2010–2019 (እ.አ.አ)
ከአውሎ ነፋሱ ስደተኛ
ኤፕረል 2016


ከአውሎ ነፋሱ ስደተኛ

ይህ ወቅት እነሱን አይገልፃቸውም፣ ነገር ግን የእኛ ምላሽ እነሱን ለመግለፅ ይረዳቸዋል።

“ተርቤ አብልታችሁልኛልና፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፤

“ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥

“… እውነት እላችኋለሁ፣ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።”1

ዛሬ በዓለም ላይ 60 ሚሊየን የሚገመቱ ስደተኞች አሉ፣ ይህም ማለት “ከ122 ሰዎች መካከል 1 … ቤቱን ትቶ ለመሄድ ተገዷል።”2 እናም ከእነዚህ ግማሾቹ ልጆች ናቸው።3 የተጋለጡትን ሰዎች የቁጥር ብዛት ማሰብ እና በእያንዳንዱ ግለሰብ ሕይወት ውስጥ ይህ ምን ማለት እንደሆነ መገመት አስደንጋጭ ነው። የአሁኑ የስራ ድርሻዬ አንድ እና እሩብ ሚሊዮን የሚሆኑት እነዚህ ስደተኞች ጦርነት ካፈራረሳቸው ከመሃል ምስራቅና ከአፍሪካ ባለፈው ዓመት በመጡባት በአውሮፓ ውስጥ ነው።4 ብዙዎቹ በለበሱት ልብስ እና በትንሽዬ ሻንጣ መሸከም የሚችሉትን ብቻ ይዘው ሲመጡ እናያለን። አብዛኛዎቹ በደንብ የተማሩ ናቸው እናም ሁሉም ቤቶችን፣ ትምህርት ቤቶችንና ስራዎችን መተው ነበረባቸው።

በቀዳም አመራር መሪነት መሰረት ቤተክርስቲያኗ በ17 አገራት ውስጥ ከ75 ድርጅቶች ጋር አብራ እየሰራች ነች። እነዚህ ድርጅቶች ከትልቅ አለም አቀፋዊ ተቋሞች እስከ ትንሽ ማህበራዊ መነሳሳቶች፣ ከመንግስት ወኪሎች እስከ እምነት ላይ ያተኮሩና መንፈሳዊ ያልሆኑ ግብረ-ሰናዮች ይዘልቃሉ። ለብዙ ዓመታት በአለም ዙሪያ ከስደተኞች ጋር አብረው ከሰሩ ሰዎች ጋር በማበራችንና ከእነሱ በመማራችን እድለኞች ነን።

እንደ የቤተክርስቲያኗ አባሎች፣ እንደ ህዝብ፣ በታሪካችን ውስጥ ወደ ኋላ ተመልሰን በተደጋጋሚ ከቤታችንና ከእርሻችን በኃይል ተባረን ስደተኞች የነበረንበትን ጊዜ ለማስታወስ ወደኋላ ለብዙም ጊዜ መመልከት አያስፈልገንም። ባለፈው የሳምን ት መጨረሻ ላይ ስለስደተኞች እየተናገረች፣ እህት ሊነዳ በርተን የቤተክርስቲያኗን ሴቶች እንዲያስቡበት እንዲህ ብላ ጠየቀች፣ “የእነሱ ታሪክ የእኔ ታሪክ ቢሆንስ።”5 ብዙ አመታት ባላልፉበት ጊዜ፣ የእነሱ ታሪክ የኛ ታሪክ ነው

በመንግስቶችና በመላ ማህበረሰቦች ውስጥ ስለስደተኛ ትርጉምና ተሰዳጆችን ለመርዳት ምን መደረግ እንዳለበት አስመልክቶ ትልቅ አለመግባባቶች አሉ። እነዚህ ሃሳቦች በምንም ዓይነት መንገድ በዛ የሞቀ ውይይት ላይ ቅርፅ እንዲይዙ፣ ወይም ስለስደት ፖለሲ ሀሳብን ለማቅረብ፣ የታለሙ አይደለም፣ ነገር ግን ከቤታቸውና ከአገራቸው በጦርነት ተሰደው ኑሮ ለመጀመር ምንም የሌላቸው ሰዎች ላይ ለማተኮር እንጂ።

አዳኙ ስደተኛ መሆን ምን አይነት ስሜት እንዳለው ያውቃል---በአንድ ወቅት እርሱም ነበረ። እንደ ወጣት ልጅ፣ ኢየሱስና ቤተሰቡ የሄሮድን ገዳይ ጎራዴዎች ለማምለጥ ወደ ግብፅ ሸሹ ። እናም ኢየሱስ በአገልግሎቱ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ማስፈራሪያ ደርሶበትና ሕይወቱ አደጋ ውስጥ ሆኖ አገኘ፣ ከዛም መጨረሻ ላይ ሞቱን ላሴሩ ለመጥፎ ሰዎች እራሱን አሳልፎ ሰጠ። ምናልባት እርስ በእርስ እንድንዋደድ፣ እርሱ እደወደደው እንድንወድ፣ ጎረቤቶቻችንን እንደራሳችን እንድንወድ በተደጋጋሚ ያስተማረን በጣም አስገራሚ የሆነብን። በእውነት “ንጹህ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፣ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ”6 እና “ድሆችን እና ችግረኞችን ይንከባከባሉ፣ እንዳይሰቃዩም በሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ ያገልግሏቸዋል”7

በዓለም ዙሪያ ያሉት የቤተክርስቲያኗ አባሎች እነዚህን ግለሰቦችና እጅግ ብዙ ያጡትን ቤተሰቦች ለመርዳት በደግነት ያዋጡትን መዋጮ መመልከት አነሳሽ ሆኗል። በተለይ በመላ አውሮፓ ለሌሎች ለመድረስ ላላቸው የጥልቅ ምኞት ምላሽ ሲሰጡና በዙሪያቸው ላሉት ከፍተኛ ፍላጎት ሲያገለግሉ የመንፈስን አስደሳች መንቃትና መጎልበት የተለማመዱ ብዙ የቤተክርስቲያኗን አባሎች አይቻለሁ። ቤተክርስቲያኗ መጠለያዎችንና የህክምና አገልግሎትን አቅርባለች። ካሳማዎችና ሚስዮኖች ብዙ ሺዎች የሚሆኑ የጤና መሳሪያዎችን ሰብስበዋል። ሌላ ካስማዎች ምግብና ውኃን፣ አልባሳትን፣ ውኃ የማያስገቡ ኮቶችን፣ ብስክሌቶችን፣ መጽሐፍቶችን፣ የጀርባ ቦርሳዎችን፣ የንባብ መነፅሮችን እና ብዙ ነገሮችን አቅርበዋል።

ከስኮትላንድ እስከ ሲሲሊ ያሉ ግለሰቦች በሁሉም የሚቻሉ ሚናዎች ላይ ተሳትፈዋል። ስደተኞች በስብሰው፣ በርዷቸውና ውኃዎችን በመሻገራቸው ደንዝዘው በደረሱበት ሰዓት ዶክተሮችና ነርሶች አገልግሎታቸውን ለግሰዋል። ስደተኞች መልሶ የመስፈርን ሂደት ሲጀምሩ እዛው ያሉ ሰዎች የተቀበላቸውን አገራት ቋንቋዎች እንዲማሩ እየረዷቸው ነው፣ ሌሎችም አሻንጉሊቶችን፣ ጥበባቶችን፣ ሙዚቃዎችን እና መጫወቾችን በማቅረብ የልጆችንና የቤተሰቦችን መንፈስ ከፍ እያደረጉ ነው። አንዳንዶች የተዋጡ ክሮችን፣ የመስፊያ መርፌዎችን እና ኪሮሶችን እየወሰዱ እነዚህን ችሎታዎች እዛ ለሚገኙ ለአረጁና ወጣት ስደተኞች እያስተማሩ ነው ።

የአመታት አገልግሎቶችንና አመራርን የሰጡ የቤተክርስቲያኗ አባሎች ለእነዛ እርዳታ ለሚሹ ሰዎች “ሁሉንም በውስጣቸው ግሩም የሆኑት በማዳን” የአገልግሎት ልምድ እንደሰጣቸው ይመሰክራሉ።

የእነዚህ ሁኔታዎች እውነታ ለመታመን መታየት አለባቸው። በክረምት ውስጣ ከብዙዎች መካከል በስደተኞች መሸጋገሪያ ካምፕ ውስጥ ልጇን በተሰጣት ሰፊ አዳራሽ ቀዝቃዛ ወለል ላይ እንደማትወልድ ማረጋገጫ የፈለገችን ከሲሪያ የመጣች እርጉዝ ሴትን አገኘሁ። በሲሪያ የአንድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ነበረች። እናም በግሪክ ውስጥ በትንሽዬ የጎማ ጀልባ ከቱርክ አቋርጠው በመምጣታቸው አሁንም ከበሰበሱ፣ ከሚንቀጠቀጡና ከፈሩ ቤተሰቦች ጋር ተነጋገርኩኝ። ከሸሹበት አስፈሪ ነገርና መጠለያ ለማግኘት ካደረጉት አደገኛ ጉዞ አይናቸውን ካየሁና ታሪካቸውን ከሰማሁ በኋላ እንደ ድሮው መሆን አልችልም።

እንክብካቤና ዕርዳታ መስጠት የሰራተኞች አብዛኛውን የፈቃደኞች ሰፊ መሰጠት ነው። አንድ የቤተክርስቲያኗን አባል ከቱርክ ወደ ግሪክ ለሚመጡት ሰዎች አፋጣኝ ፍላጎታቸው አቅርቦት እየሰጠች ለብዙ ወራት በማታ ስትሰራ አየሁ። ከብዙ ሌሎች ስራዎች መካከል የህክምና ዕርዳታ ለሚሹት ሰዎች የመጀመሪያ ዕርዳታ ግልጋሎት ሰጠች፣ ብቻቸውን የሚጓዙ ሴቶችና ልጆች እንክብካቤ እንዲያገኙ አደረገች፣ በመንገድ ላይ ሀዘን የደረሰባቸውን ሰዎች ያዘች እናም የተወሰኑ ጥሬ ዕቃዎችን ውስን ለሌለው ፍላጎቶች ለማሰማራት የተቻላትን አደረገች ። እንደ እሷ በሆኑ ብዙ ሰዎች የእሷ ስራ በእርሱ አገልግሎት ተልዕኮ ስር በነበረችው በጌታ እና በተንከባከበቻቸው ሰዎች የማይረሳ ትክክለኛ የመልአክ አገልጋይ ነበረች።

በዙሪያቸው ያለውን ስቃይ ለማብረድ እራሳቸውን የሰጡ ሰዎች በሙሉ ልክ እንደ አልማ ሕዝቦች ናቸው፥ “እናም እንዲሁ፣ በብልፅግናቸው የተራቆተ ወይም የተራበ፣ ወይም የተጠማ፣ የታመመም ቢሆን ያልተመገበም ቢሆን ማንንም አላባረሩም፤ ለሁሉም፣ ለወጣቶችም ሆነ ለሽማግሌዎች፣ ለታሰሩትም ሆነ ነፃ ለሆኑት፣ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች፣ ከቤተክርስቲያን ለሆኑም ሆነ ላልሆኑት ደግ ነበሩ፤ በችግር ለነበሩት እንዳደረጉት ሁሉ በሰዎች ፊት አላደሉም።”8

የመጀመሪያው ድንጋጤ ሲጠፋና ጦርነቱ ሲቀጥልና ቤተሰቦች መምጣታቸውን ሲቀጥሉ የስደተኞች መጥፎ ሁኔታ ዜና የተለመደ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብ። ታሪካቸው ዜና መሆን ያቆመ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሚሊዮኖች የሚሆኑ ስደተኞች አሁንም አስቸኳይ የዕርዳታ ፍላጎት ላይ ናቸው ።

“ምን ላድርግ?” ብላችሁ ከጠየቃችሁ መጀመሪያ በቤተሰቦቻችን ወጪና በሌሎች ኃላፊነቶች ማገልገል እንደሌለብን እናስታውስ፣9 እንዲሁም መሪዎቻችንን ለእኛ ፕሮጀክት እንዲያዘጋጁልን መጠበቅ የለብንም ። ነገር ግን እንደ ወጣት፣ ወንዶች፣ ሴቶች፣ እና ቤተሰቦች በዚ ታላቅ የበጎ አድራጎት ስራ ውስጥ መቀላቀል እንችላለን።

በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ስደተኞች በክርስቶስ መሰል አገልግሎት እዲሳተፉ ለቀረበው10 የቀዳሚ አመራር ግብዣ መልስ የሴቶች መረዳጃ፣ የወጣት ሴቶች እና የመጀመሪያ ክፍል አጠቃላይ ፕሬዘደንቶች “እኔም እንግዳ ነበርኩኝ” የሚል የዕርዳታ ሙከራዎች አዘጋጅተዋል። እህት በርተን ይህን ለቤተክርስቲያኗ ሴቶች ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በአጠቃላይ የሴቶች ስብሰባ ላይ አስተዋወቀች። በIWasAStranger.lds.org ላሉ አገልግሎቶች ብዙ የሚረዱ ሃሳቦች፣ ግብአቶች እና ሃሳብ ማቅረቢያዎች አሉ።

በጉልበታችሁ በመሆን በመጽለይ ጀምሩ። ከአዲስ ሁኔታዎች ጋር ለመለማመድ እርዳታ የሚፈልጉ ሶዎችን በምታገኙበት ከቤት አቅራቢያ፣ በማህበረሰባችሁ ውስጥ የሆነ ነገር ለማድረግ አስብ። እርዳታ ለሚሹ የሚደረገው የማንኛውም አገልግሎት አላማ የስራ ሰዎች እንዲሆኑና እራሳቸውን የሚያስችል ሕይወት እንዲኖራቸው ለመርዳት ነው።

የእርዳታ እጅን የምናውስበት መንገዶች መጨረሻ የላቸውም። መልሰው የሰፈሩት ስደተኞች የተቀበላቸውን አገር ቋንቋ እንዲማሩ፣ የስራ ክህሎታቸውን እንዲያድሱ ወይም የስራ ቃለ መጠይቆችን እንዲለማመዱ መርዳት ትችላላችሁ። ቤተሰብን ወይም አያላገባች እናትን ወደማያውቁት ባህል ሲገቡ፣ ወደ ምግብ መግዢያ ወይም ወደ ትምህርት ቤት አብሮ በመሄድ ቀላልበሆነው መንገድም፣ እነርሱን ለማስተማር ፈቃደኛነታችሁን ለመግለጽ ትችላላቹ። አንዳንድ ዎርዶችና ካስማዎች በማበር ለመስራት የሚታመኑ ድርጅቶች አላቸው። እናም እንደራሳችሁ ሁኔታ ለቤተክርስቲያን የሚገርም የበጎ አድራጎት ስራ መስጠት ትችላላችሁ።

እያንዳንዳችን እነዚህን ቤተሰቦች ከቤታቸው የሚያባርሩትን የዓለም ክስተቶችን ግዛቤ መጨመር እንችላለን። ከአለመቻቻል በተቃራኒ መቆም አለብን እንዲሁም ለባህሎችና ልማዶች ክብርንና መረዳትን መጠበቅ አለብን። የስደተኛ ቤተሰቦችን ማግኘት እና ከእስክሪን ወይም ከጋዜጣ ሳይሆን በጆሮቻችሁ ታሪካቸውን መስማት ርህራሄን፣ ጓደኝነትን እና የተሳካ ስብስብን ለማጎልበት የበለጠ መስራት ይቻላል። እውነተኛ ጓደነት ይገነባል እናም ርህራሄን እና ውጤታማ እጓራነትን ያስገኛል

ጌታ የፅዮን ካስማዎች “ከአውሎ ነፋስ መጠጊያ”11 እና “መሸሸጊያ” እንደሚሆኑ መመሪያ ሰጥቶናል። ከደህና ቦታዎች ወጥተን በብዛት ካለን ነገር፣ የብሩህ ወደ ፊት ተስፋን፣ በእግዚአብሔርና በሰዎች እምነት ማድረግን፣ እና ከባህልና የአስተሳሰብ ልዩነት ባሻገር የሚያይ ፍቅርን ሁላችንም የሰማይ አባታችን ልጆች የመሆናችንን ክብራማ እውነታ እናካፍል።

“እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም።”12

ስደተኛ መሆን በስደተኞች ሕይወት ውስጥ ትርጉም የሚሰጥ ወቅት ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ስደተኛ መሆን እነሱን አይገልፃቸውም። ከእነሱ በፊት እንዳሉት የማይቆጠሩ ሺዎች ይህ ጊዜ በሕይወታቸው ውስጥ አጭሩ ጊዜ እንዲሆንላቸው እንመኛለን። አንዳንዶቹ የተከበሩ ሎሬቶች፣ የህዝብ አገላጋዮች፣ ሀኪሞች፣ ሳይንቲስቶች፣ ሙዚቀኞች፣ አርቲስቶች፣ የሀይማኖት መሪዎችና በሌላ መስኮች አስተዋፅዕ አበርካቾች ይሆናሉ። በእርግጥ አብዛኛዎቹ ሁሉን ነገር ከማጣታቸው በፊት እነኚህን ነገሮች ነበሩ። ይህ ወቅት እነሱን አይገልፃቸውም፣ ነገር ግን የእኛ ምላሽ እነሱን ለመግለፅ ይረዳቸዋል።

“ እውነት እላችኋለሁ፣ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።”13 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ለተጨማሪ መረጃ፣ IWasAStranger.lds.org እና mormonchannel.org/blog/post/40-ways-to-help-refugees-in-your-communityተመልከቱ።