2010–2019 (እ.አ.አ)
በሁሉም ነገሮች ተቃርኖ
ኤፕረል 2016


በሁሉም ነገሮች ተቃርኖ

ተቃራኒ ወደ ሰማይ አባት እንድንሆን ወደሚፈልገው ለማደግ ይፈቅድልናል።

በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ ዋናው ለልጆቹ ዘለአለማዊ እድገት ያለው የሰማይ አባት እቅድ ነው። ያም እቅድ፣ በዚህ ዘመን ራዕዮች የተገለጸው፣ በሟችነት የሚያጋጥሙንን ብዙ ነገሮች እንድንገነዘብ ይረዳናል። መልእክቴ በዚያ እቅድ ላይ ተቃውሞ ምን አስፈላጊ ክፍል እንዳለው ነው።

ለእግዚአብሔር ልጆች የህይወት አላማ “ወደ ፍጹምነት እና በመጨረሻም እንደ ዘለአለም ህይወት ወራሾች መለኮታዊ አጣ ፈንታቸውን ለማግኘት”1 የሚያስፈልጋቸውን አጋጣሚ ልመቀበል ነው። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን በዚህ ጠዋት በሀይለኛ ሁኔታ እንዳስተማሩት፣ የምናድገው በመምረጥ ነው፣ በዚህም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንደምንጠብቅ እንፈተናለን (አብርሐም 3፥25 ተመልከቱ)። ለመፈተን በተለያዩ ምርጫዎች መካከል ለመምረጥ ነጻ ምርጫ ያስፈልገናል። ነጻ ምርጫችንን ለመጠቀም የምንችልበት ሌላ ዘዴ ለማቅረብ፣ ተቃራኒዎች ያስፈልጉናል።

የቀሩት ዕቅድ ክፍሎችም አስፈላጊ ናቸው። ማድረጋችን በማይቀርበት ሁኔታ፣ ትክክል ያልሆኑ ምርጫዎችን ስናደርግ፣ በኃጢያት ተጎድፈናል እናም ወደ ዘለአለማዊ እጣ ፈንታችን ፊት ለመሄድ መጸዳት አለብን። የአብ እቅድ ይህን ለማድረግ መንገድ፣ የፍትህ ዘለአለማዊ ጥያቄን ለሚያረካ መንገድ ሰጠ፥ አዳኝ ከኃጢያቶቻችን ለማዳን ዋጋውን ከፈለ። አዳኝ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የዘለአለም አብ እግዚአብሔር አንድያ ልጅ፣ የኃጥያት ክፍያው—ስቃዩ—ንስሀ የምንገባላቸው ከሆንን ለኃጢያጦጫችን ዋጋ የከፈለው ነው።

በእቅድ ውስጥ የነበረው የተቃዋሚነት ክፍል ከሁሉም የሚሻል መግለጫም የሚገኘው በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ ሌሂ ልጁን ያዕቆብን ማስተማረበት ውስጥ ነው።

“ለሁሉም ነገሮች ተቃራኒ መኖር አስፈላጊ ነውና። ካልሆነ ግን፣… ፅድቅ፣ ኃጥያት፣ ቅድስና ወይም መከራ፣ ጥሩ ወይም መጥፎ መኖር አይችልም” (2 2፥11፤ ደግሞም ቁጥር 15ተመልከቱ)።

ሌሂም እንደቀጠለው፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሰው በራሱ እንዲያደርግ ሰጠው። ስለዚህ፣ ሰው በአንዱ ወይም በሌለኛው ካልተሳቡ በስተቀር ለራሱ ማድረግ አይቻለውም” (ቁጥር16). በዚህም አይነት፣ በዚህ ዘመን ራዕይ ውስጥ ጌታ እንዳወጀው፣ “እናም ሰይጣን የሰዎችን ልጆች ይፈትን ዘንድ ግድ ነው፣ ይህ ካልሆነ በራሳቸው መምረጥ አይችሉምና” (ት. እና ቃ. 29፥39)።

ተቃራኒ በገነት የአትክልት ስፍራ ውስጥ አስፈላጊ ነበር። አዳም እና ሔዋን ሟችነትን እንዲያስተዋወቁ ያደረገውን ምርጫ ባያደርጉ ኖሮ፣ ሌሂ እንዳስተማረው፣ “በየዋህነት ይቆዩ ነበር፣ … ኃጥያትን ባለማወቃቸው መልካምን አይሰሩም” (2 ኔፊ 2፥23)።

ከመጀመሪያው ጀምሮ፣ ነጻ ምርጫ እና ተቃራኒ በአብ እቅድ ውስጥ እና ሰይጣን ላመጸበት ዋና ክፍል ነበሩ። ታ ለሙሴ እንደገለጸው፣ በሰማይ ሸንጎ ውስጥ ሰይጣን “የሰው ነጻ ምርጫ ለማጥፋት [ፍለገ]” (ሙሴ 4፥3)። ያም ድምሰሳ ሰይጣን ባቀረበው ሀሳብ ላይ ግልፅ ነበር። በአብ ፊት መጣ እና እንዲህ አለ፣ “እነሆ፣ አለሁ፣ እኔን ላከኝ፣ ልጅህም እሆናለሁኝ፣ እና አንድም ነፍስ እንዳይጠፋ፣ የሰውን ዘር አድናለሁ፣ እና በእርግጥም ይህን አደርጋለሁ፤ ስለዚህ ክብርህን ስጠኝ” (ሙሴ 4፥1)።

በዚህም፣ ሰይጣን የአብን አላማ ማከናወንን በሚገድብ እና ሰይጣንን የእርሱን ክንር በሚሰጥ መንገድ የአብን እቅድ ለማከናወን ሀሳብ አቀረበ።

ሰይጣን አላማ ፍጹም የሆነ እኩልነትን የሚያረጋግጥ ነበር፥ ይህም አንድ ነፍስም ሳይጠፋ “የሰውን ዘር በሙሉ ያድናል።” ምንም ነጻ ምርጫ ወይም በማንም ምርጫ የለም፣ ስለዚህ ተቃራኒ ምንም አያስፈልግም። ምንም ፈተና፣ ምንም ውድቀት፣ ምንም ስኬታማ የለም። አብ ለልጆቹ የፈለገው አላማን ለማግኘት ምንም እድገት አይኖርም። ቅዱሳት መጻህፍት እንደመዘገቧቸው የሰይጣን ተቃራኒነት “በሰማይ ጦርነት”(ራዕይ 12፥7)፣ ተፈጸመ፣ በዚህም ከአንድ ሶስተኛው በስተቀር ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች የአብን እቅድ በመምረት እና የሰይጣንን አመጽ በማስወገድ ስጋዊ ህይወትን ለመለማመድ መብትን አገኙ።

የሰይጣን አላና የአብን ክብርና ሀይል ለራሱ ለመስጠት ነበር ( ኢሳይያስ 14፥12–15ሙሴ 4፥1፣ 3)። “ስለዚህ፣” አብ አለ፣ “ሰይጣን ስለዐመፀብኝና፣ … እንዲጣል አደረግሁኝ” (ሙሴ 4፥3) እርሱን ለመከተል ነጻ ምርጫቸውን ከተጠቀሙበትም ጋር (ይሁዳ 1፥6ራዕይ 12፥8–9ት. እና ቃ. 29፥36–37)። ሰውነት እንደሌላቸው ነፍሶች በሟችነት ተወርውረው፣ ሰይጣን እና ተከታዮቹ የእግዚአብሔርን ልጆች ፈተኑ እናም ለማታለል እና ምርኮኛ ለማድረግ ፈለጉ ( ሙሴ 4፥4)። የአብን እቅድ የተቃወመው እና ለማጥፋት የፈለገው፣ ያ ክፉው፣ በእርግጥም ይህም እንዲያከናውን ረዳው፣ ምክንያቱም የዚህ ተቃራኒ ምርጫን እንዲያችል አደረገ እና ይህም ትክክለኛ ምርጫዎችን የማድረግ እድል ነው የአብ እቅድ ወደሆነው ወደ እድገት የሚመራው።

፪.

ከዚህ በሚበልጥም፣ ኃጢያት ለመስራት ያለ ፈተና በሟችነት የሚገኝ የተቃራኒነት አይነት ብቻ አይደለም። አባት ሌሂ እንዳስተማረው ውድቀት ባይደርስ ኖሮ፣ አዳም እና ሔዋን “በየዋህነት ይቆዩ ነበር፣ ደስታ አይኖራቸውም፣ መከራንም አያውቁምና” (2 ኔፊ 2፥23)። ያለስጋዊነት በሚገኝ ተቃራኒ ደስታም ሆነ መከራ በማይገኝበት “ሁሉም ነገሮች በአንድነት ሊጣመሩ ይገባል” (ቁጥር 11)። ስለዚህ፣ አባት ሌሂ ቀጠለ፣ እግዚአብሔር ሁሉን ነገሮች የፈጠረው “ዘለዓለማዊ አላማውን ወደ ሰው ዘር የመጨረሻ ሁኔታ ለማምጣት፣ … ተቃራኒ መኖሩ አስፈላጊ ነበር፤ እንዲሁም አንዱ ጣፋጭ ሲሆን ሌላኛው መራራ እንደሆነው የተከለከለውም ፍሬ እንደ ህይወት ዛፍ ተቃራኒ ነበር” (ቁጥር 15)።2 በዚህ የደህንነት እቅድ ክፍል ውስጥ ያጽጠማረው፡የተፈጸመው እንዲህ ነበር፥

“ነገር ግን እነሆ፣ ሁሉም ነገሮች የተደረጉት ሁሉንም ነገሮች በሚያውቀው በጌታ ጥበብ ነው።

“ሰዎች እንዲኖሩ፣ አዳም ወደቀ፤ እና ሰዎች የሚኖሩትም ደስታም እንዲኖራቸው ዘንድ ነው” (ቁጥሮች 24–25)።

በስጋዊነት በሚያጋጥሙን አስቸጋሪ ጉዳዮች ውስጥ ያለው ታቃራኒ የሟችነት እድገታችን እንዲቀጥል የሚያደርግ የእቅዱ ክፍል ነው።

፫.

ሁላችንም የሚፈትኑን የተለያዩ ተቃራኒዎች ያጋጥሙናል። አንዳንዶቹ እነዚህ ፈተናዎች ኃጢያት የመስራት ፈተናዎች ናቸው። አንዳንድም ከግል ኃጢያት የተለዩ የሟችነት ፈተናዎች ናቸው። አንዳንዶች በጣም ከባድ ናቸው። አንዳንዶች ቀላል ናቸው። አንዳንድ የሚቀጥሉ፣ እና አንዳንድም ለአጭር ጊዜ የሆኑ ናቸው። ምንኛችንም ከዚህ ነጻ አይደለንም። ተቃራኒ ወደ ሰማይ አባት እንድንሆን ወደሚፈልገው ለማደግ ይፈቅድልናል።

ጆሴፍ ስሚዝ መፅሐፈ ሞርሞንን ለመተርጎም ከጨረሰ በኋላ፣ የሚያትምለት ማግኘት ነበረበት። ይህም ቀላል አልነበረም። የዚህ ረጅም መፅሐፍ ውስብስብነት እና ብዙ ሺህ ግልባጮችን የማተም እና የማጣመድ ክፍያ የሚያስፈራ ነበር። ጆሴፍ በመጀመሪያ የፓልማይራ አሳታሚውን ኢ. ቢ. ግራንዲንን ጠየቀ፣ እርሱም እምቢ አለ።። ከዚያም በፓልማይራ ውስጥ ያለን ሌላ አሳታሚ ጠየቀ፣ እርሱም እምቢ አለው። በ40 ኪሎ ሜትር ወደሚርቀው ወደ ሮቸስተር ተጓዘ፣ እናም በምዕራብ ኒው ዮርክ ውስጥ ታዋቂ የነበረውን አሳታሚ ጠየቀ፣ እርሱም እምቢ አለው። ሌላ የሮቸስተር አሳታሚ ፈቃደኛ ነበር፣ ነገር ግን ጉዳዮች ይህን ሌላ ምርጫ ተቀባይ እንዳይሆኑ አደረጉ።

ሳምንቶች አለፉ፣ እናም ጆሴፍ መለኮታዊ ሀላፊነቱን ለማከናወን ባገኘው ተቃራኒ ተደናገሮ ነበር። ጌታ ይህን ቀላል አላደረገውም፣ ነገር ግን ይህን የሚቻል አደረገው። የጆሴፍ አምስተኛው ሙከራ፣ በፓልማይራ አሳታሚው ግራንዲን ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበበት፣ ውጤታማ ነበር።3

ከአመቶች በኋላ፣ ጆሴፍ በሊብርቲ እስር ቤት ውስጥ ለብዙ ወሮች በእስር ቤት ታስሮ ነበር። ለእረፍት በሚጸልይ ጊዜ፣ ጌታ እንዲህ ነገረው “aመንገድህን ለማሰናከል ቢጣመሩ፤ እና ከሁሉም በላይ፣ የሲኦል መንጋጋም አፍዋን በሰፊው ብትከፍትብህ፣ ልጄ ሆይ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለአንተ ልምድ እንደሚሰጡህ እና ለአንተ ጥቅም” ይሰጡሀል (ት. እና ቃ. 122፥7)።

ሁላችንም በግል ኃጢያቶች፣ በተጨማሪም ህመሞች፣ አካለ ስንኩልነት፣ እና ሞት፣ ምክንያት ካልነበራቸው ከሌሎች አይነት የሟች ተቃራኒ ጋር የተዋወቅን ነን። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንደገለጹት፥

“አንዳንዶቻችሁ በስቃይ፣ ለምን የሰማይ አባት የሚያጋጥማችሁን ፈተናዎች እንድኖሩባቸው እንደሚፈቅድ በማሰብ አንዳንዴም ታለቅሳላችሁ። …

“ሟች ህይወታችኑ፣ ግን፣ ቀላል ወይም ሁልጊዜም አስደሳች እንዲሆን የነብረ አይደለም። የሰማይ አባታችን … በከባድ ፈተናዎች፣ ልብን በሚሰብር ሀዘኖች፣ እና በአስቸጋሪ ምርጫዎች እንደምንማርና እንደምናድግ እናም እንደምንጠራ ያውቃል። እያንዳንዳችን የምናፈቅራቸው ሲሞቱ፣ ጤንነታችን የጠፉባቸው የህመም ጊዜዎች፣ የምናፈቅራቸው እኛን እንደተዉ በሚመስልበት ጊዜ የሚሰማን ችላ መባል ያጋጠሙን የጨለሙ ቀናት፡አጋጥመውናል። እነዚህ እና ሌሎች ፈተናዎች ለመፅናት ያለንን ችሎታን የሚፈትኑ እውነተኛ ፈተናዎችን ያቀርቡልናል።”4

የሰንበት ቀን ለማክበር የምናደርጋቸው ጥረቶቻችን የቀነሰ ጭንቀት ያለው የተቃራኒ ምሳሌ ነው። ሰንበትን እንድናከብር የጌታ ትእዛዝ አለን። አንዳንዱ ምርጫዎቻችን ያን ትእዛዝ ይተላለፋሉ፣ ነገር ግን እንዴት የሰንበት ጊዜ እንድምናሳልፍ የምናደጋቸው ሌሎች ምርጫዎች መልካሙን ወይም ከዚህ የሚሻለውን ወይም የሚበልጠውን እንደምናደርግ ያለን ጥያቄ የሚመልሱ ናቸው።5

ይህን የፈተናዎች ተቃራኒ በምሳሌ ለማሳየት፣ መፅሐፈ ሞርሞን ዲያብሎስ በመጨረሻው ቀናት የሚጠቀምባቸውን ሶስት ዘዲዎች ይገልጻል። መጀመሪያ፣ “በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ይቆጣል፣ እናም ጥሩ በሆነውም ላይ ለቁጣ ያነሳሳቸዋል” (2 ኔፊ 28፥20)። ሁለተኛ፣ “[አባላትን] ያረጋጋልና፣ ቀስ ብሎም ወደ ስጋዊ ደህንነት” እንዲህ በማለት፣ “ፅዮን ትለመልማለች፤ ሁሉም መልካም ነው” ያባብላል (ቁጥር 21)። ሶስተኛ፣ “ሲኦል የለም ፤ … እኔ ዲያብሎስ አይደለሁም፣ እርሱ የለምና” ይለናል (ቁጥር 22)፣ እናም ስለዚህ ምንም ትክክል እና ስህተተኛ የለም። በዚህ ተቃራኒ ምክንያት፣ “በፅዮን [እንዳንዝናና]!” ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል። (ቁጥር 24)።

ቤተክርስቲያኗ በመለኮታዊ ሚስዮኗ እና እኛም በግል ህይወታችን ውስጥ ዛሬ ተጨማሪ ተቃራኒ የሚያጋጥመን ይመስላል። ምናልባት ቤተክርስቲያኗ በጥንካሬ ስታድግ እና እኛ አባላትም በእምነት እና በታዛዥነት ስናድግ፣ ሰይጣን የተቃራኒነቱን ጥንካሬ ይጨምራል ስለዚህ “በሁሉም ነገሮች ተቃራኒ” ሲኖረን ይቀጥላል።

አንዳንዶቹ ተቃራኒዎችም ከቤተክርስቲያኗ የሚመጡ ናቸው። አንዳንዳችን የግል ምክንያቶች ወይም ጥበብ የነቢያትን መመሪያዎች ለመቃወም በመጠቀም ከተመረጡ ሰዎች የተበደሩትን ስም ይጠቀማሉ-- “ታማኝ ተቃራኒ”። በዲሞክራሲ ይህ ትክክለኛ ቢሆንም፣ ጥያቄ በሚከበሩበት እና ተቃራኒነት በማይገቡበት ቦታ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለዚህ አይነት አስተያየት ምንም ቦታ የለውም (ማቴዎስ 26፥24 ተመልከቱ)።

እንደ ሌላ ምሳሌ፣ በቤተክርስቲያናችን የመጀመሪያ ታሪኮች ውስጥ አንዳንዶች ለተቃራኒነት የሚጠቀሙባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ለሁሉም፣ እምነትን ተለማመዱበት እና “ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ” በሚለው በአዳኝ ትምህርት ላይ መመካት ይገባናል እላቸዋለሁ (ማቴዎስ 7፥16)። ቤተክርስቲያኗ ያለንን መዝገቦች በግልፅነት ለማሳየት ታላቅ ጥረት እያደረገች ነው፣ ነገር ግን ልናትማቸው ከምንችላቸው በኋላም፣ አባላቶቻችን በጥናት መረካት የማይችሉ ጥያቄዎች ይቀሯቸው ይሆናል። ያም የቤተክርስቲያኗ ታሪክ “በሁሉም ነገሮች ተቃራኒነት” የሚሆነው ነው። አንዳንድ ነገሮች በእምነት ብቻ ለመማር ይቻልባቸዋል (ት. እና ቃ. 88፥118)። በመጨረሻም የምንመካበት ከመንፈስ ቅዱስም ምስክርነት የተቀበልነው እምነት መሆን አለበት።

እግዚአብሔር ለሌሎች እረፍት በማለት በማንኛውም ልጆቹ ነጻ ምርጫ ላይ በጣልቃ ሁልጊዜም አይገባም። ነገር ግን ልክ ለአልማ ህዝብ በሄላም ምድር ላይ እንዳደረገው የስቃይን ሸከም ያቀልላል እናም እንድንሸከማቸው ያጠናክረናል። (ሞዛያ 24፥13–15ተመልከቱ)። መአቶችን ሁሉ አያስገድብም፣ ነገር ግን በፊጂ ቤተመቅደስ መቀደስን እንዳይፈጸም ያስፈራራውን አውሎ ንፋስ እንኒዞር እንዳደረገው አይነት፣6 ወይም ብዙ ህይወቶችን ያጠፋውን የአሸባሪዎች ቦምብ አራቱን ሚስዮኖቻችንን በጉዳት ብቻ እንዲያመልጡ እንዳደረገው አይነት፣ ውጤታቸውን በማስቀነስ፣ እነዚህ ዞር እንዲሉ ለምንጸልየው መልስ ይሰጣል።

በሟች ተቃራኒነት በሙሉ፣ “መከራችንን ወደ [ጥቅማችን] [እንደሚለውጥ]” የእግዚአብሔር ማረጋገጫ አለን (2 ኔፊ 2፥2)። የሟች አጋጣሚዎቻችንን እና የእርሱን ትእዛዛት፣ የህይወት አላማ ምን እንደሆነ በሚነግረን እና በአዳኝ ማረጋገጫ በሚሰጠን በደህንነት እቅዱ በኩል እንድንገነዘብም ተምረናል፣ በእርሱም ስም ስለእነዚህ ነገሮች እውነትነት የምመሰክረው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅ፣”Liahona፣ ህዳር 2010፣ 129 ተመልከቱ።

  2. በተመሳሳይም፣ የዚህ ዘመን ራዕይ እንደሚያስተምረው፣ መራራው በምንም ካልነበረን፣ ጣፋጩን፡ለማወቅ አንችልም ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 29፥39)።

  3. Michael Hubbard MacKay and Gerrit J. Dirkmaat, From Darkness unto Light: Joseph Smith’s Translation and Publication of the Book of Mormon (2015), 163–79።

  4. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “Joy in the Journey” (address given at the BYU Women’s Conference, May 2, 2008), womensconference.ce.byu.edu. አሁን የቢዋዩ ሀዋዪ ፕሬዘደንት የሆኑት፣ ጆን ኤስ. ታነር፣ ይህን አስተያየት ሁላችን ስለምናውቀው ርዕስ ስለመልካም የስፖርት ተጫዋችነት እና ዲሞክራሲ በጻፉበት ውስጥ ጨምረው ነበር፥ “በጸጋ ምሸነፍን መቀበል የህብረተሰብ ሀላፊነት ብቻ አይደለም፤ ይህም የሀይማኖታዊ ሀላፊነት ነው። እግዚአብሔር ሟችነትን የነደፈው ‘በሁሉም ነገሮች ተቃራኒን’ ለማረጋገጥ ነው (2 ኔፊ 2፥11)። ወደኋላ መሄድ እና መሸነፍ የእኛ ፍጹምነት እቅዱ ክፍል ነው። … ‘ፍጹም ለመሆን ባለን አላማ’ ውስጥ መሸነፍ አስፈላጊ ሁኔታነው” (Notes from an Amateur: A Disciple’s Life in the Academy [2011], 57).

  5. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “Good, Better, Best,” Liahona, Nov. 2007, 104–8 ተመልከቱ።

  6. Sarah Jane Weaver, “Rededication Goes Forward,” Church News, Feb. 28, 2016, 3 ተመልከቱ።