2010–2019 (እ.አ.አ)
የሚያድኑትን በማመስገን
ኤፕረል 2016


የሚያድኑትን በማመስገን

የአዳኝን ፍቅር ስንከተል፣ በእውነት ይባርከናል እናም ጋብቻችንን ለማዳን እና ቤተሰቦቻችንን የማጠንከር ፃድቅ ጥረቶቻችንን ያበለፅጋል።

ከብዙ አመታት በፊት፣ በእድሜ የገፉ ጥንዶች እጅ ለእጅ ተያይዘው ስገነዘብ በጀርመን፣ ፍራክፈርት ቤተመቅደስ ውስጥ ነበርኩ። አንዳቸው ለአንዳቸው ያሳዩት የመጨነቅ መልካምነት እና ፍቅር ልቤን አሞቀው።

ይህ ሁኔታ ለምን በጥልቀት እንደተሰማኝ ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ አይደለሁም። ምን አልባት እነኚ ሁለት ሰዎች አንዳቸው ለአንዳቸው ያካፈሉት የፍቅር ጣፋጭነት—የሚያስገድድ ተግቶ የመስራት እና የመሰጠት ምልክት ነበር። እነኚ ጥንዶች በአንድ ላይ ለረዥም ጊዜ አብረው እንደነበሩ እና አንዳቸው ለአንዳቸው ያላቸው ፍቅር እስካሁን ያለና ጠንካራ እንደሆነ ግልፅ ነበር።

ተጠቅሞ የሚጥል ህብረተሰብ

ይህ የፍቅር ሁኔታ ከእኔጋ በጣም ለረጅም ጊዜ የቆየበት ሌላ ምክንያት ከጥቂቶቹ የዘመኑ ሁኔታዎች ጋር የተለየ መሆኑ እንደሆነ አሰብኩ። በአለም ዙሪያ ባሉ ብዙ ህብረተሰቦች ውስጥ፣ ሁሉ ነገር የሚጣል ይመስላል። የሆነ ነገር መሰበር እንደጀመረ ወይም አገልግሎት መስጠት ሲያቆም—ወይም በቀላሉ ሲሰለቸን—እንወረውረዋለን እና በተሻሻለው—አዲስ በሆነ ነገር ወይም በሚያብለጨልጭ ነገር እንተካዋለን።

በስልክ፣ በልብስ፣ በመኪናዎች—እናም፣ በአሳዛኝ ሁኔታ፣ በግንኙነትንም ይህንን እናደርጋለን።

ህይወታችንን በአሁን በማያስፈልጉን ቁስ ነገሮች በማስጌጥ ውስጥ ዋጋ ያለ ቢኖርም፣ ዘላለማዊ የሆኑት—እንደ ጋብቻችን፣ ቤተሰቦቻችን፣ እና መመሪዎቻችን ያሉ ጠቃሚ ነገሮች ላይ ሲመጣ—ዘመናዊውን በመምረጥ ዋናውን የመቀየር አእምሮአዊ ውሳኔ ጥልቅ የሆነን ፀፀት ሊያመጣ ይችላል።

ለጋብቻ እና ለቤተሰብ ዋጋ የሚሰጥ ቤተክርስቲያን አካል በመሆኔ አመስጋኝ ነኝ። የኃለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት በአለም ዙሪያ ማግኘት ከምትችሉት መላካም የሆኑ ጋብቻዎች እና ቤተሰቦች መካከል ምርጡ ስላላቸው በዛ ይታወቃሉ። በዮሴፍ ስሚዝ በኩል በተመለሰው ውድ እውነት ምክንያት፣ ጋብቻዎች እና ቤተሰቦች ለዘላለም የታቀዱ እንደሆኑ አምናለሁ። ቤተሰቦች በዚህ ምድር ላይ ያሉ ነገሮችን በአመቺ መንገድ እንዲያስኬዱ እንዲሁም ሰማይ ስንደርስ እንዲጣሉ ብቻ አይደለም የታቀደው። ይልቁንም፣ የሰማይ ስርዓት ናቸው። የሴልስቲያል ንድፍ አስተጋቢዎች እና የእግዚያብሄር ዘላለማዊ እቅድ ተምሳሌት ናቸው።

ነገር ግን ጠንካራ የጋብቻ እና የቤተሰብ ግንኙነቶች የቤተክርስቲያን አባል ስለሆንን ብቻ አይከሰቱም። የማያቋርጥ እና የታሰበበት ስራን ይጠይቃሉ። የዘላለም ቤተሰቦች ትምህርት ጋብቻዎችን እና ቤተሰቦችን ለማዳን እና ለማበልፀግ ምርጡን ጥረቶቻችንን እንድናውል ሊያነሳሱን ይገባል። እነኚን አሳሳቢ፣ ዘላለማዊ ግንኙነቶችን የሚያቆዩ እና የሚንከባከቡትን ሰዎች አደንቃቸዋለሁ እንዲሁም አጨበጭብላቸዋለሁ።

ዛሬ የሚያድኑትን ሰዎች በማመስገን መናገር እመኛለሁ።

ጋብቻችንን ማዳን

ለአመታት፣ ለብዙ ተስፈኞች እና ውድ ጥንዶች የመታተም ስርዓትን ፈፅሜያለሁ። በመሰዊያው አሻግረው እርስ በእርስ አየተያዩ፣ በስተመጨረሻ እንደሚፋቱ ወይም እንደሚጎዱ የሚያስቡ፣ የትኛውንም ሰው አግኝቼ አላውቅም።

ያጋጣሚ ነገር ሆኖ፣ አንዳንዶች ያደርጉታል።

ቢሆንም፣ ቀኖቹ እየበዙ ሲመጡ እና ቆንጆ የሆነው ፍቅር ቀለም ሲቀየር፣ ቀስ በቀስ የእርስ በእርሳቸውን ደስታ ማሰብ የሚያቆሙና ትናንሽ ስህተቶችን ማስተዋል የሚጀምሩ ጥቂቶች አሉ። በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ፣ ጥቂቶች ባለቤታቸው በቂ እውቀት የላትም፣ በበቂ ሁኔታ አዝናኝ አይደለችም፣ ወይም በቂ ወጣትነት የላትም በሚለው አሳዛኝ ማጠቃለያ ይማለላሉ። እናም እንደምንም ይህ ሌላ ሰው ለመፈለግ የመጀመርን ሰበብ የሚሰጣቸውን ሀሳብ ያገኛሉ።

ወንድሞች፣ ይህ እናንተን ለመግለፅ ትንሽም ከቀረበ፣ ወደ ተሰበሩ ጋብቻዎች፣ የተሰበሩ ቤቶች፣ እና ወደ ተሰበሩ ልቦች መንገድ እንደሆናችሁ አስጠነቅቃችኃለሁ። አሁን እንድታቆሙ፣ ወደ ኋላ እንድትዞሩ፣ እና ደህንነት ወዳለበት ለቃልኪዳኖች የሀቀኝነት እና የታማኝነት መንገድ እንድትመለሱ እማፀናችኋለሁ። እናም፣ በእርግጥ፣ ተመሳሳይ መመሪያዎች ለውድ እህቶቻችንም ይሰራል።

አሁን፣ ወደ ኃይለኛ ማሽኮርመም እና ጋብቻ ከመግባታቸው በፊት መጀመሪያ “ፍፁም ሴትን” ማግኘት እንዳለባቸው ማጭበርበር ለሚከተሉ ላላገቡ ወንድሞች አንድ ቃል ብቻ አለኝ።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ላስታውሳችሁን፣ ፍፁም ሴት ኖራ ቢሆን ኖሮ፣ እናንተን ምትፈልጋችሁ ይመስላችኋልን?

በእግዚያብሄር የደስታ እቅድ ውስጥ፣ ፍፁም የሆነን ሰው አይደለም የምንፈልገው ነገር ግን አብረን፣ በህይወት ዘመን ሁሉ፣ የሚወደድ፣ የሚቆይ፣ እና ፍፁም ግንኙነትን ለመፍጠር ጥረቶችን መቀላቀል እንችላለን። አላማው ያ ነው።

ወንድሞች፣ ጋብቻቸውን የሚያድኑ ይህ ክትትል ሰዓትን፣ ትእግስትን፣ እናም ከሁሉም በላይ የኢየሱስ ክርስቶስን የሀጢያት ክፍያ በረከቶችን እንደሚጠይቅ ይረዳሉ። ደግ፣ አለመቅናትን፣ የራስን አለመሻትን፣ በቀላሉ አለመናደድን፣ ክፋትን አለማሰብን፣ እናም በእውነት ሀሴት ማረግን ይጠይቃችኋል። በሌላ አባባል፣ ልግስናን፣ ንፁሁ የክርስቶስ ፍቅርን ይጠይቃል።1

ይህ ሁሉ ወዲያው አይከሰትም። ታላቅ ጋብቻዎች ጡብ በጡብ ላይ፣ ከቀን ተቀን፣ በህይወት ቆይታ ውስጥ ነው የሚገነቡት።

እናም ያ መልካም ዜና ነው።

ምክንያቱም አሁን ላይ ግንኙነታችሁ ምንም ያህል ለጥ ያለ ቢሆንም፣ የደስታ፣ የማዘን፣ የማዳመጥ፣ የመስእዋትነት እና እራስ ወዳድ ያልሆነ ትንሽ የወነዝ ዳር ድንጋይ መጨመራችንን ከቀጠልን፣ በስተመጨረሻ ግዙፍ ፒራሚድ ማደግ ይጀምራል።

ዘላለም የሚቆይ መስሎ ከታየ፣ አስታውሱ ደስተኛ ጋብቻዎች ለዘላለም እንዲቆዩ ተደርገው ነው የተሰሩት። ስለዚህ“መልካም በማድረግ ላይ አትዛሉ፣ የታላቁን [ጋብቻ መሰረት] እየጣላችሁ ነውና። እናም ከትንንሾቹ ነገሮች ታላቅ የሆነው ይወጣል።”2

ቀስ ያለ ስራ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ደስ የማይል መሆን የለበትም። በእርግጥ፣ ግልፅ የሆነውን ለመናገር፣ ባልና ሚስት ደስተኛ ሆነው ፍቺ የመከሰቱ እድል አናሳ ነው።

ስለዚህ ደስተኛ ሁኑ!

እናም ወንድሞቼ፣ ደስተኛ የሚያረጋትን ነገር በማድረግ ሚስታችሁን አስገርሟት።

ጋብቻቸውን የሚያድኑ ደስታን መርጠዋል። አንዳንድ ስር ሰደድ ጭንቀቶች ልዩ የሆነ ህክምና እንደሚያስፈልጋቸው እርግጥ ሆኖ ሳለ፣ በአብርሀም ሊንከን የተሰጠውን ይህንን ትንሽ ጥበብ እወደዋለው፤ “አብዛኛውን ሰዎች አእምሮአቸውን እንዲሆን ባሳመኑት መጠን ደስተኞች ናቸው።” ይሄ በጥሩ መልኩ ከቅዱስ መፅሀፋዊ ቃል ጋር ይሄዳል፤ “ፈልጉ፣ ታገኙማላችሁና።”3

በባለቤቶቻችን ላይ ፍጹም ያልሆኑ ነገሮችን ወይም በትዳራችን ውስጥ የሚያበሳጩ ነገሮችን የምንፈልግ ከሆነ፣ በእርግጥ እናገኛቸዋለን ምክንያቱም ሁሉም ሰው አለውና። በሌላ በኩል፣ መልካምን ከፈለግን፣ በእርግጥም እናገኘዋለን፣ ምክንያቱም ሁሉም ሰው ብዙ መልካም ባህሪዎችም አሉት።

ጋብቻዎችን የሚያድኑ አረሞቹን አስወግደው አበባዎቹን ውሃ ያጠጣሉ። የልግስናን ፍቅራዊ ስሜቶች የሚያፈነጥቁትን የፀጋን ትንሽ ድርጊቶች ይደሰታሉ። ጋብቻዎችን የሚያድኑ መጪውን ትውልዶች ያድናሉ።

ወንድሞች፣ ለምን በፍቅር እንደወደቃቹ አስታውሱ።

ትዳራችሁን ጠንካራ እና ደስተኛ ለማድረግ በየቀኑ ስሩ።

የተወደዳችሁ ጓደኞች፣ ጋብቻቸውን ካዳኑት ከተቀደሱት እና ደስተኛ ከሆኑት ነፍሶች መካከል እንድንቆጠር የቻልነውን ሁሉ እናድርግ።

ቤተሰባችንን ማዳን

ዛሬ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ያለውን ግንኙነት ያዳኑትን በማወደስ ለመናገር እመኛለሁ። እያንዳንዱ ቤተሰብ መዳን ያስፈልገዋል።

ቤተክርስቲያኑ ጠንካራ ቤተሰቦችን በመኖሩ መታወቁ አስገራሚ ሆኖ ሳለ፣ ከእኛ ቤተሰብ ውጪ እያንዳንዱ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተሰብ ላይ አብዛኛውን ጊዜ ይህ ተግባራዊ መሆን አለበት ብለን ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን እውነታው ፍፁም ቤተሰቦች አለመኖራቸው ነው።

እያንዳንዱ ቤተሰብ የማይመች ወቅቶች አሉት።

ልክ ወላጆቻችሁ ሰልፊ እንድታነሷቸው እናንተን ሲጠይቁ፣ ወይም ቅድመ አክስታችሁ እስካሁን ያላገባችሁበት ምክንያት በጣም ስለምትመርጡ ስትላችሁ፣ ወይም ጭፍን የሆነው የወንድ አማቻችሁ የእሱ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ የወንጌል አስተሳሰብ እንደሆነ አድርጎ ሲያስብ፣ ወይም አባታቸሁ ሁሉም የቤተሰብ አባላት እሱ የሚወደውን የፊልም ገፀ ባሪያት አይነት አለባበስ ለብሰው ቤተሰቡ በቀጥታ በሰዓሊ እንዲሳሉ ሲያዘጋጅ።

እናም ቼውቤካ ባህላዊ ልብስን ስታገኙ።

ቤተሰቦች እንደዛ ናቸው።

አንድ አይነት ዘር ልንሆን እንችላለን፣ ነገር ግን አንድ አይደለንም። ልዩ የሆነ መንፈስ አለን። በልምዶቻችን በተለያዩ መንገዶች ተፅዕኖ ይደረግብናል። እናም በውጤቱ እያንዳንዶቻችን ልዩ እንሆናለን።

እራሳችን ወደ ሰራነው ቅርፅ ሌሎች እንዲገቡ ከማስገደድ ይልቅ፣ እነኚህን ለልዩነቶች ልንደሰትባቸው እና ህይወታችን ላይ ሀብትን እና ቋሚ የሆኑ ግርምቶችን የሚጨምሩትን ለማድነቅ መምረጥ እንችላለን።

ምናልባትም፣ አንዳንዴ፣ የቤተሰቦቻችን አባላት የማያሳስቡ፣ የሚጎዱ፣ ኢስነ-ምግባራዊ የሆኑ ነገሮችን ይመርጣሉ ወይም ያደርጋሉ። በእነኚ ሁኔታዎች ውስጥ ምን ማድረግ አለብን?

እያንዳንዱን ሁኔታዎች የሚሸፍን የሆነ አንድ መፍትሄ የለም። ቤተሰቦችቸውን የሚያድኑ ውጤታማ ናቸው ምክንያቱም ከባለቤታቸው እና ከቤተሰባቸው ጋር መማክርት ያደርጋሉ፣ የጌታን ፍቃድ ይሻሉ፣ እናም የመንፈስ ቅዱስን ማነሳሳቶችን ያዳምጣሉ። ለአንድ ቤተሰብ ትክክል የሆነው ነገር ለሌላ ቤተሰብ ትክክል ሊሆን እንደማይችል ያውቃሉ።

ሆኖም፣ በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ ትክክል የሆነ አንድ ነገር አለ።

በመፅሀፈ ሞርሞን ውስጥ የደስታም ሚስጢር ስላገኙ ሰዎች እንማራለን። ለብዙ ዘመናት፣ “በህዝቡ ልብ ውስጥ ባለው የእግዚያብሄር ፍቅር የተነሳ፣ …. እናም በእርግጥ በእግዚያብሄር እጅ ከተፈጠሩት ሰዎች መካከል እንደ እነዚህ ያለ ደስተኛ ሊሆን የቻለ ህዝብ አልነበረም።” እንዴት አደረጉት? “በሰዎቹ ልቦች ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር ስላደረ ።”4

ቤተሰባችሁ የትኛውም አይነት ችግሮች ቢጋፈጡም፣ ችግሩን ለመፍታት ምንም አይነት ነገር ብታደርጉም፣ የመፍትሄው መጀመሪያ እና መጨረሻ የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር የሆነው፣ ልግስና ነው። ያለዚህ ፍቅር፣ ፍፁም የሆኑ ቤተሰቦችም ቢሆኑ ይቸገራሉ። ከእሱ ጋር ተያይዞ፣ ታላቅ ፈተና ያለባቸው ቤተሰቦችም እንኳን ውጤታማ ይሆናሉ።

“ልግስና ለዘወትር አይወድቅም።”5

ያ ጋብቻዎችን ለማዳን ይሰራል! ቤተሰቦችን ለማዳን ይሰራል!

ኩራታችሁን ወደ ጎን አድርጉ

የፍቅር ታላቅ ጠላት ኩራት ነው። ጋብቻዎችን እና ቤተሰቦችን ከሚያስቸግሩ ምክንያቶች መካከል ኩራት አንዱ። ኩራት ግልፍተኛነት፣ ደግ አለመሆን፣ እና ምቀኝነት ነው። ኩራት የራሱን ጥንካሬ ያጋናል እናም የሌሎችን ዋጋዎች ችላ ይላል። ኩራት እራስ ወዳድ ነው እናም በቀላሉ ይናደዳል። ምንም በሌለበት ቦታ እና የራሱን ክፋት ጥበባዊ በሆኑ ምክንያቶች ጀርባ በመደበቅ ኩራት ክፉ ፍላጎትን ይገምታል። ኩራት ተጠራጣሪ፣ ክፉ አሳሳቢ፣ ተናዳጅ፣ እና ትግስት የሌለው ነው። በእርግጥም፣ ልግስና ንፁህ የክርስቶስ ፍቅር ከሆነ፣ ከዚያ ኩራት የሴጣንን ዓይነተኛ ፀባይ የሚያስረዳ ነው።

ኩራት ምናልባት የተለመደ የሰው ልጅ ጉድለት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የመንፈሳዊ ቅርሳችን አካል አይደለም፣ እናም በእግዚያብሄር የክህነት ስልጣን ተሸከማዊዎች መካከል ምንም ቦታ የለውም።

ወንድሞች፣ ህይወት አጭር ነች። መፀፀት ለረጅም ጊዜ መቆየት ይችላል— አንዳንዶች ለዘላለም የሚያስተጋባ እንከን ይኖራቸዋል።

ሚስቶቻችሁን ወይም ልጆቻችሁን ወይም ወላጆቻችሁን ወይም እህቶቻችሁን እና ወንድሞቻችሁን የምትንከባከቡበት መንገድ ወደ ፊት የሚመጡ ትውልዶች ላይ ተፅእኖ ማድረግ ይችላል። ለዘራችሁ መተው የምትፈልጉት ውርስ ምንድን ነው? የክፋት፣ የቂም፣ የንዴት፣ የፍርሀት፣ ወይም የብቸኛነት ነውን? ወይም ከፍቅር፣ ትህትና፣ ይቅር ባይነት፣ ርህራሄ፣ እና መንፈሳዊ እድገት እና አንድነት መካከል አንዱ?

ሁላችንም ይህንን ልናስታወስ ይገባል፣ “ምንም ምህረትን ለማያሳይ ምህረት ሌለበት ፍርድ ይሆናል።”6

ለቤተሰባችሁ ግንኙነቶች ሲባል፣ ለነብሳችሁ ሲባል፣ እባካችሁ ምህረት ይኑራችሁ፣ “ምህረትም በፍርድ ላይ ይመካልና።”7

ኩራታችሁን ወደ ጎን አድርጉ።

ለልጃችሁ፣ ለሚስታችሁ፣ ለቤተሰባችሁ፣ ወይም ለጓደኞቻችሁ ከልብ ይቅርታ መጠየቅ የድክመት ምልክት አይደለም ነገር ግን የጥንካሬ ምልክት ነው። የመንከባከብ፣ የመፈወስ፣ እና የፍቅር ሁኔታ ከማበረታታት የበለጠ ትክክል መሆን የተሻለ ጠቃሚ አይደለምን?

ድልድዮችን ገንቡ፤ አታፍርሷቸውም።

ጥፋተኛ ሳትሆኑ እንኳን—ምናልባትም በተለይ ጥፋተኛ ሳትሆኑ—ፍቅር ኩራትን እንዲያሸንፍ አድርጉ።

ይህንን ካደረጋችሁ፣ የምትጋፈጡት የትኛውም መከራ ያልፋል፣ እናም በልባችሁ ውስጥ ባለው ፍቅር አማካኝነት፣ ጠብ ይጠወልጋል። ያገባን፣ የተፋታን፣ ጋለሞታ፣ ወይም ያላገባም ብንሆንም፣ እነኚህ ግንኙነቶችን የማዳን መርሆዎች ለሁላችንም ይሰራሉ። ሁላችንም የጠንካራ ቤተሰቦች አዳኞች መሆን እንችላለን።

ታላቁ ፍቅር

ወንድሞች፣በሁሉም ነገሮች እንደምናደርገው፣ ትዳራችንን እና ቤተሰባችንን ለማዳን በምናደርገው ጥረት ውስጥ፣ የሚያድነንን ምሳሌ እንከተል። አዳኝ “ነፍሳችንን በፍቅር” 8 አሸንፏል። ኢየሱስ ክርስቶስ አስተማሪያችን ነው። የእሱ ስራ የእኛ ስራ ነው። የማዳን ስራ ነው፣ እናም የሚጀምረው በቤቶቻችን ውስጥ ነው።

ፍቅር የመዳን እቅድ ምርት ነው አራስ ወዳድ አይደለም እናም የሌሎች ደስታን ይሻል። ያ የሰማይ አባት ለእኛ ያለው ፍቅር ነው።

የአዳኝን ፍቅር ስንከተል፣ በእውነት ይባርከናል እናም ጋብቻችንን ለማዳን እና ቤተሰቦቻችንን የማጠንከር ፃድቅ ጥረቶቻችንን ያበለፅጋል።

ከሚያድኑት መካከል ትቆጠሩ ዘንድ አድካሚ እና ፃድቅ የሆነውን ጥረቶቻችሁን እና እናንተን ጌታ ይባርክ። ይህ ፀሎቴ ነው በእየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።