2010–2019 (እ.አ.አ)
ነገ ጌታ ታማራትን በመካከላችሁ ያሰራል
ኤፕረል 2016


ነገ ጌታ ታማራትን በመካከላችሁ ያሰራል

ማፍቀርን ቀጥሉ። ጥረትን ቀጥሉ። እምነት መጣላችሁን ቀጥሉበት። ማመናችሁን ቀጥሉበት። ማደጋችሁን ቀጥሉበት። ዛሬ፣ ነገና ለዘላለም መንግስተ ሰማይ ይደግፋችኋ።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ምን ያህል እንደምናፈቅራችሁ ታውቃላችሁን? ከሰዓት ወደ ሰዓት፣ ለአስር ሰአቶች፣ ፊቶቻችሁ እናያለን እናም በነፍሳችን ውስጥ ጥልቅ ደስታ ይሰማናል። በዚህ በጉባኤ አደራሳሽ ውስጥ ወይም በሩቅ በሚገኝ የስብሰባ ቦታ ውስጥ ቢሆን ወይም በኮምፒውተር አጠገብ ተሰብስበን ብንሆንም፣ በጣም ታስደስቱናላችሁ። የሰንበት መልካም ልብሳችሁን ለብሳችሁ በዚህ ከሰዓት ወደ ሰዓት በዚህ ትገኛላችሁ። ትዘምራላችሁ ወይም ትጸልያላችሁ። ትዳምጣላችሁ ወናም ታምናላችሁ። እናንተ የቤተክርስቲያኗ ታዕምራቶች ናችሁ። እናም እናፈቅራችኋለን።

ምን ዓይነት የሚያስደንቅ አጠቃላይ ጉባኤ ነበር። በፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን መገኘትና የነቢይ መልዕክቶች ተባርከናል። ፕሬዘደንት፣ እንወድዎታለን፣ ለእርስዎ እንጸልያለን፣ እናመሰግኖታለን፣ እና ከሆሉም በላይ፣ እንደግፍዎታለን። በእርስዎ እና በሚያስደንቁ የእርስዎ አማካሪዎች እንዲሁም በሌሎቹ የወንዶችና የሴቶች ታላቅ መሪዎቻችን ስለተማርን አመስጋኞች ነን። የማይነፃፀር መዝሙር ሰምተናል። በአስቸኳይ ተፀልዮልናል እንዲሁም ተለምኖልናል። በእውነት የጌታ መንፈስ በዚህ በብዛት አለ። በሁሉም መንገድ ምን ዓይነት የመነሳሳት ሳምንት ነበር ።

አሁን፣ የሚያጋጥሙን ሁለት ችግሮች ነው የማየው። አንደኛው ሁሌ ከአጠቃላይ ጉባኤ ማለቅ በኋላ በምታዘጋጁት አይስ ክሬም መካካል እኔ ብቻ መቆሜ ነው። ሌላው ችግር በቅርብ በኢንተርኔት ባየሁት ፎቶ ውስጥ የሚታይ ነው።

ምስል
ግዙፍ አውሬ ልጆችን ስያሯሩጥ

አሁን በሶፋ ስር ለሚደበቁት ለሁሉም ልጆች ይቅርታዬ እጠይቃለሁ፣ ነገር ግን የጉዳዩ እውነታ ማናችንም ነገ በዚህ የሳምንት መጨረሻ ላይ የነበረንን አስደናቂ ስሜቶች እንዲያፈርሳቸው አንፈልግም። የነበረንን መንፈሳዊ እይታዎች እንዲሁም የሰማነውን አነሳሽ ትምህርቶች ይዘን መጠበቅ እንፈልጋለን። ነገር ግን ከመንግስተ ሰማያዊ ቆይታዎች በኋላ ተስማሚ ያልሆነ ሁኔታዎች ወደሚያጋጥሙን ወደ ምድር መመለሳችንን ማስወገድ አይችልም።

ዕብራውያንን የጻፈው ይህን ሲፅፍ እንዲህ አስጠነቀቀን፣ “ብርሃን ከበራላች በኋላ መከራ በሆነበት በትልቅ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀደመውን ዘመን አስቡ።”1 ያ ብርሃን ከበራበት በኋላ ያለ መከራ ተጋድሎ ለሁላችንም በብዙ መንገድ ይመጣል። በእርግጥ በቅርብ ያገለገለ እያንዳንዱ ሚስዮኖች በአገልግሎት ቦታ ላይ ያለው ሕይወት እንደ ሚስዮን ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ከነበረው ህይወት የተለየ እንደነበር ተገንዝበዋል። ከጣፋጭ የቤተ-መቅደስ ስብሰባ ከወጣን በኋላ ወይም ከመንፈሳዊ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ከወጣን በኋላ ለሁላችንም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚሆነው።

ሙሴ ከሲና ተራራ ነጠላ ልምዱ ሲወርድ ህዝቦቹ “ኃጢያት ሰውተው” እና “ከታዘዙት መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ”2 ብለው እንዳገኛቸው አስታውሱ። ያህዌ ለሙሴ በተራራው ጫፍ ላይ በ “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ” እና “የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ”3 በሚነግርበት በዛው ሰዓት፣ በዚያም እነርሱ የወርቅ ጥጃውን ለማምለክ በማሰማመር ላይ በስራ ተጠምደው ነበሩ። በዛ ቀን ሙሴ በእስራኤላውያን መባዘን ደስተኛ አልነበረም!

በምድራዊው አገልግሎቱ ኢየሱስ ጴትሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ቅዱሳት መጽሐፍት “ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ”4 ወደሚሉት ወደ መለወጫው ተራራ ወሰዳቸው። ሰማያት ተከፈቱ የጥንት ነበያት መጡ እና አባት እግዚአብሔር ተናገረ።

ከዚህ ሰለስቲያላማ ልምድ በኋላ ኢየሱስ ምን ሊያጋጥመው ነበር ከተራራው የወረደው? መጀመሪያ በደቀ መዛሙርቱ እና በጠላቶቻቸው መካከል በወጣ ልጅ ላይ በተደረገ ቡራኬ አለመሳካት ላይ አለመግባባትን አገኘ። ከዛ ባይሳካለትም እዛ ለሚገኙ መሪዎች ለመገደል ተላልፎ እንደሚሰጥ አስራሁለቱን ለማሳመን ሞከረ። ከዛ አንድ ሰው በታማኝነት የከፈለው የእሱ ግብር እንደደረሰበት አስታወሰው። ከዛ የተወሰኑ ወንድሞ ችን በእርሱ መንግስ ውስጥ ማን ታላቅ እንደሚሆን ስለተከራከሩ መውቀስ ነበረበት። ይህ ሁሉ በአንድ ቦታ ላይ እንዲህ እንዲል አበቃው፣ “የማታምኑ ትውልዶች ሆይ፣---እሰከ መቼ እታገሳችኋለሁ?” 5በአገልግሎቱ ወቅት ያንን ጥያቄ በተደጋጋሚ የመጠየቅ ሁኔታ አጋጥሞት ነበር። የተራራው ጫፎ ላይን የብቸኝነት ፀሎት የናፈቀበት ጉዳይ ምንም አይገርምም!

ተከታታይ የሕይወት ውጣውረዶችን ለመግታት ሁላችንም ከልዶች ጫፍ መውረድ እንዳለብን በመገንዘብ አጠቃላይ ጉባኤው በሚጠናቀቅበት ሰዓት ይህን ማበረታቻ ልለግስ።

መጀመሪያ በሚመጡት ቀናት ውስጥ በዙሪያችሁ ባሉ ሰዎች ውስንነቶችን ብቻ ሳይሆን በራሳችሁ ሕይወት ውስጥ በዚህ የሳምንቱ መጨረሻ ላይ ከሰማችሁት መልዕክቶች ጋር የማይወዳደሩ ነገሮች ካገኛችሁ፣ በመንፈስ አትውረዱ እንዲሁም ተስፋ አትቁረጡ። ወንጌሉ፣ ቤተክርስቲያኗ እና እነዚህ አስደናቂ ግማሽ ዓመታዊ ስብሰባዎች የታቀዱት ተስፋንና ተነሳሽነትን ለመስጠት እንጂ አለመበረታታትን ለመስጠት አይደለም። እነዚህ እናንተ ተስፋ እንድትቆርጡ የተደረጉ አይደሉም። የሁሉም ጠላት የሆነው ብቻ ነው በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ የሚተነተኑት ሃሳቦች ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ እውን መሆን እንደማይችሉ፣ ሰዎች በእውነት እንደማይሻሻሉ፣ ማንም ሰው እድገት እንደማያሳይ ሊያሳምነን የሚሞክረው ። እና ሰይጣን ለምንድነው ያንን ንግግር የሰጠው? ምክንያቱም እሱ እንደማይሻሻል፣ እሱ እንደማያድግ፣ እሱ መጨረሻ በሌለው ዓለም ብሩህ የሆነ ነገr በጭራሽ እንደማያገኝ ስለሚያውቅ ነው። በዘላለማዊ ውስንነቶች የታሰረ በአሰቃቂ ሕይወት ውስጥ የሚኖር ሰው ነው፣ እናም እኛም ልክ እንደ እሱ በአሰቃቂ ሕይወት ውስጥ እንድንኖር ይፈልጋል። በዛ አትታለሉ። ከኃጢያት ክፍያው ስጦታና ከመንግስተ ሰማይ ሊረዳን ባለው ጥንካሬ ጋር መሻሻል እንችላለን እናም የወንጌል ታላቁ ነገር ሁልጊዜም ውጤታማ ባንሆንም ስለሞከርን ብቻ ነጥብ የምናገኝ መሆኑ ነው።

በቀደምት ቤተክርስቲያን ውስጥ ማን የመንግስተ ሰማይ በረከቶች እንደሚገባውና ማን እንደማይገባው አስመልቶ ውዝግብ በኖረበት ጊዜ፣ ጌታ ለዮሴፍ ስምዝ ይህን አወጀ፣ “በእውነት እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔር ስጦታዎች] … ለሚወዱኝ እና ሁሉንም ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ እናም ይህን ለማድረግ … የሚሹት ይጠየቁበት ዘንድ … ነው።”6 ለሚለው ለዛ ለተጨመረ መሰጠት አመስጋኞች ሁላችንም አይደለንምን! ያ ሕይወት አድን ሆኗል ምክንያም አንዳንድ ጊዜ መስጠት የምንችለው ያን ስለሆነ! እግዚአብሔር በፍፁም አመስጋኝ ለሆኑት ብቻ ሽልማት ቢሰጥ ኖሮ ብዙ የማከፋፈያ የዝርዝር መዝገብ እንደማይኖረው የማወቃችን እውነታ የተወሰነ መፅናናት ሰጥቶናል።

ስለዚህ እባካችሁ ነገ እንዲሁም ከዛ በኋላ ላሉት ቀናት ጌታ መሻሻል የሚፈልጉትን፣ የትዕዛዛትን አስፈላጊነት የሚቀበሉትንና ለመጠበቅ የሚሞክሩትን፣ ክርስቶስ መሰል ባህሪያትን የሚጠብቁትንና ለማግኘት የሚጥሩትን እንደሚባርከ አስታውሱ። ሁሉም ሰው እንደሚያደርገው በዛ ጉዞ ላይ ከተደናቀፋችሁ፣ አዳኙ እናንተን መራመዳችሁን ስትቀጥሉ ለመርዳት ይገኛል። ከወደቃችሁ፣ ተመልሳችሁ ለመነሳት የእርሱን ጥንካሬ ሰብስቡ። እንደ አልማ ድምጻችሁን ከፍ አድርጉ፣ “ኦ ኢየሱስ፣ … በእኔ ምህረት ይኑርህ።”7 እንደገና እንድትነሱ ይረዳችኋል። ከዛ ንስሃ ግቡ፣ አድሱ፣ ማስተካከል ያለባችሁን ነገር አስተካክሉ እናም መሄዳችሁን ቀጥሉ። በቅርቡ የምትሹትን ወጤታማነት ታገኙታላችሁ።

ጌታ እንዲህ በማለት አወጀ፣ “ላደርግልህ እንደምትሻው እንዲሁ ይደረግልሀል።”

“… ወደ መልካም፣ አዎን፣ በትክክል ለመስራት፣ በትህትና ለመራመድ፣ በጽድቅ ለመፍረድ፣ በሚመራው መንፈስ ላይ እምነትህን አድርግ። …

“… [ከዚያም] የጽድቅን ነገሮች በተመለከተ ከእኔ የምትሻቸውን … [ትቀበለዋለህ]።8

ያንን ትምህርት እወደዋለው! መልካምን ለማድረግ ባለን መሻት ለመሆንም በመጣራችን እንደምንባርክ እንደገና ይናገራል። ለእነዛ በረከቶች ብቁ ለመሆን ለሌሎች መከለከል እደለሌብን ማረጋገጥ ያስታውሰናል፥ በፍፁም በማዳላት ሳይሆን በሀቀኝነት መስራት አለብን፤በኩራት ሳይሆን በትህትና መራመድ አለብን፤ እኔ ብቻ ትክክል ነኝ በማለት ሳይሆን በፅድቅነት መፍረድ አለብን።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ከዘለአለም ሁሉ የመጀመሪያው ታላቅ ትእዛዝ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችን፣ ሀይል፣ አዕምሮ፣ እና ጥንካሬ ማፍቀር ነው—ያም ታላቁ የመጀመሪያ ትእዛዝ ነው። ነገር ግን ከዘለአለም ሁሉ የመጀመሪያው ታላቅ እውነት እግዚአብሔር እኛን በሙሉልቡ፣ ሀይሉ፣ አዓምሮው፣ እና ጥንካሬው እንደሚያፈቅረን ነው። ያ ፍቅር የዘላለማዊነት የመሰረት ድንጋይ ነው፣ እናም የቀን ተቀን ሕይወታችን የመሰረት ድንጋይ መሆን አለበት። በእርግጥ በነፍሳችን ውስጥ ከእዛ የመልሶ ማረጋገጫ ስሜት ጋር ብቻ ነው ማመናችንን የመቀጠል ድፍረት፣ ለመሻሻል መሞከር መቀጠል፣ ለሃጢያቶቻችን ስርየት መሻትን መቀጠል እንዲሁም ያንን ፀጋ ለጎረቤታችን ማካፈል መቀጠል ሊኖር የሚችለው።

ፕሬዘደንት ጆርጅ ኪው ካነን አንድ ጊዜ እንዲህ አስተማሩ፤ “ይንም እንኳ ፈተናው ከባድ ቢሆን፣ ስቃዩ ጥልቅ ቢሆን፣ መከራው ታላቅ ቢሆንም እግዚአብሔር በፍፁም አይክደንም። በፍፁም አድርጎት አያውቅም፣ አያደርገውምም። ማድረግ አይችልም። [ያንን ማድረግ] ባህሪው አይደለም። … [ሁሌም] ከጎናችን ይቆማል። በሚንቀለቀለው እቶን እሳት ውስጥ ልናልፍ እንችል ይሆናል፤ በጥልቅ ውኃ ውስጥ ልናልፍ እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን አንዋጥም እንዲሁም አንጥለቀለቅም። የበለጠ የተሻልንና ንፁህ ሆነን ከእነዚህ ፈተናዎችና ችግሮች እንወጣለን።”9

በዛ በንፁህነትና በፍፁምነት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይውት፣ ሞትና የኃጢያት ክፍያ ውስጥ ከሚገለፀው በሕይወታችን ውስጥ እንደ ታላቅ የማይቀየር ከሰማይ የሚመጣ ግዙፍ መንፈስ ጋር በእለት ተእለት ኑሮአችን ውስጥ በማንኛውም ዓይነት ቅርፅ የሚመጡትን የራሳችንንና የሌሎችን የኃጢያትና የማይረባነት ውጤት ማምለጥ እንችላለን። ልባችንን ለእግዚአብሔር ከሰጠን እና ወንጌልን ለመኖር ማድረግ የምንችለውን ካደረግን፣ ከዛ መሆኑን ባንገነዘበውም ነገና እያንዳንዱ ቀናት እፁብ ድንቅ ይሆናሉ ። ለምን? ምክንያቱም የሰማይ አባታችን እንዲሆን ስለሚፈልግ! ሊባርከን ይፈልጋል። የሚሸለም፣ የተትረፈረፈ እና ዘላለማዊ ሕይወት ለልጆቹ ያለው የምህረት ዕቅዱ አላማ ነው! “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ”10 በሚል እውነታ ላይ የተመሰረተ ዕቅድ ነው። ስለዚህ መሞከራችን ቀጥሉበት። ጥረትን ቀጥሉ። እምነት መጣላችሁን ቀጥሉበት። ማመናችሁን ቀጥሉበት። ማደጋችሁን ቀጥሉበት። ዛሬ፣ ነገና ለዘላለም መንግስተ ሰማይ ይደግፋችኋ።

“አላወቅህምን? አልሰማህንምን?” ኢሳይያስ እንዲህ አለቀሰ።

“[እግዚአብሔር] ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።nb}…

“… [እርሱን] በመተማመን የሚጠብቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ። …

“… እኔ አምላክ እግዚአብሔር አትፍ[ሩ] እረዳ[ችኋለሁ] ብዬ ቀኛ[ችሁን] እይዘዋለሁና።”11

“ወንድሞችና እህቶች በሰማይ የሚኖረው የሚወድን አባት ነገ ዛሬ እንዴት እንደተሰማን እንድናስታወስ ይባርከን። የእርሱ መለኮታዊው ፍቅርና የማያቋርጥ እርዳታው በተለይ በትግል ውስጥ ስንሆን እራሱ ከእኛ ጋር እንደሚሆን በማወቅ በዚህ የሳምንት መጨረሻ ላይ ሲታወጅ የሰማነውን በትህትና እና በመደጋገም እንድናጣጥምና እንድንጥር ይባርከን።

መመሪያው ከፍ ያለ ከመሰለና ወደ ፊት ባሉት ቀናት ውስጥ የግል መሻሻል የማይደረስበት ከመሰለ፣ ኢያሱ ህዝቦች ስለወደፊት ሕይወታቸው አለመተማመን ሲያጋጥማቸውን የሰጣቸውን ማበረታቻ አስታውሱ። እንዲህም አለ፣ “ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ”12 እኔም ይህን የተስፋ ቃል አውጃለሁ። ይህም ጉባኤው የተስፋ ቃል ነው። ይህም የቤተክርስቲያኗ የተስፋ ቃል ነው። ይህም ራሱ “አስደናቂው፣ አማካሪ፣ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር፣ … የሰላም ልኡል”13 የሆነው እነዚያን አስደናቂዎች ነገሮች የሚያከናውነው ቃል ኪዳን ነው። ስለእርሱም ምስክሬን እሰጣለሁ። ስለእርሱም እመሰክራለሁ። እናም ለእርሱም ይህ ጉባኤ ለእርሱ እንደ ምስክርነት ይቆማል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።