2010–2019 (እ.አ.አ)
ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም
ኤፕረል 2016


ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም

የሚያፈቅሯቸው ለሞቱባቸው በሙሉ፣ ትንሳኤ የታላቅ ተስፋ ምንጭ ነው።

ከሳምንት በፊት ፋሲካ ነበር፣ እናም ሀሳቦቻችን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ ላይ እንደገና ተተኩረው ነበር። ባለፈው አመት ስለትንሳኤ ከሌሎች ጊዜ ይበልጥ አስብበት እና አሰላስልበት ነበር።

ወደ አንድ አመት በሚቀርብ ጊዜ፣ ሴት ልካችን አሊሳ ሞተች። ለስምንት አመታት፣ ከቀዶ ጥገና፣ ከተለያዩ ህክምናዎች፣ ከሚያስደስት ታዕምራቶች፣ እና ዝልቅ ተስፋ መቁረጥ ጋር በነቀርስ በሽታ ተሰቃይታ ነበር። ወደ ስጋዊ ህይወቷ መጨረሻ ላይ ስትቀርብ የሰውነት ጉዳዩዋ ሲቀንስ ተመለከትን። ለውድ ልጃችን፣ ችሎታ ያላት፣ አስደናቂ ሴት እና እናት ወደመሆን ያደገችው ያቺ አይኗ የበራላት ህጻን ላይ የሚደርሰውን መመልከት በጣም የሚጉዳ ነበር። ልቤ እንደሚሰበር አሰብኩኝ።

ምስል
አሊሻ ጆንሰን ሊንተን

ባለፈው አመት ፋሲካ፣ ከመሞቷ አንድ ወር በፊት አካባቢ፣ አሊሳ እንዲህ ጻፈች፥ ”ፋሲካ ለራሴ ተስፋ የማደርገበትን በሙሉ እንዳስታውስ የሚያደርገኝ ነው። ያም አንድ ቀን እፈወሳለሁ እናም አንድ ቀን ሙሉ እሆናለሁ። አንድ ቀን ምንም ብረት ወይም ፕላስቲክ በሰውነቴ ውስጥ አይኖርም። አንድ ቀን ልቤ ከፍርሀት ነጻ እናም አዕምሮዌ ከከፍተኛ ጭንቀት ነጻ ይሆናል። እኔ ይህ ወዲያው እንዲሆን የምጸልይ አይደለም፣ ነገር ግን ወብታማ የሆነ ከዚህ በኋላ በሚመጣ ህይወት በእውነት በማመኔ በጣም ደስተኛ ነኝ። ”1

የኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት አሊሳ ተስፋ ያደረገችውን ይንንም ነገር ያረጋግጣል እናም በውስጣችንም “በ[እኛ] ውስጥ የሚገኝን ተስፋ” እንዲመሰረት ያደርጋል።2 ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ ከሞት መነሳትን “በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ከነበሩት ሁሉ በላይ ታላቅ” ብለውታል።3

ትንሳኤ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል የመጣ ነው እናም ለደህንነት ታላቅ እቅድ በጣም አስፈላጊ ነው።4 የሰማይ ወላጆች የመንፈስ ልጆች ነን።5 ወደዚህ ምድር ህይወት ስንመጣ፣ መንፈሳችን ከሰውነታችን ጋር አንድ ሆኑ። በሟች ህይወት ጋር የሚገናኙትን ደስታዎች እና ፈተናዎች በሙሉ ተለማመድን። ሰው ሲሞት፣ ነፍሳቸው ከሰውነታቸው ይለያያል። ትንሳኤም የሰው ሰውነት እና ነፍስ እንደገና አንድ እንዲሆኑ ለመደረግ እንዲቻል ያደርጋል፣ ነገር ግን በዚህ ግዜ ሰውነት አለሟች እና ፍጹም6—በህመም የማይነካ ነው።

ከትንሳኤ በኋላ፣ ነፍስ ከሰውነት ጋር በምንም አይለያይም ምክንያቱም የአዳኝ ትንሳኤ በሞት ላይ ፍጹም ድል አምጥቷልና። ዘለአለማዊ እጣ ፈንታዎቻችንን ለማግኘት፣ ይህ አለሟች ነፍስ—ነፍስ እና ሰውነት—ለዘለአለም አንድ ይሆናሉ። ነፍስ እና አለሟች ሰውነት በማይለያዩ ሁኔታ ተገናኝተው፣ የደስታን ሟት ለመቀበል እንችላለን።7 በእርግጥም፣ ያለ ትንሳኤ የደስታን ሙላት በምንም ለመቀበል አንችልም ነገር ግን ለዘለአለም አሰቃቂ እንሆናለን።8 ታማኝ፣ ጻድቅ ሰዎችም ሰውነታቸው ከመንፈሳቸው መለየትን እንደ እስር ይመለከቱታል። ከዚህ እስር የምንለቀቀው ከሞት ማሰሪያ እና ሰንሰለት መዳን በሆነው በትንሳኤ ነው።9 ያለ ነፍሳችን እና ሰውነታችን ምንም ደህንነት የለም።

እያንዳንዳችን ስጋዊ፣ አዕምሮአዊ፣ እና ስሜታዊ ግድቦችና ደካማነት አለን። አሁን ለመቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ የሚመስሉት እነዚህ ፈተናዎች በመጨረሻም መፍትሄ ያገኛሉ። ማንኛቸውም እነዚህ ችግሮች ከሞት ከተነሳን በኋላ አያስቸግሩንም። አሊሳ እንደነበራት አይነት ነቀርስ የሚድኑት ስንት እንደሆኑ ለማወቅ ፈተሸች፣ እናም ቁጥሮቹ የሚያበረታቱ አልነበሩም። እንዲህም ጻፈች፥ ”ነገር ግን መፈወሻ ለ፣ ስለዚህ አልፈራም። ኢየሱስ ነቀርሴን፣ የእናንተንም፣ ፈውሶታል። ... እኔ የተሻለ እሆናለሁ። ይህን በማወቄ ደስተኛ ነኝ።”10

እኛነቀርስ የሚለውን ቃል በሚያጋጥሙኝ፡በማንኛውም ሌላ የሰውነት፣ የአዕምሮ፣ ወይም የስሜት በሽታ ለመቀየር እንችላለን። በትንሳኤ ምክንያት እነዚህ በሙሉ ተፈውሰዋል። የትንሳኤ ታዕምራት፣ የመጨረሻው መፈወስ፣ ከዚህ ዘመን መድሀኒት በላይ የሆነ ሀይል ነው። ነገር ግን ከእግዚአብሔር ሀይል በላይ አይደለም። ለመከናወን እንደሚችል እናውቃለን ምክንያቱም አዳኝ ከሞት ተነስቷል እናም እያንዳንዳችንም ከሞር እንድንነሳ ያደርጋል።11

የአዳኝ ትንሳኤ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እና ያስተማረው እውነት እንደሆነ አረጋግጧል። “እንደ ተናገረ ተነሥቶአል።”12 ከመቃብር በአለሟች ሰውነት ከመምጣቱ በላይ መለኮታዊነቱን የሚያረጋግጥ ምንም ጠንካራ ማረጋገጫ የለም።

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ትንሳኤውን የመሰከሩ እንዳሉ እናውቃለን። በወንጌሎች ውስጥ ከምናነብባቸው ወንዶች እና ሴቶች በተጨማሪም፣ ብዙ፡መጦዎጭ፡ኸሞጥ የተነሳውን ጌታ እንዳዩ አዲስ ኪዳን ማረጋገጫ ይሰጠናል።13 መፅሐፈ ሞርሞንም ስለብዙ መቶዎች ይነግረናል፥ “እናም እንዲህ ሆነ ህዝቡም ሄዱ እናም እጃቸውን በጎኑ ላይ አደረጉ፣ … እናም ምስማር የተቸነከሩባቸውን እጆቹን እናም እግሮቹን ዳሰሷቸው፤ እናም በዐይኖቻቸው ተመለከቱ፣ እናም በእጆቻቸው ዳሰሱት፣ እናም በእርግጥም አወቁ እናም በነቢያቱ ስለመምጣቱም የተነገረለት እርሱ ስለመሆኑ መሰከሩ።”14

በእነዚህ የጥንት ምስክሮችም ላይ በኋለኛው ቀናት ምስክሮች ተጨምረዋል። ህያው ነቢያት እና ሐዋርያት ከሞት ስለተነሳው ህያው ክርስቶስ እውነትነት መስክረዋል።15 ስለዚህ እኛም፡እኝዲህ እንላለን፣ “እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን አሉ።”16 ስለዚህ እንዲህ እንላለን፣ “በታላቅ የምስክርነት ዳመና ተከብበናል።”17እናም እያንዳንዳችን በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በፋሲካ የምናከብረው በእውነት እንደደረሰ፣ ትንሳኤ እውነት እንደሆነ እንደ ምስክሮች ደመና ክፍል ለመሆን እንችላለን።

የአዳኝ ትንሳኤ እውነትነት የልብ መሰበራችን በተስፋ ያሸንፈዋል፣ ምክንያቱም ከዚህም ጋር የወንጌል ሌሎች ቃል ኪዳኖች በሙሉ፣ እንዲሁም ከትንሳኤ በታች ታዕምራታዊ ያልሆኑ ቃል ኪዳኖች፣ ዕውነት እንደሆኑ ካለ ማረጋገጫ ጋር፡ስለሚመጡ ነው። እኛን ከኃጢያቶቻችን ለማፅዳት ሀይል እንዳለው እናውቃለን። ህመማችንን፣ በሽታችንን፣ እና የምንሰቃይበት ፍትሀ የለሽነትን በሙሉ በራሱ ላይ እንደወሰደ እናውቃለን። 18 እርሱ “ፈውስን በክንፎቹ ይዞ ከሙታን [እንደተነሳ]” እናውቃለን።19 እርሱ በውስጣችን ምንም ቢሰበር ሙሉ እንደሚያደርገን እናውቃለን። እርሱ “እንባዎችንም ሁሉ [ከዓይኖቻችን] ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸትወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ [እንደማይሆንም]” እናውቃለን።20 እኛም እምነት ካለን እና ከተከተልን “ይህን ፍጹም የኃጢአት ክፍያን በመፈጸም … በኢየሱስ ፍጹም”21 ለመሆን እንደምንችል እናውቃለን።

በሚያነሳሳው መዝሙር መሲህ፣ መጨረሻ ላይ ሀንድል በትንሳኤ የሚደሰቱትን የሐዋርያ ጳውሎስ ወብታማ ቃላት በመዝሙሩ ውስጥ አጽገባቸው።

“እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም

“ … ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋሁላችን በድንገት በቅጽበት ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉእኛም እንለወጣለን።

“ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።

“… በዚያን ጊዜ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።

“ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ? …

“ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።”22

በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ ምክንያት ለእኛ ለሆኑት በረከቶች ምስጋና አለኝ። ልጅን በመቃብር ላስተኙ ወይም በባለቤት ወይም በሚያፈቅሯቸው የአስከሬን ሳጥን ላይ ላለቀሱ ሁሉ ትንሳኤ የተስፋ ታላቅ ምንጭ ነው። እንደ መንፈስ ብቻ ሳይሆን በሞት ከተነሳ ሰውነት ጋር እነርሱን እንደገና ማየት እንዴት አስደናቂ አጋጣሚ ይሆናል።

እናቴን እንደገና ለማየት እና የእርሷን ደግ ልካት እንዲሰማኝና ወደሚያፈቅረው አይኖቿ ለመመልከት እንዴት በጉጉት እፈልጋለሁ። የአባቴን ፈገግታ ለማየት እና ሳቁን ለመስማት እናም ከሞት እንደተነሳ ፍጹም ሰው ለማየት እፈልጋለሁ። በእምነት ላይ አይን በማስቀመጥ፣ አሊሳ ከምድር ችግሮች ወይም ከምንም የሞት ንድፍ በላይ ሆና—ከሞት የተነሳች፣ ፍጹም አሊሳ ድል የምታደርግ እና በደስታ የተሞላች እንደሆነች አያታለሁ።

ከጥቂት ፋሲካዎች በፊት፣ እንዲህ ጽፋ ነበር፥ “ህይወት በስሙ በኩል። ብዙ ተስፋዎች። ሁልጊዜም። በሁሉም ነገሮች። ትንሳኤ እንዳስታውስ እንዲያደርግ እወደዋለሁ።”23

ስለትንሳኤ እውነተኛነት እመሰክራለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው ነው፣ እናም በእርሱ ምክንያት፣ ሁላችንም እንደገና እንኖራለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።