2010–2019 (እ.አ.አ)
“እንግዳ ነበርኩኝ”
ኤፕረል 2016


“እንግዳ ነበርኩኝ”

በጸሎት—በጉዳያችሁ እና በጊዜአችሁ መሰረት—በህብረተሰቦቻችሁ ውስጥ የሚገኙትን ተሰዳጆች ለመርዳት ምን ማድረግ እንደምትችሉ ወስኑ።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር በተመሰረተበት ቀን ላይ፣ ኤማ ስሚዝ እንዲህ ብላ አወጀች፣ “አንድ ልዩ የሆነ ነገር እናደርጋለን።… ልዩ የሆኑ ወቅቶች እና አስቸኳይ ጥሪዎችን እንጠብቃለን።”1 እነኛ አስቸኳይ ጥሪዎች እና ልዩ የሆኑ ወቅቶች ልክ እንዳሁኑ—ያኔም እራሳቸውን አቅርበዋል።

ከእነሱ መካከል አንዱ የመጣው በጥቅምት 1856 (እ.አ.አ) በተደረገው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ፕሬዘደንት ብሬገም ያንግ የእጅ ጋሪ የያዙ መስራቾች በመንገዱ ላይ በረዶ በሚመጣበት ቀርተው እንደነበር ለምእመናኑ ተናገሩ። እንዲህ ብለው አወጁ፤ “እምነታችሁ፣ ሀይማኖታችሁ፣ እናም የሀይማኖታችሁ ስራ፣ እኔ አሁን እያስተማርኳችሁ ያለውን መርሆች ተሸክማችሁ እስካሌዳችሁ በስተቀር፣ በአምላካችን ሴሌስቲያል መንግስት ውስጥ የአንዳችሁንም ነፍስ በጭራሽ አያድንም። አሁን ሂዱና እነኛን ሰዎች በየሜዳዎች ላይ ያሉትን ወደ ውስጥ አምጡዋቸው፣ እናም ምድራዊ ናቸው ብለን የምንጠራቻን ነገሮች በጥብቅ ሁኔታ መፍትሄ አግኙላቸው፣ … አለበለዚያ እምነታችሁ ከንቱ ይሆናል።”2

እየተሰቃዩ የነበሩትን እነዚያን ቅዱሳን ከአደጋ ለማዳን የሄዱትን ምስጋና በተሞላበት አድናቆት እናስታውሳቸዋለን። ነገር ግን እህቶች ምን አደረጉ?

ሴቶች የቀሚሳቸውን የውስጥ ገበር ‘[በወቅቱ የፋሽን አካል የነበሩ እንዲሁም ሙቀትን የሚሰጡ የቀሚስ ስር ትልቅ ገበሮች]፣ ሰቶኪንጎችን፣ እንዲሁም ማቅረብ የሚችሉትን ሁሉ፣ እዛው በአሮጌው ምኩራብ ውስጥ [አወለቁ] እና በተራራዎቹ ላይ ላሉ ቅዱሳን ለመላክ በሰረገላዎቹ ላይ ከመሩዋቸው።’”3

ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ፣ ህይወት አድኖች እና የእጅ ጋሪ ጓዶች ወደ ሶልት ሌክ ከተማ በተቃረቡ ወቅት ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ በድጋሚ ቅዱሳንን አሰባሰቡ። በታላቅ አስቸኳይነት፣ —በተለየ መልኩ እህቶችን— እየተሰቃዩ ያሉትን እንዲያስታምሙ፣ እንዲመግቡዋቸው፣ እናም እንዲቀበሉዋቸው እንዲህ በማለት ቅዱሳንን ተማፀኑ፤ “አንዳንዱን እግሮቻቸው እስከቁርጭምጭማታቸው ድረስ በበረዶ ደንዝዘው ታገኛችኋላችሁ፤ አንዳንዶች ጉልበታቸው እና እጆቻቸው በበረዶ ደንዝዘውታገኛችኋላችሁ። … እንደ ልጆቻችሁ እንድትቀበሏቸው፣ እና ለእነርሱ እንደነርሱ አይነት ስሜት እንዲኖራችሁ አፈልጋችኋለሁ።”4

ሉሲ ሜሰርቭ ስሚዝ ይህንንም መዘገበች፤

“እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለመንከባከብ፣ በመልካም ወንድሞችና እህቶች እርዳታ የምንችለውን ያህል አደረግን። … እጆቻቸውና እግሮቻቸው በበረዶ ደንዝዘው ነበር። … ሁሉም ለመመቸት እስከሚችሉ ድረስ ያለማቋረጥ ጥረታችንን ቀጠልን። …

… ከዚ በላይ ተጨማሪ ርካታን፣ ሙሉ የሆነ ስሜት ተሰራጨ፣ አግኝቼ አላውቅም፣ እንዲሁም በህይወቴ ከሰራዋቸው የትኛውም ስራዎች ሁሉ ይህ አስደሳች ነበር ማለት እችላለሁ። …

“ለማድረግ ፍቃደኛ ለሆኑ እጆች ቀጥሎ ምን ይመጣል?”5

የተወደዳችሁ እህቶች፣ ይህ ታሪክ ከእኛ ጊዜ ጋር እና በአለም ዙሪያ እየተሰቃዩ ካሉት ሰዎች ጋር ሊዛመድ ይችላል። ሌላው “ልዩ የሆኑ ወቅት” ልቦቻችንን ይነካል።

ምስል
በስደተኞች ስፍራ ውስጥ ድንኳኖች
ምስል
በስደተኞች ስፍራ ውስጥ ልጆች
ምስል
በስደተኞች ስፍራ ውስጥ ሴቶች
ምስል
በስደተኞች ስፍራ ውስጥ ቤተሰብ
ምስል
የእርዳታ ሰራተኞች በስደተኞች ስፍራ ውስጥ በልጆች ተከብበው
ምስል
ተሰዳጅ ቤተሰቦችን ሰላምታ ሲሰጥ
ምስል
የእርዳታ ሰራተኛ ተሰዳጅን ሲያቅፉ

በአለም ዙሪያ ተገደው ያለ ቦታቸው ያሉ ሰዎችን ጨምሮ ከ60 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች አሉ። ከእነዚያ ግማሾቹ ልጆች ነበሩ።6 “እነዚህ ግለሰቦች ከባድ ችግር ነበራቸው እናም … በአዲስ አገሮች እና ባህሎች እንደገና ይጀምራሉ። አንዳንድ በመኖሪያ ቦታና በመሰረታዊ አስፈላጊ ነገሮች ላይ እርዳታን የሚደርጉላቸው ድርጅቶች እያሉ ሳለ፣ የሚያስፈልጋቸው ጓደኛ እና አዲሱን ቤታቸውን እንዲለማመዱ መርዳት የሚችል ተባባሪ፣ ቋንቋውን፣ አሰራሮቹን እንዲማሩ እና እንደተግባቡ እንዲሰማቸው እነሱን መርዳት ሚችል ሰው ነው።”7

ምስል
ይቨት ቡጂንጎ

ባለፈው በጋ ላይ አባቷ ከተገደለ በኋላ እንዲሁም የእርስ በእርስ ጦርነት ያለበት የአለም ክፍል ውስጥ የጠፉባት ሶስት ወንድሞች ያሏት በ11 አመቷ ከቦታ ቦታ ስትሸሽ የነበረችውን እህት ያቬት ቡጂነጎን አገኘሁ። የቨት እና የቀሩት ቤተሰቦቿ በመጓዣ፣ በትምህርት፣ እና በሌሎች ነገሮች በሚንከባከቡ ባልና ሚስት በሚባረኩበት ወደ ቋሚ ቤት ለመሄድ እስከሚችሉ ድረስ በመጨረሻ በጎረቤት አገር ውስጥ እንደ ተሰዳጆች ኖሩ። እንዲህ አለች፣ እነርሱም “ለጸሎታችን መልስ ነበሩ።”8 ወብታማዋ እናቷ እና ቆንጆዋ እህቷ በዚህ ምሽት፣ ከዘማሪዎች ጋር በመዘመር ይገኛሉ። ይህችን ቆንጆ እህት ካገኘሁ ጀምሮ በብዙ ጊዜ “ የእነሱ ታሪክ የእኔ ታሪክ ቢሆንስ?” ብዬ እጠይቃለሁ።

እንደ እህቶች፣ የሰማይ አባት ልጆችን ለመርዳት ከጌታ የማከማቻ ቤት ከግማሽ በላይ እንሸፍናለን። የእሱ ማከመቻ ቤት በመልካሞች ብቻ ብቻ ሳይሆን የተሰራው ነገር ግን በጊዜ፣ ተሰጥኦዎች፣ ክህሎቶች እናም በእኛ መለኮታዊ ተፈጥሮም የተሞላ ነው። እህት ሮስመሪ ኤም. ዊሶም እንዲህ አስተማረች፣ “በእና ውስጥ ያለው መለኮታዊ ተፈጥሮ ለሌሎች እንድንደርስ በሻታችንን ያቀጣጥሉታል እናም እንድንተገብር ያበረታቱናል።”9

እንድንተገብር የሚያነሳሳንን የኛን መለኮታዊ ተፈጥሮን በመገንዘብ፣ ፕሬዘደንት ሩስል እም. ኔልሰን እንዲህ አብራሩ፤

“በእምነታቸው ጠቃሚ ነገሮችን እንዲከሰቱ ማድረግ የሚችሉ ሴቶች ያስፈልጉናል እናም በዚህች በሃጢያት የታመመች አለም ውስጥ ቅንነትን እና ቤተሰቦችን የሚከላከሉ ብርቱ ሴቶች … ፤ ልጆችን እና ቤተሰቦችን ለመከላከል የሰማይን ሀይሎች መጥራት እንዴት እንደሚችሉ የሚያውቁ ሴቶች ያስፈልጉናል። …

“… ያገባችሁ ወይም ያላገባችሁ፣ እናንተ እህቶች ግልፅ ችሎታዎች እና ከእግዚያብሄር የተቀበላችሁት የልዩ ስሜት ስጦታ ተላብሳችኋል። እኛ ወንድሞች እናንተ ያላችሁን ልዩ ተፅእኖ ማባዛት አንችልም”10

በጥቅምት 27፣ 2015 (እ.አ.አ) የቀዳሚ አመራር ደብዳቤ ለቤተክርስቲያን፣ ከእርስ በእርስ ጦርነት እና ከሌሎች ችግሮች እፎይታን ለማግኘት ቤታቸውን ትተው ለሸሹት ሚሊዮን ሰዎች ታላቅ ሃሳብ እና ርህራሄን ይገልፃል። የቀዳሚ አመራር ግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን እንዲሁም የቤተክርስቲያን ቅርንጫፎችን በሀገር ውስጥ ያሉ የስደት ማረፊያ ፕሮጀክቶችን ክርስቶስ መሰል በሆነ ባህሪይ አገልግሎት ላይ እንድንሳተፍ፣ እና በመተግበር ባለበት አካባቢ ላይ ለቤተክርስቲያን በጎ አድራጎት ገንዘብ እንድናዋጣ ጋብዘውናል።

አጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣ የወጣት ሴቶች፣ እናም የህፃናት ክፍል አመራር ለቀዳሚ አመራር ግብዣ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚችሉ አስበዋል። እናንተ፣ በሁሉም እድሜ ላይ ያሉ ውድ እህቶቻችን፣ ከሁሉም የህይወት እርምጃዎች እንደመጣችሁ እና በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ እንደምትኖሩ እናውቃለን። እያንዳንዷ የዚህች የአለም አቀፍ እህትነት አባላት በጥምቀቷ “ለመፅናናት የሚያስፈልጋቸውን ለማፅናናት”11 ቃል ገብታለች። ግን ማንኛችንም ካለኝ ጥንካሬ በላይ ለመሮጥ እንደማይገባን ማስታወስም አለብን።12

እነዚህን እውነቶች በኧእምሮአችን እያወቅን፣ “እንግዳ ነበርኩኝ” የሚባል የእረፍት ጥረትን አደራጅተናል። በጸሎት—በጉዳያችሁ እና በጊዜአችሁ መሰረት—በህብረተሰቦቻችሁ ውስጥ የሚገኙትን ተሰዳጆች ለመርዳት ምን ማድረግ እንደምትችሉ እንድትወስኑ ተስፋችን ነው። አንድ ለአንድ፣ በቤተሰቦች ውስጥ እናም በድርጅት ውስጥ ጓደኝነትን ለማቅረብ፣ መካሪ መሆን እና ሌሎች ክርስቶስ መሰል ግልጋሎትን ለመስጠት ለማገልገል ይህ እድል ነው።

በየፀሎታዊ ጥረታችን ውስጥ፣ ንጉስ ቢንያም በችግር ላይ ላሉት ሰዎች እንዲጨነቁ ከመከራቸው በኋላ ለህዝቡ የሰጣቸውን ብልህ ምክር መተግበር አለብን። “ሁሉም ነገሮች በጥበብ እና በስርዓት መደረጋቸውን ተመልከቱ”13

እህቶች፣ ለሌሎች በፍቅር መድረስ ለጌታ ትርጉም ያለው ነገር እንደሆነ እናውቃለን። የዚህን ተግሳፃዊ ቅዱስ መፅሀፍ አሰላስሉ፤

“ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገር ልጅ ይሁንላችሁ፤ እርሱንም እንደ ራስህ ውደድ።”14

“እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና”15

አዳኝ እራሱ እንዲህ አለ፥

“ተርቤ አብልታችሁልኛልና፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፤

“ታርዤ አልብሳችሁኛልና፤ ታምሜ ጠይቃችሁልኛልና።”16

ምስል
ባሏ የሞተባት ሴት ሳንቲም

ሁለት ሳንቲም ብቻ ያዋጣችውን ባሏ የሞተባት ሴት ያላትን ስለሰጠች አዳኝ ፍቅር በተሞላበት መንገድ እውቅናን ሰጣት።17 እንዲሁም— እንደዚ በሚል አረፍተ ነገር የዘጋውን ስለ ደጉ ሳምራው ምሳሌንም ተናገረ “ሂዱ፣ እና እንደዛው አድርጉ።”18 ለመርዳት መዘርጋት አንዳንዴ አይመቻችም። ነገር ግን በፍቅር እና በአንድነት አብረን ስንሰራ፣ የሰማይን እርዳታ መጠበቅ እንችላለን።

ድንቅ የሆነችው የእግዚያብሄር ሴት ልጅ የቀብር ስርዓት ላይ፣ አንድ ሰው ይህንን አካፈለ፣ ይህች ሴት እንደ የካስማ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘዳንት እንደመሆኗ፤ በካስማዋ ውስጥ ከነበሩ ሌሎች ሰዎች ጋር በመስራት ሙቀት እንዲያገዠኙ የአልጋ ልብሶችን 1990 (እ.አ.አ) አመቶች ወቅት በኮሶቮ ውስጥ ለነበሩ በስቃይ ላይ ለነበሩ ሰዎች አዋጡላቸው። እናም ልክ እንደ ደጉ ሳምራዊ፣ እስዋ እና ሴት ልጇ በእነዛ አልጋ ልብሶች የተሞላ የጭነት መኪና ከለንደን ወደ ኮሶቮ ሲነዱ ተጨማሪ ለማድረግ በራስዋ መንገድ ሄደች። ወደ ቤቷ በመጓዝ ላይ ሳለች፣ ወደ ልቧ ጠልቆ የገባ የማይሳሳት መንፈሳው ስሜትን ተቀበለች። ስሜቱ እንዲህ ነበር፤ “ያረግሺው ነገር በጣም መልካም ነገር ነው። አሁን ቤትሽ ሂጂ፣ መንገዱን አቋርጪ፣ እናም ጎረቤትሽን አገልግዪ!”19

ይህች ታማኝ ሴት እንዴት ልዩ እና እስቸቀኳይ ጥሪዎችን እንደተገነዘበች እና መልስ እንዴት እንደሰጠች ባለው ታሪክ—እና እንዲሁም በእሷ ተፅእኖ ዙሪያ ባሉ በተለመዱ ወቅቶች ቀብሩ በተጨማሪ መነሳሳት ተሞልቶ ነበር። ለምሳሌ፣ ቀንም ይሁን ማታ በየትኛውም ሰአት በችግር ላይ ያሉ ወጣት ሰዎችን ለመርዳት ቤቷን እና ልቧን ከፈተች።

ተወዳጅ እህቶቼ፣ ስንበረከክ እና የእርሱን ልጆች ለመባረክ መለኮታዊ ምሬትን ስንጠይቅ የሰማይ አባት እርዳታን በእርግጠኛነት ልናገኝ እንችላለን። የሰማይ አባት፤ አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ እና መንፈስ ቅዱስ ለመርዳት ዝግጁ ናቸው።

ፕሬዘዳንት ሄነሪ ቢ. ኤይሪንግ ለቤተክርስቲያኑ ሴቶች ይህንን ሃይለኛ ምስክርነት አካፈሉ፤

“ለሱ ባላችሁ አገልግሎታችሁ እንድትፀኑ እንዲረዳችሁ እና ምሬትን ለማግኘት የምታደርጉትን የእምነታችሁን ፀሎት የሰማይ አባት ይሰማል እናም ይመልሳል።

“ለእናንተ እና ለምትጨነቁላቸው ሰዎች መንፈስ ቅዱስ ተልኳል። ጠንካሮች ትደረጋላችሁ እናም የማገልገል አቅማችሁን መጠኖቻችሁን እና ልካችሁን እንድታውቁ ትነሳሳላችሁ። ‘በቂ አድርጌያለሁን?’ ብላችሁ ስትጠይቁ መንፈስ ቅዱስ ያፅናናችኋል”20

የእኛን እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን “አስቸኳይ ጥሪዎች?” ስናሰላስል፣ እራሳችንን እንዲህ ብለን እንጠይቅ፣ “ የእነሱ ታሪክ የእኔ ታሪክ ቢሆን ኖሮስ?” ከዚያን መነሳሳትን እንሻ፣ የምንቀበለው ስሜቶች ላይ እንተግብር፣ እናም እንደምንችለው እና እንድናደርግ እንደተነሳሳነው እርዳታን ለሚያስፈልጋቸው ለመርዳት በአንድነት እንድረስላቸው። ከዚያ ምናልባት አዳኝ ለእሱ ስላገለገለችው ውድ እህት እንደተናገረው፣ ስለ እኛም እንደዛው ሊባልልን ይችል ይሆናል። “ጥሩ ስራ አምጥታለች። … ለማድረግ የምትችለውን አድርጋለች።”21 ያን አስደናቂ ብዬ እጠራዋለሁ! በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ኤማ ስሚዝ፣ በ Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011)፣ 14።

  2. ብሬገም ያንግ፣ በ Daughters in My Kingdom, 36።

  3. Daughters in My Kingdom, 36–37።

  4. Brigham Young, in James E. Faust, “Go Bring Them in from the Plains,” Liahona, Nov. 1997, 7; see also LeRoy R. and Ann W. Hafen, Handcarts to Zion: The Story of a Unique Western Migration 1856–1860 (1960), 139.

  5. Lucy Meserve Smith, in Jill Mulvay Derr and others, eds., The First Fifty Years of Relief Society: Key Documents in Latter-day Saint Women’s History (2016), 217, 218, spelling and punctuation standardized; see also Daughters in My Kingdom, 37.

  6. See “Facts and Figures about Refugees,” unhcr.org.uk/about-us/key-facts-and-figures.html.

  7. 40 Ways to Help Refugees in Your Community,” Sept. 9, 2015, mormonchannel.org.

  8. Email from Yvette Bugingo, Mar. 12, 2016.

  9. Rosemary M. Wixom, “Discovering the Divinity Within,” Liahona, Nov. 2015, 8. በዊሊ የእጅ ጋሪ ቡድን አንዷ የነበረችው ኤምሊ ዉድማንሲ መለኮታዊ ፍጡርን እንዲህ ገለጸች (ትንሽ እኔ ቀይሬው ነበር)፥

    የመላዕክቶች ሀለፊነት ነው፤

    እና ይህም፣ እንደ እህቶች፣ ለማግኘት የምንችለ፥

    ምንም ረጋ ያለ የ [የክርስቶስ አይነት]፣

    በ[አዳኝ] ስም ለማስደሰት እና ለመባረክ። (“As Sisters in Zion,” Hymns, no. 309)

  10. Russell M. Nelson, “A Plea to My Sisters,”Liahona, Nov. 2015, 96, 97.

  11. ሞዛያ18፥9

  12. ሞዛያ 4፥27ተመልከቱ፡፤

  13. ሞዛያ 4፥27

  14. ዘሌዋውያን 19፥34

  15. ዕብራውያን 13፥2

  16. ማቴዎስ 25፥35–36

  17. የሉቃስ ወንጌል 21፥1–4ተመልከቱ።

  18. ሉቃስ 10፥37

  19. Funeral service for Rosemary Curtis Neider, Jan. 2015.

  20. Henry B. Eyring, “The Caregiver,”Liahona, Nov. 2012, 124.

  21. የማርቆስ ወንጌል 14፥6, 8