2010–2019 (እ.አ.አ)
የሰላም ንድፍ
ኤፕረል 2016


የሰላም ንድፍ

ሁላችንም የምንፈልገው ሰላም ስለኢየሱስ ክርስቶች በመማር፣ ቃላቱን ለማዳመጥ፣ እና ከእርሱ ጋር በመራመድ እንድንሰራ ይፈልገናል።

ከጥቂት አመታት በፊት፣ ሴት ልጃችን እና ባለቤቷ አብረው አምስት ቀልጣፋ የአራት አመት ትትንሽ ወንድ ልጆችን በመጀመሪያ ክፍል እንዲያስተምሩ ተጠይቀው ነበር። ሴት ልጃችን እንድታስተምር የተመደበች እና ባለቤቷ ጸባያቸውን እንዲያስተካከሉ የሚከታተል ነበሩ፣ እናም ለልጆቹ የወንጌል መሰረቶችን ለማስተማር በአንዳንድ ብጥብጥ መካከል ጸጥተኛነትን ለማስገኘት በደንብ ጣሩ።

በአንድ አስቸጋሪ በሆነ ክፍል ጊዜ፣ በሀይል ለተሞላ ልጅ የተደጋገሙ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ በኋላ፣ አማቻችን የአራት አመት ልጅን ከክፍል አውጥቶ ወሰደ። ከክፍሉ ከወጡ በኋላ፣ እና ስለጸባዩ እና ከወላጆቹ ጋር ስለመነጋገር ከትንሽ ልጅ ጋር ሊነጋገር ሲል፣ ትንሹ ልጅ አማቻችንን አንድ ቃል ከመናገር በፊት አስቆመው እና፣ እጆቹን ወደ ላይ ከፍ አድርጎ እና በታላቅ ስሜት፣ እንዲህ አለ፣ “አንዳንዴ ስለኢየሱስ ለማሰብ ያስቸግረኛል!”

በሟችነ ጉዞአችን ውስጥ፣ ምንም የወደፊት የምንደርስበት ምንም ግርማዊ የሆነ እናም ጎዞው በጣም አስደሳች የሆነ ቢሆንም፣ በመንገዱም በፈተናዎች እና ስቃዮች የምንጋፈጥ ነን። ሽማግሌ ጆሴፍ ቢ. ዎርዝልን እንዳስተማሩት፥ “የሀዘን ማጠቆሚያ በመጨረሻም በእኛ ላይ ይጠቁማል። በአንድ ወይም በሌላ ህዜ፣ እያንዳንዳችን ሀዘን ያጋጥመናል። ማንም በዚህ ከሀላፊነት ውጪ አይደለም።”1 “ጌታ በጥበቡ መሰረት ማንንም ከሀዝን አይሸፍንም።”2 ይህን መንገድ ሰላም መጓዛችን ወይም አለመጓዛችንን፣ በአብዛኛው ጊዜ፣ በክፍል የሚወስነው ስለኢየሱስ ለማሰብ አስቸጋሪ ጊዜ እንዳለን ወይም እንደሌለን ነው።

የአዕምሮ ሰላም፣ የህሊና ሰላም፣ እና የልብ ሰላም የሚወሰኑት ፈተናዎችን፣ ሀዘኖችን፣ እና የልብ ህመሞችን ለማስወገድ በምናደርግበት ችሎታችን አይደለም። ቅን ልመና ቢኖረንም፣ ማንኛውም አይነት አውሎ ንፋስ መንገድ አይቀየርም፣ ማንኛውም አይነት ህመም አይፈወስም፣ እናም በነቢያት፣ ባለራዕዮች፣ እና ገ፤አጮም የምንማራቸውን ሁሉንም ትምህርት፣ መሰረታዊ መርሆ፣ ወይም ድርጊት በሙሉ ለምረዳት አንችልም ይሆናል። ምንም ቢሆን፣ የተያያዘ ነገር ያለው ሰላም ቃል ተገብቶልናል።

በዮሀንስ ወንጌል ውስጥ፣ አዳኝ እንዳስተማረው፣ በህይወት ፈተናዎች ቦኖሩም፣ ደስተኛ ለመሆን እንችላለን፣ ተስፋ ሊነርን እንችላለን፣ እናም ምንም ፍርሀት አያስፈልገንም፣ ምክንያቱም እርሱ እንዳወጀም፣ “በእኔ ሰላም ይኖራችኋል።”3 በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጥያት ክፍያ መስዋዕቱ ማመን፣ አሁን እናም ለዘለአለም የወንጌል የመጀመሪያው ምሰረታዊ መርሆ እና “በዚህ አለም ውስጥ ሰላም፣ እና በሚመጣው አለም የዘለአለም ህይወት” ለማግኘት ያለን ተስፋ የተመሰረተበት ነው።4

በየቀኑ የህይወት ፈተናዎች መካከል ሰላም በምንፈልግበት ውስጥ እንዲረዳን፣ ሀሳባችን እንዲህ ባለው በአዳኝ ላይ የምናተኩርበት ቀላል የሆነ ንድፍ ተሰጥቶናል፥ “ከእኔ ተማር፣ እናም ቃላቴን አድምጥ፤ በመንፈሴ በትህትና ተጓዝ፣ እናም በእኔ ሰላምን ታገኛለህ። እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ።”5

ተማሩ፣ አዳምጡ፣ እናም ተራመዱ -- የተስፋ ቃል ያላቸው ሶስት ደረጃዎች

የመጀመሪያው እርምጃ፥ “ከእኔ ተማሩ”

በኢሳይያስ እንዲህ እናነባለን፣ “ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፣ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ።”6

ምድርን በሚሸፍኗት ቁጥራቸው በሚጨምሩት ቤተመቅደሶች ውስጥ፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና እንደዚህች አለም ፈጣሪ፣ እንደ አዳኝና ቤዛ፣ እና እንደ ሰላማችን ምንጭ፣ በአብ እቅድ ውስጥ ስላለው ሀላፊነት እንማራለን።

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንደገለጹት፥ “ይህ አለም የሚፈትን እና ለመኖር አስቸጋሪ ቦታ ሊሆን ይችላል። … እናንተ እና እኔ ወደ እግዚአብሔር ቅዱስ ቤቶች ስንሄድ፣ በውስጣቸው የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ስናስታውስ፣ እያንዳንዱን ችግር ለመቋቋም እና እያንዳንዱን ፈተናዎች ለማሸነፍ ተጨማሪ ችሎታ ይኖረናል። በዚህ ቅዱስ መሸሸጊያ፣ ሰላም እናገኛለን።”7

ከትንሽ አመት በፊት በደቡብ አሜሪካ በማገለግልበት በካስማ ጉባኤ ውስጥ፣ በህጻን ልጃቸው ሞት በማዘን ላይ ያሉ ወላጆች ጋር ተገናኘሁ።

በጉባኤው የቃል ጥያቄ ጊዜ ነበር ወንድም ቱሚር ጋር የተገናኘሁት እና ስላጣውም የተማርኩት። ስንነጋገር፣ በልጁ ሞት ምክንያት ከማዘኑ በተጨማሪ እርሱን እንደገና ለማየት በማይችልበት ሀሳብ በጣም አዝኖ ነበር። እንደ ቤተክርስቲያኗ አዲስ አባል፣ ትንሽ ወንድ ልጁ ከመወለዱ በፊት ወደ ቤተመቅደስ አንድ ጊዜ ለመሄድ ገንዘብ አጠራቅመው ነበረ እናም እንደ ባልና ሚስት ከልጆቻቸው ጋር ተሳስረው እንደነበር ገለጸ። ወደ ቤተመቅደስ ለመመለስ ገንዘ እያጠራቀሙ እንደነበሩ ነገር ግን ከወንዱ ልጃቸው ጋር ለመተሳሰር እንዲችሉ እርሱን ገና ለመውሰድ ችለው እንዳልነበርም ገለጸ።

ያልተረዳበት እንዳለ በማወቅ፣ በታማኝነት ከቀጠለ ልጁን እንደገና እንደሚያየው ገለፅኩለት፣ ምክንያቱም ከባለቤቱ እና ከሴትልጆቹ ጋር ያስተሳሰረው ስርዓት ልጁንም ከእነርሱ ጋር ለማስተሳሰር ብቁ ነበር፣ እርሱም የተወለደው በቃል ኪዳን ስር ነበርና።

በመገረም፣ ይህ እውነት እንደሆነ ጠየቀ፣ እናም ይህ እውነት እንደሆነ ሳረጋግጥለት፣ ከልጁ ሞት ባለፉት ሁለት ሳምንት ለመፅናናት ያልቻለቸውን ባለቤቱን ለመነጋገር ፈቃደኛ እንደሆንኩኝ ጠየቀኝ።

በእሁድ ከሰዓት በኋላ፣ ክጉባኤው በኋላ፣ ከእህት ቱሚሪ ጋር ተገናኘኁ እናም ይህን ግርማዊ ትምህርት ለእርሷም ገለጽኩኝ። ያጣችውን አዲስ ነበር፣ ግን ተስፋ እየታያት፣ በእምባ እንዲህ ጠየቀች፣ “ትንሹን ልጄን በእውነት እንደገና ላቅፈው እችላለሁን? እርሱ በእውነት ለዘለአለም የእኔ ነው?” ቃል ኪዳኗን ከጠበቀች፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣን ውጤታማ የሆነው በቤተመቅደስ ውስጥ የሚገኘው የመተሳሰር ሀይል በእርግጥም ከልጇ ጋር እንድትሆን እነ እንድታቅፈውም እንደሚያስችላት አረጋገጥኩላት።

እህት ቱሚሪ፣ በወንድ ልጇ ሞት ልቧ የተሰበረ ብትሆነ፣ በአዳኛችን እንዲሆነ በተደረገው የቤተመቅደስ ቅዱስ ስርዓቶች ምክንያት በምስጋና እምባዎች እና በሰላም ተሞልታ ከስብሰባችን ወጣት።

ወደቤተመቅደስ በምንሄድበት ጊዜ በሙሉ—በምንሰማቸው፣ በምናደርጋቸው በሙሉ፤ በምንሳተፍባቸው ሰዓቶች በሙሉ፣ እና በምገባባቸው ቃል ኪዳኖች በሙሉ—ወደ ክርስቶስ እንጠቆማለን። ቅላቱን ስንሰማ እና ከምሳሌው ስንማር ሰላም ይሰማናል። ፕሬዘደንት ሒንክሊ እንዳስተማሩት፣ “ወደጌታ ቤት ሂዱ እና በዚያም መንፈሱን ይሰማችሁ እናም ከእርሱ ጋር ተገናኙ፣ እናም በምንም ቦታ የማታገኙት ሰላም ታውቁታላችሁና።”8

ሀለተኛው ደረጃ፥ “ቃላቴን አድምጡ”

“ይፈጸማል፣ በእኔ ድምጽ ሆነ በአገልጋዮቼ ድምጽ፣ ያም አንድ ነው።”9 ከአዳም ቀናት እስከ አህን ነብያችን፣ ቶማስ ኤስ ሞንሰን፣ ድረስ ጌታ በእርሱ ስልጣን በተሰጣቸው ወኪሉ በኩል ተናግሯል። በነቢያቱ በኩል የተሰጡትን የጌታን ቃላት ለማድመጥ እና ለመከተል የመረጡት ደህንነትና ሰላምን ያገኛሉ።

በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የነቢያትን ምክሮች የመከተል እና ከነቢያት ጋር አብሮ መቆም አስፈላጊነት፣ በተጨማሪም በ1 ኔፊ ምዕራፍ 8 ውስጥ የሚገኘው የሌሂ የህይወት ዛር ራዕይ፣ ጋር ብዙ ምሳሌዎች አሉ። ታልቁ እና ሰፊው ህንጻ በቀናችን እንደሆኑት እንደዚህ ብዙ ሰዎች ያለበት ወይም ከተከፈቱ መስኮቶቹ የሚመጡት ድምጾች እንደዚህ የተሳሳቱ፣ የሚያሳለቁ፣ እና የሚያምታቱ አልነበሩም። በዚህ ጥቅሰትም ስለሁለት ቡድኖች ኣ ከህንጻው ለሚመጡት ጩኸቶች መልሳቸው ምን እንደነበር እናነባለን።

ምስል
የሌሂ ህልም

ቁጥር 26 ጀምረን፣ እንዲህ እናነባለን፥

“እኔም ደግሞ አይኖቼን በዙሪያው ጣልኩኝ፣ እና ከውሃው ወንዝ ባሻገር፣ ትልቅና ሰፊ ህንፃን ተመለከትኩ። …

“…[በ]ሰዎች ተሞልቶ ነበር፣ … ፍሬውንም መጥተው ወደበሉት ላይ እጃቸውን እየጠቆሙና እየተሳለቁባቸው ነበር።

“በእነዚያ በሚያላገጡባቸውም ምክንያት፣ ፍሬውን ከቀመሱ በኋላ አፈሩ፤ ወደተከለከለውም መንገድ ገቡና ጠፉ።”10

ቁጥር 33 ከህንጻው፡ለሚመጣው ማሾፊያ እና መሳለቂያ የተለየ መልስ ያላቸውን እናነባለን። በህንጻው ውስጥ ያሉት “ፍሬውን ይካፈሉ በነበሩት ላይ ደግሞ የፌዝ ጣታቸውን ይጠቁሙ ነበር፤ ነገር ግን እኛ አላደመጥናቸውም።”11

ካፈሩት እና ከወደቁት፣ እና ከጠፉት እና ከህንጻው የሚመጣውን መሳለቂያ ችላ ካሉት እና ከነቢዩ ጋር ከቆሙት ጋር መካከል ባሉት መካከል ያለው ቁልፍ ልዩነት ሁለት ሀረጎች ናቸው፥ መጀመሪያ፣ “እነርሱ ቀመሱ” እና ሁለተኛ፣ “እነርሱ ተመገቡ።

የመጀመሪያው ቡድን ወደ ዛፉ ሲደርሱ፣ ለግዜ ከነቢዩ ጋር ቆሙ፣ ግን ፍሬውን ቀምሰው ብቻ ነበር። ለመመገብ ባለመቀጠል፣ ከህንጻ የሚመጣ ማንጓጠጫው እንዲነካቸው፣ ከነቢዮ ተለይተው እና ወደጠፉበት ወደተከለከለው መንገድ እንዲስባቸው አደረጉት።

ከቀመሱ እና ተንቀዋለው ከሄዱት ጋር የሚነጻጸሩት ፍሬውን በመመገብ ቀጥለው የነበሩት ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች የህንጻውን ሁከታ ችላ አሉ፣ በነቢዩ አጠገብ ቆሙ፣ እናም አብሮ ያለውን ደህንነት እና ሰላም ተደሰቱበት። ለጌታ እና ላገልጋዮቹ ያለን የመከተል ውሳኔ የግማሽ ጊዜ ውሳኔ መሆን አይችልም። ይህ ከሆነ፣ ሰላማችንን ለማጥፋት ለሚፈልጉት የተጋለጥን እንሆናለን። ጌታን ስልጣን እሰጣቸው አገልጋዮቹ በኩል ስናዳምጥ፣ በቅዱስ ቦታዎች እንቆማለን እና እናም አንነቃነቅም።

ጠላት መልስ ለመስጠት የሚመስሉ የሚያጭበረብሩ መፍትሄ ያቀርባል ነግር ግን ከምንፈልገው ሰላይ እያራቀ ይወስደናል። ህልምን ህጋዊ እና ደህንነት እንደሆነ ያስመስላል ነገረ ግን በመጨረሻም፣ እንደ ትልቅ እና ሰፊ ህንጻው፣ በግድግዳዎቹ ውስጥ ሰላም የሚፈልጉትን እየደመሰሰ ይፈርሳል።

እውነት በመጀመሪያ ክፍል መዝሙር ውስጥ ይገኛል፥ “የነቢያት ቃላት፥ ትእዛዛትን ጠብቁ። በዚህ ውስጥ ደህንነት እና ሰላም አለ።”12

ሶስተኛው ደረጃ፥ “በመንፈሴ በትህትና ተጓዝ”

ምንም ያህል ከመንገዱ ተንገላተን ብንሄድም፣ አዳኝ እንድንመለስና ከእርሱ ጋር እንድንጓዝ ይጋብዘናል። ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመጓዝ ያለው ግብዣ ከእርሱ ጋር ወደ ገትሰመኔ ለመሄድ እና ከገትሰመኔ ወደ ካልቨሪ እናም ከካልቨሪ ወደ አትክልት ስፍራ መቃብር አብሮ ለመሄድ የሚጋብዝ ነው። ይህም መጨረሻ ስለሌለው እያንዳንዱ ላይ የሚደርሰውን ታላቅ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕትን ለመቀበል እና ለመጠቀም የሚጋብዝ ነው። ንስሀ ለመግባት፣ የሚያጸዳው ሀይሉን ወደ እኛ ለማቅርብ፣ እናም አፍቃሪ፣ የተዘረጋውን ክንዶቹን ለመያዝ የሚጋብዝ ነው። ይህም ሰላም ለመሆን የሚጋብዝ ነው።

ምስል
ከእርሱ ጋር እንድንራመድ ጋብዞናል።

በህይወታችን ውስጥ አንዳንዴ፣ ከኃጢያት እና መተላለፍ ጋር የሚመጣውን ህመም እና የልብ መሰበር ተሰምቶናል፣ ምክንያቱም “ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።”13 ነገር ግን፣ “ኃጢአታች[ን] እንደ አለላ ብትሆንም” የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት ክፍያን ስንጠቀም እና ከእርሱ ጋር ንስሀ በመግባት ስንጓዝ “እንደ አመዳይ ትነጻለች።”14 በጥፋተኛነት ሸከም ወደታች ብንወርድም፣ ሰላምን እናገኛለን።

ምስል
ንስሀ እንድንገባ ተጋብዘናል።

ታናሹ አልማ በጌታ መላእክት ሲጎበኝ ኀጢያቶቹን እንዲጋፈጥ ተገፋፍቶ ነበር። አጋጣሚዎን በእነዚህ ቃላት ገልጾ ነበር፥

“ነፍሴ በታላቅ ደረጃ ተጨንቃ፣ እናም በኃጢአቶቼ ሁሉ ተሰቃይታ ነበር።

“… አዎን፣ በአምላኬ ላይ ማመፄን፣ እናም ቅዱሳን ትዕዛዛቱን አለመጠበቄን ተመልክቻለሁ።”15

ኃጢያቱ ታላቅ ቢሆንም፣ እና በስቃዩ መካከል፣ እንዲህ ቀጠለ፥

“እነሆ የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተባለው፣ የዓለምን ኃጥያት ለመክፈል ስለሚመጣው፣ የአባቴን ትንቢት መስማቴን አስታወስኩኝ።

“… በልቤ እንዲህ በማለት አለቀስኩ፥ የ የእግዚአብሔር ልጅ የሆንከው ኢየሱስ ሆይ፣ ምህረትህ በእኔ ላይ አድርግልኝ።”16

“እናም ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለምህረት እስከምጮህ ድረስ ለኃጢአቴ ስርየትን በጭራሽ አላገኘሁም ነበር። ነገር ግን እነሆ፣ ወደ እርሱ ጮህኩና፣ለነፍሴም ሰላምን አገኘሁ።17

እንደ አልማ፣ ከኢየሱስ ካር ስንራመድ ፣ ለኃጢያቶቻችን ንስሀ ስንገባ፣ እና የእርሱን የመፈወሻ ሀይል በህይወታችን ውስጥ እናደርግ፣ በነፍሳችን ሰላም እናገኛለን።

ሁላችን የምንፈልገው ሰላም ከፍላጎት በላይ ያስፈልገዋል። ይህም ስለእርሱ በመማር፣ ቃላቱን በማዳመጥ፣ እና ከእርሱ ጋር በመራመድ እንድንሰራ ይጠብቅብናል። በአካባቢያችን የሚሆኑትን ነገሮች ለመቆጣጠር አንችልም፣ ነገር ግን ጌታ የሰጠውን የሰላም ንድፍ፣ ስለኢየሱስ ሁልጊዜ እንድናስታውስ ቀላል የሚያደርገውን ንድፍ፣ እንዴት እንደምንጠቀምበት ለመቆጣጠር እንችላለን።

ምስል
የአዳኝ ንድፍን ለመጠቀም እንችላለን።

ኢየሱስ ክርስቶስ “መንገድ፣ እውነት፣ እና ህይወት እንደሆነ”18 እና እውነተኛ ሰላም በዚህ ህይወት እና የሰለአለም ህይወት በሚመጣው አለም ለማግኘት የምንችለው በእርሱ በኩል ብቻ እንደሆነ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።