2010–2019 (እ.አ.አ)
ራሳችሁን በቤተመቅደስ ውስጥ ተመልከቱ
ኤፕረል 2016


ራሳችሁን በቤተመቅደስ ውስጥ ተመልከቱ

እያንዳንዳችን አዳኝን እንድናከብር እና ራሳችንን በቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ ለማየት የሚያስችልንን ማንኛውን ለውጥ እንድናደርግ እጸልያለሁ።

በዚህ የሙሉነት ዘመን ጊዜ ወደ ፊት እየገሰገሰ ያለው የጌታ የመዳን እቅድ ከመረዳት አቅም በላይ ነው ማለት ይቻላል።1 በዚህ የጉባኤ ክፍል ላይ የ4 አዲስ ቤተመቅደሶችን ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ማስተዋወቃቸው የዚህ ምሳሌ ነው። በ1963 (እ.አ.አ) ፕሬዘዳንት ሞንሰን እንደ ሀዋርያ ተደርገው ሲጠሩ፣ በአለም ላይ በስራ ላይ ያሉ 12 ቤተመቅደሶች ብቻ ነበሩ።2 ዛሬ ከፕሮቮ ከተማ ሴንተር ቤተመቅደስ ቡራኬ ጋር 150 ናቸው፣ እንዲሁም ሁሉም የተተዋወቁት ቤተመቅደሶች ቡራኬ ሲሰጣቸው 177 ይሆናሉ። በትህትና ሀሴት እንድናደርግ ይህ ምክንያት ነው።

ከአንድ መቶ ሰማንያ አመት በፊት፣ በዚህች ቀን፣ ሚያዝያ 3፣ 1836 (እ.አ.አ)፣ በከርተላንድ ቤተመቅደስ ውስጥ ለነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ኮዋድሪይ እፁብ ድንቅ የሆነ ራእይ ታያቸው። ይህ የተከሰተው ቤተመቅደሱ ቡራኬ ከተደረገበት ልክ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነበር። በራእይ ውስጥ በቤተመቅደሱ ውስጥ ጌታን በመድረኩ መቆሚያ ላይ ቆሞ አዩት። ከሌሎች ነገሮች መሃል፣ ጌታ ይህንን አወጀ፤

“በሀይላቸው ይህን ቤት ለስሜ የገነቡት ህዝቦቼ ልብ ይደሰት።

“እነሆ፣ ይህን ቤተ ተቀብያለሁ፣ እናም ስሜም በዚህ ይሆናል፤ እናም በምህረት በዚህ ቤት ውስጥ ለህዝቤ ራሴን አሳያለሁ።”3

በዚያ ቅዱስ ጊዜ፣ የጥንት ነቢያት፣ በተጨማሪም ለቤተመቅደስ ስርዓቶች አስፈላጊ የሆኑትን ቁልፎች የሰጠው ኤልያስም፣ ታዩ።

ከአንድ አመት በፊት ቤተመቅደስ በባንኮክ፣ በታይላንድ፣ እንደሚገነባ ሲተዋወቅ ከነበረው በመነሳት በኩዊንቶ፣ ኤክወዶር፤ ሀራሬ፣ ዚምቧቤ፣ ቤሌም፣ ብራዚል፣ እና በሊማ ፔሩ በአባሎች እና በሚሲኦናዊያኖች ላይ እየተከሰተ ስላለው ደስታ በጥቂቱ ስሜቱ አለን። እህት ሼሊ ሲኒየር፣ በወቅቱ የታይላንድ ሚስዮን ፕሬዘዳንት የነበረው የዴቪድ ሲኒየር ሚስት የሆነችው፣ ፕሬዘዳንት ሞንሰን ያንን ቤተመቅደስ ካስተዋወቁ በኋላ “ለ12 ሰዓታት እንቅልፍ አልባነት እና ብዙ የደስታ እምባዎች” እንደነበር ለቤተሰብ እና ለጓደኞች ለመንገር ኢሜል አደረገች። Tበሚስዮን የሚረዷቸውን በማታ 5:30 ጠሩ እና ነገሯቸው። ረጆዎችን ሚስዮኖችን በሙሉ ጥሩ። “ሚስዮኑ በሙሉ በምሽት መሀከል ላይ ከመኝታ ዘልለው በመውረድ ከእንቅልስ ተነሱ” የሚል ሀተታ መጣ። እህት ሲኒየር በሚያስቅ ሁኔታ ቤተሰብ እና ጓደኖችን፣ “እባካችሁ ለምሽን ክፍል እንዳትነግሩ!” በማለት አስጠነቀቀቻቸው።4

በታይላንድ ያሉ አባላት ጥልቅ የመንፈሳዊ ምላሽ በእኩል ሁኔታ ጠንካራ ነበር። እነኚህ አዳዲስ የተዋወቁት ቤተመቅደሶች የት እንደሚገነቡ በልቦች፣ በቤቶች ውስጥ መንፈሳዊ ዝግጅቶች እና ከሰማይ ቅዱሳንን የሚያዘጋጁ መገለፆች እንደነበሩ እርግጠኛ ነኝ።

ምስል
Thai young women with a mirror that says, “See Yourself in the Temple.”

እህት ሲኒየር፣ በታይላንድ፣ ልዩ የሆኑ በእጅ የተሰሩ መስታዎቶችን ለግሏ አስተማረች፣ በተለይ ከእህቶች ጋር። በመስታዎት ላይ “ራስህን በቤተመቅደስ ውስጥ ተመልከቺ” የሚል የተጻፈበት የቤተመቅደስ ሰእል ተስሎበት ነበር። ሰዎች ወደ መስታወቱ አትኩረው ሲመለከቱ፣ እራሳቸውን በቤተመቅደስ ውስጥ ይመለከታሉ። አዲስ የቤተክርስቲያን ተከታታዎች እና የቤተክርስቲያን አባላት እራሳቸውን ቤተመቅደስ ውስጥ እንዲስሉ እና አስፈላጊውን የአኗኗር ዘይቤ እንዲቀይሩ እና መንፈሳዊ ዝግጅቶችን እንዲያደርጉ እነ ሲኒየር አስተማሩ።

ዛሬ በዚህ ጠዋት ለእያንዳንዳችን ያለኝ ፈተና፣ የትም እንኑር የት፣ እራሳችንን በቤተመቅደስ ውስጥ እንድናይ ነው። ፕሬዘዳንት ሞንሰን እንዲህ ገለፁ፤ “የጌታ ቤት ውስጥ እስክትገቡ እና እዛ የሚጠብቋችሁን በረከቶች እስክትቀበሉ ድረስ፣ ቤተክርስቲያኑ የሚያቀርባቸውን ነገሮች ሙሉ ለሙሉ አላገኛችሁም። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሚገኝ እና ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆኑ የአባልነት በረከቶች በእግዚአብሔር ቤተመቅደሶች ውስጥ የምንቀበላቸው በረከቶች ናቸው።”5

በአሁኑ ጊዜ የፅድቅ እጥረት ቢኖርም እንኳ፣ የምንኖረው በተቀደሰ፣ ቅዱስ ጊዜ ነው። ነቢያት፣ በፍቅር እና በሚናፍቅ ልብ፣ የኛን ዘመናት ለብዙ መቶ አመቶች ገልጸው ነበር።6

ነብዩ ዮሴፍ ስሚዝ፣ ከብሉ ኪዳን ላይ አብዲዩ 7 እና ከአዲስ ኪዳን 1ኛ ጴጥሮስ 8ን በመጥቀስ፣ ለሙታን ጥምቀትን በማዘጋጀት እና በፅዮን ተራራ ላይ አዳኞች እንድንሆን የፈቀደልንን የእግዚአብሔርን ታላቅ አላማ እውቅና ሰጠ።9

ጌታ ህዝባችን ሀብት እንዲበለፅጉ አደረገ እናም ለህያው እና ለሙታን ያሉንን የቤተመቅደስ ሀላፊነት እንድናከናውን ዘንድ ነገሮችን እና የነቢያት መመሪያዎችን ሰጠን።

ዳግም በተመለሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምክንያት፣ የህይወት አላማን፣ አብ ለልጆቹ ደህንነት ስላለው እቅድን፣ የአዳኝ የቤዛነት መስዋዕትን፣ እና በሰማይ ድርጅት ውስጥ ቤተሰቦች ዋና ሀላፊነት እንዳላቸው ለመረዳት ችለናል።10

በቁጥር የጨመሩት ቤተመቅደሶች እና ለቅድመ ዘመዶቻችን ለምናሟላቸው ቅዱስ የቤተሰብ ታሪክ ሀላፊነቶች ያለው የተሻሻለ ቴክኖሎጂ ተጨምሮ ይህንን ወቅት በታሪክ ሁሉ የተባረከ ጊዜ ያደርገዋል። ቅድመ አያቶቻቸውን ለማግኘት እና ከዚያም የመጠመቅ እና የማረጋገጫ ስራን በቤተመቅደስ ውስጥ በሚያከናውኑት ወጣቶች አስደናዊ እምነት እደሰታለሁ። በራዕይ የተባሉባቸው የፅዮን ተራራ አዳኞች መካከል እናንተ በእርግጥም ናችሁ።

ለቤተመቅደስ እንዴት እንዘጋጃለን?

ጻድቅነት እና ቅደሳ ለቤተመቅደስ የመዘጋጃ ዋና ክፍሎች እንደሆኑ እናውቃለን።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 97 ውስጥ፣ እንዲህ እናነባለን፣ “እናም ህዝቤ በጌታ ስም ቤት እስከገነቡልኝ ድረስ፣ እና ምንም ጉድፍ ነገር ወደዚያ እንዲገባ እስካልፈቀዱ፣ እና እንዳይረክስ ካደረጉ፣ ግርማዬ በዚህ ላይ ያርፋል።”11

የቤተመቅደስን ቅድስና ለመጠበቅ ሲባል እስከ እ.አ.አ 1891 ድረስ የቤተክርስቲን ፕሬዘዳንት እያንዳንዱ የቤተመቅደስ መግቢያ ላይ ይፈርሙ ነበር። ከዚያን ያ ሃላፊነት ለኤጲስ ቆጶሶችና ለካስማ ፕሬዘዳንቶች ተላልፎ ነበር።

የቤተክርስቲያኗ አባላት ለቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ብቁ በመሆን እንዲኖሩ ታላቅ ፍላጎታችን ነው። ቤተመቅደስን እንደ ራቀ ወይም ለማግኘት እንደማይቻል አላማ እባካችሁ አትመልከቱት። አብዛኛው አባላት ብቁ ለመሆን ቆራጥነት እና ሙሉ ለሙሉ ለሰሩት መተላለፎች ንሰሃ ከገቡ ከኤጲስ ቆጶሳቸው ጋር በመስራት ሁሉንም ፃድቅ መጠይቆችን በአንፃራዊ በአጭር ጊዜ ማሳካት ይችላሉ። ይህ ሌሎችን ይቅር የማለት ፍቃደኝነትን እና ፍፁም አለመሆናችን ወይም ሀጢያተኛ መሆናችን ቅዱስ ቤተመቅደስ መቼም እንዳንገባ ብቁ እንደማያደርጉን ትኩረት አለማድረግን ያካትታል።

የአዳኝ ቤዛነት የተፈፀመው ለሁሉም የእግዚያብሄር ልጆች ነው። የእርሱ የቤዛነትመስዋእት በእውነት ንስሀ ለሚገቡ ሁሉ የፍትህ ጥያቄዎችን ያረካል። ቅዱስ መፅሀፍት ይህን በጣም በሚያምር መልክ ይገልፁታል፤

“እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዞት ትጠራለች።”12

“በምንም [አላስታውሳቸውም።”13

ፃዲቅ የሆኑ መርሆዎችን መኖር ለእናንተ እና ለቤተሰባችሁ ደስታ፣ ስኬት፣ እና ሰላምን እንደሚያመጣላችሁ እናረጋግጥላችኋለን።14 አባላቶች፣ ጎልማሶች እና ወጣቶችን ጨምሮ፣15 የቤተመቅደስ መግቢያ ጥያቄዎችን ሲመልሱ የእራሳቸውን ብቁነት ያረጋግጣሉ። ጠቃሚው መጠይቅ የአባት እግዚያብሄር፣ ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስተቶስ፤ እና የተመለሰው ወንጌሉ ላይ እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎትን መለማመድ ላይ ምስክርነትን ማሳደግ ነው።

የቤተመቅደስ በረከቶች ቁጥር የለሽ ናቸው

የቤተመቅደስ ዋና በረከቶች የዘለአለማዊነት ስርዓቶች ናቸው። የወንጌል እቅድ ስለ ዘላለም ደህንነት እና ከእግዚያብሄር ጋር ቃልኪዳን መግባት እና መጠበቅን የሚያጠቃልል ነው። ጥምቀት እና ማረጋገጫ ካልሆነ በቀር፣ እነኚህ ስርዓቶች እና ቃልኪዳኖች በህይወት ላሉ የሚፈፀሙት እና የሚቀበሉት ቤተመቅደስ ውስጥ ነው። ለሞቱት፣ ሁሉም የማዳን ስርዓቶች እና ቃልኪዳኖችነን የሚቀበሉት በቤተመቅደስ ውስጥ ነው።

ብሬገም ያንግ እንዲህ አስተማሩ፣ “ጌታ ለሰዎች ልጆች ቤተሰብ መዳን ማድረግ እየቻለ ችላ ያለው አንዳችም ነገር የለም፤…እራሳቸውን ችለው፣ ለደህንነታቸው መፈፀም የሚቻለውን ነገር ሁሉ፣ በአዳኝ አማካኝነት እና በራሱ ተፈፅሟል።”16

የቤተክርስቲያን መሪዎች በፀሎት ቤቶቻችን እና ሌሎች ህንፃዎች ውስጥ ካስማዎችን፣ አጥቢያዎችን፣ ጉባዔዎችን፣ የቤተክርስቲያን ቡድኖችን፣ ምሽኖች፣ ወ.ዘ.ተ ያቋቁማሉ። ጌታ ዘለአለማዊ ቤተሰቦችን በቤተመቅደስ ውስጥ ያደራጃል።

የተሰበረ ልቦች እና የተዋረደ መንፈሶች ያላቸው እና ሀጢያታቸውን በእውነት ንስሃ የገቡ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ በጌታ በቅዱስ ቤቱ ተቀባይነት እንዳላቸው ግልፅ ነው።17 “እግዚያብሄር ሰውን እንደማይመርጥ” እናውቃለን።18 ስለ ቤተመቅደስ ከምወዳቸው ውድ ነገሮች አንዱ እዛ በሚካፈሉት ሰዎች መካከል የሀብት፣ የደረጃ ወይም የትኛውም አይነት የስራ ደረጃ መለያየት አለመኖሩ ነው። በእግዚአብሔር ፊት ሁላችንም እኩል ነን። ንፁህ እና ፃድቅ መሆናችንን ለማመልከት ሁሉም ሰው ነጭ ይለብሳል። 19 የአፍቃሪ ሰማይ አባት ወንድ ልጆች እና ሴት ልጆች በልቦቻቸው ውስጥ ብቁ ከመሆን መሻት ጋር ሁሉም ጎን ለጎን ይቀመጣል።

ምስል
የቤተመቅደስ መተሳሰሪያ ክፍል

አስቡት፣ በአለም ዙሪያ ሁሉ ወንዶች እና ሴቶች በቅዱስ ቤተመቅደስ ቅስጥ በሚገኘው “ቅዱስ በሆነ ስርዓቶችና ቃልኪዳኖች” አማካኝነት ወደ እግዚያብሄር ፊት ተመልሰው እና …. ለዘላለም አብረው መኖር ይችላሉ። 20 ይህንን የሚያደርጉት ለሁሉም ለቤተመቅደስ ብቁ የሆኑ አባላት ክፍት በሆነው በሚያምረው ቅዱስ የመታተሚያ ክፍል ውስጥ ነው። ወደ እነዚህ ቃልኪዳኞች ከገቡ በኋላ፣ ፊት ለፊት በሆኑ መስታዎቶች “እራሳቸውን በቤተመቅደስ ውስጥ ማየት” ይችላሉ። “በአንድ ላይ የቤተመቅደስ መስታዎቶች ወደ ዘላለም በሚመስል መልኩ ምስሎችን ወደ ኋላ እና ወደ ፊት ያንፀባርቃሉ።” 21 እነኚ የሚንፀባረቁ ምስሎች ወላጆችን፣ አያቶችን፣ እና ሁሉንም ያለፉ ትውልዶችን እንድናስብ ይረዱናል። ከቀጣይ ትውልዶች ሁሉ ያቆራኙንን ቅዱስ ቃልኪዳኖች እንድንገነዘብ ይረዱናል። ይህ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፣ እናም የሚጀምረው እራሳችሁን በቤተመቅደስ ውስጥ ስትመለከቱ ነው።

ምስል
በቤተመቅደስ መተሳሰሪያ ክፍል ውስጥ ያለ መስታዎቶች

ፕሬዘዳንት ሀዋረድ ደብሊው. ሀንተር እንዲህ ብሎ መከረን “ነብዩ ዮሴፍ ስሚዝ በራእይ የተሰጠኝ ነው ያለውን ፀሎት፣ የታላቁ ከርትላንድ ቤተመቅደስ ቡራኬ ላይ የተሰጠውን ግርማ ያለውን ትምህርት ተገንዘቡ። በእኛ በየግላችን ላይ፣ በእኛ በቤተሰቦች ላይ፣ እናም እንደ ሰዎች መልስ ማግኘቱን የቀጠለ ፀሎት ነው ምክንያቱም ጌታ የሱ ቅዱስ ቤተመቅደሱን እንድንጠቀም የክህነት ስልጣን ሰጥቶናል።” 22የፕሬዘዳንት ሀንተር ማስጠንቀቂያ የሆነውን “እንደ [የእኛ] አባልነት ታላቅ ምልክትነት የጌታን ቤተመቅደስ ማቋቋም።” የሚለውን በመከተለል እና የትምህርትና ቃልኪዳን ክፍል 109ኝን በማጥናት መልካም እናደርጋለን። 23

ቤተመቅደስ የመጠለያ፣ ምስጋና የመስጫ፣ የመመሪያ፣ የመረዳት፣ እነዲሁም “የእግዚያብሄርን መንግስት በተመለከተ በምድር ላይ ሁሉ ነገሮችን” የያዘ ቦታ ነው። 24 በሁከት አለም ውስጥ በህይወቴ ሁሉ የፀጥታና የሰላም ቦታ ሆኖልኛል።25 በዛ ቅዱስ አካባቢ የአለምን ጭንቀት ትቶ መሄድ አስደናቂ ነው።

በቤተመቅደስ አብዛኛውን ጊዜ በቤተሰብ ታሪክ ምርምር ላይ ስንካፈል፣ መነሳሳቶችን ይሰማናል እናም ከመንፈስ ቅዱስ መነሳሳቶች ይኖረናል።26 አልፎ አልፎ በቤተመቅደስ ውስጥ፣ በእኛ እና በዛኛው በኩል ባሉት መካከል ያለው መጋረጃው በጣም ይሳሳል። በፅዮን ተራራ አዳኝ ለመሆን በምንጥርበት ተጨማሪ ረጂዎች አግኝተናል።

ከብዙ አመት በፊት በመሀከላዊ አሜሪካ ቤተመቅደስ ውስጥ፣ ድሮ እንደ አጠቃላይ ባለስልጣን ያገለግሉ የነበሩት ባለቤት አባት፣ እናት፣ እና ልጆቻቸውን የቤተመቅደስ መስታዎቶች በሚገኝበት በመተሳሰሪያ ክፍል ውስጥ የዘለአለም ቃል ኪዳኖችን እንዲቀበሉ ረዷቸው። ሲፈጽሙ እና በመስታዎቶችን ፊት ሲቆሙ፣ በክፍሉ ውስጥ የማይገኝ ሰው ፊት በመስታዎቶች ውስጥ አየች። እናትየዋን ጠየቀች እና ሴት ልጇ እንደሞተች እና በሰውነት በዚያ እንደማትገኝ ተማረች። የሞተችው ሴት ልጅ በቅዱስ ስራአት ውስጥ በምትክ ተጨምራ ነበር።27 ከመጋረጃው ሌላ በኩል በቤተመቅደስ ውስጥ የሚሰጠውን እርዳታ ዝቅ አድርገን አትገምቱ።

እባካችሁ ሁሉም ሰው ጠቃሚ ለውጦችን በማምጣት ለቤተመቅደስ ብቁ እንዲሆን በቅንነት እንደምንሻ እወቁልን። በፀሎት መንፈስ በመሆን በህይወታችሁ የት እንዳላችሁ ገምግሙ፣ የመንፈስ ቅዱስ ምሬትን እሹ፣ እናም እራሳችሁን ለቤተመቅደስ ስለ ማዘጋጀት ኤጲስ ቆጶሳችሁን አናግሩ። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዳሉት፣ “ወደ ቤተመቅደስ ለመግባት ብቁ ከመሆን በላይ የሆነ እናንተ የምትሰሩበት አስፈላጊ የሆነ ምንም አላም የለም።”28

አዳኝ “የእምነታችን እና የእርሱ ቤተክርስቲያን ዋና የማይነቃነቅ የማእዘን ድንጋይ ነው።”

ከሁለት ወር በፊት የሱቫ ፊጂ ቤተመቅደስ ዳግም ቡራኬ ላይ ከፕሬዘዳንት ሄነሪይ ቢ. አይሪንግ ጋር የመካፈል እድል አግኝቼ ነበር። ይህም ልዩ፣ እና ቅዱስ ጊዜ ነበር። የፕሬዘዳንት አይሪንግ ብርታት እና ጠንካራ መንፈሳዊ መነሳሳቶች በደቡብ ግዛት ከተመዘገቡት ሁሉ በጣም አደገኛው አውሎ ንፋስ ቢኖርም እንኳን ዳግም ቡራኬው እንዲቀጥል አስችሏል። አካላዊ እና መንፈሳዊ ከለላዎች ለወጣቶች፣ ለሚሲዮናዊያኖች፣ እና ለአባላት ቀርቦ ነበር። 29 የጌታ እጅ በግልፅ ታይቶ ነበር። የፊጂ ሱቫ ቤተመቅደስ ድጋሚ ቡራኬ ከወጀቡ መጠለያ ነበር። አብዛኛውን ጊዜ የህይወት ወጀብ ሲያጋጥመን፣ ዘላለም ከለላዎችን በማዘጋጀት ውስጥ የጌታን እጅ እንመለከታለን።

በሰኔ 18፣ 2000 (እ.አ.አ) የተደረገው የመጀመሪያው የፊጂ ሱቫ ቤተመቅደስ ቡራኬም አስደናቂ ነበር። ቤተመቅደሱ ማለቂያው ሲቃረብ፣ የፓርላማ አባላት በአማፂያን ቡድን ታግተው ነበር። ሱቫ፣ ፊጂ ተሰርቆ እና ተቃጥሎ ነበር። ወታደራዊ ጦሩ የጦርነት ህግን አወጀ።

እንደ ክልል ፕሬዘደንት፣ በፊጂ ውስጥ ካሉት አራት የካስማ ፕሬዘደንቶች ጋር ከጦር ሀይል መሪዎች ጋር በንግስት ኤልዛቤት የወታደር ሰፈር ውስጥ ተገናኘን የታሰበውን ቡራኬ ካብራራን በኋላ፣ አጋዥ ነበሩ ነገር ግን የፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ ደህንነት አሳስቧቸው ነበር። በቤተመቅደስ ውጪ ምንም ድርጊት የማይደረግበት ትንሽ በአል እንድናከናውን ሀሳብ አቀረቡ። በቤተመቅደሷ ውጪ የሚገኝ አመፅ እንደሚደርስባቸው በጥብቅ አስጠናቀቁ።

ፕሬዘዳንት ሂንክሊን ከአዲሱ የቤተመቅደስ አመራር እና ጥቂት የሀገር ውስጥ መሪዎችን ያሉበት አንድ ትንሽ የቡራኬ ክፍል እንዲደረግ ፈቀዱ፤ በአደጋው ምክንያት ማንም ሌላ ሰው አልተጋበዙም ነበር። ምንም እንኳ፣ አጥብቆ ቢናገርም፣ “ቤተመቅደሱን ቡራኬ ከሰጠን፣ የማእዘን ድንጋይ ማስመረቅ ስርዓት ይኖረናል ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና የማእዘን ድንጋይ ነ፤2ው፣ እንዲሁም ይህ የሱ ቤተክርስቲያን ነው።”

ለማእዘን ድንጋይ ማስመረቅ ስርዓት ወደ ውጪ ስንወጣ፣ አንድም የቤተክርስቲያን አባል ያልሆኑ፣ ህፃናት፣ ሚዲያ፣ ወይም ሌሎች የሉም ነበር። ነገር ግን አማኙ ነብይ ለአዳኝ ብርታታቸውን እና የማይንቀሳቀሰውን ቆራጥነታቸውን አሳዩ።

በኋላም ፕሬዘደንት ሒንክሊ፣ ስለአዳኝ በመናገር፣ እንዲህ አሉ፥ “ከእርሱ እኩል የሆነ ምንም የለም። ማንም አልነበረም። ማንም አይሆኑም። ህይወቱን እኛ እንድንኖር አሳልፎ ለሰጠው፣ የእምነታችን እና የቤተክርስቲያኑ የማይነቃነቅ የማዕዘን ድንጋይ ለሆነው፣ ለተወዳጅ ልጁ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።”30

ወንድሞች እና እህቶች፣ እያንዳንዳችን አዳኝ እንድናከብር እና በቅዱስ ቤተመቅደሱ ውስጥ ራሳችንን ለማየት የሚያስፈልገውን ማንኛውን እንቀይር ዘንድ እጸልያለሁ። ይህንን በማድረግ፣ የሱን ቅዱስ አላማ መፈፀም እንችላለን እናም እራሳችንን እና ቤተሰቦቻችንን ለሁሉም የጌታ እና የእሱ ቤተክርስቲያኑ በዚህ ምድር እና በዘላለም ለሚሸልሙት በረከቶች እናዘጋጃለን። አዳኝ ህያው እንደሆነ እርግጠኛ ምስክሬን እሰጣለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 112፥30–32ተመልከቱ።

  2. 12ኛው ቤተመቅደስ የሆነው የለንደን፣ እንግሊዝ ቤተመቅደስ የተቀደሰው በመስከረም 7፣ 1958 (እ.አ.አ)።

  3. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥6–7

  4. Shelly Senior, email, Apr. 6, 2015.

  5. ቶማስ ኤስ ሞንሰን፣ “The Holy Temple—a Beacon to the World,”Liahona, ግንቦት 2011 (እ.አ.አ.)፣ 93።

  6. ኢሳይያስ 2፥2 ተመልከቱ።

  7. አብድዩ 1፥21 ተመልከቱ።

  8. 1 ጴጥሮስ 4፥6 ተመልከቱ።

  9. See Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith (2007), 409.

  10. See Teachings of Presidents of the Church: Wilford Woodruff (2004), 177, 192–93.

  11. ትምህርተ እና ቃልኪዳኖች 97፥15፤ ደግሞም ቁጥር 17 ተመልከቱ።

  12. ኢሳይያስ 1፥18

  13. ኤርምያስ 31፥34

  14. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥23 ተመልከቱ።

  15. የመንፈሳዊ ስጦታን ከተቀበሉ ጎልማሳዎች በተጨማሪ፣ ለሙታን ለመጠመቅ የሚቻልበት የተወሰነ ፈቃድ የሚሰጥ ወረቀት ብቁ ለሆኑ ወጣቶች እና መንፈሳዊ ስጦታ ላለተቀበሉ ጎልማሳዎች ለመሰጠት ይቻላል። ሁሉቱም የመግቢያ ፈቃዶች የሚቀበለው ሰው ብቁነቱን በማረጋገጥ መፈረም ያስፈልጋቸዋል። የተወሰነ ፈቃድ የሚሰጥ ወረቀትን ለአንድ አመት ለመጠቀም ይቻላል እናም የኤጲስ ቆጶስ አመራር ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ስለራሱወይም ስለራሷ ብቁነት በየአመት የሚወያዩበት እድል ያቀርባል።

  16. Teachings of Presidents of the Church: Brigham Young (1997), 32.

  17. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42 ተመልከቱ።

  18. የሐዋርያት ስራ 10፥34፤ ደግሞም ሞሮኒ 8፥12ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥35 38፥16 ተመልከቱ።

  19. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 100፥16 ተመልከቱ።

  20. “ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅ,” Liahona, ህዳር 2010, 129።

  21. Gerrit W. Gong, “Temple Mirrors of Eternity: A Testimony of Family,” Liahona, Nov. 2010, 37.

  22. Teachings of Presidents of the Church: Howard W. Hunter (2015), 183.

  23. Teachings: Howard W. Hunter (2015), 178.

  24. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥13–14ተመልከቱ።

  25. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥26–27ተመልከቱ።

  26. በአብዛኛው ጊዜ ይህን የኤልያስ መንፈስ ብለን እናውቀዋለን። ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን የኤልያስ መንፈስ “መንፈስ ቅዱስ ስለቤተሰብ መለኮታዊ ፍጥረት ሲመሰክር የሚያሳይበት ነው” ብለው አስተምረዋል (“A New Harvest Time,” Ensign, May 1998, 34)።

  27. ለመካፈል ፈቃድ ተሰጥቷል

  28. Thomas S. Monson, “The Holy Temple—a Beacon to the World,” 93.

  29. ከሌሎቹ ደሴቶች የመጡት ሚስዮኖች እና ወጣቶች በቤተክርስቲያኗ ትምህርት ቤቶች እና በቤተክርስቲያኗ ህንጻዎች ውስጥ በደህና እንዲቆዩ ተደርገው ነበር እናም ከዊንስተን አውሎንፋስ በደህና ተጠብቀው ነበር።

  30. Henry B. Eyring, “The Caregiver,”Liahona, Nov. 2004, 4.