሁም የእንደዚህ አይነት ድርጅቶችን አስፈላጊነት የሚክዱ እንዳሉ እረዳለሁ። የሀይማኖት ልምምድ ለእነርሱ የግል ምርጫ ነው። ነገር ግን ቤተክርስቲያን የመንፈሳዊነታችን ማእከል የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ፍጥረት ነው። የሰውን ሟች አለመሆን እና ዘለአለማዊነት ለማምጣት የሆነውን የእርሱን እና የአባቱን ስራ ለመፈጸም ቤተክርስቲያንን፣ የራሱን ቤተክርስቲያን፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣እርሱ ለምን እንደመረጠ ቆም ብሎ ማሰብ አስፈላጊ ነው።1

ከአዳም ጀምሮ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ተሰብኮ ነበር፣ እናም እንደ ጥምቀት አይነት የደህንነት አስፈላጊ ስርዓቶች በአባቶች አለቃ ክህነት ስራአት በኩል ይከናወኑ ነበር።2 ህብረተሰቦች ከዘመዶች በላይ ውስብስብ እየሆኑ ሲመጡ፣ እግዚአብሔር ሌሎች ነቢያት፣ መልእክተኞች፣ እና አስተማሪዎች ጠራ። በሙሴ ዘመን ሽማግሌዎችን፣ ካህናት፣ እና ዳኛዎችን ስለሚጨምር መደበኛ ድርጅት እናነብ ነበር። በመፅሐፈ ሞርሞን ታሪክ ውስጥ፣ አልማ ቤተክርስቲያን ከካህናት እና አስተማሪዎች ጋር መሰረተ።

ከዚያም በዘመን ማካከል ውስጥ፣ ኢየሱስ ወንጌል በብዙ ሀገሮች እና በተለያዩ ህዝቦች መካከልየሚመሰረትበት መንገድ ስራውን አደራጀ። ይህች የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው “በሀዋሪያት እና ነቢያት፣ ኢየሱስ ክርስቶች ራሱ የማዕዘን አለት ሆኖ” ተመሰረተች።3 ይህችም እንደ ሰባዎች፣ሽማግሌዎች፣ ኤጲስ ቆጶሶች፣ ካህናት፣ አስተማሪዎች፣ እና ዲያቆኖች አይነት ተጨማሪ ሀላፊዎች ነበሯት። ኢየሱስ ከትንሳኤው በኋላ እንደዚህም በምዕራብ የአለም ግማሽ ውስጥ ቤተክርስቲያኑን መሰረተ።

በምድር ላይ እያለ ያደራጃት ቤተክርስቲያ ከወደቀች እና ከተሰባበረች በኋላ፣ ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ለሁለተኛ እና ለመጨረሻ ጊዜ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል መሰረተ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምስራችን መስበክ እና የደህንነት ስርዓቶችን ማከናወ፣ በሌላም አባባል፣ ህዝቦችን ወደ ክርስቶስ ማምጣት እና ይህም በሙሉ ያለው ትርጉም፣ የሆነው የጥንት አላማ አሁንም አለ።4 አሁን በዚህች በዳግም በተመለሰችው ቤተክራቲያን መሳሪያነት፣ የቤዛነት ቃል ኪዳን፣ እንዲሁም በስጋዊ ህይወታቸው ስለአዳኝ ጸጋ ምንም አያውቁ ለነበሩት መንፈሳት ሁሉ፣ የሚደረስባት ነች።

ቤተክርስቲያኑ የጌታን አላማ እንዴት ታከናውናለች? የእግዚአብሔር ዋና እቅድ የእኛ እድገት እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ፍላጎቶቹ እርሱ የሚሰጠውን በሙሉ “[እስከምንቀበል] ከጸጋ ወደ ጸጋ”5 እንድንቀጥል ነው። ያም ጥሩ ወይም መንፈሳዊ ከመሆን በላይ የሚያስፈልግ ነው። ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት፣ ንስሀ መግባት፣ በውሀና በመንፈስ መጠመቅ፣ እና እስከመጨረሻ በእምነት መጽናት የሚያስፈልግ ነው።6 ይህን ለብቻ ለማድረግ የሚችሉ ትንሽ፣ ምናልባት ማንም የሉም፣ እና የሚችሉ ከሆኑም የምንቀረውል መርዳት ያስፈልጋቸውል። ሰው ይህን አይነት መለየት በሙሉ ለማግኘት አይችልም። ስለዚህ ጌታ ቤተክርስቲያን የሰራበት ዋናው አላማ “ወደ ዘለአለም ህይወት በሚመራው በቀጥተኛ እና በጠበበ ጎዳና”7 እርስ በራስ የሚደጋገፉ የቅዱሳን ህብረተሰብ ለመፍጠር ነው።

“[ክርስቶስም] አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤

“…ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።”

“ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፣ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ።”8

ኢየሱስ ክርስቶስ “[የእምነታችን] ጸሀፊ እና ፈጻሚ” ነው።9 ራሳችንን ከክርስቶስ ሰውነት–ቤተክርስቲያኗ– ጋር አንድ ማድረግ በራሳችን ላይ ስሙን የመውሰድ አስፈላጊ ክፍል ነው።10 የጥንት ቤተክርስቲያን “...ለመፆም እናም ለመፀለይ፣...ሁል ጊዜ በቤተክርስቲያን [እንደሚገኙ]”11 “እና የጌታን ድምጽ ለመስማት”12 እንደሚገናኙ ተነግረናል። ስለዚህ ዛሬም በቤተክርስቲያኗ እንዲህ ነው። በእምነት አንድ በመሆን፣ እርስ በራስ እናስተምራለን እናም እንሻሻላለን እናም የደቀ መዛሙርትነትን ሙሉ ሚዛን፣ “ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ሚዛን ፍጹማን”13 ሆኖ ለመቅረብ እንጥራለን። “እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን። እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር”14 የተባለው እስኪደርስ ድረስ፣ እርስ በራስ ለመረዳዳት፣ ጌታን ለማወቅ፣

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስለመለኮታዊ ትምህርት ብቻ አይደለም የምንማረው፤ የዚህን ጥቅምም እንለማመዳለን። እንደ ክርስቶስ ሰውነት፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት እርስ በራስ ስለ ቀን በቀን ህይወት እውንታ ልመማር ይረዳዳሉ። ሁላችንም ፍጹም አይደለንም፤ እናስከፋለን እናም እንከፋለን። በብዙ ጊዜ በልዩ ጸባዮቻችን እርስ በራስ እንፈታተናለን። አንዳንዴ እግዚአብሔር በእያንዳንዱ አውራጃ እና ቅርንጫፍ ልዩ የጸባይ ሁኔታቸው የሌሎችን ሁሉ ትዕግስት የሚፈትን አንዳንድ አባላት ያስገባ እንደሆነ ይመስላል። በክርስቶስ ሰውነት ውስጥ፣ ከግንዛቤ እና ከከፍተኛ ቃላት በላይ መማር ያስገልገናል እናም “በፍቅር አብረን ለመኖር”15 ስንማር እውነተኛ የሆነ የግል ልምምድ እንዲኖረን ያስፈልገናል።

ይህ ሀይማኖት ስለራስ ብቻ የሚያስብ አይደለም፤ ሁላችንም ለማገልገል የተጠራን ነን። የሰውነት አይኖች፣ እጆች፣ ራስ፣ እግሮች፣ እና ሌሎች ብልቶች ነን፣ እንዲሁም “ደካሞች የሚመስሉ የአካል ብልቶች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው።”16 እነዚህን ጥሪዎች ያስፈልጉናል፣ እናም ማገልገልም ያስፈልገናል።

በአውራጃችን ከሚገኙ ሰዎች አንዱ ያለወላጆች ድጋፍ በማጣት ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ተሳትፎው የወላጆች ተቃውሞ ባለበት ነበር ያደገው። ይህን አስተያየት በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ አድርጎ ነበር፥ “አባቴ በበረዶ መንሸራተት እየተቻለ ለምን ሰው ወደቤተክርስቲያን እንደሚሄድ አይገባውም ነበር፣ ነገር ግን እኔ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ እወዳለሁ። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ ሁላችንም በአንድ ጉዞ ላይ ነን፣ እናም በዚህ ጉዞ በጠንካራ ወጣቶች፣ በንጹህ ልጆች፣ እና ከሌሎች ጎልማሶች ከምሰማቸው እና ከምማራቸው ነገሮች እነሳሳለሁ። በመግባባት እጠነክራለሁ እናም ወንጌልን በመኖር እደሰታለሁ።”

በዚህም ጊዜ፣ የቤተክርስቲያኗ አውራጃዎች እና ቅርንጫፎች የየሳምንቱ ማረፊያ እና ማሳደሻ፣ አለምን ትተን የምንሄድበት እና የምንገባበት ቦታ–ሰንበትን ይሰጡናል። ከቅዱስ ቁርባን ጋር የሚመጣውን መፈወስ የምንለማመድበ “በእግዚአብሔር ደስ”17 የምትልበት፣ እና መንፈሱ ከእኛ ጋር እንዲሆን አዳሽ ቃል ኪዳን የምንቀበልበት ቀን ነው።18

የክልስቶስ አካል ክፍል የመሆን ታላቅ ከሆኑት በረከቶች ሁሉ አንዱ፣ በጊዜው በረከት እንደሆነማይመስልም፣ በኃጢያት እና በስህተት መገሰጽ ነው። ምክንያት ለመስጠት እና ስህተታችንን እንደ ትክክል ለመመልከት ደካማ ነን፣ እናም አንዳንዴ የት ለመሻሻል ወይም እንዲት ለማድረግ አናውቅም እንላለን። “በመንፈስ ቅዱስ በሚነሳሱበት ጊዜ፣ በሀይል”19 የሚገስጹን ከሌሉ፣ ለመቀየር እና መምህርን በፍጹምነት ለመከተል ብርታት አይኖረንም። ንስሀ መግባት ግላዊ ነው፣ ነገር ግን በዚያ አንዳንዴ በሚጎዳው ጉዞ ውስጥ ጓደኝነት የሚገኘው በቤተክርስቲያኗ ነው።20

በዚህ ቤተክርስቲያኗን እንደ ክርስቶስ አካል በምንወያይበት ጊዜ፣ ሁለት ነገሮች ሁልጊዜም ማስታወስ አለብን። አንድ፣ ለመቀየር የምንጥረው ወደ ቤተክርስቲያኗ ሳይሆን ወደ ክርስቶስ እና ወንጌሉ ነው፣ ይህም ቅያሬ በቤተክርስቲያኗ የሚደገፍ ነው።21 መፅሐፈ ሞርሞን ይህንንም ህዝቡ “ወደ ጌታ ተለወጡ ፣ እናም ከክርስቶስ ቤተክርስቲያንም ጋር ተቀላቀሉ22 በማለት ይገልፃል።ሁለተኛ፣ በመጀመሪያ ቤተክርስቲያኗ ቤተሰብ እንደነበረች፣ እናም አሁንም እንደ ተለያዩ ድርጅቶች፣ ቤተሰብ እና ቤተክርስቲያኗ እርስ በራስ እንደሚያገለግሉ እና እንደሚጠነካከሩ ማስታወስ አለብን። ማንኛዎቹም ከሌላም በላይ አይደሉም፣ እናም በእርግጥ ቤተክርስቲያኗ፣ ከሁሉም በሚሻለው ጊዜዋም፣ ወላጆችን ለመወከል አትችልም። በቤተክርስቲያኗ የወንጌል ትምህርት የማስተማር እና የክህነት ስርዓት የመከናወን አላማ ቤተሰቦች ለኧለአለም ህይወት ብቁ እንዲሆኑ ነው።

አዳኝ በቤተክርስቲያን፣ በቤተክርስቲያኑ፣ በኩል የሚሰራበት ሁለተኛ ታላቅ ምክንያት አለ፣ እና ያም በግለሰቦች ወይም በትንሽ ቡድኖች ለመከናወን የማይችሉ አስፈላጊ ነገሮችን ለመፈጸም ነው። አንዱ ግልጽ ምሳሌም ድህነትን መቋቋም ነው። እንደ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች የሌሎችን ስጋዊ ፍላጎት ለማሟላት ፣ “በፍላጎታቸውና ፈቃዳቸው ያላቸውን በመካፈል”23 መጣራችን እውነት ነው። ነገር ግን በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በአንድነት፣ ደሆችን እና እርዳታ የሚፈልጉትን የሰፋ ፍላጎቶችን ለማሟላት የመንከባከብ ችሎታ ይበዛል፣ እና ልብዙዎችም ራስን የመርዳት ተስፋ እውነት ይሆናል።24 በተጨማሪም፣ ቤተክርስቲያኗ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበሮቿ፣ እና የክህነት ቡድኖቿ በብዙ ቦታዎች በመአት፣ በጦርነት፣ እና በመሳደድ የሚሰቃዩትን እረፍት እንዲያገኙ ይረዳሉ።

ያለዚህ የእርሱ ቤተክርስቲያን ችሎታዎች፣ ወንጌልን ለአለም ሁሉ ለመውሰድ የሰጠው ሀላፊነት አይሟላም።25 የሐዋርያት ቁልፎች፣ ድርጅት፣ ቴክኖሎጂ፣ ብዙ ሚልዮን ብሮች፣ እናየብዙ መቶ ሺህ ሚስዮኖች አምልኮና መስዋዕት አይኖርም። አስታውሱ፣ “ይህ የመንግስቱ ወንጌል በአለም በሙሉ፣ ለአህዛብ ሁሉ ምስክርነት፣ መሰበክ [አለብት]፣ እና ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።”26

ቤተክርስቲያኗ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች የሚከናወኑባቸው ቤተመቅደሶችን፣ የጌታን ቤቶች፣ መገንባት እና ማስተዳደር ትችላለች። ጆሴፍ ስሚዝ እንዳለው እግዚአብሔር ህዝቡን በማንኛውም ዘመን የሚሰበስብበት ምክንያት “እርሱ ለህዝቡ የቤቱን ስርዓቶች እና የመንግስቱን ክብሮች ለህዝቡ ለመግለጽ የሚችልበት፣ እና ህዝብን የደህንነት መንገድን የሚያስተምርበት ቤት ለጌታ እንዲገነቡ ነው፤ ምክንያቱም አንዳንድ ስርዓቶች እና መሰረታዊ መርሆች፣ ሲማሩ እና ሲጠቀሙበት፣ ለዚህ አላም በተሰሩ ቦታዎች ወይም ቤቶች ውስጥ መከናወን አለባቸው።”27

አንድ ሰው ሁሉም መንገዶች ወደ ሰማይ ያመራሉ ወይም ለደህንነት ምንም አስቀድሞ የሚያስፈልግ ነገር የለም ብሎ የሚያምን ከሆነ፣ እርሱ ወይም እርሷ ወንጌልን ለመስበክ ወይም ህያውን ወይም ሙታንን የሚያድን ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች አስፈላጊነት አይታየውም ወይም አይታያትም። ነገር ግን ሟች ስለአለመሆን ብቻ ሳይሆን፣ ግን ስለዘለአለም ህይወት ነው የምንናገረው፣ እና ለዚህም የወንጌል መንገድ እና የወንጌል ቃል ኪዳን አስፈላጊ ነው። እናም አዳኝ እነዚህን ለእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ፣ ለህያው እና ለሙታን፣ እንዲገኙ ለማድረግ ቤተክርስቲያን ያስፈልገዋል።

ጌታ ቤተክርስቲያኑን ከመስረተበት ከምጠቁማቸው ምክንያቶች የመጨረሻው በጣም ልዩ ነው–ቤተክርስቲያኗ በምድር ላይ የእግዚአብሔር መንግስት ናት።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በ1830 (እ.አ.አ) በተመሰረተችበት ጊዜ፣ ጌታ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ አለ፣ “ልባችሁን ከፍ አድርጉ እና ተደሰቱ፣ ለእናንተ መንግስት፣ ወይም በሌላ አባባል፣ የቤተክርስቲያኗ ቁልፎች ተሰጥተዋለና።”28 በእነዚህ ቁልፎች ስልጣን የአዳኝ ወንጌልን ለመስበክ እና የማዳን ስርዓቶችን የማከናወን ስልጣንን የያዙ ናቸው።29 የቤተክርስቲያኗ የክህነት ሀላፊዎች የትምህርትን ንፁህነት እና የስርዓቶችን ፅኑ አቋም ይጠብቃሉ። እነዚህን ለመቀበል የሚፈልጉትን ለማዘጋጀት ይረዳሉ፣ የአመልካቾች ብቁነትን ላይ ይፈርዳሉ፣ እናም እነዚህንም ያከናውኗቸዋል።

በመንግስቱ ቁልፎች፣ የጌታ አገልጋዮች እውነትን እና ውሸትን ለመለየት፣ እና እንደገናም በስልጣን “ጌታ እንዲህ አለ” ለማለት ይችላሉ። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ አንዳንድ የራሳቸውን እውነት ለመተርጎም ስለሚፈልጉ በቤተክርስቲያኗ ይናደዳሉ፣ ነገር ግን በእውነትም ጌታ ይህን ለመግለጽ ፈቃደኛ እስከሆነ ድረስ “ነገሮች እንዳሉ፣ እና እንደነበሩ፣ እና እንደሚሆኑ እውቀትን”30 ማግኘት ታላቅ በረከት ነው።

የባቢሎን ንጉስን ናቡከደነፆር ህልምን ለንጉሱ “በኋለኛው ዘመን የሚሆነውን”31 በሚገልጽበት ጊዜ፣ እንዲህ አወጀ፣ “በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል፤ ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል፤ [ሌሎች] መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፥ ለዘላለምም ትቆማለች።”32 ቤተክርስቲያኗ የተተነበየችው በሰው ሳትፈጠር በሰማይ እግዚአብሔር ተመስርታ እና አለምን ለሞምላት እጅ ሳይነካው ከተራራ እንደተፈነቀለ ድንጋይ የምትንከባለለው የኋለኛው ቀን መንግስት ነች።33

እጣ ፈንታዋውም ለኢየሱስ ክርስቶስ መመለስ እና ለአንድ ሺህ አመት መምራት ፅዮንን ለማዘጋጀት ነው። ከዚያ ቀን በፊት፣ ይህም በፖለቲካ ህኔታ መንግስት አይደለችም–አዳኝ እንዳለው፣ “መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም።”34 እርሷም በምድር ላይ የስልጣኑ ማሳረፊያ፣ የቅዱስ ቃል ኪዳኖቹ አስተዳዳሪ፣ የቤተክርስቲያኑኦቹ ጠባቂ፣ የእውነቱ ጠባቂና አዋጅ፣ የተበተነችው እስራኤል መሰብሰቢያ ቦታ፣ እና “መከላከያ፣ እናም…ከአውሎ ንፋስ፣ እናም በምድር ሙሉ ላይ ሳይቀላቀል ቁጣ ከሚፈስበት፣ መሰደጃ” ነች።35

በነቢይ ተማፅኖ እና ጸሎት እፈጽማለሁ፥

“በዚህ ኗሪዎችዎም እንዲቀበሉት፣ መንግስቱም በምድር ላይ እንዲሄድ፣ ጌታን ጥሩ፣ እናም የሰው ልጅ የክብሩን ብርሀን ለብሶ ከሰማይ በምድር ከተሰራችው የእግዚአብሔር መንግስት ጋር ለመገናኘት በሚገለጥበት ወደ ፊት ለሚመጡት ቀናትም ተዘጋጁ።

ስለዚህ፣ መንግስተ ሰማያት እንድትመጣ፣ የእግዚአብሔር መንግስት ወደ ፊት ይሂድ፣ አንተም፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ በሰማይም እንደከበርህ እንዲሁ በምድርም ትከበር ዘንድ፣ ጠላቶችህም ይዋረዱ ዘንድ፤ ክብርም፣ ኃይልም፣ እና ግርማም የአንተ ናትና፣ ከዘለአለም እስከዘለዓለም።”36

በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።