2010–2019 (እ.አ.አ)
መንፈስ ቅዱስ
ኤፕረል 2016


መንፈስ ቅዱስ

በእርሱ አማካኝነት ፍላጎቱን የሚገልፅበት እና እኛን ስለሚደግፈን፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እኔ ለእግዚአብሔር ፍቅሬን እና ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ተወዳጅ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ዛሬ እንደ የጌታ አገልጋይ እና እንደ ቅድመ አያትነቴ እናገርራለሁ። ለእናንተ እና ለተወዳጅ ዘሮቼ፣ የመንፈስ ቅዱስን ግሩም ስጦታ አስተምራለሁ እናም ምስክርነቴን አካፍላለሁ።

“ወደ እዚህ አለም ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ” የሚሰጠው የክርስቶስ ብርሀንን እውቅና በመስጠት እጀምራለሁ።1 ከእዚህ ቅዱስ ብርሀን ሁላችንም እንጠቀማለን። “በሁሉም እና በማንኛውም ነገር ውስጥ” ነው፣2 እናም ትክክለኛውን ከስህተቱ እንድንለይ ያስችለናል።3

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ከክርስቶስ ብርሀን የተለየ ነው። የስላሴዎች ሶስተኛ አባል ነው፣ ከተቀደሱ ሀላፊነቶች ጋር በመንፈስ የተለየ ማንነት ያለው እና ከአብ እና ከወልድ ጋር በአላማ አንድ ነው።4

እንደ ቤተክርስቲያን አባልነታችን፣ የመንፈስ ቅዱስን አጋርነት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ልንለማመደው እንችላለን። በተመለሰው የእግዚአብሔር ክህነት አማካኝነት፣ ለሀጢያታችን ስርየት በመጥለቅ ተጠምቀናል እናም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነት ማረጋገጫን ተቀብለናል። በእዚህ ስርአት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን የክህነት ስልጣን በያዙት እጅ በመጫን ተሰጥቶናል። ከዛም በኋላ፣5 ሁሌም አዳኝን በማስታወስ፣ ትእዛዛቱን በመጠበቅ፣ ከሀጢያታችን ንሰሀ በመግባት፣ እና በሰንበት ቀን በቅድስና ቅዱስ ቁርባን በመካፈል የመንፈስ ቅዱስን አጋርነት ማግኘት እና መጠበቅ እንችላለን።

መንፈስ ቅዱስ እንደ ትምህርት፣ ሚስኦን፣ ስራ፣ ትዳር፣ ልጆች፣ ከቤተሰቦቻችን ጋር የት እንደምንኖር፣ እና የመሳሰሉትን አይነት ዋና የህይወት ውሳኔዎችን ለማድረግ እንዲረዳን የግል መገለጥን ይሰጠናል። በዚህ ጉዳይ፣ ነፃ ምርጫችንን እንድንጠቀም፣ በወንጌል መርሆዎች መሰረት ሁኔታውን በአእምሮአችን እንድናጠና፣ እና በፀሎት ውሳኔን ወደ እርሱ እንድናመጣ የሰማይ አባት ከእኛ ይጠብቃል።

የግል መገለጥ ወሳኝ ነው፣ ነገር ግን ያ የመንፈስ ቅዱስ አንዱ የስራው ክፍል ብቻ ነው። ቅዱሳን መፅሀፍት እንደሚያረጋግጡት፣ መንፈስ ቅዱስ ስለ አዳኝ እና እግዚአብሔር አብም ይመሰክራል።6 “ስለ መንግስቱ ሳላማዊ ነገሮች” ያስተምረናል7 እና “በተስፋ እንድንፀና” ምክንያት ይሆነናል።8 “መልካም እንድናደርግ… እና በቅድስና እንድንፈርድ ይመራናል።”9 “ሁሉም ይጠቀሙ ዘንድ.. ለሁሉም ወንዶች እና ሴቶች፣ መንፈሳዊ ስጦታዎችን” ይሰጣል። 10 “እውቀትን ይሰጠናል” 11 እናም “ሁሉንም ነገር ያስታውሰናል።”12 በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፣ ልንቀደስ13 እና ለሀጢያታችን ስረየትን ልንቀበል እንችላለን።14 እርሱ አፅናኝ ነው፣ ያም “ለአዳኝ ደቀመዛሙርት ቃል የተገባው እራሱ ነው።”15

መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን እኛን እንዲቆጣጠር እንዳልሆነ ለሁላችንም አስታውሳለሁ። አንዳንዶቻችን በትንንሽ የህይወት ውሳኔዎቻችን ሁሉ የመንፈስ ቅዱስን ምሬት ያለብልሀት እንሻለን። ይህ የእርሱን ቅዱስ ሚና ያረክሰዋል። መንፈስ ቅዱስ የነፃ ምርጫን መርህ ያከብራል። ስለሚመጡት ብዙ ውጤቶች በእርጋታ ለአእምሮአችን እና ለልባችን ይናገራል።16

እያንዳንዳችን የመንፈስ ቅዱስ ተፅእኖ በተለያየ መልኩ ይሆናል የሚሰማን። እንደ ግል አስፈላጊነቱ እና ሁኔታዎች የእርሱ መነሳሳቶች በተለያየ የጥልቀት ደረጃዎች ይሰማናል።

በእነዚህ የኋለኛው ቀናት፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ለአጠቃላዩ ቤተክርስቲያን መገለጥን የሚቀበለው ነብዩ ብቻ እንደሆነ እናረጋግጣለን። አንዳንዶች ይህን ይረሳሉ፣ አሮን እና ማሪያም ከእነርሱ ጋር እንዲስማማ ሙሴን ሊያስማሙ እንደሞከሩት ሁሉ። ነገር ግን ጌታ እነርሱን እና እኛን እንዲህ አስተማረ። እንዲህ አለ፥

“በመካከላችሁ ነብይ ቢኖር፣ እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ። …

“ወይም በህልም አናግረዋለሁ።”17

አንዳንዴ ሰይጣን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንዲመሳሰልብን በሀሰተኛ ሀሳቦች ይፈታነናል። ትእዛዛትን በመጠበቅ እና ቃልኪዳናችንን በመጠበቅ መታመን ከመታለል እንደሚጠብቀን እመሰክራለሁ። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፣ ለአስተምሮት የሰዎችን ትእዛዛት የሚያስተምሩ ሀሰተኛ ነብያትን ለይተን ማወቅ እንችላለን።18

ለእራሳችን የመንፈስ ቅዱስ መነሳሳትን ከተቀበልን በኋላ፣ ለሌሎች መገለጥን መቀበል እንደማንችል ማስታወስ ብልህነት ነው። እንዲህ ብሎ አንድ ወጣት ለአንድ ወጣት ሴት የነገራትን አውቃለሁ፣ “አንቺ ሚስቴ እንደምትሆኚ በህልሜ አይቻለሁ።” ወጣቷ ሴት ያንን አርፍተ ነገር አሰበችበት እና እንዲህ ብላ መለሰች፣ “ተመሳሳይ ህልምን እኔም ሳይ፣ እመጣ እና አነግርሀለሁ።”

የግል ፍላጎቶቻቻን ከመንፈስ ቅዱስ ምሬት እንዲበልጡ ለማድረግ ሁላችንም እንፈተን ይሆናል። የመጀመሪያዎቹን የመፅሀፈ ሞርሞን 116 ገልፆች ለማርቲን ሀሪስ ለማዋስ ፍቃድ ለማግኘት ጆሴፍ ስሚዝ የሰማይ አባትን ተማፀነ። ጆሴፍ መልካም ሀሳብ ነው ብሎ አስቦ ነበር። በመጀመሪያ መንፈስ ቅዱስ የማረጋገጫ ስሜትን አልሰጠውም ነበር። በመጨረሻም፣ ጌታ ጆሴፍ ጽሁፎቹን በብድር እንዲሰጥ ፈቀደ። ማርቲን ገልፆቹ ጠፉበት። ለአንድ ወቅት፣ ነብዩ የነበረውን የትርጉም ስጦታ ጌታ አነሳበት፣ እና ጆሴፍ ቀሪ የአገልግሎት ጊዜውን የቀረፀውን የሚያም ነገር ግን ጠቃሚ ትምህርትን ተማረ።

መንፈስ ቅዱስ የዳግም መመለሱ ማእከል ነው። ወጣት ሳለ ከያቆብ 1፣5 ያነበበውን አስመልክቶ፣ ነብዩ ጆሴፍ እንዲህ ያስታውሳል፣ “በዚህ ጊዜ ለእኔ እንደሆነው የቅዱስ መፅሀፍ ጥቅስ ወደ ሰው ልብ በእንዲህ አይነት ጠንካራ ሀይል መጥቶ አያውቅም።” 19 በጆሴፍ ስሚዝ የተገለፀው ሀይል የመንፈስ ቅዱስ ተፅእኖ ነው። በውጤቱም፣ ጆሴፍ በቤቱ አቅራቢያ ወዳለው ጫካ ሄደ እናም እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ተንበረከከ። የመጀመሪያው ዕራእይ ቅፅበታዊ እና አስገራሚም ነበር። ነገር ግን ወደ አብ እና ወልድ የግል ጉብኝት ያመራው መንገድ የጀመረው ለመፀለይ ከመንፈስ ቅዱስ በመጣው መነሳሳት ነበር።

የተመለሰው ወንጌል እውነታዎች የተገለፁት በፀሎት የመሻት ሂደት፣ ከዛም በመቀበል እና የመንፈስ ቅዱስን መነሳሳት በመከተል የመጡ ናቸው። እነዚህን ምሳሌዎች አስቧቸው፤ መፅሀፈ ሞርሞንን መተርጎም፣ በጥምቀት የጀመረው የክህነት እና ስርአቶቹ ዳግም መመለስ፣ እና የቤተክርስቲያኑ መመስረት፣ ጥቂቶቹ ናቸው። ዛሬ፣ ከእግዚአብሔር የሚመጣው መገለጥ ለቀዳሚ አመራሮች እና ለአስራ ሁለቱ የሚመጣው በዚሁ በተመሳሳይ ቅዱስ ሂደት ነው። ይህም የግል ራዕይን የሚፈቅድ አንድ አይነት ንድፍ ነው።

ከራሱ ከጆሴፍ ስሚዝ ቤተሰብ አባሎች ጀምሮ፣ ዳግም የተመለሰውን ወንጌል ለመቀበል መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉትን ሁሉ እናከብራለን። ወጣቱ ጆሴፍ ለአባቱ ስለ ሞሮኒ ጉብኝት ሲነግረው፣ አባቱ ለራሱ የማረጋገጫ ምስክርነትን ተቀበለ። ወዲያውም፣ ጆሴፍ ከግብርና ሀላፊነቶቹ ተነሳ እናም የመላእኩን ምሬት እንዲከተል ተበረታታ።

እንደ ወላጆች እና መሪዎች፣ እንደዚህም እናድርግ። የመንፈስ ቅዱስን ምሬት እንዲከተሉ ልጆቻችንን እና ሌሎችንም እናበረታታ። ይህንን በማድረግ፣ በእርጋታ በመምራት፣ በየዋህነት፣ በደግነት፣ በመፅናት፣ በማያስመስል ፍቅር፣ እኛ እራሳችን የመንፈስ ቅዱስን ምሳሌ እንከተል።20

በቤተሰብ እና በመላው ቤተክርስቲያን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ስራ ማእከል ነው። በዚያ መረዳት፣ በእራሴ ህይወት እና በቤተክርሰቲያን አገልግሎቴ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥቂት የግል ምሳሌዎችን ላካፍላችሁን? መንፈስ ቅዱስ ሁላችንንም እንደሚባርከን የግል ምስክርነቴን አካፈልኳቸው።

ከብዙ አመታት በፊት፣ እህት ሄልስ እና እኔ ጥቂት የስራ ባልደረባዎቼን ለልዩ እራት እቤት ለመጋበዝ አቀድን። ከቢሮ ወደ ቤት እየሄድኩ ሳለው፣ ቤት ለቤት ሳስተምራት በነበረች አንድ ጋለሞታ ቤት ለመቆም ተነሳሳሁ። የእህቷን ቤት ሳንኳኳ፣ እንዲህ አለች፣ “አንቺ እንድትጪ ስፀልይ ነበር።” ያ የመነሳሳት ስሜት የመጣው ከየት ነበር? ከመንፈስ ቅዱስ ነው።

አንዴ፣ ከከባድ ህመም በኋላ፣ በካስማ ጉባኤን መራሁ። አቅሜን ለመሰብሰብ፣ ልክ የክህነት አመራር ጉባኤ እንዳለቀ ከቤተክርስቲያኑ ለመሄድ አቀድኩ። ነገር ግን፣ ከመጨረሻው ጸሎት በኋላ፣ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ አለኝ፣ “የት ነው የምትሄደው?” ክፍሉን ለቀው ሲወጡ ሁሉንም እጃቸውን እንድጨብት ተነሳሳሁ። አንድ ወጣት ኤልደር ወደ ፊት ሲጠጋ፣ ይህንን ልዩ መልእክት እንድሰጠው ተሰማኝ፤ ወደታች እየተመለከተ ነበር፣ እናም አይኑን ከፍ እስከሚያደርግ እና እኔን እስከሚያይ ድረስ ጠበኩኝ፣ እናም “ወደ ሰማይ አባት ጸልይ፣ መንፈስ ቅዱስን አድምጥ፣ መነሳሻ የምትቀበለውን ተከተል፣ እናም በህይወትህ ሁሉም መልካም ይሆናል” ለማለት ቻልኩኝ። በኋላም ወጣቱ ከሚስኦን አገልግሎቱ አስቀድሞ እንደተመለሰ የካስማ ፕሬዘዳንቱ አጫወተኝ። ግልፅ በሆነ የመነሳሳት ስሜት ላይ በመመስረት፣ የካስማ ፕሬዘዳንቱ ለወጣቱ አባት ልጃቸውን ይዘው ወደ ክህነት ስብሰባው ከመጡ “ሽማግሌ ሄልስ ያናግረዋል።”በማለት ቃል ገብቶላቸው ነበር፣ የሁሉንም እጅ ለመጨበጥ የቆምኩት ለምን ነበር? ከዚህ ልዩ ወጣት ልጅ ጋር ለመነጋገር ለምን ቆምኩኝ? የምክሬ ምንጭ ምንድን ነበር? ይህም ቀላል ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ነው።

በ2005 መጀመሪያ ላይ፣ ስለ ቀደሙ የሚስኦን ጥንዶች በአጠቃላይ ጉባኤ ላይ መልእክት ለማካፈል እንድዘጋጅ ምሬት ተቀብዬ ነበር። ጉባኤውን ተከትሎ፣ አንድ ወንድም እንዲህ አስታወሰ፤ “ጉባኤውን ስናዳምጥ፣ … ወዲያው የጌታ መንፈስ ነብሴን በጥልቀት ነካው። … መልእክቱ ለእኔ እና ለተወዳጄ እንደነበር ምንም ስህተት አልነበረም። ሚስኦን ልናገለግል ነበር፣ እናም ሰአቱ አሁን ነበር። እኔ ሚስቴን ስመለከታት፣ እርሷም ከመንፈስ ተመሳሳይ የመነሳሳት ስሜትን እንደተቀበለች አስተዋልኩ።”21 ይህንን ጠንካራ በአንዴ የፈጠረ ምላሽ ያመጣው ምንድን ነው? ከመንፈስ ቅዱስ ነው።

ለእራሴ ትውልዶች እና በድምፄ ስር ላሉ ሁሉ፣ ወደ ቤተሰባችን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ስለመጡት የግል መገለጥ እና በቀጣይነት የሚፈሰው የየቀን ምሬት፣ ማስጠንቀቂያ፣ ማበረታቻ፣ ጥንካሬ፣ የመንፈሳዊ መንፃት፣ መጽናናት፣ እና የሰላም ምስክርነቴን አካፍላለሁ። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፣ “የ[ክርስቶስን] ተወዳጅ ምህረቶች ብዛት” 22 እና የማያልቁ ተአምራቶችን እንለማመዳለን።23

አዳኝ ህያው እንደሆነ ልዩ ምስክርነቴን አካፍላለሁ። በእርሱ አማካኝነት ፍላጎቱን የሚገልፅበት እና በህይወታችን እኛን ስለሚደግፈን፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እኔ ለእግዚአብሔር ፍቅሬን እና ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።